2022-10-09 22:23:04
#የጥሩ_ባል_መገለጫዎች
ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር #የማንኛዋም_ሴት_ምኞት ነው
የጥሩ ትዳር መሰረቱ ጥሩ ባል ነው፣
#ከጥሩ_ባል መገለጫዎች በጥቂቱ ፥
1☞በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል
2☞ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር #ይኗኗራል
3☞በተቻለው ያክል #ቃሉን ይሞላል
4☞ለሚስትና ለልጆቹ መልካም #አርዓያ_ይሆናል
5☞ንግግርና #ተግባሩ_አንድ ነው (አታላይ አይደለም)
6☞#ሚስቱን_ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል
7☞ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ #ይጠብቃል
8☞ ዘመድና #ቤተሰቦቿን ያከብራል
9☞በሆነ #ባልሆነው አይጨቃጨቅም
10☞ትርፍ ቃል ከመናገር #በመታቀብ_በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል
11☞ሚስቱ #አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም
12☞ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ #ስሜቷን ይጋራል
13☞ከሚስቱ ጋር በመተባበር #ልጆቹን_በኢስላማዊ_አደብና እውቀት ቀርጾ
ያሳድጋል
14☞#ሚስቱ_ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ
እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል (ንጽህና ይጠብቃል)
15☞#ቤቷን_ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም #አልፎ
የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል
16☞#ለቤቱ_በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ
ያመሰግናታል
#ድምበር_ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል
17☞በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና #ትዕግስትን_ተላብሶ ይኖራል
18☞አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም #ሚስቱን_እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ
#በማዘን_ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና #ቁጣውን_ዋጥ በማድረግ
መፍትሄ ይፈልጋል::•••••••
#አላህ_ለርሰበርሳችን ጥሩዎች ያድርገን
ላገቡትም ላላገቡትም #መልካምና_ስኬታማ_ትዳር ይወፍቀን
Nun Tube
t.me/+erRKiinjTgc3MDE0
t.me/+erRKiinjTgc3MDE0
597 viewsالحب الأسود, 19:23