Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 18.51K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-10-02 10:48:30 ★ዉድ አንባቢዎች ይሄን ታሪክ እንዲቀርብ የፈለኩት ለኔ ባይጠቅመኝም ግን እንደ እኔ ብዙ የተጎዱ ስላሉ ከኔ ትምህርት እንዲወስዱ እና ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባቸዉ ለማስታወስ ያህል ነዉ
★ፀሀፊ አሚር ሰይድ ከደሴ ከተማ ከልብ አመሰግናለሁ በየaudio የላኩልህን እና በስልክ ያጫወኩህን ዉሸት ሳትጨምር እንደዚህ በሚያምሩ ቃላት አሳምረህ በማቅረብህ ከልብ አመሰግናሀለሁ፡፡


የኔ የአሚር ሰይድ ለማጠናቀቅ ያህል በዚህ እዉነተኛ ታሪክ የተወሰነ ልበል፡፡
በዚህ በነዋል ታሪክ ለእሷ ጥንቃቄ ሲባል የእሷ ስም የምትኖርበት ከተማ ተቀይሯል...
   ባለታሪኳ ነዋል ታሪኩን የነገረችኝ ለካሊድ መደፈሯን ከነገረችዉ ቡሀላ ሽማግሌ ሊልክ ሲል ነበር....ከዛ ቤተሰቦቿ ሲጣሉ ሚፍታህ መልሼ ልላክ ሲል እንደ አጋጣሚ እኔን ነበር የምታማክረዉ በሚዲያ ያገናኘን ምርጥ እህት ወንድም ሁነን ነበር ጠዋት ማታ ነበር የተፈጠረዉን እየደወለች እየነገረችኝ በመመካከር ነበር ለዚህ ትዳር  እንድትደርስ የሆነችዉ
☞ሚፍታህ መልሶ ልላክ ሲል የነዋል ሁብ የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነዉና..ሚፍታህን ፊት እንዳትሰጥ ማግባት እንደሌለባት ያሳመንኳት እኔ ነበርኩ....እኔ ከሚፍታህ የካሊድ ደጋፊ ነበርኩ ሚፍታህን እንዳታገባ ካሊድን እንድታገባ ያደረኩት እሷ ጋር ስንመካከር በማሳመን ነበር መቼም ከታሪኩ ትረዳላችሁ፡ መቼም አላህም የፃፈዉ ነዉ ካሊድ ጋር በመሆኗ ምንም ቁጭት እንደሌለዉ  ትረዱኛላችሁ ብየ አስባለሁ...
ሚፍታህን ነዋል እንደምወደዉ ባቅም ግን የሴት ልጅ ፍቅር ለትዳር በቂ አይደለም እሷን ከ3 አመት በላይ የሚወዳት ብታገባ ይሻላል ብየ ነዉ፡፡ ሲጀመር ሚፍታህ ለሰዉ ልዳርሽ ብሎ ጀምሮ ነዉ በሰዉ እርዚቅ ገብቶ ነዋል ጋር የጀመሩት ካሊድ ግን ሁሌም ይወዳታል ነዋል ትገበዋለች ብየ እኔም በተደዋወልን ቁጥር በሚፍታህ ፍቅር ብትቸገርም ካሊድን እንድታገባ ተፅእኖ ፈጥሬበታለሁ፡፡ የነዋል ባህሪ ደስ የሚለዉ ሰዉ ትሰማለች ታገናዝባለች እንደአሁን ሴቶች ችኩል አይደለችም ..በፊት እሷ በዛ ችግሯ እኔን አማካሪዋ በማድረጓ ሁሌም ትዝ ባለኝ ቁጥር ደስተኛ ነኝ፡፡
ሚፍታህ ሌላ ሲያገባ ምንም እንዳይመስልሽ ነበር ብየ ከእሷ አግብቶ በመራቁ ሞራል ስሰጣት የነበረዉ..ሚፍታህም ጓደኛዉ የሱፍም ሲያገቡ አዉቅ ነበር ለምን ከነገረችኝ ቡሀላ ታሪኩ ላይ ያልተፃፈ ብዙ ፈተና ስለነበር..ይሄን ፈተና እኔ ከደሴ ሁኜ አብረን ነበር በመወያየት በመመካከር ለዚህ ደረጃ ነዋል የደረሰችዉ
☞እኔም ጋር ስታወራ ነዋል በኔ አመለካከት ድንግል ነሽ ብየ ነዉ የማስበዉ ብየ እነግራት ነበር...አራት አመትሽ ነዉ ወዳዉ እናትሽ ደርሳበታለች አንቺም በጊዜዉ ታመሽ አልተኛሽም እናም አትጨነቂ አንቺ ድንግል ነሽ አንቺን የሚያስቸግርሽ የሰዉ ወሬ ተደፍረሻል እያለ እንጂ አንቺ ድንግል ነሽ እላት ነበር፡፡
በነገራችን ላይ እሷ ስታገባ covid ባይሆን እንደ እቅዷ ሀይለኛ ሰርግ ብታዘጋጅ ሰርጉ ለመገኘት ቃል ገብቼ ነበር ግን covid ሁኖ ሰርግ ስለተከለከለ የተካበደ ሰርግ አላረገችም እኔም አልሄድኩም...በሰርጉ ማግስት ሰኞ ለት ጠዋት አሚር የሚገርም ነዉ ድንግል ነበርኩ ስትለኝ ወላሂ ያንን message ሳየዉ የደስታ ለቅሶ ነበር ያለቀስኩት...ለምን በስልክ ከ6ወር በላይ ተወያይተናል ሚስጥሯን ስለነገረችኝ የሆነ ሙሲባ ሲመጣባት ደዉላ አማክራኝ ተወያይተን ነበር የምንፈታዉና

☞ #ይሄን_ታሪክ ከፃፍኩት ቡሀላ በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜ ማጣት ላለማቅረብ ወስኜ ነበር ነገር ግን 2012 ረመዷን ሶስተኛዉ ቀን ላይ እሁድ ቀን እንደ አጋጣሚ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ቡሀላ በሪሞት እየቀያየርኩ prgram ሳይ 2012 ላይ ፋናtv ላይ የሆነ እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም አይኔ አረፈ
አንዲት ሴት ልጅ ከልጅነቷ ጀምሮ በአባቷ የወሲብ ጥቃት ይደርስባት ነበር ..አባቷ መጠጥ እየጠጣ ማታ ማታ ሁሌ ያስቸግራታል ..ሳትወድ በግዷ አባቷ ጋር ብዙ ቀን ታድራለች...ከዛም ወደ 18ቹ አመት ሲጠጋት ከአባቷ ታረግዛለች...ግን ለማን ታዉራ ለማን ትናገር
??ሁለት ታላቅ ወንድሞች አሏት ግን የየራሳቸዉ ስራ አላቸዉ እቤት አይኖሩም..አባቴ ይደፍረኛል ብላም ለመናገር ትፈራለች...ከዛም ሲቸግራት ለጓደኛዋ ትነግራታለች ..ጓደኛዋ እና ልጅቷ ሁነዉ ጓደኛ መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ ..ጓደኛዋ ለእናቷ ነግራት እንርዳት ስትላት..ከአሁን ቡሀላ እሷ ጋር ጓደኛ እንዳትሆኝ ብላ የጓደኛዋ እናትም ከቤት አስወጣቻት...ከዛም ሲጨንቃት ለአባቷ እህት(አክስቷ)ታማክራታለች ..አክስቷም አመነጫጭቃ ከአሁን ቡሀላ ወንድሜን እንደዚህ ብለሽ ብታነሺ በእኔ እጅ ነዉ የምሞችዉ ብላ ከቤት አባረረቻት....ታዳ ይሄን በደሏን የሚረዳት ስታጣ ጓደኛዋ የምትፅፈዉን ደፍተር ብቻ አደረገች

ይቺ ሚስኪን ልጅ ከአባቷ አርግዛ ሆዷ ገፋ..አባትየዉ በሰፈር ልጄ ዱርየ ሆነች ዲቃላዋን ይዛብኝ መጣች እያለ ወሬዉን አናፈሰዉ...የልጅቱ ሁለቱ ወንድሞችም እርጉዝ በመሆኗ ዱርየ ሆነች ብለዉ ከማን አረገዝሽ ብለዉ እንኳ ሳይጠይቁ አኮረፏት... ይቺ ልጅ ለማን ተናግራ ማን ይረዳት??ሒወቷ ገና በልጅነቷ ተበላሸ ህልሟ በአባቷ ጨለመ...ይሄም ሳያንሰዉ በሰፈር ልጄ ዲቃላ አመጣችብኝ እያለ በዉሸት ወሬዉን ነዛዉ፡፡ ልጅቱ የወሰደችዉ እርምጃ መጠኑ ያልታወቀ ኪኒን ዉጣ እራሷን አጠፋች ከሞተች ቡሀላ ወንድሞቿ ቢያለቅሱ የጓደኛዋ እናት ብትቆጭ ለልጂቱ የጠቀማት ነገር የለም ..
ፓሊስ የሞተችበትን ሲያጣራ በደብተር ላይ የፃፈችዉን መኝታ ክፍሏ አግኝቶ አባቷን አስሮ .ስንት አመት እንደሆነ እረሳሁት እስር ተፈረደበት፡፡

ቆይ እስኪ እንደዚህ አይነት አባት....በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች ምክንያት የሆኑ ወንዶች የሞት ፍርድ ካልተፈረደበት የሴት ልጅ አስገድዶ መደፈር ያቆማል ወይ???በጭራሽ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ እየበደለ ታስሮ እስከተፈታ ድረስ በልጅነታቸዉ የሚደፈሩ ሴት ልጆች መቼም መቆም አይችልም

የሞተ ተጎዳ አባትየዉ ከእስር ይፈታል መልሶ መኖር ይጀምራል ...እራሷን ያጠፋችዉ ልጅ ግን ወላሂ አሳዘነችኝ አስለቀሰኝ የነዋል ታሪክ ጋር ሳመዛዝነዉ የዝች ልጅ ታሪክ አሁን ድረስ ከአእምሮየ ሊጠፋ አልቻለም.. ይሄን እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም ካየሁ ቡሀላ ነዉ የነዋልን ታሪክ ለማቅረብ ያነሰሳኝ፡፡

#የእኔ_አሚር_ሰይድ ልባዊ ምኞቴ ይሄን ታሪክ ያነበበዉ ሰዉ ...ወንድ ለሴት ወገኖቹ እንዲያስብ ..ሴቶችም የወደፊት ትዉልድ በእነሱ ማህፀን የተቋጠረ ስለሆነ በተርቢያ በዲን አሳድገዉ ለዲነል ኢስላም የሚያስረክቡ እንስቶች ካሉበት ተጨባጭ እራሳቸዉን እንዲፈትሹ ነዉ፡፡

እኔ የምፅፋቸዉን ያነበበ ሰዉ እራሱን ቀይሮ ወደ ፈጣሪዉ እንዲቃረብ እና ወደ ወንጀል መንደርደር የያዙ እንዲያፈገፍጉ እና በወንጀል የተዘፈቁ ጥርት ያለ ተዉበት ቶብተዉ ወደ ፈጣሪያቸዉ ያለዉን መንገዳቸዉን እንዲያስተካክሉ እና ማንኛዉም ሰዉ እራሱ ተቀይሮ ማንኛዉንም ሰዉ የመቀየር ተሰጥኦ ስላለዉ ይሄን ተሰጥኦ በተግባር እንዲያሳይ ብር ያለዉ በብር..ሀሳብ ያለዉ በሀሳቡ..እዉቀት ያለዉ በእዉቀቱ...ዲነል ኢስላምና ኢስላም ወንድም እህቶቹ ጎን እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነዉ፡፡
#ተ............ #ፈ............ #ፀ...... #መ.....

ታሪኩ በ2013 ተነቦ በድጋሜ አሁን የቀረበ ነዉ
ከይቅርታ ጋር ጥሩም መጥፎም ማንኛዉንም አስተያየት አልቀበልም
1.0K viewsedited  07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 10:48:21 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ #የመጨረሻዉ_ክፍል

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


ከዚህ ፍልሚያ ቡሀላ ያልተጠበቀ ይሆናል ብላችሁ የማጠብቁት ነገር ተፈጠረ

እኔም ካሊድም ገረመን አላህ ምን ይሳነዋል..
ይገርማል አረ በጣም ይገርማል ገርሞም ይገርማል የሚገርም ነዉ... #ድንግል ነበርኩኝ ፡፡ በአራት አመቴ ተደፍሪያለሁ እያልኩ ሳለቅስ ኑሬ ...በትምህርት ቤት በሰፈር በልጅነትሽ የተደፈርሽዉ እያሉ ሲያስለቅሱኝ ሲያገሉኝ ያለፉት የኖርኩባቸዉ አመት አላህ እኔን እየፈተነኝ እንደሆነ ተረዳሁኝ
...ካሊድም እየተገረመ ነዋል ታስታዉሻለሽ በምታለቅሽበት ጊዜ የአላህ ነገር አይታወቅም ድንግልም ልትሆኝ ትችያለሽ ስልሽ አላምንም ብለሽ ነበር ከአላህ ምንም ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም አለኝ

#የጫጉላየ_ምሽት

ፊቴ አብርቶ ጥርሴ ይስቃል
ከጀርባ ያለዉ ሀዘን ከቶ ማን ያዉቃል
እንዲህ ደምቄ ፈክቼ ላየኝ ሰዉ
በሆዴ ፍም እሳት ያለም አይመስለዉ

ዛሬ ላይ ሁኜ የትናንቱን ግፍ አስታዉሳለሁ
በትዝታ መስኮት እያንዳንዱን ህመም እመለከታለሁ

በጨቅላ እድሜየ ክፉን ከደጉ ባለየሁበት
ጫማ ለመልበስ ግራዉን ከቀኙ ባላወኩበት
ስጋና አጥንቴ ከደሜ ጋራ ሳይዋሀዱ
ሁለቱ እግሮቼ እንኳን እርቀዉ ሳይራመዱ
ሲመሩኝ ምመራ ኩልትፍትፍ የምል
ዉብ ፅጌሬዳ ሲያዩኝ ደስ የምል

እንኳን ጭካኔ ለኔ ሊገባኝ
ለቁንጥጫ እንኳን የማሳሳ ነኝ
ምን ዋጋ አለዉ የሰዉ አዉሬ ጨከነብኝ
ለማይረባ ለደቂቃ ስሜቱ ተጫወተብኝ
ከሰዉ በታች አድርጎ እንዳልነሳ ቀበረኝ
አንገቴን ላይነሳ እንድደፋ አደረገኝ

ያ! ሰው መሳይ ሰው ያልሆነው
ህልሜን በአንድ ቀን አጠልሽቶ በላዉ
ቅስሜን ሰብሮ ልቤን አደማዉ
ያ የሰዉ አዉሬ ደስታየን ነጥቆ ሀዘን አሸከመኝ
ሚስጥሩን ያወቀም ከጎኔ እንዲሸሽ አረገኝ


ሂወትን በጠላሁ ሰው ባጣሁ ሰአት
ሞቴን ስናፍቃት ቀብሬን ስመኛት
ትዝ አለኝ አንድ ቃል የመጠጊያዬ
ለምኑኝ ሰጣለው ያለውን ጌታዬ

ያኔ በጥዋት በማታ በቀን በለሊት
እንባየ ሲፈስ ለብዙ አመታት
አብሽሪ የሚለኝ ሀዘኔን አይቶ
እንባየን አባሽ አንድ ሰዉ ጠፍቶ
ተደፍረሻል ብለዉ ሰዎች ሲሸሹኝ
እጆቼን ዘርግቼ ያረቢ አልኩኝ

እኔም ሁሉንም ትቼ ወደሱ ሸሸሁ
እንደመርየም ንፁህ መሆንን ተመኘሁ
ማንነቴን የሚቀበለኝ ደግ ባሪያህን ስጠኝ ብየ አንገቴን ሱጁድ ላይ ደፋሁ
ሌት ተቀን እየሰገድኩ አምርሬ አነባሁ
ያረብ አልኩት አላህም ዱአየን ሰምቶኝ
ማንነቴን ተቀብሎ የወደድኩት የወደደኝ
ደጉን ባሪያዉን የዱአሽ ዉጤት ብሎ ሰጠኝ
ሀዘንሽ ሀዘኔ ደስታሽም ደስታየ ብሎ ተቀበለኝ

የበደለኛ እንባ መች ይቀራል ፈሶ
ትአምር አየሁ ዱአየ ደርሶ
ልክ እንደመርየም እንደጠየኩት
ቢክራ አደረገኝ በሰርጌ ምሽት
በደቂቃዎች ሁኔታዎችን የሚቀያይር
ለኛም አሳየን የማይታመን ትልቅ ታአምር

ነብዩ ዪኑስን
ከአሳ ነባሪ ፈልቅቆ አወጣዉ

ነብዩ ሙሳን
ከሚያሰምጥ ዉሀ ነፃ አወጣዉ
ነቢዩ እስማኤልን
በአንገታቸዉ ላይ ያንን ቢላዋ አቅም አሳጣዉ

ለነቢ ኢሳ
የሞተዉን ሰዉ ህያዉ እንዲያደርግ ችሎታ ሰጠዉ

ነቢ ኢብራሂምን
ከዛ ከነበልባሉ ከአስፈሪዉ እሳት ነፃ አወጣዉ

የሰዉ ዘርን
ከአፈር ከጭቃ በታላቅ ጥበብ አቡክቶ ሰራዉ

ከመርየም ገላ ክብርዋ ሳይነካ ልጅ ፈጠረው

ታድያ...!

ይሄን ያረገ ታላቁ ያመውላ
ድንግል ማድረግ የነዋልን ገላ
እንዴታ ይሳነው እሱ እኮ ጌታ ነው
ሁሉ ሚታዘዘው ሁን ሲል የሚሆን ነው

ዛሬ ያሁሉ ሀዘንና ስቃይ ተወግዶ
በደስታ ተተካ የሀዘን ተራራዉ ተንዶ
አልሀምዱሊላህ ከማለት ዉጭ ምን ይባላል
በርግጥም ሁኔታዉ አጃኢብ ያስብላል
እልፍ ምስጋና ጥራት ይገባዉ
ለአንዱ ጌታችን ወደር ለሌለዉ

ይሄዉ ከአራት አመቴ ጀምሮ ሳለቅስ የኖርኩትን በአንድ ቀን ወደ ደስታ ቀየረዉ...በጣም ደስተኛ ነኝ ያለፉትን ጊዜያት ሀዘኔ  ከአሁኑ ደስታ ሳወዳድረዉ የሰማይና የምድር ልዩነት አለዉ ሌላ ምን ይባላል አልሀምዱላህ


ልብ በይ እህቴ!!!! በሴቶች ላይ የሚገኘዉ ገቢ በዓመት ከ7ቢሊየን ዶላር እንደደረሰና..ይህም ገቢ ከመሳሪያ ሽያጭና ከአደንዛዥ እፅ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናቶች ይገልፃሉ

እህቴ ሆይ የሴቶች እኩልነት ብለዉ ምዕራባዉያን ለአንቺ የሰጡሽ መብት ምን አንቺን ለማጃጃል እንደሆነ ምን ያህል ታቂያለሽ? ለምሳሌ ስፔን እንዉሰድ የሴቶች መብት ተብሎ መስሪያ ቤት ገብተዉ እየሰሩ ነዉ ..በስፔን በተደረገዉ ጥናት ከአንድ ሚሊየን በላይ ሴቶች በየመስሪያ ቤቱ የመደፈር ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ ብቻ በተደረገዉ ጥናት 13100 ሴቶች በአለቃዎቻቸዉና በስራ ባልደቦቻቸዉ የመደፈር ሙከራ ተደርጎባቸዋል..በአጠቃላይ 15% የሚሆኑት የስፔን ሴት ሰራተኞች በጠቅላላ 8ሚሊየን 425 ሺ ሴት ሰራተኞች ለመደፈር አደጋ እንደተጋለጡ ጥናት ያሳያል፡፡ደፈራ የተደረገባቸዉ ሴቶች ስማቸዉን ለመጠበቅ እና ከሀፍረታቸዉ የተነሳ ለሚመለከተዉ አካል ክስ አይመሰርቱም ..ክስ ለመመስረት ሙከራ ያደረጉት 25% ብቻ ናቸዉ..56% ተደብቀዉ ይገኛሉ..8% የሚሆኑት ክስ በመመስረታቸዉ ከአለቆቻቸዉ ከሚሰሩት ድርጅት ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል..45% የሚሆኑት ከስራቸዉ እንዳይባረሩ የመደፈርን ችግር ተቀብለዉ ጊዚያቸዉን ያሳልፋሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሴቶች ለጭንቀት ለመረበሽ ሰላምና እንቅልፍ አልባ ለመሆን አደጋ ስለተጋለጡ የማስታገሻና የማረጋጋት መድሀኒት ለመዉሰድ ተገደዋል፡፡ ሴቶች በእኩልነት ወደ መስሪያ ቤት በመግባት ባስከተለባቸዉ የጭንቀት በሽታ በአሜሪካ 61% በኢማራት 38% የጭንቀት ማስታገሻ መድሀኒት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እናም እህቶቼ መብቴ ነዉ እያልሽ በዚህ አዘቅት ዉስጥ እንዳትገቢ አንቺም ተጠንቀቂ ሰዉ ሲሸወድ ሲዘነጋ በአንድ ቀን አይለይም በሒደት በጊዜ ብዛት እየተንሸራተተ ነዉ የሚሄደዉ የአቋም መዋዠቅ ሲገጥምሽ ጠርጥሪ

★ የሴት ልጅ ጥቃት መቼ ነዉ የሚያበቃዉ? አንተም እሱም እነሱም እነዛም ዘር ብሔር ሀይማኖት ሳይለያየን ከጎናችን ቁሙሉን ..ሴት እናትህ ነች እህትህ ነች ለቅሷዋ ሊያስለቅስህ ሊያስዝነን ይገባል፡፡ ለሴት ልጅ ክብር የሚጨነቅ ሴትን ልጅ ለስሜት ብቻ ማሰብ ትተን በሆዷ ዉስጥ አፍና የምትዞረዉን የፉም እሳት ለመረዳት ሞክሩ .ሴት ልጅ ሀዘን በዉስጧ እያለ በጥርሷ ደስተኛ ተጨዋች መስላ መኖር የምትችል ፍጥረት ነች .ማንኛዉም ሴት ስለሳቀች ስለተደሰተች ደስተኛ አይደሉም ብዙዎቹ ለሊት ላይ ሲጨነቁ ሲጠበቡ ሲያለቅሱ የሚያድሩ በብዙ የሀሳብ ማዕበል እና ሆዳቸዉ ዉስጥ ተናገረዉ የማይወጣ የሚቀጣጠል ጥፋ ቢሉት የማይጠፋ እንደዉም እየተፏፏመ የሚሄድ የእሳት ማዕበል ተሸክመዉ የሚሄዱ ናቸዉ ..እናም አንተ ወንድ ነህ በእሳት ላይ እሳት ከመጨመር በሆዷ ያለዉን እሳት አንተዉ ተረድተህ በስሜት መነዳቱን ትተህ ሸክማን በሀሳብህ ተቀብለህ እሳቱን በብልሀት አጥፋላት..የዛን ጊዜ አንተ ለሷ የደስታ ምንጭ እና የህሊና እረፍት ታገኛህ
ታሪኬ ከሞላ ጎደል ይሄን ይመስላል፡፡
አሁን ላይ የአንድ ልጅ እናት ነኝ...ወንድ ልጅ አላህ ሰጥቶኛል አድጎ ለዲነል ኢስላም የሚጠቅም ልጅ እንዲሆን ዱአ አድርጉልኝ፡፡
1.1K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 08:43:38 ......እናቴም፡- በጭራሽ ካሊድ ጋር እንድትጋቡ አልፈቅድልሽም ... ለምን ብትይ ሹፌር አይታመንም ሴቶችን ሲያጀዝቡ አይደል እንዴ የሚዉሉት ??..እኔ በካሊድ አልስማማም አይኔ እያየ ለካሊድ አልድርሽም አለችኝ
...እናቴ ጋር በዚሁ ምሽት ዉርክብ ብጥብጥ ተፈጠረ በጭራሽ መግባባት አልቻልንም ... አባቴም በኔ ምርጫ ጣልቃ ላለመግባት ፈልጎ...ነዋል ትዳር ቀልድ አይደለም ተረጋግተሽ እሰቢበት አለኝ..እናቴ ደግሞ ሹፌር መቼም ቢሆን አታገቢም እያለች እየደነፋች ነዉ፡፡

ለነገሩ በእናቴም አልፈርድም አሁን ዘመን ላይ ያሉ ሹፌሮች አላማቸዉን የረሱ ከትርፉ ላይፉ እያሉ ራሳቸዉን እና ሞኝ ተላላ ሴቶችን የሚታልሉ ብዙ ፡ናቸዉ ...ደግሞ በተዘዋዋሪ ሹፌሮችን የሚያስቸግሩ ሴቶችንም እያስተዋልን ነዉ...

ጃፓን መኪናዉን ስትሰራዉ መሪዉ ላይ ሹፌር ሹፌር የሚያስብል የቀበረችበት ያለ ነዉ የሚመስለዉ...ግን ከሁሉ የሚያናደኝ በነዚህ ጋጠወጥ ሹፌሮች እንደ ካሊድ ያሉ ምርጥ ለሴት ልጆች የሚያስቡ ሹፌሮች አብረዉ መወቀሳቸዉ እና መሰደባቸዉ አሳዛኝ ነዉ

★★★ አንዲት አበባል አለች ጭልፊት የወደቀ ስጋን እንጂ በቁሙ ያልተገፈፈ በግን እንደማይነካ የታወቀ ነዉ፡፡
እህቴ ሆይ ሒወትሽ እንደ በግ ነጋዴ በግ ተራ እንደወሰደዉ በግ እጣ ፈንታ አትወስኝ...አንድ በግ ሊሸጥ ሲል በጣም ብዙ ገዥ አገላብጦ ሽንጡን እየያየዘ ስጋ አለዉ የለዉም እያለ ያየዋል..ከተቻለ ዛሬ አለዛም ነገ ቀይም ከነገ ወዳ ሲገላበጥ ቢቆይም ይሸጣል.. አንቺም እንደዚህ እንደሚሸጥ በግ አላማቸዉን ከዘነጉ ተኩላ ወንዶች እያገላበጡ እየታየሽ አለፈች ወደቀች እየተባልሽ በየመንገዱ ስትሄጅ ግምገማ አትቀረቢ...መስሪያ ቤት ግምገማዉ በወር ወይ በአመት ነዉ...አንቺ ግን ኮስሞቲክስ እየተጠቀምሽ ቀን በቀን የወንዶች መሳለቂያ አትሁኝ...ሒወትሽ ሊሸጥ ገበያ የሄደ በግ አይነት እንዲሆን በራስሽ ጊዜ አትፍቀጅ...
ብዙዎች ሴቶች በመጥፎ ጓደኛ ግፊት እንየሚበላሹ የማይካድ ሀቅ ነዉ
ግን እህቴ ሴት ልጅ ብዙ ነገሮችን ተቋቁማ ወደ ትዳር አለም ትገባለች ያንን እንዴት ነዉ ፈተናዉን ማለፍ ያለብሽ?? ..ሴቶች ተማሪዎች አብረሽ መደበኛ ትምህርት ስትማሪ ሁሉንም ትምህርት ሂሳብ እንግሊዝ አማረኛ civics ወ.ዘ.ተ ዉጤትሽ ጥሩ ሊሆን ይችላል ግን ከትምህርት ዉጤትሽ በላይ የአንቺ የሂወት ዉጤትሽ ጓደኞችሽ ሲሆኑ  የጓደኞችሽ ግፊት አንቺን ወደ ማፈልጊዉ ወደ ማታቂዉ አለም ትገቢያለሽ ...ስምንት ማትሪክ ስትፈተኝ ጥሩ ዉጤት አመጣሽ ወደ ዘጠኝ አለፍሽ ከዛስ አስርም አለ ማትሪክን ስትወስጅ ከዘጠኝ እና ከአስረኛ ክፍል ከበፊቱ ምን ለዉጥ አለኝ?? ቂርአት ላይ ጥሩ ነኝ ወይስ መጥፎ የሴት ጓደኞች አሉኝ ወይስ በሀራም ከወንድ ጋር ሀራም የሆነ የማይጨረስ ፍቅር ጀምሪያለሁ ወይ?? ወ.ዘ.ተ የሚለዉን አንቺ እራስሽ ለራስሽ ጥያቄዉን አቅርበሽ መመለስ አለብሽ
ከዛስ ማትሪክ ተፈተንኩ ትምህርቴን ካለፍኩኝ 11 ክፍል ስገባ አላማየ ምን መሆን አለበት ከ10 ብወድቅስ ? ብለሽ እሰቢ

እህቶቼ አራት አመት ፈተናዉን ማለፍ መታገስ ከቻላችሁ የወደፊት የእናንተ ከአላህ ጋር የአርባ አመት ፕላናችሁ መስተካከል ይችላል ፡፡ ግን አራት አመት ላይ ግን የምትሸወዱ ከሆነ በሀራም ከአጂ ነቢ ጋር ግንኙነት ከጀመራችሁ ለአንድቀን ለዛዉም 20 ደቂቃ ለማይሞላ ስሜት የ40 አመታት ፕላናችሁን ታበላሻላችሁ ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ አራት አመታት እነማን ናቸዉ ካልን ከዘጠነኛ ክፍል እስከ 12 ክፍል ያሉትን አመታት ፋየር ኤጅ ሁሉም አለሁ አለሁ ከሰዉ በላይ ነኝ የሚባልበት እድሜ ነዉ ስለሆነም እነዚህ የትምህርት አመታት የወደፊት ሂወታችሁ ወሳኝ ናቸዉ፡፡ University በምገቡበት ጊዜ እናንተ የአራት አመቱ ምርት ዉጤት ናችሁ አራት አመቱን በመጃጃል ያሳለፍሽ ከሆነ university ከቤተሰብ ቁጥጥር ዉጭ ነሽ ለቤተሰብም ለሀገርም ለአንቺም አጠቅሚ ትበላሻለሽ ..


...በዚህ ሁኔታ እኔ ካሊድን አገባለሁ እናቴም በጭራሽ አታገቢም እያለች ቀን በቀን ስንጨቃጨቅ የአላህ ነገር ይሄ covid 19 መጥቶ ከችክችክ ከንዝንዝ አረፍኩኝ...የሰዉ ወሬ ስለዚሁ በሽታ ሲሆን እናቴም ጋር ስለትዳሩ ሁኔታ ማዉራት አቆምን

..የእኔ እናት አላማዋ እኔን ከሀብታም ጋር በትልቅ ድግስ በሰፊ ሰርግ እኔን ለመዳር ነበር ....የነብዩ ሰ.ዐ.ወ የሰርግ ስነ-ስርአት እና ሱና ነገሮች ለመተግበር የመጣ ይመስላል ኮረና ደሀም ሀብታምም ሰርጉ ልዩነት የለዉም ሁሉም በኒካህ ኢስራፍ ከሆነ ከሰርግ ወጭ ገላግሏል፡፡

ቤተሰቦቼም በአባቴ ጥረት ብዙ ነገሮችን ከጠየቀኝ ቡሀላ አባቴ ተስማምቶ እናቴም ባይዋጥላትም በግድ ካሊድን እንዳገባ ፈቀደችልኝ .. ከካሊድ የ 2012 ረመዷን ሊደርስ የተወሰኑ ቀናት ሲቀረዉ በትንሹ ሰርግ ተደግሶ ...እኔም ጂልባቤን ለብሼ መፍቱሀ እና ሩቅያም ሌሎች የዓሊይ መስጂድ የጀመአ ጓደኞቼም በጅልባባቸዉ አምረዉ ድምቅ ብለዉ ከጎኔ ሁነዋል...አልሀምዲሊላህ እኔም ከምወደዉ ከሚወደኝ ካሊድ ጋር የሰርጌ ቀን ደረሰ...

ካሊድም የተወሰኑ ጓደኞቹን ይዞ መጥቶ ኒካህ ታስሮ ያሁሉ ጉፍ መከራ ለቅሶ አልፎ የሚስትነት ማዕረጉን ይዤ ከእናት አባቶቼ ተለይቼ  ካሊድ ጋር የትዳርን ህይወት አሀዱ ብለን ልንጀምር እሱ ጋር የሰርጌ ምሽት ሄድኩ ፡፡ ሁለታችንንም የናፈቀንን የሀላል ጨዋታ ምሽት ላይ ጀምረናል፡፡ ሰርግ ላይ ሲጨፈር የምሰማት ግጥም ትዝ አለችኝ እስኪ ልበላት
ካሊድ ምሽት 3:45 ታላቅ ፍልሚያ አለዉ
እኛም አላገዝነዉ አላህ ይሁነዉ
የሚሏት ግጥም እዉነትም ከፕሪሚየርሊግ የበለጠ ፍልሚያ ነዉ ...

ከዚህ ፍልሚያ ቡሀላ ያልተጠበቀ ይሆናል ብላችሁ የማጠብቁት ነገር እኔም ማመን ያልቻልኩት ነገር ተፈጠረ ...

#የመጨረሻዉ_ክፍል

ይ.......ቀ.........ጥ............ላ................ል

          `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.6K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 08:43:22 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ ስድስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ

ከዛም ጁምአ ቀን ያልተሳበ ይሆናል ብየ በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል...ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም ፡፡
 
     ቅዳሜ ካሊድ ሽማግሌ ሊልክ ጁምአ እናቴ ከአባቴ ጋር ተጣልታ ዘመዶቿ ጋር ሄደች ፡፡ በእኛ ሰፈር የሚገኙ ሽማግሌ ተሰብስበዉ ሁለቱም እንዲታረቁ ቢለመኑ ..አንታረቅም የኛ መጨረሻዉ ፍች ብቻ ነዉ መፍትሄዉ ብለዉ በጭራሽ ሊስማማሙ አልቻሉም፡፡
...እኔም ለካሊድ ደዉየ ቤተሰቦቼ እንደተጣሉ እና ሽማግሌዎቹን እንዳይልክ ነገርኩት

ጊዜያቶች እየነገዱ ነዉ....አባቴ ሌላ ሴት ለማግባት እየፈለገ ነዉ...እናቴም ፍርድ ቤት ከሳ ንበረቱን ተካፍላ ከቤት ይዉጣልኝ እያለች ነዉ፡፡ ነገሩ በጣም ሲጠና ...አባቴ ለልጆቼ ብየ እታረቃለሁ ቢልም ..እናቴ ግን በጭራሽ አልታረቅም ብላ አሻፈረኝ አለች.... የሰፈር ታዋቂ ሸሆች... የመስጊድ ኢማማችን ሳይቀር ቢለምኗት እምቢ አለች፡፡


እኔ እና ካሊድ ለመጋባት 100% ጨርሰናል ሁለታችንም ለትዳር ልባችን ቢንጠለጠልም ግን እናት እና አባቴ ተለያይተዉ በሚኖሩበት ቤት በተበታተነ ቤተሰብ ለማን ሽምግልና ይላካል??? ዱአ ከማድረግ ዉጭ ምንም አማራጭ የለም...

   ደግሞ አዲስ ነገር የማይፈጠር የለም ...ሚፍታህ ደወለልኝ እና ...ነዋል አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ነዋል ከልቤ ነዉ እወድሻለሁ ሽማግሌ ልልክ ነዉ አለኝ
......እኔም ሚፍታህ አሁን መቼም ቢሆን የአንተ መሆን አልችልም ለሁሉም ጊዜ አለዉ አንተም በጊዜህ እኔን ትተህኛል...አሁን እኔም ልቤ የሌላ ነዉ ...ተስፋ ቁረጥ እንደፈለክ የምከፍተዉ የምዘጋዉ የቤትህ በር አይደለሁም አልኩት ቆጣ ብየ
 

አይጠቅምም ብለዉ የጣሉት እቃ ሌላ ሰዉ አንስቶ ሲጠቀምበት ምነዉ ባልጣልኩት ብለዉ ይቆጩ የለ... ..ሚፍታህ እኔን ትቶኝ ላገባ ፕሮሰስ ላይ መሆኔን ሲያቅ ..እንደገና ካላገባሁ ሙቼ እገኛለሁ..ሽማግሌ ልልክ ነዉ እያለ አሁንም ተስፋ ያልቆረኩ ይመስለዋል..ሴት ልጅ ስወድ ወደደች ነዉ ከጠላች ደግሞ በእሷ መስፈርት ሁሉንም አሟልተህ ብትገኝ ከጠላችህ መቼም በልቧ መግባት እንደማችል እንደነ ሚፍታህ ያሉ ወንዶች ዘንግተዉታል... መቼም ካሊድን በማንም የማልቀይረዉ እዉነተኛ የትዳር አጋሬ ነዉ፡፡

✿✿✿ ምርጥ ጓደኛየ መፍቱሀም ተመርቃ የግል ሆስፒታል ዉስጥ ገብታ እየሰራች ነዉ..

✿✿✿ብሩክታይትም ቢላል የሚባል የወንዶች የጀመአ አባል ብሩክታይት ዲነል ኢስላምን አስተምራለሁ ቁርአን አቀራታለሁ ብሎ መፍቱሀን እና እኔን አማከረን ...እኛም ብሩክታይትን አማከርናት ... ቢላልን ታቀዋለች በትዳር ጥያቄዉ ተስማማች .. ስሟንም በራሷ ፍቃድ ብሩክ ታይት ሳይሆን ራዉዳ ነኝ ብላ ከቢላል ጋር እህል እና ዉሀቸዉ ገጥሞ በትዳር አለም አብረዉ መኖር ጀምረዋል፡፡

✿✿✿ ካስታወሳችሁ በአለፉት ክፍል ናርዶስ(በአጎቷ እና በአባቷ ጓደኛ በልጅነቷ የተደፈረችዉ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ተምራ ተመርቃለች

✿✿✿ የሱፍ (ለሚፍታህ ነዋልን ዳረኝ ብሎ ስልኩን የሰጠዉ) እሱ ደግሞ ሚፍታህ ጋር አንዴ ተጣልተዉ...ነገሩ ከብዶ ፓሊስ ጣቢያ ድረስ ሂደዉ ነበር በሽምግልና ታረቁ ቢባል የሱፍ በጭራሽ አልታረቅም እበቀለዋለሁ እንዳለ ቂም እንደያዘ .. በመጨረሻም የሱፍም ቤተሰቦች እነሱዉ አምጥተዉ እሱም ጎጆ ቀልሶ እየኖረ ነዉ፡፡

✿✿ ሚፍታህም በንዴት ይሁን አስቦበት አላቅም እኔ ላገባ ነዉ ከአሁን ቡሀላ አንተ እና እኔ አንድ ላይ መሆን አንችልም ካልኩት ቡሀላ ...ብዙም ሳይቆይ አንድ ወር ባልመላ ቀናት ዉስጥ እኔን አናዳታለሁ ብሎ አስቦ ይሁን ..ትዳሩን አምኖበት ይሆን...ነዋልን ልቀደማት ብል አስቦም ይሆን አላቅም እሱም የትዳር ጎጆዉን ቀልሷል

✿✿✿ ካሊድም የቤት እቃ እያማሏ ነዉ ፡፡ እኔም ነገሮች እስከሚስተካከሉ ብየ ጅማ የሚገኝ የመንግስት ሆስፒታል በተመረኩበት ፊልድ ማገልገል ጀመርኩኝ...አልሀምዱሊላህ አባቴ ያሰበዉ ደረጃ ደረስኩኝ ..

ሆስፒታል መቼም የብዙ ሰዉ ብሶት መቀበያ አይደል....እንደ እኔ በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች በጣም ብዙ ገጥመዉኛል ..ልጆችን በማፅናናት ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን ማገዝ የአእምሮ ጭንቀት እንዳይዛቸዉ የስነልቦና አገልግሎት መስጠት የዘወትር ስራየ ነዉ. .በተጨማሪም በፍቅር ለተጎዱ ሴቶች ...እንደ እኔ በቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ለአደጉ ልጆች..በተለያዩ ጉዳዮች ዲፕሬሽን(በአእምሮው ጭንቀት) የተጎዱ የዱንያ የአኼራ እህቶቼን ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን መንከባከብ በሀሳባቸዉ ተረድቼ መፍትሄ ስሰጥ ለኔ የዉስጥ ደስታ ሰላም ይሰጠኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ደስታዉ ብቻዉን መቀየሩ ደስታን ማግኘቱ ሳይሆን በእሱ የተነሳ ስንት ሰዉ መቀየሩ መደሰቱ ታላቅ ደስታ ነዉ..

የሚገርማችሁ እዛዉ ጤና ጣቢያ በሴት ልጆች ላይ የሚደርሰዉ በደል ሳይ የኔ ምን አለበት አልሀምዱሊላህ ያልኩባቸዉ ብዙ ቀናቶች አሉ..
እኔ ከገጠመኝ በታላቅ ወንድሞቻቸዉ የተደፈሩ ልጆች ገጥሞኛል..በተዘዋዋሪ ጭካኔ የበዛበት ዘመን መሆኑ ያሳዝናል ብዙ ህፃናት በአባቶቻቸዉ ተደፍረዉ የሚመጡ ብዙ ልጆች ገጥመዉኛል፡፡እኔ አንድ ሴት ነኝ ከጎኔ ማን አለ?? ሁሉም ከጎኔ ባይሆኔም ግን እንደ እኔ ተብድለዉ በሆዳቸዉ አፍነዉ የሚኖሩ ቤት ይቁጠረዉ,..... መቼ ድረስ ነዉ የሴት ልጅ እምባ መዉረድ የሚያቆመዉ ??? ሁሌም በልቤ ቁጭት አለ ታዳ ምን ያደርጋል አንድ ሰዉ አስቦ አንድ በሬ ስቦ አይሆንም...እኔ የራሴን ታሪክ በፁሁፍ ዘረገፍኩት እንጂ ብዙ ሴቶች አሁን ድረስ ዛሬ ከነገ ይሻላል ቢሉም ግን የብስ እየጨለመ የሚሰቃዩ ለቁጥር አይገባም. ... እንደ እኔ እንቅልፍ አጥተዉ የሚኖሩ ሴቶች አይናገሩ ሰሚ የለ ....ለማን ይነገር?? በእንባ ጎርፍ ለፈጣሪ አቤት ከማለት በቀር ፡፡ ስለሆነም ወንዶች እባካችሁ ለሴት ልጆች እዘኑ ይሄ ሁሉ ለቅሶየ ስቃየ በኔ በራሴ የመጣ አይደለም በጨካኝ ስሜቱን መቆጣጠር በአቃተዉ ወንድ የተፈጠረብኝ በልጅነት መደፈር ነዉ ፈጣሪ ሁላችንንም ልቦና ይስጠን

ቢያንስ ከ5 ወራት ቡሀላ በስንት ሽምግልና አልሀምዱሊላህ እናት እና አባቴ ተስማምተዉ መልሰዉ አብረዉ መኖር ጀመሩ ..

እናት እና አባቴ ታርቀዉ ብዙም ቀን ሳይቆዩ በቤተሰብ የትዳር ጥያቄ መጣ ...
ማታ ላይ ሳሎን ቁጭ ብለን አባቴም፡- ነዋል ይሄ መታለፍ መመለስ የሌለበት ትዳር ነዉ..እኛ እንተማመንበታለን ጥሩ ሰዉ አላህን ፈሪ ነዉ ፡፡ነዋል እኔ አባትሽ ለምወድሽ ልጄ መጥፎ ምርጫ እንደማልመርጥ ታቂያለሽ .. አሁን የመጣዉን ትዳር እንድታገቢ ምርጫየ ነዉ እሺ በይኝ አለኝ
....... አባቴ አንተ የተናገርከዉ ልክ ነህ ...ነገር ግን እኔ ትልቅ ልጅ ነኝ የሚጠቅመኝን የሚጎዳኝን ለይቻለሁ ..እኔን በደስታ ሊያኖረኝ የሚችል የኔ የራሴ የምለዉ አንድ ሰዉ አለኝ አልኩት
.....አባቴም ማን ነዉ ልጁ እኔ አቀዋለሁ??አለኝ
....እኔም አዎ ታቀዋለህ ካሊድ ነዉ ብየ ... እሱን እንዲያቁት በምልክት ሰፈሩን ቤተሰቡን ስነግራቸዉ እናቴም አባቴም አወቁት
1.4K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 09:23:21 ....እኔም አልሀምዱሊላህ ደህና ነኝ አልኩት
.......እሱም ቀለበቴን እያየ ነዋል ልታገቢ ነዉ እንዴ ??? አለኝ
....እኔም...አዎ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን አስቢያለሁ አልኩት
ሚፍታህም :- ሽማግሌ ተልኳል ወይስ አልተላከም??? አለኝ
....እኔም ገና አልተላከም በቅርብ ቀን ይልካል አልኩት
....... ነዋል ወላሂ ብየ ነዉ የምነግርሽ በጣም ነዉ የምወድሽ ..አንቺ የሌላ ስትሆኝ ማየት አልችልም... ወላሂ ሁሌም ህልሜ አንቺ ጋር ተጋብቶ መኖር ነዉ፡፡

አንድ ነገር እንድታቂልኝ እፈልጋለሁ ... አንቺ የሌላ ሰዉ ሁነሽ ..ትዳር ከሌላ ሰዉ ጋር ብትመሰርች ፀቤ ከአንቺ ወይም ከአገባሽ ሰዉ አይደለም..ፀቤ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር ነዉ..... ለምን ብትይ ሀጅ ባደረኩበት ጊዜ አላህን ከሁሉም ሀጃየ አስበልጬ ስጠይቀዉ ስለምነዉ የነበረዉ....አንቺ የኔ እኔድትሆኝ ነበር... አላህን ስለምነዉ የነበረዉ ከአንቺ ልጅ መዉለድ እስከ እለተ ሞቴ አንቺ ጋር አብሮ መኖር ነዉ አለኝ
....ይሄን ሲለኝ አብረዉ ጓደኞቹ ነበሩ... ይሄን እየተናገረ ሚፍታህ እምባ ነዉ የቀረዉ፡፡
ቁርጤን ንገሪኝ ቁርጤን ንገሪኝ ..የሌላ ስትሆኝ ማየት አልፈልግም የኔ ብቻ ሁኜ እባክሽ እያለ ይለምነኛል
........እኔም በጣም ተወዛገብኩ ግራ ገባኝ...ሚፍታህ ዉሳኔየን በስልክ ደዉየ አሳዉቅሀለሁ አልኩት

ከሱቁ ወጥቼ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ ነዉ... ልቤ ተሸበረ ...ዉሳኔ መወሰን አልቻልኩም ...የማልክደዉ እዉነት ቢኖረዉ ሚፍታህ በጣም እወደዉ ነበር ለመጋባት ድረስ ደርሰን ቤተሰብ ለቤተሰብ ተጠይቆ እሺ ተብሎ ጨርሰን እንደነበር በአለፈዉ ታሪክ ላይ ታስታዉሳላችሁ...ሚፍታህ አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ሲለኝ የማላቀዉ ስሜት ከየት መጣ የማልለዉ ወረረኝ ...እሱ ጋር ያሳለፍኳቸዉ የፍቅር ገጠመኞች ጊዚያቶች ፊቴ ላይ እንደመስተዋት መልሶ ያሳየኛል

  ከዛ እንደዚህ እየተጨናነኩ የምወስነዉ ግራ ገብቶኝ ሁለት ልብ ሁኜ ለካሊድ ደወልኩለት፡፡
  ሰላምታ ከተለዋወጥን ----- ካሊድ እኔን ብታጣኝ የሌላ ብሆን ምን ይፈጠራል ብለህ ታስባለህ ? እኔን አጥተህ ብትኖር ምን ይሰማሀል ??? ብየ ጠየኩት
......ካሊዶ ለካ እንደሌሎቹ ወንዶች አይደለም የመለሰልኝ መልስ አስገራሚ ነበር እንደዚህ አለኝ ... #አንቺን_ማጣት_ምን_እንደሆነ_ነዋል_የኔ_ባትሆን_የሚለዉን_በጭራሽ_ማሰብም_መገመትም_አልፈልግም ፡፡ አንቺ የሌላ ስትሆኝ እንዲህ እሆናለሁ ብየ ምሳሌ እንኳ መስጠት አልፈልግም ... ነዋል እኔን ለመቀለድ ብለሽ እንኳን እንደዚህ አይነት ጥያቄ ዳግመኛ እንዳትጠይቂኝ...አለኝ

ወላሂ ጥፋቱ የኔ ነዉ.... ሶስት አመት በትዕግስት ጠብቆ ከነማንነቴ ተቀብሎኝ...ገና ሚፍታህ አንቺን ነዉ ማግባት የምፈልገዉ ሲለኝ ልቤ ወላዉሎ ካሊድን ይሄን ጥያቄ መጠየቄ ከደወልኩ ቡሀላ ብቻየን አፈርኩኝ..

ዉየ ሳላድር ወዳዉኑ ለሚፍታህ Text ላኩለት ...እንደዚህ አልኩት>>>>> ሚፍታህ ከአሁን ቡሀላ ወደ ሆላ መመለስ አንችልም ትናንት ከትናንትናዉ ጋር አብሮ አልፏል ..በርግጥ የማልዋሸህ በፊት እወድህ ነበር ያደግሞ በጊዜዉ አልፏል ...፡፡ አሁን ላይ መጉዳት የማልፈልገዉ የምወደዉ የሚወደኝ እሱን አጥቼ እሱም እኔን አጥቶ መኖር የማይችል እኔም እሱን አጥቼ መኖር አልችል ሁኜ ልቤ ዉስጥ ያስቀመኩት እሱም ያስቀመጠኝ ሰዉ አለ ብየ ላኩለት......
 

  ሚፍታህ ጋር በዚሁ message አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያየን...አንድ የወንድ ልጅ ድክመት አለች እየወደዱ ማግባት እየፈለጉ የተሻለ አገኛለሁ ብሎ ከኔ ዉጭ አታገባም ትጠብቀኛለች ብለዉ እያሰቡ ነገር ግን እሷን የሚወዳት አግኝታ ልታገባ ስትል ትጠብቀኛለች ብሎ ያሰበዉ እንደ አዲስ ከእንቅልፉ ሲባንን ይስተዋላል፡፡ ታዳ ሚፍታህም አገባሻለሁ ብሎ ሽማግሌ ልኮ አጭቶኝ ጥፋቴን ሳላቀዉ አመታት ያህል ረስቶኝ ነገር ግን ላገባ ነዉ ስለዉ እንደገና በቅናት ተንገብግቦ አንቺን ነዉ የማገባዉ ማለቱ አግባብ አይደለም..ሴትነት የእናት ነት የእህትነት ደረጃ እንጂ የምርጫ የቅርጫ ለትዳር መወዳደሪያ አይደለችምና፡፡



ካሊድ ከ 15 ቀን ቡሀላ ቅዳሜ ሽማግሌ እልካለሁ አለኝ
....እኔም መርሀባ ብየ ተስማማሁኝ፡፡


እነዚህ አስራምስት ቀናት ለሁለታችንም እርቃልብናለች ቀን በቀን በተደዋወልን ቁጥር ይሄ ቀን ቀረን እያልን ሲቀርብ ሲቀርብ ..ሶስትም አልፎ ሁለት ቀናት ቀረን ፡ ነገ ቅዳሜ ሁኖ ዛሬ ጁምአ ላይ ደርሰናል  
......ከዛም ጁምአ ቀን የኔ ፈተና መቼም አይለቅ ...ያልተሳበ ይሆናል ብየ ያልገመትኩት በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል....ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም.....



#ክፍል

ይ...............ቀ.............
..........ጥ...........ላ...............ል

Join
_ ___
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.8K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 09:23:08 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ አምስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? አልኩት
......ካሊድም ቤተሰቦቼ በሌላዉ ሒወቴ እንጂ ጣልቃ የሚገቡት በዚህ የትዳር ሒወት የምወስነዉ እራሴ ነኝ ...ደግሞም ቤተሰቦቼ ስለፀባይ ስለዲን ነዉ የሚጠይቁኝ እንጂ አንቺ ስለምትይዉ በጭራሽ ትዝም አይላቸዉ አለኝ

  እኛ ሀገር አንድ ባህል አለ ..ሁለት ጥንዶች እንደተጋቡ ...አዳሩ ላይ በሩ ላይ ሁነዉ ዘመዶች ያዳምጣሉ የሴቷ የጩኸት የማቃሰት ድምፅ ካልሰሙ አይተኙም ...ከአዳራቸዉ ቡሀላ ጠዋት ላይ የወንዱ ዘመዶች በር ላይ ሁነዉ ይጠብቃሉ... አዲሱ ሙሽራ በቀይ ደም የተበከለዉን አንሶላ ካላሳያቸዉ ድንግል ናት ብለዉ አያምኑትም፡፡ ማታ የወንዱ ቤተሰብች ገብተዉ አንሶላዉን ያነጥፋሉ ጠዋት ደግሞ አንሶላዉን ማሳየት አለበት ፡፡ ሙሽራዉ ድንግል ናት ብሎ ሲናገር..የወንዱ ቤተሰቦች ደስታ በደስታ ነዉ የሚሆነት እልልታዉ ጭፈራዉ #ሰበታ_መቀነት ይባላል... ከሰርጉ ያልተናነሰ ጭፈራ ይጨፈራል የወንድ ቤተሰብ ቤት ይደምቃል ፡፡ ከዛም ሴቷ ቤተሰብ ቤት ተሂዶ ልጃችሁ ስነስርአት ያላት አደበኛ ጨዋ የሽማግሌ ልጅ ናት ተብሎ ስጦታ ይሰጣል ......

እኔም ይሄን ባህል ስለማቀዉ ካሊድ ለቤተሰቦችህ እንዴት ልታደርግ ነዉ አንተ ??? አልኩት
.....እሱም አብረን የምናድረዉ እኔ እና አንቺ ነን እነሱ ምን አገባቸዉ መቼም መኝታ ክፍላችን ገብተዉ አፍጥጠዉ አያድሩ ...እኔ እራሴ የምላቸዉን አቃለሁ ....ለምን እንደዚህ አይነት ሀሳብ ታስቢያለሽ ???  ብሎ እኔ በተናገርኩት እሱ ይናደዳል ...
ነዋል እኔ ብቸኛ አንድ መሆኔ ሰልችቶኛል ..ከአንድ ይልቅ ሁለት መሆን ስቃይ ደስታን ለመጋራት ይመቻል...እኔ የናፈቀኝ ሀሳብ የሆነብኝ መቼ ይሆን እኔ እና አንቺ እኔም የአንቺ አንቺም የኔ የምትሆኝዉ ነዉ ሀሳቤ ጭንቀቴ....እናም ትዳር ነዉ የናፈቀኝ አለኝ..

ትዳር ሐላል አክሲዮን ነው፡፡ አክሲዮኑ በሁለት ተፈቃቃጅ በሆኑ ወንድ እና ሴት መካከል የሚመሰረት ግንኙነት ነዉና እንደዋዛ መታየት የለበትም፡፡ እንደዋዛ ከታየ እንደዋዛ ይፈርሳል፡፡

ትዳር ከሐራም ኑሮ ወደ ሐላል ግቢ ሽሽት ነው፡፡ ከጉድለት ሕይወት ወደ ሙሉነት ቤት ሩጫ ነው፡፡ ጠፍቶ የቆየን ግራ ጎን ማሟያ ፍለጋ ፅድቅ ስደት ነው፡፡

ትዳር የንፅህና ሻወር ነው፡፡ ሲንከራተት ለኖረ ዐይን ማረፊያ ነው፡፡ ሲባዝን ለኖረ ልብ ማስከኛ ነው፡፡ ፍላጎትን ሐላል እና ነፍስ በምትወደው መልኩ ለማሳካት ምክንያት ነው፡፡

ትዳር ባልና ሚስት ተፈጥሯዊ ስሜታቸዉን ሐላል እና አላህ በፈቀደው መልኩ የሚያረኩበት ጥምረት ነው፡፡ ለዚህ ጥምረት ዘላቂነትና ስኬት ከወዲሁ ሀሳብን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ “ከሞቀኝ እቀጥላለሁ ከበረደኝ እወጣለሁ” በሚል ስሜት የተገባበት ቤት የመፍረስ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከሙቀቱ ይልቅ ብርዱ ሊበዛ ይችላልና፡፡ ሀብት ንብረት ለመካፈል ብለው የሚገቡበት ጥምረት ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ሀብት ንብረቱ አልገኝ ሲል ያነጫንጫልና፡፡ “አለው” ብለው የተቀበሉት ኪዳን አይዘልቅም፡፡ ያጡ ቀን ባህሪን ያባላሻልና፡፡

ትዳር በሕይወት በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ባልና ሚስት የሚኖሩበት ህንፃ ነው፡፡ በዚህ ህንፃ ግንባታ ላይ የአላህ እጅ እንዲኖርበት መፍቀድ ብልህነት ነው፡፡ ብቻችንን የምንሰራው ቤት.. ቤት አይሆንም፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) የሌለበት ቤት መሰረቱ ደካማ ነው፤ ጣሪያውም ያፈሳል፣ ግድግዳው በቀላሉ ይዘማል፣ ምሰሶው ያረገርጋል፣ ሁለመናው ስጢጥ ስጢጥ ይላል፡፡
ትዳርን ስናስብ ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ሰበቡን እናሟላ፡፡ አላህን በቤታችን ስናኖረው ያኔ የቤታችን መሰረት ፅኑ ይሆናል፣ ምሰሶው መሬት ይይዛል፣ ግድግዳው ቀጥ ይላል፡፡
ለአላህ ብለው ያሰቡት ነገር የሱ ጥበቃ አለበት፡፡ አላህ የሰራው ቤት አይፈርስም፣ እሱ ያነጸው ህንፃ አይዘምም፡፡ አላህን ከፊታችን እናድርገው፡፡ ትዳር ወሳኝ ነገር ነዉና ቤታችንን በበረከትና በፍቅር ይሞላልን ዘንድ እሱን እናስቀድመው፡፡ ዋናዉና መቅደም ያለበት እሱ ነዉና የሚቀድመውን በማስቀደም የሚከተለውን እናስከትል፡፡ ለባለትዳሩም የትዳር እድሜ ይስጣችሁ ..ላላገባንም አላህ ፈላጊ ከፈላጊ ያገናኝ አሚን...

           ካሊድ ለኔ ያንን ሁሉ የሒወት ዉጣ ዉረድ አልፌ ለዚህ በቃሁኝ ....ደስተኛ ለመሆን መሞከር ረጅም ለመሆን የሞመከር ያህል ለኔ በጣም ከባድ ነበር የሆነብኝ
ዛሬ የምወደዉ የሚወደኝ ፍቅር ምን እንደሆነ በዱንያ ምድር ካሊድ አሳየኝ፡፡ ፍቅር ማለት ይሄ ነዉ ..ፍቅር ከሆነ ግድ መተማመን አለ .. ካሊድ ቢወደኝ ቢያመነኝ ነዉ ሒወቴን ያረጋጋዉ...ደግሞ ባለፈዉ ታሪኬ እንደ ዶክተር ሷሊህ ያለ ተስፋ እንድቆርጥ የስነልቦና ጫና አድሬሶብኝ...ወንድ እና ቁንጫ በልቶ እሩጫ ብየ ከትዳር አለም ተስፋ ቆርጬ ነበር........የብዙ አመት ጠባሳየ ሲያመኝ ሳለቅስ ከሰዉ በታች ነኝ ብየ ሁሌ እራሴን እንደ አሰብኩ እንደ ካሊድ አይነት ጥሩ አስተሳሰብ ያለዉ ሒወቴን ልቤን ማንነቴ ሳይቀር በእሱ መለሰልኝ ..እኔ ሁሌ ድንግል ነኝ ብየ እንዳስብ አረገኝ...አዎ ሁሌም እኔ ድንግል ነኝ... ለምን አስቤበት አምኜበት ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ አሳልፌ የሰጠሁት አይደለም... ገና በልጅነቴ እህሉን ከአፈር በማለይበት ጊዜ ተገድጄ የተቀበልኩት ነዉ፡፡

በሳምንቱ ጁምአ ደርሶ በተለመደዉ ሰአት ተገናኝተን...... ካሊዶ ጋር እያወራን ሁሌም ድንግል ባለመሆኔ ስቆጭ
.....እንደዚህ አለኝ ... ነዋል አትሰቢ አትጨናነቂ ይሄ ተራነገር ነዉ እኮ...አንቺ ግድ መሆን አለብኝ ብለሽ ካሰብሽ የአላህ ነገር አይታወቅም ተስፋ መቁረጥ አንችልም ..... ድንግልም ልትሆኝም ትችያለሽ እኮ.......ለምን ብትይኝ ገና በልጅነትሽ በ4 አመትሽ ነዉ ይሄ በደል የደረሰብሽ ..እና በዛ እድሜ ደግሞ ልጅ ስለሆንሽ የሚጠብቅሽ መላኢካ ነዉ ..እናም ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጭ በአላህ ፍቃድ አንቺ የለኝም ብለሽ የምታስቢዉ ነገር ሊኖር ይችላል አለኝ......


.....,እኔም የHealth ተማሪ እንደመሆኔ መጠን አንዴ ድንግልና ከሄደ እንደማይመለስ አቃለሁ ..ካሊድ በጭራሽ መሆን አልችልም አልኩት
..... ምነዉ ነዋል ከአላህ እኮ ተስፋ አይቆረጥም አለኝ፡፡ ካሊዶ እንደዚህ ሲለኝ እዉነቱን ነዉ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብየ እንደገና ሞራል ሰጠኝ፡፡

    አንድ ቀን የሞባይሌ ባትሪ ተበላሽቶ ለመግዛት ጂማ መርካቶ ሰፈር አካባቢ አንድ ኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ስገባ..ያየሁትነ ማመን አቃተኝ ...በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ሚፍታህ ጋር ተገናኘን
....እሱም ድንጋጦ ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
.......እኔም ወአለይኩም ሰላም ሰላም ነዉ አልኩት
....እሱም እንዴት ነሽ ሁሉ ሰላም ቤተሰብ ሰላም ናቸዉ?? አንቺስ እንዴት ነሽ ??አለኝ
1.5K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 08:37:46 ከወንጀል ተከልክለዉ ኑረዉ... ትዳር ላይ ሲገቡ ምሽት ላይ በማታየዉ ምልክት አጅሬዉ ነብር ይመስል ደም ካላየ አንቺ ድንግል አይደለሽም እየተባለች ባልሰራቸዉ ስራ ባልሰራቸዉ ዚና በባሎች ተጠርጥራ በግራ አይን እንድትታይ .... ነገሩም ከከፋ እስከ መፋታት ድረስ የሚደርሱ ብዙ ትዳሮች እያየን ነዉ፡፡ ዉድ እንቁ እህቶች በዚህ ምክንያት ፈጣሪ በሰጣቸዉ ፀጋ ለምን ደም አላየንም አንቺ ዉሸታም ድንግል ነኝ ብለሽ ዋሸሽኝ እየተባለች በባሎች ማሸማቀቅ ምነዉ አግብቼ ባልነበር እያሉ ሲያለቅሱ የሚኖሩ ብዙ እህቶች እንዳሉ ቤት ይቁጠረዉ ፡፡ ወንድሜ ሆይ!!!!! ደም መድማት ብቻ ነዉ እንዴ የድንግልና መገለጫ ??? አትሳሳት ከአእምሮህ ላይ ደም ብቻ ነዉ የሚለዉን ፍቀህ አዉጣዉ....ደም ማየት ብቻ የድንግልና ማረጋገጫ አይደለም፡፡

መጀመሪያ ስለድንግልና ትርጉም እወቅ.. ድንግልና ለሴት ልጅ ብቻ አይደለም ለወንድም አለ...ነገር ግን ምን ይደረግ የወንድ በሴት ልጅ መታወቅ አይችልም..አንተ አወኩኝ ብለህ የምታሸማቅቅ ከሆነ ...የአንተን ማንነት የሚያቅ ፈጣሪ እንዳለ አደራ አንዳትዘነጋ ፡፡ #ድንግልና ማለት የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም ማለት ከግብረ ስጋ ግንኙነት (ከሩካቤ ስጋ) መቆጠብን ይመሰክራል ፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነት ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና(የንፅህና ክብር) ወይም ድንግልና ይባላል፡፡

#ድንግልና_በምን_ይገለፃል?
በእርግጥ ሁለቱም ፆታዎች መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡንና መፅናቱን ተከትሎ የሚታይ የአካል ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል።
ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው።

ይሄ በጣም ስስ የሰዉነት ክፍል(አካል) በቀላሉ ሴት ልጅ ልታጣው ትችላለች፡፡ ለምሳሌ፡- ሳይክል በመንዳት ፣ ፈረስ በመጋለብ ፣ ጅምናስቲክ የመሳሰሉ እስፖርቶችን በመስራት...በሀይድ መደራረብ...በከባድ ህመም ወዘተ ያለምንም ፆታዊ ተራክቦ ታጣዋለች።

#የድንግልና_አይነቶች_ስንትናቸው?
አምስት አይነት የድንግልና አይነቶች አሉ። እነርሱም #አንደኛዉ ➊ ☞ ሙሉ የብልት አካል በራፍ ላይ እንደ መጋረጃ የዘጋው ሲሆን የእጃችን ቀዳዳ ምታክል ክፍተት አለው ለወር አበባ መፍሰሺያ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ። ይሄ ቀዳዳ ሙሉ የድንግልናውን ቦታ አይሸፍንም የድንግልናውን መጋረጃ ሩብ ምታክለዋ ቀዳዳ ናት።

#ሁለተኛ ➋☞ ብዙ ጊዜ ባይሆንም አንዳንድ ሴቶች ላይ የወንፊት መልክ በተያዘ በርካታ የተበሳሱ ቀዳዳዎች የተሞላ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ።

#ሶስተኛ ➌☞ በተፈጥሮዋ ምንም የተጋረደ ነገር የለዉም ፡፡ በመጀመሪያው ግንኙነትዋ ጊዜ የሚፈስ ደም የሌላት ሴት አለች ድንግል እንደሆነች የምታውቀው እርስዋ ብቻ ናት ምንም ድንግል እንደሆነች ምልክት አታሳይም ደም አይፈሳትም።

#አራተኛ ➍☞ ድንግልናው በተፈጥሮ የጠነከረና በወንዱ ብልት ሊበጠስ የማይችል ነው ፡፡ይሄ አይነት ድንግልና ያላቸው ሴቶች ድንግልናቸውን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በሰርጀሪ ወይም በቀዶ ጥገና ወቶላቸው ነው ግንኙነት የሚፈፅሙት።

#አምስተኛ ➎☞ ሴትዋ ምንም አይነት የድንግልና መጋረጃ ሳይኖራት በብልትዋ ግርግዳ በኩል ብቻ ትናንሽ ሄመኖች ሲገኙ እነሱም የሚወገዱት በወንዱ ብልት ፍትጊያ ነው።
የሴቶች ድንግልና እላይ በጠቀስኳቸዉ አምስቱ ምክንያት ከፈጣሪ የሚሰጣቸው የተፈጥሮ ፀጋ ነው፡፡
.ይህ ፀጋ ደሞ የሚገኘው በመወለድ አንድ ጊዜ ነዉ፡፡ እድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሳ አሻራን ጥሎ ሚያልፍ ነው። ብዙዎቻቹ የመጀመሪያ ግንኙነታቹን አይረሱትም ለዛ ነዉ ወንዱ ድንግል ምርጫዉ ያደረገዉ፡፡ እናም ወንድሞቼ ደም ካላየሁ ድንግል አይደለችም ብለህ ንፁህ እህትህን ሚስትህን ለተናግሮ ተናጋሪ እንዳትሰጥ በተጨማሪ ከእኔ በፊት ከሌላ ጋር ባልጋለች ብለህ እቺን ንፁህ እንስት እንዳታረክስ ፡፡ የለቅሶዋ ምክንያት እንዳትሆን፡፡


ከዛም ጁምአ ደረሰ እና ብቻችንን ሂደን የምናወራበት፡ቦታ በመኪናዉ ሄድን ... ከአሁን ቡሀላ ጊዜ አንፍጅ አንቺም እቤት አሳዉቂ እኔም አሳዉቃለሁ በቅርብ ቀን ሽማግሌ ልልክ አስቢያለሁ ..አንቺ ምን ሀሳብ አለሽ ?? አለኝ
.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? ብየ ጠየኩት
.....ካሊድም እንዲህ አለኝ_

#ክፍል

ይ.............ቀ.................
........ጥ............ላ...................ል

join

        . t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
441 viewsedited  05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ