Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ #የመጨረሻዉ_ክፍል

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


ከዚህ ፍልሚያ ቡሀላ ያልተጠበቀ ይሆናል ብላችሁ የማጠብቁት ነገር ተፈጠረ

እኔም ካሊድም ገረመን አላህ ምን ይሳነዋል..
ይገርማል አረ በጣም ይገርማል ገርሞም ይገርማል የሚገርም ነዉ... #ድንግል ነበርኩኝ ፡፡ በአራት አመቴ ተደፍሪያለሁ እያልኩ ሳለቅስ ኑሬ ...በትምህርት ቤት በሰፈር በልጅነትሽ የተደፈርሽዉ እያሉ ሲያስለቅሱኝ ሲያገሉኝ ያለፉት የኖርኩባቸዉ አመት አላህ እኔን እየፈተነኝ እንደሆነ ተረዳሁኝ
...ካሊድም እየተገረመ ነዋል ታስታዉሻለሽ በምታለቅሽበት ጊዜ የአላህ ነገር አይታወቅም ድንግልም ልትሆኝ ትችያለሽ ስልሽ አላምንም ብለሽ ነበር ከአላህ ምንም ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም አለኝ

#የጫጉላየ_ምሽት

ፊቴ አብርቶ ጥርሴ ይስቃል
ከጀርባ ያለዉ ሀዘን ከቶ ማን ያዉቃል
እንዲህ ደምቄ ፈክቼ ላየኝ ሰዉ
በሆዴ ፍም እሳት ያለም አይመስለዉ

ዛሬ ላይ ሁኜ የትናንቱን ግፍ አስታዉሳለሁ
በትዝታ መስኮት እያንዳንዱን ህመም እመለከታለሁ

በጨቅላ እድሜየ ክፉን ከደጉ ባለየሁበት
ጫማ ለመልበስ ግራዉን ከቀኙ ባላወኩበት
ስጋና አጥንቴ ከደሜ ጋራ ሳይዋሀዱ
ሁለቱ እግሮቼ እንኳን እርቀዉ ሳይራመዱ
ሲመሩኝ ምመራ ኩልትፍትፍ የምል
ዉብ ፅጌሬዳ ሲያዩኝ ደስ የምል

እንኳን ጭካኔ ለኔ ሊገባኝ
ለቁንጥጫ እንኳን የማሳሳ ነኝ
ምን ዋጋ አለዉ የሰዉ አዉሬ ጨከነብኝ
ለማይረባ ለደቂቃ ስሜቱ ተጫወተብኝ
ከሰዉ በታች አድርጎ እንዳልነሳ ቀበረኝ
አንገቴን ላይነሳ እንድደፋ አደረገኝ

ያ! ሰው መሳይ ሰው ያልሆነው
ህልሜን በአንድ ቀን አጠልሽቶ በላዉ
ቅስሜን ሰብሮ ልቤን አደማዉ
ያ የሰዉ አዉሬ ደስታየን ነጥቆ ሀዘን አሸከመኝ
ሚስጥሩን ያወቀም ከጎኔ እንዲሸሽ አረገኝ


ሂወትን በጠላሁ ሰው ባጣሁ ሰአት
ሞቴን ስናፍቃት ቀብሬን ስመኛት
ትዝ አለኝ አንድ ቃል የመጠጊያዬ
ለምኑኝ ሰጣለው ያለውን ጌታዬ

ያኔ በጥዋት በማታ በቀን በለሊት
እንባየ ሲፈስ ለብዙ አመታት
አብሽሪ የሚለኝ ሀዘኔን አይቶ
እንባየን አባሽ አንድ ሰዉ ጠፍቶ
ተደፍረሻል ብለዉ ሰዎች ሲሸሹኝ
እጆቼን ዘርግቼ ያረቢ አልኩኝ

እኔም ሁሉንም ትቼ ወደሱ ሸሸሁ
እንደመርየም ንፁህ መሆንን ተመኘሁ
ማንነቴን የሚቀበለኝ ደግ ባሪያህን ስጠኝ ብየ አንገቴን ሱጁድ ላይ ደፋሁ
ሌት ተቀን እየሰገድኩ አምርሬ አነባሁ
ያረብ አልኩት አላህም ዱአየን ሰምቶኝ
ማንነቴን ተቀብሎ የወደድኩት የወደደኝ
ደጉን ባሪያዉን የዱአሽ ዉጤት ብሎ ሰጠኝ
ሀዘንሽ ሀዘኔ ደስታሽም ደስታየ ብሎ ተቀበለኝ

የበደለኛ እንባ መች ይቀራል ፈሶ
ትአምር አየሁ ዱአየ ደርሶ
ልክ እንደመርየም እንደጠየኩት
ቢክራ አደረገኝ በሰርጌ ምሽት
በደቂቃዎች ሁኔታዎችን የሚቀያይር
ለኛም አሳየን የማይታመን ትልቅ ታአምር

ነብዩ ዪኑስን
ከአሳ ነባሪ ፈልቅቆ አወጣዉ

ነብዩ ሙሳን
ከሚያሰምጥ ዉሀ ነፃ አወጣዉ
ነቢዩ እስማኤልን
በአንገታቸዉ ላይ ያንን ቢላዋ አቅም አሳጣዉ

ለነቢ ኢሳ
የሞተዉን ሰዉ ህያዉ እንዲያደርግ ችሎታ ሰጠዉ

ነቢ ኢብራሂምን
ከዛ ከነበልባሉ ከአስፈሪዉ እሳት ነፃ አወጣዉ

የሰዉ ዘርን
ከአፈር ከጭቃ በታላቅ ጥበብ አቡክቶ ሰራዉ

ከመርየም ገላ ክብርዋ ሳይነካ ልጅ ፈጠረው

ታድያ...!

ይሄን ያረገ ታላቁ ያመውላ
ድንግል ማድረግ የነዋልን ገላ
እንዴታ ይሳነው እሱ እኮ ጌታ ነው
ሁሉ ሚታዘዘው ሁን ሲል የሚሆን ነው

ዛሬ ያሁሉ ሀዘንና ስቃይ ተወግዶ
በደስታ ተተካ የሀዘን ተራራዉ ተንዶ
አልሀምዱሊላህ ከማለት ዉጭ ምን ይባላል
በርግጥም ሁኔታዉ አጃኢብ ያስብላል
እልፍ ምስጋና ጥራት ይገባዉ
ለአንዱ ጌታችን ወደር ለሌለዉ

ይሄዉ ከአራት አመቴ ጀምሮ ሳለቅስ የኖርኩትን በአንድ ቀን ወደ ደስታ ቀየረዉ...በጣም ደስተኛ ነኝ ያለፉትን ጊዜያት ሀዘኔ  ከአሁኑ ደስታ ሳወዳድረዉ የሰማይና የምድር ልዩነት አለዉ ሌላ ምን ይባላል አልሀምዱላህ


ልብ በይ እህቴ!!!! በሴቶች ላይ የሚገኘዉ ገቢ በዓመት ከ7ቢሊየን ዶላር እንደደረሰና..ይህም ገቢ ከመሳሪያ ሽያጭና ከአደንዛዥ እፅ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናቶች ይገልፃሉ

እህቴ ሆይ የሴቶች እኩልነት ብለዉ ምዕራባዉያን ለአንቺ የሰጡሽ መብት ምን አንቺን ለማጃጃል እንደሆነ ምን ያህል ታቂያለሽ? ለምሳሌ ስፔን እንዉሰድ የሴቶች መብት ተብሎ መስሪያ ቤት ገብተዉ እየሰሩ ነዉ ..በስፔን በተደረገዉ ጥናት ከአንድ ሚሊየን በላይ ሴቶች በየመስሪያ ቤቱ የመደፈር ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ ብቻ በተደረገዉ ጥናት 13100 ሴቶች በአለቃዎቻቸዉና በስራ ባልደቦቻቸዉ የመደፈር ሙከራ ተደርጎባቸዋል..በአጠቃላይ 15% የሚሆኑት የስፔን ሴት ሰራተኞች በጠቅላላ 8ሚሊየን 425 ሺ ሴት ሰራተኞች ለመደፈር አደጋ እንደተጋለጡ ጥናት ያሳያል፡፡ደፈራ የተደረገባቸዉ ሴቶች ስማቸዉን ለመጠበቅ እና ከሀፍረታቸዉ የተነሳ ለሚመለከተዉ አካል ክስ አይመሰርቱም ..ክስ ለመመስረት ሙከራ ያደረጉት 25% ብቻ ናቸዉ..56% ተደብቀዉ ይገኛሉ..8% የሚሆኑት ክስ በመመስረታቸዉ ከአለቆቻቸዉ ከሚሰሩት ድርጅት ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል..45% የሚሆኑት ከስራቸዉ እንዳይባረሩ የመደፈርን ችግር ተቀብለዉ ጊዚያቸዉን ያሳልፋሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሴቶች ለጭንቀት ለመረበሽ ሰላምና እንቅልፍ አልባ ለመሆን አደጋ ስለተጋለጡ የማስታገሻና የማረጋጋት መድሀኒት ለመዉሰድ ተገደዋል፡፡ ሴቶች በእኩልነት ወደ መስሪያ ቤት በመግባት ባስከተለባቸዉ የጭንቀት በሽታ በአሜሪካ 61% በኢማራት 38% የጭንቀት ማስታገሻ መድሀኒት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እናም እህቶቼ መብቴ ነዉ እያልሽ በዚህ አዘቅት ዉስጥ እንዳትገቢ አንቺም ተጠንቀቂ ሰዉ ሲሸወድ ሲዘነጋ በአንድ ቀን አይለይም በሒደት በጊዜ ብዛት እየተንሸራተተ ነዉ የሚሄደዉ የአቋም መዋዠቅ ሲገጥምሽ ጠርጥሪ

★ የሴት ልጅ ጥቃት መቼ ነዉ የሚያበቃዉ? አንተም እሱም እነሱም እነዛም ዘር ብሔር ሀይማኖት ሳይለያየን ከጎናችን ቁሙሉን ..ሴት እናትህ ነች እህትህ ነች ለቅሷዋ ሊያስለቅስህ ሊያስዝነን ይገባል፡፡ ለሴት ልጅ ክብር የሚጨነቅ ሴትን ልጅ ለስሜት ብቻ ማሰብ ትተን በሆዷ ዉስጥ አፍና የምትዞረዉን የፉም እሳት ለመረዳት ሞክሩ .ሴት ልጅ ሀዘን በዉስጧ እያለ በጥርሷ ደስተኛ ተጨዋች መስላ መኖር የምትችል ፍጥረት ነች .ማንኛዉም ሴት ስለሳቀች ስለተደሰተች ደስተኛ አይደሉም ብዙዎቹ ለሊት ላይ ሲጨነቁ ሲጠበቡ ሲያለቅሱ የሚያድሩ በብዙ የሀሳብ ማዕበል እና ሆዳቸዉ ዉስጥ ተናገረዉ የማይወጣ የሚቀጣጠል ጥፋ ቢሉት የማይጠፋ እንደዉም እየተፏፏመ የሚሄድ የእሳት ማዕበል ተሸክመዉ የሚሄዱ ናቸዉ ..እናም አንተ ወንድ ነህ በእሳት ላይ እሳት ከመጨመር በሆዷ ያለዉን እሳት አንተዉ ተረድተህ በስሜት መነዳቱን ትተህ ሸክማን በሀሳብህ ተቀብለህ እሳቱን በብልሀት አጥፋላት..የዛን ጊዜ አንተ ለሷ የደስታ ምንጭ እና የህሊና እረፍት ታገኛህ
ታሪኬ ከሞላ ጎደል ይሄን ይመስላል፡፡
አሁን ላይ የአንድ ልጅ እናት ነኝ...ወንድ ልጅ አላህ ሰጥቶኛል አድጎ ለዲነል ኢስላም የሚጠቅም ልጅ እንዲሆን ዱአ አድርጉልኝ፡፡