Get Mystery Box with random crypto!

★ዉድ አንባቢዎች ይሄን ታሪክ እንዲቀርብ የፈለኩት ለኔ ባይጠቅመኝም ግን እንደ እኔ ብዙ የተጎዱ ስ | ISLAMIC SCHOOL

★ዉድ አንባቢዎች ይሄን ታሪክ እንዲቀርብ የፈለኩት ለኔ ባይጠቅመኝም ግን እንደ እኔ ብዙ የተጎዱ ስላሉ ከኔ ትምህርት እንዲወስዱ እና ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባቸዉ ለማስታወስ ያህል ነዉ
★ፀሀፊ አሚር ሰይድ ከደሴ ከተማ ከልብ አመሰግናለሁ በየaudio የላኩልህን እና በስልክ ያጫወኩህን ዉሸት ሳትጨምር እንደዚህ በሚያምሩ ቃላት አሳምረህ በማቅረብህ ከልብ አመሰግናሀለሁ፡፡


የኔ የአሚር ሰይድ ለማጠናቀቅ ያህል በዚህ እዉነተኛ ታሪክ የተወሰነ ልበል፡፡
በዚህ በነዋል ታሪክ ለእሷ ጥንቃቄ ሲባል የእሷ ስም የምትኖርበት ከተማ ተቀይሯል...
   ባለታሪኳ ነዋል ታሪኩን የነገረችኝ ለካሊድ መደፈሯን ከነገረችዉ ቡሀላ ሽማግሌ ሊልክ ሲል ነበር....ከዛ ቤተሰቦቿ ሲጣሉ ሚፍታህ መልሼ ልላክ ሲል እንደ አጋጣሚ እኔን ነበር የምታማክረዉ በሚዲያ ያገናኘን ምርጥ እህት ወንድም ሁነን ነበር ጠዋት ማታ ነበር የተፈጠረዉን እየደወለች እየነገረችኝ በመመካከር ነበር ለዚህ ትዳር  እንድትደርስ የሆነችዉ
☞ሚፍታህ መልሶ ልላክ ሲል የነዋል ሁብ የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነዉና..ሚፍታህን ፊት እንዳትሰጥ ማግባት እንደሌለባት ያሳመንኳት እኔ ነበርኩ....እኔ ከሚፍታህ የካሊድ ደጋፊ ነበርኩ ሚፍታህን እንዳታገባ ካሊድን እንድታገባ ያደረኩት እሷ ጋር ስንመካከር በማሳመን ነበር መቼም ከታሪኩ ትረዳላችሁ፡ መቼም አላህም የፃፈዉ ነዉ ካሊድ ጋር በመሆኗ ምንም ቁጭት እንደሌለዉ  ትረዱኛላችሁ ብየ አስባለሁ...
ሚፍታህን ነዋል እንደምወደዉ ባቅም ግን የሴት ልጅ ፍቅር ለትዳር በቂ አይደለም እሷን ከ3 አመት በላይ የሚወዳት ብታገባ ይሻላል ብየ ነዉ፡፡ ሲጀመር ሚፍታህ ለሰዉ ልዳርሽ ብሎ ጀምሮ ነዉ በሰዉ እርዚቅ ገብቶ ነዋል ጋር የጀመሩት ካሊድ ግን ሁሌም ይወዳታል ነዋል ትገበዋለች ብየ እኔም በተደዋወልን ቁጥር በሚፍታህ ፍቅር ብትቸገርም ካሊድን እንድታገባ ተፅእኖ ፈጥሬበታለሁ፡፡ የነዋል ባህሪ ደስ የሚለዉ ሰዉ ትሰማለች ታገናዝባለች እንደአሁን ሴቶች ችኩል አይደለችም ..በፊት እሷ በዛ ችግሯ እኔን አማካሪዋ በማድረጓ ሁሌም ትዝ ባለኝ ቁጥር ደስተኛ ነኝ፡፡
ሚፍታህ ሌላ ሲያገባ ምንም እንዳይመስልሽ ነበር ብየ ከእሷ አግብቶ በመራቁ ሞራል ስሰጣት የነበረዉ..ሚፍታህም ጓደኛዉ የሱፍም ሲያገቡ አዉቅ ነበር ለምን ከነገረችኝ ቡሀላ ታሪኩ ላይ ያልተፃፈ ብዙ ፈተና ስለነበር..ይሄን ፈተና እኔ ከደሴ ሁኜ አብረን ነበር በመወያየት በመመካከር ለዚህ ደረጃ ነዋል የደረሰችዉ
☞እኔም ጋር ስታወራ ነዋል በኔ አመለካከት ድንግል ነሽ ብየ ነዉ የማስበዉ ብየ እነግራት ነበር...አራት አመትሽ ነዉ ወዳዉ እናትሽ ደርሳበታለች አንቺም በጊዜዉ ታመሽ አልተኛሽም እናም አትጨነቂ አንቺ ድንግል ነሽ አንቺን የሚያስቸግርሽ የሰዉ ወሬ ተደፍረሻል እያለ እንጂ አንቺ ድንግል ነሽ እላት ነበር፡፡
በነገራችን ላይ እሷ ስታገባ covid ባይሆን እንደ እቅዷ ሀይለኛ ሰርግ ብታዘጋጅ ሰርጉ ለመገኘት ቃል ገብቼ ነበር ግን covid ሁኖ ሰርግ ስለተከለከለ የተካበደ ሰርግ አላረገችም እኔም አልሄድኩም...በሰርጉ ማግስት ሰኞ ለት ጠዋት አሚር የሚገርም ነዉ ድንግል ነበርኩ ስትለኝ ወላሂ ያንን message ሳየዉ የደስታ ለቅሶ ነበር ያለቀስኩት...ለምን በስልክ ከ6ወር በላይ ተወያይተናል ሚስጥሯን ስለነገረችኝ የሆነ ሙሲባ ሲመጣባት ደዉላ አማክራኝ ተወያይተን ነበር የምንፈታዉና

☞ #ይሄን_ታሪክ ከፃፍኩት ቡሀላ በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜ ማጣት ላለማቅረብ ወስኜ ነበር ነገር ግን 2012 ረመዷን ሶስተኛዉ ቀን ላይ እሁድ ቀን እንደ አጋጣሚ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ቡሀላ በሪሞት እየቀያየርኩ prgram ሳይ 2012 ላይ ፋናtv ላይ የሆነ እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም አይኔ አረፈ
አንዲት ሴት ልጅ ከልጅነቷ ጀምሮ በአባቷ የወሲብ ጥቃት ይደርስባት ነበር ..አባቷ መጠጥ እየጠጣ ማታ ማታ ሁሌ ያስቸግራታል ..ሳትወድ በግዷ አባቷ ጋር ብዙ ቀን ታድራለች...ከዛም ወደ 18ቹ አመት ሲጠጋት ከአባቷ ታረግዛለች...ግን ለማን ታዉራ ለማን ትናገር
??ሁለት ታላቅ ወንድሞች አሏት ግን የየራሳቸዉ ስራ አላቸዉ እቤት አይኖሩም..አባቴ ይደፍረኛል ብላም ለመናገር ትፈራለች...ከዛም ሲቸግራት ለጓደኛዋ ትነግራታለች ..ጓደኛዋ እና ልጅቷ ሁነዉ ጓደኛ መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ ..ጓደኛዋ ለእናቷ ነግራት እንርዳት ስትላት..ከአሁን ቡሀላ እሷ ጋር ጓደኛ እንዳትሆኝ ብላ የጓደኛዋ እናትም ከቤት አስወጣቻት...ከዛም ሲጨንቃት ለአባቷ እህት(አክስቷ)ታማክራታለች ..አክስቷም አመነጫጭቃ ከአሁን ቡሀላ ወንድሜን እንደዚህ ብለሽ ብታነሺ በእኔ እጅ ነዉ የምሞችዉ ብላ ከቤት አባረረቻት....ታዳ ይሄን በደሏን የሚረዳት ስታጣ ጓደኛዋ የምትፅፈዉን ደፍተር ብቻ አደረገች

ይቺ ሚስኪን ልጅ ከአባቷ አርግዛ ሆዷ ገፋ..አባትየዉ በሰፈር ልጄ ዱርየ ሆነች ዲቃላዋን ይዛብኝ መጣች እያለ ወሬዉን አናፈሰዉ...የልጅቱ ሁለቱ ወንድሞችም እርጉዝ በመሆኗ ዱርየ ሆነች ብለዉ ከማን አረገዝሽ ብለዉ እንኳ ሳይጠይቁ አኮረፏት... ይቺ ልጅ ለማን ተናግራ ማን ይረዳት??ሒወቷ ገና በልጅነቷ ተበላሸ ህልሟ በአባቷ ጨለመ...ይሄም ሳያንሰዉ በሰፈር ልጄ ዲቃላ አመጣችብኝ እያለ በዉሸት ወሬዉን ነዛዉ፡፡ ልጅቱ የወሰደችዉ እርምጃ መጠኑ ያልታወቀ ኪኒን ዉጣ እራሷን አጠፋች ከሞተች ቡሀላ ወንድሞቿ ቢያለቅሱ የጓደኛዋ እናት ብትቆጭ ለልጂቱ የጠቀማት ነገር የለም ..
ፓሊስ የሞተችበትን ሲያጣራ በደብተር ላይ የፃፈችዉን መኝታ ክፍሏ አግኝቶ አባቷን አስሮ .ስንት አመት እንደሆነ እረሳሁት እስር ተፈረደበት፡፡

ቆይ እስኪ እንደዚህ አይነት አባት....በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች ምክንያት የሆኑ ወንዶች የሞት ፍርድ ካልተፈረደበት የሴት ልጅ አስገድዶ መደፈር ያቆማል ወይ???በጭራሽ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ እየበደለ ታስሮ እስከተፈታ ድረስ በልጅነታቸዉ የሚደፈሩ ሴት ልጆች መቼም መቆም አይችልም

የሞተ ተጎዳ አባትየዉ ከእስር ይፈታል መልሶ መኖር ይጀምራል ...እራሷን ያጠፋችዉ ልጅ ግን ወላሂ አሳዘነችኝ አስለቀሰኝ የነዋል ታሪክ ጋር ሳመዛዝነዉ የዝች ልጅ ታሪክ አሁን ድረስ ከአእምሮየ ሊጠፋ አልቻለም.. ይሄን እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም ካየሁ ቡሀላ ነዉ የነዋልን ታሪክ ለማቅረብ ያነሰሳኝ፡፡

#የእኔ_አሚር_ሰይድ ልባዊ ምኞቴ ይሄን ታሪክ ያነበበዉ ሰዉ ...ወንድ ለሴት ወገኖቹ እንዲያስብ ..ሴቶችም የወደፊት ትዉልድ በእነሱ ማህፀን የተቋጠረ ስለሆነ በተርቢያ በዲን አሳድገዉ ለዲነል ኢስላም የሚያስረክቡ እንስቶች ካሉበት ተጨባጭ እራሳቸዉን እንዲፈትሹ ነዉ፡፡

እኔ የምፅፋቸዉን ያነበበ ሰዉ እራሱን ቀይሮ ወደ ፈጣሪዉ እንዲቃረብ እና ወደ ወንጀል መንደርደር የያዙ እንዲያፈገፍጉ እና በወንጀል የተዘፈቁ ጥርት ያለ ተዉበት ቶብተዉ ወደ ፈጣሪያቸዉ ያለዉን መንገዳቸዉን እንዲያስተካክሉ እና ማንኛዉም ሰዉ እራሱ ተቀይሮ ማንኛዉንም ሰዉ የመቀየር ተሰጥኦ ስላለዉ ይሄን ተሰጥኦ በተግባር እንዲያሳይ ብር ያለዉ በብር..ሀሳብ ያለዉ በሀሳቡ..እዉቀት ያለዉ በእዉቀቱ...ዲነል ኢስላምና ኢስላም ወንድም እህቶቹ ጎን እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነዉ፡፡
#ተ............ #ፈ............ #ፀ...... #መ.....

ታሪኩ በ2013 ተነቦ በድጋሜ አሁን የቀረበ ነዉ
ከይቅርታ ጋር ጥሩም መጥፎም ማንኛዉንም አስተያየት አልቀበልም