Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 18.51K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-25 08:51:51 .የትምህርት ቤት ጓደኝቼ ነዋል ለምን አታገቢም?? ቆንጆ ነሽ ደግሞም ብዙ የትዳር ጥያቄ መጥቶልሻል ይሉኛል
....የአሁን ወንድ አምኜ ከማገባ እንደ መብራት ፓል ቁሜ ብቀር ይሻለኛል ሆነ የዘወትር መልሴ

ማንኛቸዉም እኔን የሚቀርቡኝ የሴት ጓደኞቼ ነዋል ላገባ ነበር ብላ ካማከረችኝ...አረ ወንድ አትመኝ ..ዛሬ አገባሽ ነገ አብረሽ እንደምትኖሪ እንደማትፋቺ እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ ???የአሁን ወንድ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ቢልሽ ከአፉ ነዉ ከልቡ አይደለም አትመኝ እያልኩ ክፉ መካሪ ሆንኩ ፡፡ በሰፈር እና በሬፍት ቫሊ ኮሌጅ ተሰሚነት ተቀባይነት ስላለኝ አምነዉኝ ብዙ ጓደኞቼ ትዳር መልሰዋል፡፡ አላህ ይቅር ይበለኝ

እኔ ትዳር የሚባለዉ ጠላሁኝ በጭራሽ ስለትዳርም ማሰብ አልፈልግም..እኔ ለትዳር ያለኝ አመለካከት በጣም የወረደ ሆነ፡፡ደግሞ ትዳር አርአያ ያስፈልገዋል እኔ ሳድግ ከቤተሰቦቼ ያየሁት ሲጨቃጨቁ ሲጣሉ ነዉ እንጂ የቤተሰብ ፍቅር አላየሁም አሁን ድረስ የሚገርመኝ እናት እና አባቴ የመጨረሻዋን እህቴን ከወለዱ ቡሀላ አብረዉ እንኳ ሲተኙ አይቻቸዉ አላቅም፡፡የየራሳቸዉ ክፍል አላቸዉ፡፡
እናትና አባቴ ከመቀያየማቸዉ የተነሳ መኖሪያ ቤት ሲገቡ አሰላሙ አለይኩም ማለት ጎጂ ባህል ነዉ የተባሉ ይመስል አባቴ ሳሎን ከተቀመጠ እናቴ ሌላ ክላስ ነዉ የምትሆነዉ ...ዋ ሳትጣሉ ታድሩና የተባሉ ይመስል በተለያዩ ምክንያት ለምን ዉሀ ቀጠነ በሚል ስበብ ቤቱን በአንድ እግር ያቆሙታል ...
ይወደኛል ያለአንቺ መኖር አልችልም ሲለኝ ከዛም አልፎ እኔን ሊያገባ ሽማግሌ የላከዉም ሚፍታህ እስከ ነመፈጠሬም ረስቶኛል ፡፡ የተማረ ይግደለኝ በሚለዉ የዋህ ህዝብ ባህል አድጌ እንደ ዶክተር ሷሊህ ያለም ሙሁር እሱም ሊያገባኝ ሽማግሌ ልኮ ግን አላማዉ ሌላ ሁኖ እንደዉም የብስ ስለትዳር ተስፋ አስቆረጠኝ ፡፡ ታዳ ስለትዳር ማንን ጥሩ አርአያ ላድርግ??

በኔ በደረሰብኝ በደል ታማኝ ወንድ የለም...ይሄን ስታነቡ ሁሉም ሊያጉመተምት ይችላል እደግመዋለሁ ታማኝ ወንድ የለም ....ወንድ ልጅ ሴትን ህልም እንደሌላት የወንድ ልጅ መጠቀሚያ ብቻ አድርጎ ያስባል፡፡ ሴት ልጅ ስትፈጠር ጀምራ በእሾህ የተከበበች ናት እኛ ሴቶች ግዴታችን እሾሁን እየነቀልን መሄድ ነዉ ..ግን የሚያሳዝነዉ በሴት ዙሪያ የተሰከሰከዉ እሾህ ከሴት ማህፀን የወጣዉ ለሴት ልጅ እዝነት ክብር የሌለዉ አላማዉን የዘነጋ ወንድ ልጅ ነዉ፡፡ ሴት ልጅ በሒወቷ ብዙ ፈተና ችግር መሰናክል ብታሳልፍም ብዙ መስዋአትነት ለሱ ከፍላ አንድ ጎዶሎ ካገኘባት ምን ሁነሽ ነዉ?? በምን ምክንያት ይሆን የተሳሳትሽዉ?? ብሎ ሳይጠይቅ በራሱ አስተሳሰብ ብቻ የሚጓዝ ከሴት በላይ ነኝ ምን ታመጣለች ብሎ የሚያስብ ነዉ፡፡ ከዛም የፈለገዉን ካረገ ቡሀላ ወይም መወደዱን ካረጋገጠ በሴት ልጅ ንፁህ የዋህ ልብ ሞት አፋፍ እንደቀረበች ቁንጫ በእጁ እያፍተለተለ መጨዋት ይፈልጋል..ታዳ እኔ ንፁህ ልቤን ሰጥቼ ተጎዳሁ አይበቃኝም??

በቃ አላገባም ምን እሆናለሁ?? ባላገባ ምን የሚቀርብኝ አለ ?? ከስሜትና ከዘር ማስቀጠል ዉጭ ትዳር ለኔ ምን ይጠቅመኛል ??አግብቼ ማንነቴን የማይቀበል ወንድ ለኔ ምን ይጠቅመኛል??? የሰዉ ልጅ ለስሜት ብቻ ነዉ እንዴ የተፈጠረዉ??? እስኪ ንገሩኝ፡፡ አላማ አለኝ ተምሬ እመረቃለሁ Coc አልፌ ስኮላርሽፕ እማራለሁ ከዛም ...ትልቅ ሰዉ ስሆን ከጎን አንድ ልጅ ያስፈልገኛል.....ልጅ መዉለድ እንኳ ቢያምረኝ ከህፃናት ማሳደጊያ ጉድፈቻ አንዲት ሴት ልጅ ወስጄ አሳድጋለሁ ብየ እራሴን አሳመንኩኝ ይሄ የራሴ አስተሳሰብ ብቻ ነዉ ..ለኔ የምኖረዉ እኔ ነኝ ከዚህም ዉጭ ብዙ ማሰብ እችላለሁ

     ለወንድ ልጅ የተጣመመ የተወላገደ አስተሳሰብ እያለኝ ከካሊድ ጋር በጣም መደዋወል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተቀራርበን ማዉራት ተያይዘነዋል፡፡ ካሊድ ባጃጅ አለዉ ቀን በቀን ትምህርት ቤት በር ላይ እየጠበቀ ከትምህርት ስወጣ ባጃጁን ይዞ መጥቶ እቤቴ ድረስ ይሸኘኛል..

ካሊድን የማደንቀዉ ባህሪ አለ ስራዉን አክባሪ በጣም ጎበዝ ነዉ ሁለት ባጃጅ አሉት አንዱን እራሱ እየሰራ አንዱን ለሹፌር ሰጥቷል.....በጊዜ ብዛት በእነዚህ ባጃጆች ስራየን ሰርቼ ሀይሮፍ መኪና ገዛሁ ሲለኝ በጣምምምም ገረመኝ ፡፡
ስራ አክባሪዋን ታከብራለች ይባላል እዉነት ነዉ ደግሞ ሲኖር ከሰዉ በታች ሁኖ ነዉ እንጂ አለሁ አለሁ ልታይ ልታይ አይልም..ጉረኛም በጭራሽ አይደለም

ካሊድ በተፈጥሮዉ እንከን የሌለዉ ሰዉ ነዉ....መጥፎ አይናገር ሰዉ ጋር አይጣላ በስራ ቦታ ስለ እሱ ሁሉም በጥሩነቱ እንጂ በመጥፎ ማንም የሚያነሳዉ የሌለ ሁሉም ሰዉ ጋር ተግባቢ ነዉ፡፡
....ካሊድ ለኔ 1% እንኳ ባያስቀይመኝም ባያስከፋኝም እኔ ጥሩነቱን ልቤ መቀበል አልቻለም ምክንያቱም ወንድ ማመን ስልችቶኛል ..በተለያዩ ወንዶች የተወጋዉ ልቤ ቆስሏል ገና አላገገምኩም ....በተለይ ደግሞ አፍቅሮ ማጣት እንዴት እንደሚጎዳ ስሜቱን ስለማቀዉ ከካሊድ ለመራቅ ወሰንኩኝ

....ካሊድ ጋር የመጣያ መንገድ ማፈላለግ ጀመርኩ ..እሱ የሚሰራበት አካባቢ የባጃጅ ፌርማታ የሚቆምበት ቦታ እየሄድኩ..መቼም የባጃጅ ሹፌር ስራቸዉ ሴት ጋር መጃጃል ሶስት እግር ሲይዙ ከእነሱ በላይ ሰዉ ያለ አይመስላቸዉም ..ብዙዎቹ ከትርፉ ላይፉ እያሉ ነዉ ባጃጅ ገዝተዉ ስራ የሚጀምሩት፡፡ ታዳ የአሁን ዘመን ሴቶች ሁለት ወይ ሶስት ብር ትራንስፓርት ሸኘሁሽ አልቀበልሽም ሲላት በአዉሮፕላን በሌላ ሀገር የሸኛት ይመስል ተደስታ በዚህ ሶስት ብር ዉለታህን አረሳም ብላ ዉለታዋን ለባጃጅ ሹፌር የፈለገዉን ክብሯን አሳልፋ ስትሰጥ እያየን ነዉ..አይ ሴትነት በሁለት በሶስት ብር ብለሽ ሹፌር ያዝናናል ነጋዴ ጊዜ የለዉም እያልሽ በረከሱ ሹፌሮች ማንነትሽን አታርክሺ....እኔም ካሊድ እንደነዚህ አይነት የባጃጅ ሹፌሮች ቢሆን ብየ ለመጣላት ስለሚያመች የተለያዩ ሰዎችን ስለእሱ ባህሪ በተለያዩ ዘዴ ለማዉጣጣት ብሞክር የእሱን መጥፎ ጎን የሚነግረኝ አንድ ሰዉ እንኳን አጣሁ፡፡

ካሊድ መጥፎ ባህሪ አለበት ሴት ጋር ይሄዳል የሴት ጓደኛ አለዉ ወይ ጫት ይቅማል ወይ ሲጋራ ያጨሳል የሚል አጣሁ...በምን ምክንያት ልጣላዉ ???
ካሊድ ሲደዉልልኝም አዉቄ እንዲናገረኝ ተናግሬዉ እንዳስቀይመዉ እያልኩ መጥፎ ቃላቶች ስናገረዉ እሱ በኸይር ነዉ የሚመልስልኝ....ብዙ ከካሊድ መራራቂያ ዘዴ በተለያየ ምክንያት ከዉሸቱም ከእዉነቱም እየደባለኩ ብናገረዉ ካሊድ በጭራሽ ሊርቀኝ አልቻለም...እኔም እሱን የምጣላበት ምክንያት አጣሁኝ.... ወላሂ ሱመወላሂ ካሊድን አንድ ጥፋት እንከን ባገኝበት ልርቀዉ 100% ወስኛለሁ ግን በጭራሽ እንዴት ጥፋት ላግኝበት?? አልቻልኩም

ካሊድ በስልክ ደዉሎ እንደዚህ አለኝ
...ነዋል ከቤተሰቦቼ ወጥቼ #ቤት_ተከራይቼ_ብቻየን_መኖር_ጀመርኩኝ አለኝ



#ክፍል

ይ........ቀ.........ጥ
...........ላ.........................ል


          `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
663 viewsedited  05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 08:51:51 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ሷሊህ እንደዚህ አለኝ>>>>> አላህንማ የማፈሪዉ አንቺ ነሽ....... የትም ስትልከሰከሺ ማንም ጋር ስትተኚ ስትማግጪ ላስወሰድሽዉ ድንግልና ምን ታካብጃለሽ... ባለፈዉ እኮ በልጅነቴ ተደፍሪያለሁ ብለሽ ስትነግሪኝ የተቀበልኩሽ በዉበትሽ ተማርኬ ነዉ እንጂ እዉነት እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ... ዉበት ደግሞ ለማንኛችንም ወንድ ልጆች አስቸጋሪ ነዉ የፍቅር ሳይሆን የዉበት ፈላጊ ነን ....እኔ የወደፊት ባልሽ ነኝ እስከምንጋባ ድረስ አብረን አንዳንዴ ማሳለፍ አለብን ..አብሮ ለመተኛት አዲስ አትሁኚ የለመድሽዉ ነዉ አለኝ፡፡

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም አይደል የሚባለዉ ሷሊህ ሆዱ ያለዉን በዚህ ቅፅበት ዘረገፈዉ

.....,.እኔም ምንም አላልኩትም ከዶክተር ሷሊህ ቤት ወዳዉኑ ወጥቼ እቤቴ እስከምድርስ በጅማ ጥቁር አስባልት መንገድ ጥቁር እድሌን ይዤ ከለር በሌለዉ እምባ ልስልስ ባሉት ጉንጮቼ አዘንባቸዉ ይዣለሁ ፡፡
አይ ሷሊህ የተማረ ብዙ ነገር ያቃል ተብሎ ለዛዉም በዶክተርነት ዲግሪ ይዞ የብዙ ሰዎችን ሂወት ያተርፋል ተብሎ ተስፋ የተሰጠዉ ሰዉ ..ከአፋቸዉ ጤነኛ መስለዉ ዉስጣቸዉ ግን እንደ አባጨጓሬ የኮሰኮሰ ማንነት በነጭ ጋወናቸዉ ተሸክመዉ ይዞራሉ ፡፡በሷሊህ አነጋገር ልቤ እየደማ ከሚፍታህ መለየት በላይ ወደ ዉስጥ ብሶቴ ገብቶ ብዙ ግፍ ወደ ተሸከመዉ ወደ መኖሪያ ቤቴ በለቅሶ አይኔ ቅልት ብሎ ተመለስኩኝ......
 
እቤት ክላሴ ገብቼ -----የፈጠርከኝ አላህ ሆይ!!!!! አረ ምንድን ነዉ ወንጀሌ??? አላህ ሆይ ፈተናየ በዛ ፈተናዉ ይበቃሻል በለኝ... ፅናቱን ስጠኝ እያልኩ እያለቀስኩ ዱአ ሳደርግ ..ሶላትም ስሰግድ አደርኩ፡፡
አዳሬን ለሰከንድ እንኳ እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ ጨለማ ለጀንበር አስረከበች .......,



ጠዋት እቤት መሆን ሲያስጠላኝ ተነስቼ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ፡፡ግን ምን ይደረጋል እራሴን በጣም ስላመመኝ መማር ስላልቻልኩ መልሼ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ

ሷሊህ የብስ የኔን ሞራል ለመጉዳት በሶስት ቀን በሳምንት  ይደዉልና ያንን ነገር አመቻቸሽ የኛ ጨዋ መቼ አብረን እንደር ?? ወይስ የመጀመሪያሽ ወንድ ከኔ ይሻልሻል?? እያለ ይቀልድብኛል

እኔ መልስም አልመልስለት ፈጣሪ የስራዉን ይስጠዉ ፡፡ግን ከእንደዚህ ያለ ሰዉ ለሰዉ አርአያ መሆን ከሚችል ሰዉ ለምን ይሄ መጥፎ ባህሪ ጎልቶ ይንፀባረቃል??? ሷሊህ ለህዝብ ተስፋ መሆን ሲገባዉ በተለይ እንደኔ ተቸግረዉ ተስፋ ላጡ የሚረዳቸዉ አጥተዉ የሚሰቃዩ ላሉ ወገኖቹ አብሽሩ ከጎናችሁ ነኝ ብሎ ማፅናናት ተስፋ መስጠት ሲገባዉ ...ነገር ግን እንደ እሱ የወረደ አስተሳሰብ ይዞ እንደዚህ እኔን ማሸማቀቅ መስደብ ምን ያደርጋል ?? ቢቻል ማግባቱ ቢቀር ለኔ ሒወት እንዲስተካከል የስነልቦና ጫና አለብሽ ብሎ መፍትሄ እንደመስጠት እየደወለ የሚያሳምም ንግግር በቃላት እየወረወረ የብስ ሒወትን ተራራ እንደመግፋት አደረገብኝ....ታዳ ምሁርነቱ ዶኮተርነቱ ምኑ ላይ ነዉ ??መማር ማለት ይሄን ካላገናዘበ ምኑ ላይ ነዉ መማሩ ??? ነጭ ጋወን መልበሱ እና ከስራዉ ጋር የማይሄድ ስም ሷሊህ ቢሉት ጥቅም የለዉም..



በኮሌጅ ሁለተኛ አመት ፍቅር በሚባል የሰዉ አላማ ፕላን ጋር የማይመጥን የሒወት አዙሪት ጊዜየን ፈጅቼ
የሁለተኛ አመት Coc ስፈተን ወደኩኝ...ደግሞ ከወደኩኝ ሶስተኛ አመት ኮርስ መቀጠል አልችልም

ከዛም ለCoc ለመፈተን ብየ መስከረም ወር ላይ የጅማ የቅርብ ጎረቤት ወደ ሆነችዉ አጋሮ ከተማ ሄድኩኝ ..

አጋሮ ፈተና በሄድኩበት ጊዜ ከነመፈጠሩ የረሳሁት ካሊድ እየደወለ በስልክ ማዉራት ጀመርን በጣም ተቀራረብን...ጠዋት ማታ እየደወለ አብሽሪ አላህ ያሳካልሽ ይለኛል፡፡ ካሊድ ጋር ማዉራቱን እንደ አዲሱን ተያይዘንዋል አጋሮ ሁኜ እሱ ጋር ማዉራት ሱስ እስከሚሆብኝ ድረስ በስልክ እያወራን ነዉ....

ካሊድ ብዙ ጊዜ ሲደዉልልኝ እንደዚህ ይለኛል #ነዋል_ቆጣሪዉ_እየቆጠረ_ነዉ ፡፡ የምትለዉን ቃላት እየደጋገማት ነዉ
....,እኔ ደግሞ እኔ ጋር ስደዉል ነዉ ማለት ነዉ ካርድህ የሚያልቀዉ?? እለዋለሁ ..ቆጣሪ እየቆጠረ ነዉ የሚለዉን ቃላት በቀላል ማዕናዉን መረዳት አልቻልኩም

....,ለካ ይሄ ቆጣሪ መቁጠር ቡሀላ ማዕናዉ ትርጉሙን ሳቀዉ ፍቅርሽ እየጨመረብኝ ነዉ ማለት እንደሆነ በጊዜ ሳይገባኝ ከብዙ ቀን ቡሀላ ተረዳሁኝ

ካሊድ ጋር በስልክ በጣም መቃለድ ተያይዘነዋል....እሱም እንደበፊቱ አይደለም አሁን ፍርሀቱ ለቆታል.....ግን እኔ ካሊድ ጋር ስናወራ ለትዳር ይሆናል ብየ በጭራሽ አስቤዉም ትዝም ብሎኝ አያቅም ...ለምን በፊት ካሊድን እንደማልፈልገዉ ነግሬዉ እሱም ተስማምቷል ፡፡ አሁንም አጀማመራችን በእህትነትና በወንድምነት ተባብለን ነዉ፡፡ ግን ይቺ ወንድነትና እህትነት የምትለዉ ቃላት ይአጅበኛል እሱም እቤቱ ወንድም እህት እያለዉ እኔም እቤቴ ወንድም እህት እያለኝ ተጨማሪ የባዳ እህትና ወንድም ለምን አስፈለገ???ስንት በቁጥር ለመግለፅ የተጀመረ የሀላልም የሀራሙም ግንኙነት በእህትነትና በወንድምነት እየተጀመረ ከአንድ ማህፀን ዉስጥ ለወጣዉ ወንድሟ የማታወራዉን ሚስጥር እንደ ወንድምሽ እይኝ ላላት ስንቱን የቆጥ የማገሩን ስታወራ ትዉላለች??? እሱም ቢሆን እቤቱ የምታገለግለዉን አይቡን የምሸፍንለት እህቱ እያለች በሚዲያ ለተዋወቃት እህት ተብየ ምን አዲስ ነገር አለ ስትለዉ ዘጠኝ አህጉር የሰማዉን ወሬ ሲቀባጥር ይስተዋላል፡፡ በዚህ በእህት ወንድም ግንኙነት ስንት ሀራም ወንጀል እየተሰራ ነዉ??? መቼም እኔ እህት ሁኚኝ ወንድም ልሁንሽ ሲልሽ የአንቺ መልስ መሆን ያለበት እቤት ያሉት ወንድሞቼ በቂ ናቸዉ ካልሆነ ሒወትሽ አደጋ ላይ ነዉ እህቴ.,

coc ተፈተን አልሀምዱሊላህ አለፍኩኝ ..መልሼ ወደ ጂማ ተመለስኩኝ ፡፡ ትምህርቴን ሶስተኛ አመት ተመዘገብኩኝ፡፡ በዚህ ሶስተኛ አመት ትምህርት ግሬድ ለማሻሻል ፍቅር የሚባለዉን ከልቤ ፍቄ ለማጥናት ወሰንኩኝ፡፡
በዚህ አመት እቅድ ብየ ብዙ ሀሳቦችን ካሰብኩኝ ቡሀላ በጠረንፔዛ ዙሪያ ዉይይት በተረጋጋ መልኩ እኔዉ ብቻየን በብቻየ ክላስ ተቀምጬ ተወያይቼ ወሰንኩኝ፡፡ ዉሳኔየም ለአሁኑ አመት የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪ ነኝ  ቸክየ ተምሬ coc ካለፍኩኝ ስራ የማግኘት እድል አለኝ..በተጨማሪም በትምህርት ቤታችን ግሬድ ከፍተኛ ነጥብ አለኝ ዲግሪ በስኮላር ሺፕ እማራለሁ፡፡ ብየ ወሰንኩኝ


ወላሂ ቢላሂ ወንድ የሚባል ፍጡር በትምህርት ቤትም ሆነ ሰፈርም በየአየሁት አጋጣሚ እንኳን ለማዉራት በአይኔ ለማየት ጠላሁኝ ..ጭራሽ ከወንድ ልጅ ፍቅር ከመጠበቅ ጆንያ ሙሉ ቁንጫ ለቆ እነሱ ይመጣሉ ብሎ መጠበቅ ይሻላል የምትለዉን አባባል አያብሰለሰልኩ እራሴን አሳመንኩ...ፍቅር ስሙ እንጂ ተግባሩ ወንድ ልጅ ጋር የለም ብየ በአራት ነጥብ ደመደምኩ ፡፡

የሚገርማችሁ ብዙ ሴት ጓደኞቼ በትምህርት ቤትም በሰፈርም ነዋል ልናገባ አስበናል ስለትዳር ምን ትመክሪናለሽ ??ብለዉ ሲጠይቁኝ
...እኔም መልሴ ጥምም ያለ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንጂ ተስፋ የሚዘራ ከአፌ በጭራሽ አይወጣም ... የዘንድሮ ወንድን አምናችሁ አታግቡ እኔ ትዳር አለመክራችሁም...ወንድ ልጅ የሚያገባዉ ለስሜቱ እንጂ አንቺን አስደስቶ ለመኖር አይደለም እያልኩ የብዙ ሴት ጓደኞችን ሒወት በተጣመመ የትዳር እና የወንድ ልጅ አመለካከት በልቤ ቋጥሬ አበላሸሁ
601 viewsedited  05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:39:59 እኔ ባልወደዉም እሱ ከወደደኝ በቂ ነዉ
ተጋብተን  አብረን ስንኖር እወደዋለሁ ብየ አሰብኩኝ ...እኔም እሺ ሽማግሌ ላክ አልኩት
.......እሱም እሁድ ቀን ሽማግሌ ላከ የኔ ቤተሰቦች እና የተላኩት ሽማግሌዎች እኔን ለመስጠት ከተስማማሙ ቡሀላ ኒካሁን እና የሰርጉን ቀን እንወስናለን ተባብለዉ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ

ዶክተር ሷሊህ የወደፊቱ ባሌ ጋር እየተደዋወልን ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ሚፍታህን መርሻ ይሆንልኛል ብየ አሰብኩኝ..ሚፍታህ ቢተወኝም ማንነቴን የተረዳኝ እስከማንነቴ የሚያገባኝ አገኘሁኝ እያልኩ በአንድ ጎን ደስታ በአንድ ጎን የሚፍታህ ትዝታ ለሁለት ከፋፈለኝ....መቼም አላህ የተሻለ አለዉ፡፡

...ጊዜዉ ይሄዳል ረመዷን ወር ደርሰናል...ፆምም ላይ ነን፡፡ ረመዷን ፆም ጀምረን ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ ሷሊህ ደዉሎ ዛሬ ከሰአት መኖሪያ ቤቱ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ
....,,እኔም ሌላ ምንም አልጠረጠርኩም ስለሰርጉ ሁኔታ ልንነጋገር ይሆናል ብየ መኖሪያ ቤቱ ሄድኩኝ

.....መኖሪያ ቤቱ እንደደረስኩ ትንሽ ተቀምጠን አንዳንድ ወሬ እያወራን ከቆየን ቡሀላ መጥቶ ከጎኔ ቁጭ አለ እና ይሄን የዉድ ከንፈሬን ጉንጬን እንደፈለገ ማረጉን ተያይዞታል...ከዚህም አልፎ የማይነኩ ቦታዎችን መነካካት ጀምሯል...
.....ከዛም እኔ አኡዙቢላሂ ብየ ብድግ ብየ ማልቀስ ጀመርኩኝ  ...ከዛም ሷሊህ ምነዉ ተነሳሽ እሳ ምን ያስለቅስሻል?? ነይ እንጂ ልብሰሽን አዉልቂ እንጂ ምን ታካብጃለሽ   ???አለኝ አፉን ሞልቶ
......እኔም አላህን አፈራም እንዴ ??? ኒካህ የለንም እንዴት የኔን ሰዉነት ለሰሜት ማብረጃ ልትጠቀምብኝ ነዉ እንዴ ?? እንዴት እንኳን እኔ ገና ኒካህ ያላሰርን ብናስርስ ረመዷን ፆም ይዘን አይቻልም እንዴት ይሄን ታስባለህ ??? አልኩት በመናደድ
.....ዶክተር ሷሊህም መቼም ቢሆን ከአእምሮየ የማይጠፋ የመርዝ ቃሉን ተፋብኝ.. ሷሊህን የመሰለ ስም ይዟል ግን ተግባር ዜሮ ነዉ...ስሙን ያወጡለት ጉቦ የበላ ቃልቻ መሆን አለበት
....እኔን እንደዚህ አለኝ አላህንማ የማፈሪዉ አንቺ ነሽ.......

#ክፍል
ይ...............ቀ............
.........ጥ...........ላ........ል

❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
 
368 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:39:40 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ዘጠኝ

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



ምክንያቱን በማላቀዉ መልኩ ሚፍታህ የእኔን ስልክ block አረገዉ የጓደኞቼንም አያነሳም....በጣም ግራ ገባኝ ምን ይሆን ምክንያቱ ????

ሚፍታህ ጋር ምክንያቱን ሳይነግረኝ ጥፋቴን ሳላዉቀዉ በዚህ መልኩ ተለያየን መደዋወል አቆምን ሒወት ማለት እንዲህ ናት እየወደዱ መለያየት እንዴት ከባድ ነዉ ፡፡ ሚፍታህን እያፈቀርኩት እየወደድኩት በማንነቴ  እኔ ተወኝ ስለዉ እምቢ ብሎኝ እንደገና በራሱ ጊዜ በማላቀዉ ጥፋት ሲተወኝ በጣምም ያማል፡፡  አላህ ፅናቱን ይስጠኝ

ከተለያየን ቡሀላ ብዙ ጊዜ መንገድ ላይ እንገናኛለን፡፡መንገድ ላይ ሲያየኝ እንደሚወደኝ ያስመስላል ከዛም እንደገና ወደ እሱ ለመጠጋት ሳስብ ደግሞ መልሶ ይርቀኛል...ሚፍታህ አሙለጭላጭ ሳሙና ሁኗል....በሒደት ከሚፍታህ ጋር መንገድ ላይ ስንገናኝ እንዴት ነህ----- እንዴት ነሽ ያለፈ ወሬ ማዉራት ካቆምን ቆየን ....እኔም ዲፕሬሽን ዉስጥ ወደኩ..ሚፍታህን ማጣቴ ጥፋቴን ሳይነግረኝ መጣላቴ በጣም ጎዳኝ እንቅልፍ አይወስደኝ...ብቸኝነት ማብዛት ሁኗል ስራየ...ንፋስ ይነፍሳል እንጂ ተራራን አይገፋም ይባል የለ እኔም ብናፍቅም ብወደዉም ባፈቅረዉም ሚፍታህ ለኔ የወደፊት የደስታየ ምንጭ መስሎኝ ብዙ አሳልፈን የማይረሳ የቅዠት ህልም መስሎ እኔን አእምሮ መጨነቅ እና መጥፎ የተለያዩ ሀሳበች ዉስጥ ከተተኝ.....
ሚፍታህ መቼ ነዉ የሚደዉልልኝ? እያልኩ ዛሬ ወይ ነገ አልያም ከነገ ወዳ ይሆን?እያልኩ ስልኬን ይዤ የሱን ስልክ መጠበቅ ሁኗል ስራየ...ምግብ ለራሱ ቀንሻለሁ..ትምህርት ቤት ቀን በቀን መሄድ አቁሚያለሁ ..ሰዉን ማዉራት ለራሱ በጣም አስጠልቶኛል..አባቴ ጋር ለራሱ ቀርበን ማዉራት አቁመናል..የኔ ፀባይ መቀያየር አባቴን በጣም ግራ ገብቶታል...የጀመአ ልጆች ጋር ለራሱ መገናኘት አቆምኩ...ምን ልበላችሁ የሚያረገኝን ለመግለፅ ቃላት የለኝም ..ሚፍታህ ካልደወለልኝ ይሄ የተፈራረቀ እኔን የሚጎዳኝ የፍቅር ስሜት የሚለቀኝ አልመሰለኝም...አንዳንዴ በህልሜ ሚፍታህ ሌላ ሴት አግብቶ እያየሁ በድንጋጤ ህልም አይሉት ቅዠት ብንን እላለሁ ...ሀሳቤ ሚፍታህ ብቻ ሆነ...

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደዚህ የሚያደርገዉ የፍቅር በሽታ (ላይመራንስ)የሚሉት ይሆን እንዴ እኔንም የያዘኝ???

ግን ላይመራንስ(የፍቅር በሽታ) ማለት ምን ማለት ነዉ???
በአሁኑ ሰአት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን በየአጋጣሚዉ የምንሰማዉ ፍቅር ነዉ እየተባለ የምናየዉ የፍቅር ልክፍት በሽታ እንጂ ትክክለኛ ፍቅር አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጎን ለጎን ቁጥራቸዉ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ግራ ተጋብተዉ ግራ ሲያጋቡ ይታያሉ ...እንዲሁም ፍቅር ምን እንደሆነ በፍፁም ያልገባቸዉ ግለሶቦች ፍቅር ጀምረዉ ሳይሳካላቸዉ ሲቀር ፍቅርን ሲረግሙት እና ሲያማርሩት ..አፍቅረዉና ተፋቅረዉ ለስሜታቸዉ ደስታን ያገኙበት ደግሞ ሲያሞግሱት እና ያለ እርሱ መኖር እንደማይቻል ሲገልፁ ይስታወላሉ፡፡

የሳይካሪስት ተመራማሪዎች ይህን የፍቅር አባዜ ወይም በፍቅር በሽታ የመነደፍ ልማድ ከነጭራሹ ፍቅር አይባልም እነሱ እንዳሉት #ላይመራንስ በማለት ይጠሩታል፡፡፡
ይህ የፍቅር በሽታ ወይም የፍቅር ልክፍት ላይመራንስ ሳይመቱ ያስለቅሳል፡ማዘንና መተከዝን ያፈሩበታል፡ከፍ ብሎ ሲገኝ ራስን ወደ ማጥፋት ሊያመራ ይችላል፡፡ አፈቀርኩት ከሚሉት ግለሰብ ዉጭ ሌላ ግለሰብን ማፍቀርም ማግባትም እንደማይችሉ ይሰማቸዋል..ይህን ሀሳብ ለዉስጣዊዉ አእምሯችን ክፍል ይነግረዋል..እርሱም ሁሉንም ነገር ሊያከናዉን ወደሚችለዉና ነገሮችን ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሚያደርገዉ የአእምሮችን ክፍል ያስተላልፈዋል ..ይሄኔ ነገራቶች ሁሉ በፅልመት አይን መታየት ይጀምራል ..አንዳንዶቹ ሌላ ተቃራኒ ፆታን ሲያዩ ተቀራኒ ፆታ እስከማይመስላቸዉ ይደርሳሉ..አልፎ አልፎም እስከ መጥላት ይደርሳሉ ..ለዚህ አይነት ጎጂ የተዛባ አስተሳሰብ ላይመራንስ ወይም የአፍላ ፍቅር ልክፍት ነዉ..

በዚህ ፍቅር በሽታ በርካቶች ተጎድተዋል..አሁንም እየተሰቃዩ ነዉ በጣም ብዙ ተሰቃይተዋል ..ጭንቀት መከራ ላይ ወድቀዋል .ለወደፊትም የሚሰቃዩ ብዙ ናቸዉ .. አሁን ላይ ያለነዉ ፍቅር ተብየ ጨዋታ የምንጫወት ከዚህ የዉሸት ፍቅር መላቀቅ ካልተቻለ ብዙ የከፋ ነገር እንደሚፈጠር ማሰብ አለብን፡፡ ይህን ፍቅር ተብሎ የተተበተበ የሳምንት ወይ የወር ወይም የአመታት የቃላት ጨዋታ በጊዜ የማይላቀቁ ከሆነ ከዚህም ሲከፋ ከሚወዱት አምላካዊ መመሪያ በመራቅ ህይወታቸዉን ለከፋ አደጋ አጋልጠን እንሰጣለን ፡፡

በዚህ ላይመራስ በሽታ በርካቶች ተምረዉ የት ይደርሳሉ የተባሉ በየመንገዱ ቀርተዋል..ሀብታቸዉን በማጣት ለከባድ ዉድቀት ተዳርገዋል..በዚህም ከሰዉነት ማዕረግ ወጥተዉ ተራና ርካሽ ተግባር ዉስጥ ተዘፍቀዋል .ልመና ስርቆት ሲጋራና መጠጥ ሱስ ዉስጥ በመግባት ስቃያቸዉን ለመርሳት ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ተስተዉለዋል፡፡የላይመሪንስ በሽታዉን ለማስወገድ ስቃዩን ለመርሳት በየቡና ቤቶች. በጫት መሸጫ ተራ .የሺሻና የሀሺሽ መንደሮች . በየፊልምና በየካራንቡላ ቤቶች ገብቶ መደበቅ እንደ አማራጭ የሚጠቀሟቸዉ ስልቶች ናቸዉ፡፡ በተለይ ሴቶች የተለያዩ አማረኛ እንግሊዘኛ የፍቅር ፊልሞችን እያዩ የማልቀስ እና ሙዚቃ ማዳመጥ ለመርሳት እያሉ የሚያረጉት ተግባር ሁኗል፡፡
በጣም የሚገርመዉ በላይመራንስ በሽታ የተለከፈ ሰዉ ጤነኛ እንዳትሉት በነፃ የአእምሮዉ ክፍል እያሰበ ነፃ ምርጫዉን ተጠቅሞ መንቀሳቀስ መወሰን ይከብዳቸዋል ..በስሜትና በሞራል መጎዳታቸዉ ሳያንሳቸዉ ሌሎች የሰዉነት ክፍሎችን ጤና ሲያዉክና ስርዓታቸዉን ሲያዛባ ይስተዋላል፡፡

የላይመራስ በሽታ የምግብ መጠጥ ፍላጎት ይቀንሳል. ለእንቅልፍ እጦት ይዳርጋል. የአካል መድከም ድብርት .ከባድ የራስ ምታት. የስራ ፍላጎት መቀነስ .ብቸኝነት መምረጥ .የአእምሮ ነፃ ምርጫን ማጣትና እራሱን የመምራት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይስተዋላል ፡፡ሲበዛ እብደትን እስከማስከተል ይደርሳል...
ለላይመራንስ በሽታ መድሀኒቱ አንድ ብቸኛ መፍትሄ አለ ወደ አሏህ መንገድ መመለስ እና ቁርአንን መቅራት እንደሆነ ብዙ ደርሶባቸዉ ከዚህ የፍቅር ልክፍት የዳኑ ሰዎች ይናገራሉ..... ለሰዉ የሰጠሀዉን ፍቅር ሰዉን ለፈጠረዉ ፈጣሪ አሏህ መልሰህ ስትሰጠዉ ዱንያዉም አኼራዉም ያምራል፡፡



       በዚህ የስቃይ ጊዜ ዉስጥ ሁኜ ጊዜ ደጉ የማያሳየን የማይፈጠር የለም ሌላ አዲስ ነገር ተፈጠረ... ለትዳር እኔን ጠየቀኝ ስሙም ሷሊህ ይባላል፡፡ ሽማግሌም እቤት ላከ

    እስኪ ስለ  ሷሊህ አንዳንድ ነገር ልንገራችሁ ሷሊህ በጂማ ከተማ በእራሱ ህንፃ ላይ የግል ሆስፒታል ያለዉ ነዉ፡፡ ዶክተር ሷሊህ ጋር የተዋወቅነዉ እሱ ሆስፒታል አፓረንት ወጥቼ ነበር የዛን ጊዜ አየኝ ወደድኩሽ ካላገባሁ ሞቼ እገኛለሁ እያለ እርይ አለብኝ፡፡ ከአፓረንት ወጥቼ ለራሱ መግቢያ መዉጫ አሳጣኝ ...ከዛም ለቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ልልክ ነዉ እያለ አስቸገረኝ
.....,እኔም እንደዚህ ሲያስቸግረኝ ካፌ ተቀምጠን የኔን ማንነቴን በልጅነቴ ስለተደፈርኩ ድንግል አይደለሁም ብየ አንድ ባንድ ነገርኩት
......ዶክተሬ ሷሊህም እሺ ማንነትሽን አምኜ ተቀብያለሁ ...እኔ የምፈልገዉ አንቺን አግብቶ ልጅ መዉለድ ነዉ አለኝ

በኔ ጓደኞች በስልክም በአካልም በአገኘኝ ቁጥር ጠዋት ማታ አንቺን ካላገባሁ ሙቼ እገኛለሁ እያለ አስቸገረኝ
373 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:08:26 የሒወቴ ከባዱ ፈተና ይህ አመት ነዉ

ልጅ ሁኜ ትምህርት ቤት ያለዉ ተፅእኖ ያሳለፍኩት አሁን ካለሁበት ሳነፃፅረዉ በልጅነቴ ሲሰድቡኝ ሲጠቋቆሙብኝ የነበረዉ ቀላል ነዉ ...የኔን ማንነት ለማያቅ ሰዉ ነገ አብሬዉ ለምኖረዉ ለትዳር አጋሬ እንዴት ብየ ነዉ ድንግል አለመሆኔን የምነግረዉ ??
እኔ እወደዋለሁ እሱም ይወደኛል ለመጋባት በመሀከላችን ምንም የሚያጣላን የሚያለያየን ነገር የለም ..ነገር ግን የኔን ማንነት ይቀበለኛል ወይ ? ?? አግብቼ ከሚፍታህ ጋር በዚሁ ምክንያት ከትዳር መለያየት ቢመጣ ነዋል አግብታ ፈታች እየተባለ የቡና መጠጫ ወሬ እሆናለሁ ...

ደግሞ እኔን የሚያቁኝ ሰዎች ከሌሎች ሴቶች ለኔ ቦታ አላቸዉ በትምህርቷ ጎበዝ ናት፡ ዲን አላት ፡ጥሩ ፀባይ አላት ፡ ጅልባብ ለባሽ ናት ብሎ ማንኛዉም ሰዉ ይመሰክርልኛል....ነገር ግን ዉስጤ ያለዉ ቁስል ነዶ የማያልቅ የፉም እሷት ጨብጬ ይዣለሁ ...እንዴት አርጌ ልንገረዉ ??? እያልኩ ብቻየን መጨነቅ መኝታ ክፍል ሁኜ ማልቀስ ሁኗል ስራየ

ሚፍታህ ተወኝ ብለዉ አይተወኝም...,,ደግሞ ካልተወኝ ለወደፊት ግንኙነታችን ለመጋባት ስለጨረስን ይሄን ነገር ማወቅ አለበት ...ከተጋባን ቡሀላ ድንግል አለመሆኔን ያዉቃል ከዛ ምን ይፈጠር ይሆን ???እላለሁ 

ለሊት እየተነሳሁ ረከአተይን ሰግጄ ዱአ አደርጋለሁ ... ደግሞም በማንኛዉም ሰአት እና ከሶላት ቡሀላ ዱአ አደርጋለሁ...የሚገርማችሁ ነገር ይሄን ዱአ በመደጋገም አደርግ ነበር >>>

#አላህዋ_መርየመን_ያለድንግል_ማንም_ሳይነካት እንድትወልድ ያረካት ጌታ ሆይ የመርየምን ድንግል ለኔ ስጠኝ<<<<<<<< ብየ ብዙ ጊዜ አልቅሼ ዱአ አድርጌያለሁ በሒወቴ ከባዱ ገጠመኝ በማንነቴ ያለቀስኩበት የተጎዳሁበት አመት ይሄ አመት ነዉ ፡፡

ኮሌጅ የሁለተኛ አመትን እንደዚህ ነበር ያሳለፍኩት....እናም አመት ዙሮ ረመዷን ቢደርስም የዚህ አመት ረመዷንን በመጨናነቅ በማሰብ አሰለፍኩኝ.....አስከትሎም ኢድም አልፎ ዛሬ ልንገረዉ አልንገረዉ እያልኩኝ ስወዛገብ ሳለቅስ ኑሬ ...... ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመንገር ተዘጋጀሁ...ለመንገር ለሚፍታህ ልደዉል ስልኬ ከተቀመጠበት ሳነሳ በእጄ እንዳለ ስልኬ ጠራ ..የደወለዉም ሚፍታህ ነዉ፡፡

ስልኩን አንስቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.....ነዋል ልሄድ ነዉ አለኝ
.........,,እኔም ልቤ እየደነገጠ የት ነዉ የምትሄደዉ ??አልኩት
...እሱም አረፋን የምዉለዉ ሀጃጆች ጋር ነዉ.. በዚህ አስር ቀን ዉስጥ ሳዉዲ አረቢያ ሀጅ ልሄድ ነዉ ከሀጅ ስመለሰ እናወራለን እዛ ሁኜ በimo እና telegram እንገናኛለን አለኝ......
...እኔም እሄዳለሁ ሲለኝ ደንጋጤም ጥርጣሬም አስቤ ነበር ..ተረጋግቼ መርሀባ አላህ ያሳካልህ ሀጅህንም ይቀበልህ እኔም ብዙ ሀጃ አለኝ በዱአህ አትርሳኝ አልኩት
....እሱም አልረሳሽም አለኝ

ሚፍታህ ለሀጅ ወደ ሳዉዲ አረብያ ሄደ ..ሳዉዲ ከገባበት ሰአት ጀምሮ እኔ እዛ የሄድኩ እስኪመስለኝ ሳዉዲን በየሄደበት በtelegram እና በimo video እየቀረፀ እየላከ ያሳየኛል፡፡ ጠዋፍ ሲያደርግ..ሶፋ እና መርዋ ላይ ሲወጣ..አረፋ ተራራ ..ስንቱን ላዉራዉ ሀጅ በሚያደርገበት ቀን በቀን ያለዉን ሁኔታ እስከሚመለስ ድረስ በimo እየላከ ያሳየኛል፡፡ አሁን ላይ ሁኜ ሳስበዉ ሀጅ የሚሰራዉ ሀጅ አደረገ ለመባል ነዉ ወይስ ግዴታ አላህ እንደአዘዘዉ ሰርቶ ወንጀሉን እንዲማር ነዉ ??
እስኪ እንደዚህ አድርጎ ያረገዉ ሀጅ ከአላህ ጋር ተቀባይነት ያገኝ ይሆን ??? እላለሁ፡፡ ታዳ ይሄ አይነት አላህን ይፈራል ብሎ መገመት ይቻላልን??


ታዳ እንደሚፍታህ ያሉ ሀጃጆች ስንት ስራቸዉን አበላሽተዋል??? ቤት ይቁጠረዉ ..አላህ ሆይ አንተ ያዘዝከንን ስንሰራ ከሰዉ ምስጋናን ሳይሆን የአንተን ሀቅ አሟልተን ከአንተ ሽልማት የምናገኝ አድርገን

ሚፍታህ ሀጅ አድርጎ ሲመጣ ጂማ የሚገኘዉ መርካቶ ሰፈር ኤሌክትሮኒስ ሱቅ ከፈተ ...ታላቅ ወንድሙ ከዉጭ ሀገር እቃ ይልካል አንድ ወንድሙ አዲስ አበባ ይሸጣል ለሚፍታህ ደግም ወደ ጅማ ይላክለታል.....ሚፍታህ ኑሮዉንም አዚሁ ጅማ አደረገ ፡፡ ለኔ በጣም ደስ አለኝ በስልክ ሳይሆን ሲናፍቀኝ አይኑን ማየት እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡


አንድ ቀን እለቱ ቅዳሜ ቀን ነዉ የኔን ማንነት በልጅነቴ መደፈሬን ልንግረዉ ብየ እራሴን አሳምኜ ደወልኩለት
....... ስልኩን አነሳዉ
............ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ሚፍታህ ዛሬ ትልቅ ሚስጥር ነዉ የምነግርህ ..አደራህን የምነግርህን ተረዳኝ በነገርኩህ ነገር ተቀይመህ ወይም እኔን እንደአሰብከኝ አለመሆኔን ስታቅ ከአንተ አፍ የሚወጣዉ ቃላት እኔን አንተን የሚወደዉን ልቤን እንዳያደማዉ ተጠንቀቅ ..እኔ ለአንተ ያልነገርኩህ ብዙ የሚያስጨንቁ በሆዴ የታፈኑ ማንነቶች አሉኝ..አንተ እኔን እንደምታስበኝ ሴት አይደለሁም.. የአንተ የትዳር መስፈርትህ እኔ ካለኝ ማንነት ጋር በጣም ሰፊ ልዩነት አለ አልሆንህም .....እያልኩ ወደ ዋናዉ ቁም ነገር መደፈሬን ልነግረዉ ከአፌ ላወጣዉ ስል...,ሚፍታህ ወሬየን አስቆመኝ
.....ነዋል ወሬዉን አቁሚዉ እና አሁኑኑ በአካል እፈልግሻለሁ እቤት ነይ አለኝ.....
.....እኔም እሺ ብየ ከጠየቀኝ አንድ ባንድ እነግረዋለሁ ብየ ወደ ቤቱ ሄድኩኝ

... እቤቱ እንደደረስኩ ያየሁት ነገር አይኔን ማመን አቃተኝ...እኔ ያሰብኩት ሌላ የሚሆነዉ ሌላ ነዉ
.......ሚፍታህ ቢያንስ ከ6 የሚበልጡ ጓደኞች ባሉበት ነዋል እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም  ይሄዉ በጓደኞቼ ፊት እመሰክርልሻለሁ ...,በተጨማሪም አንድ የማረሳዉ ንግግር እንዲህ አለኝ
>>>>>>እኔ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እንደፈለኩ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ስል ቆይቼ ተወኝ ስትይኝ የምተወዉ አንስተሽ የምትወረዉሪኝ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እኔ የፍቅር የመዉደድ ስሜት የለኝም እንዴ??" ...እኔ አልሆንህም ስትይኝ እኮ ልቤ እየደማ ነዉ ነዋል እባክሽ ሌላ ፈልግ አትበይኝ እንደዚህ ስትይኝ ፍቅርሽ ያሳደረብኝ ዉጋት እየጨመረብኝ ነዉ <<<<<<አለኝ፡፡

እኔም እንደዚህ ሲለኝ ሆዴ ባባ አሳዘነኝ እሺ ከአሁን ቡሀላ እንዲህ አልልህም አልኩት

ወደ ቤቴ ተመለስኩ ... ማታ ተኝቼ ዛሬ ሚፍታህ እቤቱ ሂጄ በነገረኝ ቃላቶች አስተነተንኩኝ እንደሚወደኝ እርግጠኛ ሆንኩ በጓደኞቼ ፊት ነዉ ቃል የገባልኝ... ሚፍታህ እንደዚህ ቢለኝም ግን ይሄ ማንነቴን መናገር አለብኝኝ ግዴታየ ነዉ ....በልጅነቴ መደፈሬን ተገናኝተን ሻይ ቡና እያልን ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ ወሰንኩኝ ፡፡ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ የወሰንኩት ዛሬ በተናገሩኝ ቃላቶች እኔ አልሆንህም ሁለተኛ እንዳትይኝ ስላለኝ ደስታዉን በዚህ ሳምንት ላለማደፍረስ በማሰብ ነዉ፡፡

  ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ይሄን ጉዳይ ለመንገር ... ስደዉልለት ስልኬን block አድርጎታል.....በጣም ግራ ገባኝ በጓደኞቼ እና በሌላ ሰዎች ስልክ ስደዉልም የኔ ድምፅ መሆኑን ሲሰማ ጆሮየ ላይ ይዘጋብኛል.. ስልክ ማንሳቱንም አቆመ ..
ምክንያቱን በማላቀዉ መልኩ ሚፍታህ የእኔን ስልክ block አረገዉ የጓደኞቼንም አያነሳም...በጣም ግራ ገባኝ ምን ይሆን ምክንያቱ ????

#ክፍል
ይ..........ቀ.......
....ጥ..........ላ............ል

    t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
948 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:08:26 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ስምንት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



ሚፍታህን አሳማኝም በሆነ የማያሳምን የተለያዩ ለፀብ ለቁርሾ የሚሆን ስበብ ፈልጌ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልርቀዉ ወሰንኩኝ .........
በተለያዩ ዘዴዎች አዉቄ ሁለታችንን ሊያጣላን የሚችል ጥፋት እያጠፋሁ ነገር እየፈለኩት በራሴ ጥፋት ሚፍታህን መጣላት ጀመርኩኝ....ግን በተጣላን ማግስት ሚፍታህ ከቤቴ ስወጣ መንገድ ላይ እየጠበቀ በራሴ ጥፋት ይቅርታ አርጊልኝ  ይለኛል

በተለያዩ ዘዴዎች የዉሸት ምክንያቶች እየደረደርኩ ብዙ ጊዜ አስቀየምኩት ግን ሚፍታህ ይቅርታ አርጊልኝ እያለ ሊርቀኝ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ በጭራሽ አልቻለም.....

ከትንሽ ቀን ቡሀላ ሚፍታህ ለስራ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ ፡፡ አሁን ሚፍታህን በአካል አላገኘዉም በስልክ ብቻ ነዉ የምንገናኘዉ...ለመለያየት ከኔ ተስፋ ለመቁረጥ ጥሩ ጊዜ ነዉ ብየ አሰብኩኝ ...ለእኔም ለሚፍታህም የሚጎዳ ከባድ ዉሳኔ ወሰንኩኝ....

ሚፍታህ ከልቡ ቆርጦ እንዲጠላኝ ስልኩን block አረኩት ... ምክንያቱም እሱን ባወራሁት ድምፁን በሰማሁት ቁጥር የበለጠ እየወደድኩት እያፈቀርኩት መሀባዉ እየጨመረብኝ ሄደ ፡፡ ደግሞ በዚህ ሁኔታ ሁኜ መለየት አቅቶኝ እያለቅሱኩኝ ከዚህ በላይ ደግሞ ብወደዉ አብጄ ልብሴን መቅደዴ አልቀረም.
ፍቅር ግን ምንድን ነዉ የበፊት ምርጥ ትወልዶች፡ፍቅርን እንዴት ነበር የገለፁት??? መጀመሪያ የፍጡራን ፈጣሪ የሆነዉን የአለማት ጌታ ለአላህ ነበር ፍቅራቸዉ..እስኪ የዚችን ንፁህ ልብ ያላት ወጣት የፍቅር ታሪክ ልጋብዛችሁ

★★★ ኡመር(ረ.ዐ)በመዲና ጎዳናዎች ላይ በጨለማ ሲዘዋወሩ አንድ ቤት አጠገብ ሲደርሱ እናት እና ልጅ ሲከራከሩ ይሰማሉ
እናት፡-ልጄ ሆይ ነገ ከምንሸጠዉ ወተት ላይ ጥቂት ዉሀ ጨምሪበት
ልጅ፡-እማዬ ኸሊፋዉ ኡመር ወተት ላይ ዉሀ እንዳንጨምር ከልክለዉናል ትላታለች እናቷን
እናትም፡-ኸሊፋዉ እኮ አሁን የምንሰራዉን አያየንም አለቻት
ልጅም፡ አላህን በመፍራት ለእርሱ ባላት ፍቅር ልቧ የተሳበዉ ወጣት እንዲህ አለቻት ..እናቴ ሆይ!!!ይህን ድርጊታችንን ኸሊፋዉ ባይመለከተንም ከአላህ ግን ልንደብቀዉ አንችልም አለቻት፡፡
ልጅቱ ለእናቷ የሰጠቻት መልስ ኡመርን በቆሙበት ቦታ በሲቃ ናጣቸዉ፡፡ ከዛም ሲነጋ ቤቱ የማን ቤት እንደሆነ አረጋግጠዉ ያቺን ልጃገረድ ልጃቸዉ እንዲያገባ ሁኔታዉን አመቻቹለት፡፡ ምክንያቱም ልጅቱ ለአላህ የነበራት ፍራቻ ከርሷ የሚጠበቅ አልነበረምና፡፡ ከእነዚህ ጥንዶች የተወለደዉ በኢስላም አምስተኛዉ በትክክል የመራ ኸሊፋ እንደሆነ የተመሰከረለት ኡመር ኢብኑ አብደል አዚዝ የተገኘዉ፡፡ እናቱ አላህን ፈሪ ስለሆነች በዛ ተርብያ ስላሳደገችዉ ለዲነል ኢስላም መሪ የሆነ ልጅ አበርክታለች....እንደዚህ ለአላህ የነበራቸዉ ፍቅር ላይ ያለፉ ትዉልዶች ስንት ስቃይ አሳልፈዉ እኔ ግን በሚፍታህ ፍቅር እርብሽብሽ ለቅሶ በለቅሶ ሁኛለሁ

... እኔም እንዲህ ብየ አሰብኩኝ
>>>> #ትዳር_ለኔ_አልተፈጠረም_ቢክራ_ስላልሆንክ_የወደድኩትን_ሰዉ_ማግባት_አልችልም<<<<<<<ብየ ከሰዉ በታች እንደሆንኩ ሁሌ ይሰማኛል፡፡

 
.....ሚፍታህ በጭራሽ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ አልቻለም ፡፡ በተለያዩ የተለያዩ ሰልክ ቁጥር ቢደዉል ቢደዉል እኔ አላነሳ ስለዉ በእናቴ ስልክ ይደዉላል ፡፡
እናቴም፡- ሚፍታህ ነዉ ነዋልን ፈልጊያት ነዉ አገናኚኝ እያለ ነዉ በስልክ አግኝዉ ስትለኝ
እኔም፡- አሁን ማናገር አልፈልግም እላታለሁ......

በሌላ ስልክ ሲደዉል እንደ አጋጣሚ ካነሳሁት የእሱ ድምፅ መሆኑን ስሰማ አላናግረዉም......እንዲዚህ እያልን 3ወር ያህል የሚፍታህን ድምፅ ሳልሰማ block እንዳደረኩበት ጨከንኩበት፡፡


አንድ ቀን አባቴ ብር አሰግቢ ብሎኝ ብር ላስገባ ባንክ ቤት ሄድኩ.. የአላህ ነገር ሁኖ ሚፍታህ ጋር ባንክ ቤት ተገናኘን
.....ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
....እኔም ያልጠበኩት ነገር ነዉ ደንግጬ ወአለይኩም ሰላም አልኩት
.........የሚገርም ነዉ ገና ትናንት ከአዲስ አበባ መጥቼ ነዉ .ከአዲስ አበባ የመጣሁበትም ምክንያት ለአንቺ ብየ ነዉ ምን ሁነሽ ነዉ ስልኬን block ያረክሽዉ ??
አሁኑኑ ስልኩን ከblock አንሺዉ አለኝ
....እኔም ዉሳኔየ ነዉ አሁን አላነሳዉም አልኩት
.......ሚፍታህም ባንክ ቤት ተገልጋዮች ባሉበት ሰዉ ፊት ነዋል ምን አድርጌሽ ነዉ Block ያረግሽኝ??ምን አርጌሽ ነዉ ??? ጥፋት ካለኝ እዚሁ ሰዉ በተሰበሰበበት ጥፋቴን ንገሪኝ ፡፡ እኔ ወላሂ በጣም ነዉ የዎወድሽ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም አንቺን ተለይቶ መኖር ልቤ መቼም አይፈቅድልኝም.. ለምንድን ነዉ ብሎክ ያረግሽኝ??? እያለ ሲጮህ
በጣም ደነገጥኩኝ
....ሚፍታህም ጥፋት የለብኝም ሰዉ ፊት ነዉ ጥፋቴን የጠየኩሽ አሁኑኑ አይኔ እያየ block አንሺዉ አለኝ
...እኔ ደንግጫለሁ ብሎኩን አንስቼለት ቶሎ ብየ ከባንክ ቤቱ ወጣሁ፡፡

ከዚህ ቀን ቡሀላ የሚፍታህ ፀባይ አስተሳሰብ የተቀየረ መሰለኝ..በጣም የሚወደኝ ያለኔ መኖር የማይችልም መሰለኝ.....እንደበፊቱ በስልክ ማዉራት ጀመርን ፡፡ እቤት አባቴ በትምህርትሽ እንዳትሳነፊ  ብዙ ስልክ ማዉራት ቀንሱ ተብሎ ተከልክለናል...የማወራዉ ተደብቄ ነዉ ፡፡ እንደበፊቱ ብዙ ነገሮች ማዉራት ጀመርን ያዉ በወሬ በወሬ እኔ የምሸማቀቅበት አንገቴን የምደፋበት ስለትዳር እና ስለ ድንግልና እኔን በቀጥታ መጠየቅ ቢፈራኝም ግን በተዘዋዋሪ እንደበፊቱ የጓደኞቹን ታሪክ እያነሳ ያወራኛል
....እኔም ይሄ ወሬ መደጋገም ሲበዛብኝ ..ምራቄን ዉጬ እንዲህ አልኩት
ሚፍታህ እኔ እንደምጠብቀኝ አይነት ልጅ አይደለሁም ከኔ የተሻሉ ብዙ ሴቶች አሉ ሌላ ሴት አግባ ...እኔ አንተ ላቀረብካቸዉ የትዳር መስፈርትህ ማሟላት አልችልም አልኩት...
...እሱም ነዋል እንደዚህ አትበይ ከአንቺ የተሻለ ሴት መቼም አላገኝም እወድሻለሁ እኮ ..አንቺ የኔን የትዳር ዉሳኔ አሁን መወሰን አትችይም እኔ አንቺን መርጫለሁ ወደ ሆላ አትመልሽኝ ፡፡ በፀባይ በዲን በአስተሳሰብ ከአንቺ የተሻለ አላገኝም ይለኛል፡፡

እኔ በልጅነቴ ልደፈር አልደፈር ይወቅ አይወቅ የማቀዉ ነገር የለኝም፡፡ ግን የሱፍ ያቃል ..የሱፍ ታስታዉሱ እንደሆነ ገና ታሪኩ እንደጀመረ ልጅ ሁኜ ተራዊህ ልንሰግድ ገብተን እናቴ ነዋል በልጅነቷ ተደፍራለች ብላ ነግራኛለች ብላ የተጣላሇት ልጅ እህቱ ናት( part ➎ላይ ያለችዉ ልጅ) ፡፡
የሱፍ የኔን ታሪክ ያዉቃል..ግን ለሚፍታህ ይንገረዉ አይንገረዉ የማቀዉ ነገር የለኝም...

ግን ሚፍታህ ጋር በአወራን ቁጥር የእኔ ባለቤት ድንግል ካልሆነች ቀልድ የለም ይለኛል ..እንደዚህ ሲል መደፈሬን አልሰማም ማለት ነዉ ብየ አሰብኩኝ... ግን አሁን ድረስ ግራ የሚገባኝ ለኔም ያልተመለሰልኝ መልስ ሚፍታህ ስለኔ ያቃል አያቅም??የሚለዉ የተወዛገባ ሀሳብ በጭራሽ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም....ብቻየን በሀሳብ ማዕበል እጓዛለሁ ..ግን ምን ዉሳኔ እንደምወስን ይጨንቀኛል ..ደግሞም ልንገረዉ ብየ እወስንና እንዴት ብየ ልንገረዉ??እያልኩ ደግሞ ሀሳብ ይሆንብኛል ግን ያለኝ አንድና አንድ ብቻ ነዉ ...ካልደፈረሰ አይጠራም በልጅነቴ መደፈሬን ለመንገር ወሰንኩኝ

ሚፍታህ ሲደዉልልኝ ከዛሬ ነገ ልንገረዉ?? መቼ አልንገረዉ ???እያልኩ እኔዉ ለራሴ ሀሳብ ሆነኝ እንዴት ብየ ልንገረዉ???...ዉይ ሒወት የስቃይ ማዕበል
864 viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 09:15:29 አባቴም:- ኡስታዝ እናንተ መጥታችሁ እንዴት እምቢ እላለሁ ??? እሺ ተስማማቻለሁ ነገር ግን ነዋል የሁለተኛ አመት ተማሪ ናት ዘንድሮን ትማር ከዛም ሶስተኛ አመቷ ላይ ኒካህ ያስራሉ ከዛም ትምህርት ስጨርስ ቀጥታ ይጋባሉ ብሎ አባቴ አስተያየት አቀረበ .
...የሚፍታህ አባትም መርሀባ ተስማምተናል ብለዉ የኔ እና የሚፍታህን ወደ ትዳር የምንገባበት ፈትል መፈተል ተጀመረ፡፡

ሰዉ ሁሉ ጆሮ ደረሰ ሚፍታህ እና ነዋል ሊጋቡ ነዉ ተብሎ በእኛ ሰፈር በአንዴ ተናፈሰ፡፡ ካሊድም ይሄዉ ወሬ ጆሮዉ ደረሰ
ካሊድም በtelegram እንዲህ ብሎ ላከልኝ
""' ወሬዉን ሰምቻለሁ አንቺ ደስተኛ ከሆንሽ ጥሩ ነዉ ..ግን አንድ ነገር እወቄ ልታገቢ ነዉ ተብሏል ነገር ግን መቼም ቢሆን እኔ ከአንቺ ተስፋ አልቆርጥም.. #ከአሏህ_ጋር_የኔ_እንደምትሆኝ_ተስፋ_አልቆርጥም አለኝ """"
   የሚፍታህ ጓደኛ የሱፍ ይሄን ወሬ ሲሰማ ከባድ ፀብ ተፈጠረ ....ሚፍታህን እገለሀለሁ አንተ ከሀዲ ጓደኛየ ነህ አምንሀለሁ ነዋልን እወዳታለሁ አንተ ጠይቅልኝ ብልህ እኔን አብሮ አደግ ጓደኛህን አሞኝተህ ሸዉደህ ለራስህ ልታገባት ነዉ አይደል ...አማናሀን በላህ ቃልህን በላህ አንተ ከሀዲ መቼም ቢሆን አንተን አለቅህም ብሎ ዝቶበት ከቤተሰብ ድረስ የደረሰ ከባድ ፀብ ተጣሉ፡፡
   
ከአሁን በፊትም እኔ ሚፍታህ በስልክ በምናወራበት  ጊዜ የሱፍ መረጃዉ ደርሶት ብዙ ጊዜ ተጣልተዋል፡፡ ጂማ ሲመጣ እና በአካል ሲገናኙ ደግሞም የትዳር ወሬዉን ሲሰማ የሱፍ መቋቋም አልቻለም፡፡ 

   እኔና ሚፍታህ የየሱፍ ፉከራ ድንፋታና እገልሀለሁ ቢልም በስልክ ማዉራታችን ተያይዘንዋል...እንደዉም ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ስለወደፊቱ የትዳር ሒወታችን እያወራን ነዉ ...በስልክ ስንደዋወል ነዋል ስንት ልጅ ከኔ መዉለድ ትፈልጊያለሽ???ይለኛል
...እኔም አንተን ደስ የሚልህን ያህል እወልድልሀለሁ እለዋለሁ
..እኔም በተራየ ሚፍታህ ስንት ልጅ መዉለድ ትፈልጋለህ??? እለዋለሁ...
...እሱም አንቺ መዉለድ እስከምታቆሚ እወልዳለሁ ይሄን ያህል ማለት አልፈልግም ይለኛል ..

    የብዙ ቀን የደስታ ህይወት በሰከንዶች ወደ ሀዘን የሚቀይረዉን ጌታ ኩን በሚለዉ ቃሉ ዱንያ የደስታ ህይወት መኖሪያ ስላልሆነ የሀዘን ማቅ ያኮናንባል .. በቀናት በሰከንድ በደቂቃ ምን እንደሚፈጠር አናቅም ..በሀያሉ አሏህ ትዕዛዝ በአንድ ሰከንድ የስንት አመት ደስታን ማደብዘዝ ሲችል. በተዘዋዋሪ ደግሞ በአንድ ሰከንድ የብዙ አመታት ስቃይ ለቅሶን ወደ ደስታ መቀየር አይሳነዉም ..ታዳ በጊዜ ብዛት ሚፍታህ የሚያወራዉ ወሬ የማይሆን ለጆሮ የሚቀፍ ሆነብኝ ..ይህን አዲስ ባህሪ ከየት አመጣዉ እስከምል ድረስ ፀባዩ ተቀያየረብኝ ..... ስልክ ስንደዋወል እንዲህ ማለት ጀመረ>>>>>>

#ነዋል_ሚስቴ_ድንግል_ካልሆነች_መቼም_አፍርባታለሁ፡፡ የእኔ ሚስት ሁሌም ምኞቴ ድልግል እንድትሆን ነዉ..ባለፈዉ  ጓደኛየ አግብቶ  ሚስቱ ቢክራ ባለመሆና በጣም ተናዷል....እኔ ሚስቴ ቢክራ ባትሆን ሳልዉል ሳላድር ቀጥታ ለቤተሰቦቿ ነዉ የምመልሳት....
.....ጓደኛዉን ስሙን እየጠቀሰ እንትና ጓደኛየ ሚስት ቨርጅን ናት .. እንዴት ደስ እንዳለዉ ልነግርሽ አልችልም ጓደኛየ አሁን ድረስ ወሬዉ ሚስቴ እኮ ቢክራ አገኘሁባት እናንተ የምታገቡትን ሚስት አይቼ እያለን ነዉ ይለኛል.... በስልክ በተከታታይ ቀናት በደወለ ቁጥር የጓደኞቹን የትዳር ገጠመኝ ይነግረኝ ይዟል...

ስለጓደኞቹ ታሪክ ይተርክልኝ ይዟል .. ሚስቶቻቸዉ ጋር የተጣሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ ...ከጓደኞቹ ሚስቶክ ቢክራ የሆኑት ማን እንደሆኑ እና ቢክራ ያልሆኑት ማን እንደሆኑ ታሪካቸዉን ይተርክልኛል ፡፡
....እኔም ሁሌም ታወራላችሁ ማለት ነዉ ስለዚህ ጉዳይ ??ብየ ጠየኩት
....እሱም አዎ ግድ ነዉ ጓደኞቼ ሚስጥር አይደብቁኝም እኔም አልደብቃቸዉም አለኝ

ሚፍታህ እንደዚህ ሲለኝ የኔ እጣ ፈንታ ምንድን ነዉ ???ነገ እኔም ስንጋባ ቨርጅን አይደለሁም አይቤን ለጓደኞቹ ሊያወጣብኝ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ ሚፍታህ እኔን እስከማንነቴ አይቀበለኝም ብየ እራሴን አሳመንኩት፡፡ እየወደድኩት እያፈቀርኩት በልጅነቴ ስለተደፈርኩ ድንግል አይደለሁም ብየ ራሴን አሳምኜ ሚፍታህን ልለየዉ ወሰንኩኝ...



በልጅነቴ የደፈረኝን ቶፊቅን በመጥፎ ጎኑ እያሰብኩ ስሙን በመጥፎ እያነሳሁ ብቻየን መኝታ ክፍሌ ቁጭ ብየ አይኔ ቀይ ሸክላ አፈር እስኪመስል ድረስ አለቅስ ይዣለሁ .....ምን ይደረጋል ማንነት በእምባ አይመለስም...ፈሶ አያልቅ ወይ ከዚህ ጭንቀት አይገላግለኝ ..ይሄን ሁሉ የዘረገፍኩት እምባ አላህን ፈርቼ አንድ ቀን ባለቅስበት ስንት ሀጃየን ያሳካልኝ ነበር??ብየ አስባለሁ
ከአሁን ቡሀላ በአላህ ተወኩል ማድረግ አለብኝ አላህ ያለዉ ይሆናል ካልሆነ ይቀራል ብየ እራሴን አሳመንኩ...አላህ ያለዉ ሚፍታህ ለኔ ካለዉ ከነማንነቴ ከተቀበለኝ በሩ ክፍት ነዉ ካልሆነም አላህ የተሻለ ይሰጠኛል ብየ ሙሉ በሙሉ ሁሉ ነገሬን ለአሏህ ሰጠሁኝ...ይሄ የድንግልና ጉዳይ ሲነሳ ጉልበቴ የሚፍረከረከዉ እምባየ የሚፈሰዉ ለምንድን ነዉ?? ሰነፍ ደካማ መሆን የለብኝም እምነቴን ሙሉ በሙሉ ለአላህ መስጠት እንዳለብኝ እራሴን አሳመንኩኝ

    ሁሉን ነገር አየሁት ደስተኛ የምወደዉን አግብቼ ደስተኛ  ለመሆን ሞከርኩ አልተሳካም የብስ ስቃይ ይዞብኝ መጣ... ለሊት ቀን በቀን በመነሳት አልቅሼ ዱአየን አድርጌ ሁሉንም ሀጃየን ለአላህ ሰጠሁኝ

.....የእኔም የሚፍታህም ቤተሰቦች ሁለታችን እንድንጋባ ተጠይቆ እሺ ስለተባለ ..እኔ ደግሞ ሚፍታህ ከትዳር በፊት
እኔ በልጅነቴ ስለተደፈርኩ የዛ ጠባሳ ሳያንሰኝ በሚናገራቸዉ ቃላቶች  ልቤን እያደማዉ እያቆሰለዉ  ስለሆነ ...የጓደኞቼ ሚስቶች ቢክራ ናቸዉ ሚስቴ ቢክራ ካልሆነች በምላሹ እናቷ ቤት ነዉ የምልካት እያለ በተደጋጋሚ ስለነገረኝ ...ሚስት ብሎ እኔን ምርጫዉ አርጎኛል የእሱን መስፈርት ስለማላሟላ
ሚፍታህን አሳማኝም ሆነ የማያሳምን የተለያዩ ለፀብ ለቁርሾ የሚሆን ስበብ ፈልጌ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልርቀዉ ወሰንኩኝ .........


#ክፍል
ይ.............ቀ............
.........ጥ............ላ..............ል


JOIN
´´´´´´´t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.4K viewsedited  06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ