Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ስምንት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



ሚፍታህን አሳማኝም በሆነ የማያሳምን የተለያዩ ለፀብ ለቁርሾ የሚሆን ስበብ ፈልጌ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልርቀዉ ወሰንኩኝ .........
በተለያዩ ዘዴዎች አዉቄ ሁለታችንን ሊያጣላን የሚችል ጥፋት እያጠፋሁ ነገር እየፈለኩት በራሴ ጥፋት ሚፍታህን መጣላት ጀመርኩኝ....ግን በተጣላን ማግስት ሚፍታህ ከቤቴ ስወጣ መንገድ ላይ እየጠበቀ በራሴ ጥፋት ይቅርታ አርጊልኝ  ይለኛል

በተለያዩ ዘዴዎች የዉሸት ምክንያቶች እየደረደርኩ ብዙ ጊዜ አስቀየምኩት ግን ሚፍታህ ይቅርታ አርጊልኝ እያለ ሊርቀኝ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ በጭራሽ አልቻለም.....

ከትንሽ ቀን ቡሀላ ሚፍታህ ለስራ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ ፡፡ አሁን ሚፍታህን በአካል አላገኘዉም በስልክ ብቻ ነዉ የምንገናኘዉ...ለመለያየት ከኔ ተስፋ ለመቁረጥ ጥሩ ጊዜ ነዉ ብየ አሰብኩኝ ...ለእኔም ለሚፍታህም የሚጎዳ ከባድ ዉሳኔ ወሰንኩኝ....

ሚፍታህ ከልቡ ቆርጦ እንዲጠላኝ ስልኩን block አረኩት ... ምክንያቱም እሱን ባወራሁት ድምፁን በሰማሁት ቁጥር የበለጠ እየወደድኩት እያፈቀርኩት መሀባዉ እየጨመረብኝ ሄደ ፡፡ ደግሞ በዚህ ሁኔታ ሁኜ መለየት አቅቶኝ እያለቅሱኩኝ ከዚህ በላይ ደግሞ ብወደዉ አብጄ ልብሴን መቅደዴ አልቀረም.
ፍቅር ግን ምንድን ነዉ የበፊት ምርጥ ትወልዶች፡ፍቅርን እንዴት ነበር የገለፁት??? መጀመሪያ የፍጡራን ፈጣሪ የሆነዉን የአለማት ጌታ ለአላህ ነበር ፍቅራቸዉ..እስኪ የዚችን ንፁህ ልብ ያላት ወጣት የፍቅር ታሪክ ልጋብዛችሁ

★★★ ኡመር(ረ.ዐ)በመዲና ጎዳናዎች ላይ በጨለማ ሲዘዋወሩ አንድ ቤት አጠገብ ሲደርሱ እናት እና ልጅ ሲከራከሩ ይሰማሉ
እናት፡-ልጄ ሆይ ነገ ከምንሸጠዉ ወተት ላይ ጥቂት ዉሀ ጨምሪበት
ልጅ፡-እማዬ ኸሊፋዉ ኡመር ወተት ላይ ዉሀ እንዳንጨምር ከልክለዉናል ትላታለች እናቷን
እናትም፡-ኸሊፋዉ እኮ አሁን የምንሰራዉን አያየንም አለቻት
ልጅም፡ አላህን በመፍራት ለእርሱ ባላት ፍቅር ልቧ የተሳበዉ ወጣት እንዲህ አለቻት ..እናቴ ሆይ!!!ይህን ድርጊታችንን ኸሊፋዉ ባይመለከተንም ከአላህ ግን ልንደብቀዉ አንችልም አለቻት፡፡
ልጅቱ ለእናቷ የሰጠቻት መልስ ኡመርን በቆሙበት ቦታ በሲቃ ናጣቸዉ፡፡ ከዛም ሲነጋ ቤቱ የማን ቤት እንደሆነ አረጋግጠዉ ያቺን ልጃገረድ ልጃቸዉ እንዲያገባ ሁኔታዉን አመቻቹለት፡፡ ምክንያቱም ልጅቱ ለአላህ የነበራት ፍራቻ ከርሷ የሚጠበቅ አልነበረምና፡፡ ከእነዚህ ጥንዶች የተወለደዉ በኢስላም አምስተኛዉ በትክክል የመራ ኸሊፋ እንደሆነ የተመሰከረለት ኡመር ኢብኑ አብደል አዚዝ የተገኘዉ፡፡ እናቱ አላህን ፈሪ ስለሆነች በዛ ተርብያ ስላሳደገችዉ ለዲነል ኢስላም መሪ የሆነ ልጅ አበርክታለች....እንደዚህ ለአላህ የነበራቸዉ ፍቅር ላይ ያለፉ ትዉልዶች ስንት ስቃይ አሳልፈዉ እኔ ግን በሚፍታህ ፍቅር እርብሽብሽ ለቅሶ በለቅሶ ሁኛለሁ

... እኔም እንዲህ ብየ አሰብኩኝ
>>>> #ትዳር_ለኔ_አልተፈጠረም_ቢክራ_ስላልሆንክ_የወደድኩትን_ሰዉ_ማግባት_አልችልም<<<<<<<ብየ ከሰዉ በታች እንደሆንኩ ሁሌ ይሰማኛል፡፡

 
.....ሚፍታህ በጭራሽ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ አልቻለም ፡፡ በተለያዩ የተለያዩ ሰልክ ቁጥር ቢደዉል ቢደዉል እኔ አላነሳ ስለዉ በእናቴ ስልክ ይደዉላል ፡፡
እናቴም፡- ሚፍታህ ነዉ ነዋልን ፈልጊያት ነዉ አገናኚኝ እያለ ነዉ በስልክ አግኝዉ ስትለኝ
እኔም፡- አሁን ማናገር አልፈልግም እላታለሁ......

በሌላ ስልክ ሲደዉል እንደ አጋጣሚ ካነሳሁት የእሱ ድምፅ መሆኑን ስሰማ አላናግረዉም......እንዲዚህ እያልን 3ወር ያህል የሚፍታህን ድምፅ ሳልሰማ block እንዳደረኩበት ጨከንኩበት፡፡


አንድ ቀን አባቴ ብር አሰግቢ ብሎኝ ብር ላስገባ ባንክ ቤት ሄድኩ.. የአላህ ነገር ሁኖ ሚፍታህ ጋር ባንክ ቤት ተገናኘን
.....ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
....እኔም ያልጠበኩት ነገር ነዉ ደንግጬ ወአለይኩም ሰላም አልኩት
.........የሚገርም ነዉ ገና ትናንት ከአዲስ አበባ መጥቼ ነዉ .ከአዲስ አበባ የመጣሁበትም ምክንያት ለአንቺ ብየ ነዉ ምን ሁነሽ ነዉ ስልኬን block ያረክሽዉ ??
አሁኑኑ ስልኩን ከblock አንሺዉ አለኝ
....እኔም ዉሳኔየ ነዉ አሁን አላነሳዉም አልኩት
.......ሚፍታህም ባንክ ቤት ተገልጋዮች ባሉበት ሰዉ ፊት ነዋል ምን አድርጌሽ ነዉ Block ያረግሽኝ??ምን አርጌሽ ነዉ ??? ጥፋት ካለኝ እዚሁ ሰዉ በተሰበሰበበት ጥፋቴን ንገሪኝ ፡፡ እኔ ወላሂ በጣም ነዉ የዎወድሽ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም አንቺን ተለይቶ መኖር ልቤ መቼም አይፈቅድልኝም.. ለምንድን ነዉ ብሎክ ያረግሽኝ??? እያለ ሲጮህ
በጣም ደነገጥኩኝ
....ሚፍታህም ጥፋት የለብኝም ሰዉ ፊት ነዉ ጥፋቴን የጠየኩሽ አሁኑኑ አይኔ እያየ block አንሺዉ አለኝ
...እኔ ደንግጫለሁ ብሎኩን አንስቼለት ቶሎ ብየ ከባንክ ቤቱ ወጣሁ፡፡

ከዚህ ቀን ቡሀላ የሚፍታህ ፀባይ አስተሳሰብ የተቀየረ መሰለኝ..በጣም የሚወደኝ ያለኔ መኖር የማይችልም መሰለኝ.....እንደበፊቱ በስልክ ማዉራት ጀመርን ፡፡ እቤት አባቴ በትምህርትሽ እንዳትሳነፊ  ብዙ ስልክ ማዉራት ቀንሱ ተብሎ ተከልክለናል...የማወራዉ ተደብቄ ነዉ ፡፡ እንደበፊቱ ብዙ ነገሮች ማዉራት ጀመርን ያዉ በወሬ በወሬ እኔ የምሸማቀቅበት አንገቴን የምደፋበት ስለትዳር እና ስለ ድንግልና እኔን በቀጥታ መጠየቅ ቢፈራኝም ግን በተዘዋዋሪ እንደበፊቱ የጓደኞቹን ታሪክ እያነሳ ያወራኛል
....እኔም ይሄ ወሬ መደጋገም ሲበዛብኝ ..ምራቄን ዉጬ እንዲህ አልኩት
ሚፍታህ እኔ እንደምጠብቀኝ አይነት ልጅ አይደለሁም ከኔ የተሻሉ ብዙ ሴቶች አሉ ሌላ ሴት አግባ ...እኔ አንተ ላቀረብካቸዉ የትዳር መስፈርትህ ማሟላት አልችልም አልኩት...
...እሱም ነዋል እንደዚህ አትበይ ከአንቺ የተሻለ ሴት መቼም አላገኝም እወድሻለሁ እኮ ..አንቺ የኔን የትዳር ዉሳኔ አሁን መወሰን አትችይም እኔ አንቺን መርጫለሁ ወደ ሆላ አትመልሽኝ ፡፡ በፀባይ በዲን በአስተሳሰብ ከአንቺ የተሻለ አላገኝም ይለኛል፡፡

እኔ በልጅነቴ ልደፈር አልደፈር ይወቅ አይወቅ የማቀዉ ነገር የለኝም፡፡ ግን የሱፍ ያቃል ..የሱፍ ታስታዉሱ እንደሆነ ገና ታሪኩ እንደጀመረ ልጅ ሁኜ ተራዊህ ልንሰግድ ገብተን እናቴ ነዋል በልጅነቷ ተደፍራለች ብላ ነግራኛለች ብላ የተጣላሇት ልጅ እህቱ ናት( part ➎ላይ ያለችዉ ልጅ) ፡፡
የሱፍ የኔን ታሪክ ያዉቃል..ግን ለሚፍታህ ይንገረዉ አይንገረዉ የማቀዉ ነገር የለኝም...

ግን ሚፍታህ ጋር በአወራን ቁጥር የእኔ ባለቤት ድንግል ካልሆነች ቀልድ የለም ይለኛል ..እንደዚህ ሲል መደፈሬን አልሰማም ማለት ነዉ ብየ አሰብኩኝ... ግን አሁን ድረስ ግራ የሚገባኝ ለኔም ያልተመለሰልኝ መልስ ሚፍታህ ስለኔ ያቃል አያቅም??የሚለዉ የተወዛገባ ሀሳብ በጭራሽ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም....ብቻየን በሀሳብ ማዕበል እጓዛለሁ ..ግን ምን ዉሳኔ እንደምወስን ይጨንቀኛል ..ደግሞም ልንገረዉ ብየ እወስንና እንዴት ብየ ልንገረዉ??እያልኩ ደግሞ ሀሳብ ይሆንብኛል ግን ያለኝ አንድና አንድ ብቻ ነዉ ...ካልደፈረሰ አይጠራም በልጅነቴ መደፈሬን ለመንገር ወሰንኩኝ

ሚፍታህ ሲደዉልልኝ ከዛሬ ነገ ልንገረዉ?? መቼ አልንገረዉ ???እያልኩ እኔዉ ለራሴ ሀሳብ ሆነኝ እንዴት ብየ ልንገረዉ???...ዉይ ሒወት የስቃይ ማዕበል