Get Mystery Box with random crypto!

የሒወቴ ከባዱ ፈተና ይህ አመት ነዉ ልጅ ሁኜ ትምህርት ቤት ያለዉ ተፅእኖ ያሳለፍኩት አሁን ካለ | ISLAMIC SCHOOL

የሒወቴ ከባዱ ፈተና ይህ አመት ነዉ

ልጅ ሁኜ ትምህርት ቤት ያለዉ ተፅእኖ ያሳለፍኩት አሁን ካለሁበት ሳነፃፅረዉ በልጅነቴ ሲሰድቡኝ ሲጠቋቆሙብኝ የነበረዉ ቀላል ነዉ ...የኔን ማንነት ለማያቅ ሰዉ ነገ አብሬዉ ለምኖረዉ ለትዳር አጋሬ እንዴት ብየ ነዉ ድንግል አለመሆኔን የምነግረዉ ??
እኔ እወደዋለሁ እሱም ይወደኛል ለመጋባት በመሀከላችን ምንም የሚያጣላን የሚያለያየን ነገር የለም ..ነገር ግን የኔን ማንነት ይቀበለኛል ወይ ? ?? አግብቼ ከሚፍታህ ጋር በዚሁ ምክንያት ከትዳር መለያየት ቢመጣ ነዋል አግብታ ፈታች እየተባለ የቡና መጠጫ ወሬ እሆናለሁ ...

ደግሞ እኔን የሚያቁኝ ሰዎች ከሌሎች ሴቶች ለኔ ቦታ አላቸዉ በትምህርቷ ጎበዝ ናት፡ ዲን አላት ፡ጥሩ ፀባይ አላት ፡ ጅልባብ ለባሽ ናት ብሎ ማንኛዉም ሰዉ ይመሰክርልኛል....ነገር ግን ዉስጤ ያለዉ ቁስል ነዶ የማያልቅ የፉም እሷት ጨብጬ ይዣለሁ ...እንዴት አርጌ ልንገረዉ ??? እያልኩ ብቻየን መጨነቅ መኝታ ክፍል ሁኜ ማልቀስ ሁኗል ስራየ

ሚፍታህ ተወኝ ብለዉ አይተወኝም...,,ደግሞ ካልተወኝ ለወደፊት ግንኙነታችን ለመጋባት ስለጨረስን ይሄን ነገር ማወቅ አለበት ...ከተጋባን ቡሀላ ድንግል አለመሆኔን ያዉቃል ከዛ ምን ይፈጠር ይሆን ???እላለሁ 

ለሊት እየተነሳሁ ረከአተይን ሰግጄ ዱአ አደርጋለሁ ... ደግሞም በማንኛዉም ሰአት እና ከሶላት ቡሀላ ዱአ አደርጋለሁ...የሚገርማችሁ ነገር ይሄን ዱአ በመደጋገም አደርግ ነበር >>>

#አላህዋ_መርየመን_ያለድንግል_ማንም_ሳይነካት እንድትወልድ ያረካት ጌታ ሆይ የመርየምን ድንግል ለኔ ስጠኝ<<<<<<<< ብየ ብዙ ጊዜ አልቅሼ ዱአ አድርጌያለሁ በሒወቴ ከባዱ ገጠመኝ በማንነቴ ያለቀስኩበት የተጎዳሁበት አመት ይሄ አመት ነዉ ፡፡

ኮሌጅ የሁለተኛ አመትን እንደዚህ ነበር ያሳለፍኩት....እናም አመት ዙሮ ረመዷን ቢደርስም የዚህ አመት ረመዷንን በመጨናነቅ በማሰብ አሰለፍኩኝ.....አስከትሎም ኢድም አልፎ ዛሬ ልንገረዉ አልንገረዉ እያልኩኝ ስወዛገብ ሳለቅስ ኑሬ ...... ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመንገር ተዘጋጀሁ...ለመንገር ለሚፍታህ ልደዉል ስልኬ ከተቀመጠበት ሳነሳ በእጄ እንዳለ ስልኬ ጠራ ..የደወለዉም ሚፍታህ ነዉ፡፡

ስልኩን አንስቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.....ነዋል ልሄድ ነዉ አለኝ
.........,,እኔም ልቤ እየደነገጠ የት ነዉ የምትሄደዉ ??አልኩት
...እሱም አረፋን የምዉለዉ ሀጃጆች ጋር ነዉ.. በዚህ አስር ቀን ዉስጥ ሳዉዲ አረቢያ ሀጅ ልሄድ ነዉ ከሀጅ ስመለሰ እናወራለን እዛ ሁኜ በimo እና telegram እንገናኛለን አለኝ......
...እኔም እሄዳለሁ ሲለኝ ደንጋጤም ጥርጣሬም አስቤ ነበር ..ተረጋግቼ መርሀባ አላህ ያሳካልህ ሀጅህንም ይቀበልህ እኔም ብዙ ሀጃ አለኝ በዱአህ አትርሳኝ አልኩት
....እሱም አልረሳሽም አለኝ

ሚፍታህ ለሀጅ ወደ ሳዉዲ አረብያ ሄደ ..ሳዉዲ ከገባበት ሰአት ጀምሮ እኔ እዛ የሄድኩ እስኪመስለኝ ሳዉዲን በየሄደበት በtelegram እና በimo video እየቀረፀ እየላከ ያሳየኛል፡፡ ጠዋፍ ሲያደርግ..ሶፋ እና መርዋ ላይ ሲወጣ..አረፋ ተራራ ..ስንቱን ላዉራዉ ሀጅ በሚያደርገበት ቀን በቀን ያለዉን ሁኔታ እስከሚመለስ ድረስ በimo እየላከ ያሳየኛል፡፡ አሁን ላይ ሁኜ ሳስበዉ ሀጅ የሚሰራዉ ሀጅ አደረገ ለመባል ነዉ ወይስ ግዴታ አላህ እንደአዘዘዉ ሰርቶ ወንጀሉን እንዲማር ነዉ ??
እስኪ እንደዚህ አድርጎ ያረገዉ ሀጅ ከአላህ ጋር ተቀባይነት ያገኝ ይሆን ??? እላለሁ፡፡ ታዳ ይሄ አይነት አላህን ይፈራል ብሎ መገመት ይቻላልን??


ታዳ እንደሚፍታህ ያሉ ሀጃጆች ስንት ስራቸዉን አበላሽተዋል??? ቤት ይቁጠረዉ ..አላህ ሆይ አንተ ያዘዝከንን ስንሰራ ከሰዉ ምስጋናን ሳይሆን የአንተን ሀቅ አሟልተን ከአንተ ሽልማት የምናገኝ አድርገን

ሚፍታህ ሀጅ አድርጎ ሲመጣ ጂማ የሚገኘዉ መርካቶ ሰፈር ኤሌክትሮኒስ ሱቅ ከፈተ ...ታላቅ ወንድሙ ከዉጭ ሀገር እቃ ይልካል አንድ ወንድሙ አዲስ አበባ ይሸጣል ለሚፍታህ ደግም ወደ ጅማ ይላክለታል.....ሚፍታህ ኑሮዉንም አዚሁ ጅማ አደረገ ፡፡ ለኔ በጣም ደስ አለኝ በስልክ ሳይሆን ሲናፍቀኝ አይኑን ማየት እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡


አንድ ቀን እለቱ ቅዳሜ ቀን ነዉ የኔን ማንነት በልጅነቴ መደፈሬን ልንግረዉ ብየ እራሴን አሳምኜ ደወልኩለት
....... ስልኩን አነሳዉ
............ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ሚፍታህ ዛሬ ትልቅ ሚስጥር ነዉ የምነግርህ ..አደራህን የምነግርህን ተረዳኝ በነገርኩህ ነገር ተቀይመህ ወይም እኔን እንደአሰብከኝ አለመሆኔን ስታቅ ከአንተ አፍ የሚወጣዉ ቃላት እኔን አንተን የሚወደዉን ልቤን እንዳያደማዉ ተጠንቀቅ ..እኔ ለአንተ ያልነገርኩህ ብዙ የሚያስጨንቁ በሆዴ የታፈኑ ማንነቶች አሉኝ..አንተ እኔን እንደምታስበኝ ሴት አይደለሁም.. የአንተ የትዳር መስፈርትህ እኔ ካለኝ ማንነት ጋር በጣም ሰፊ ልዩነት አለ አልሆንህም .....እያልኩ ወደ ዋናዉ ቁም ነገር መደፈሬን ልነግረዉ ከአፌ ላወጣዉ ስል...,ሚፍታህ ወሬየን አስቆመኝ
.....ነዋል ወሬዉን አቁሚዉ እና አሁኑኑ በአካል እፈልግሻለሁ እቤት ነይ አለኝ.....
.....እኔም እሺ ብየ ከጠየቀኝ አንድ ባንድ እነግረዋለሁ ብየ ወደ ቤቱ ሄድኩኝ

... እቤቱ እንደደረስኩ ያየሁት ነገር አይኔን ማመን አቃተኝ...እኔ ያሰብኩት ሌላ የሚሆነዉ ሌላ ነዉ
.......ሚፍታህ ቢያንስ ከ6 የሚበልጡ ጓደኞች ባሉበት ነዋል እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም  ይሄዉ በጓደኞቼ ፊት እመሰክርልሻለሁ ...,በተጨማሪም አንድ የማረሳዉ ንግግር እንዲህ አለኝ
>>>>>>እኔ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እንደፈለኩ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ስል ቆይቼ ተወኝ ስትይኝ የምተወዉ አንስተሽ የምትወረዉሪኝ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እኔ የፍቅር የመዉደድ ስሜት የለኝም እንዴ??" ...እኔ አልሆንህም ስትይኝ እኮ ልቤ እየደማ ነዉ ነዋል እባክሽ ሌላ ፈልግ አትበይኝ እንደዚህ ስትይኝ ፍቅርሽ ያሳደረብኝ ዉጋት እየጨመረብኝ ነዉ <<<<<<አለኝ፡፡

እኔም እንደዚህ ሲለኝ ሆዴ ባባ አሳዘነኝ እሺ ከአሁን ቡሀላ እንዲህ አልልህም አልኩት

ወደ ቤቴ ተመለስኩ ... ማታ ተኝቼ ዛሬ ሚፍታህ እቤቱ ሂጄ በነገረኝ ቃላቶች አስተነተንኩኝ እንደሚወደኝ እርግጠኛ ሆንኩ በጓደኞቼ ፊት ነዉ ቃል የገባልኝ... ሚፍታህ እንደዚህ ቢለኝም ግን ይሄ ማንነቴን መናገር አለብኝኝ ግዴታየ ነዉ ....በልጅነቴ መደፈሬን ተገናኝተን ሻይ ቡና እያልን ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ ወሰንኩኝ ፡፡ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ የወሰንኩት ዛሬ በተናገሩኝ ቃላቶች እኔ አልሆንህም ሁለተኛ እንዳትይኝ ስላለኝ ደስታዉን በዚህ ሳምንት ላለማደፍረስ በማሰብ ነዉ፡፡

  ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ይሄን ጉዳይ ለመንገር ... ስደዉልለት ስልኬን block አድርጎታል.....በጣም ግራ ገባኝ በጓደኞቼ እና በሌላ ሰዎች ስልክ ስደዉልም የኔ ድምፅ መሆኑን ሲሰማ ጆሮየ ላይ ይዘጋብኛል.. ስልክ ማንሳቱንም አቆመ ..
ምክንያቱን በማላቀዉ መልኩ ሚፍታህ የእኔን ስልክ block አረገዉ የጓደኞቼንም አያነሳም...በጣም ግራ ገባኝ ምን ይሆን ምክንያቱ ????

#ክፍል
ይ..........ቀ.......
....ጥ..........ላ............ል

    t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•