Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.55K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-19 06:31:16 ልቧ ባይቆሽሽ አትራቆትም ነበር ከሂጃብ መራቆቷ ራሱ የወንጀል መብዛት አንዱ ምልክት ነው ሸይጧን ሴትን ልጅ ወንጀል እንድታበዛና እንድትሰራ ይገፋፋታል ከዛ በኋላ ግን ከሂጃቧ እንድትገፈፍና ክብር እንዳይኖራትና በባለጌዎች እንድትደፈርና እንደ ቀላል እንድትታይ ያደርጋል፡፡ ሒጃቧን በአግባቡ የምትለብስ ሴት ግን ሁሉም ዘንድ ክብር አላት ባለጌዎች ዘንድም ክብር አላት እሷን ቀና ብለው እንኳን አያዩዋትም መልካም ሰዎች ዘንድም ልዩ ክብር አላት።

⇘ሒጃብ ኢማን ነው ኢማን ማለት:– በልብ ማመን በምላስ መናገር በአካል መተግበር ነውና።
አንዳንዶች ካሉበት ሸሪዓን የሚቃረን ተግባር እንዲመለሱ ሲነገራቸው ኢማን በልብ ነው ልቤን ከፍተህ አይተሀል? እያሉ የውሸት ቅንብራቸውን ስያቀናብሩ ይስተዋላሉ። ጥያቄ አለኝ ልባችሁ ካመነበት ተግባራችሁ ሊመሰክር ምን ከለከላችሁ? ለአላህ ግን መዋሸት አይቻልም! ለማነኛውም ኢማን ሶስት ክፍሎች አሉት ከነዛ ውስጥ ምንም ማጉደል አይቻል ታዲያ 3ኛው በአካል መተግበር ነውና ተግብሪ ሒጃብሽን ጠብቂ አንቺ ሒጃብ ብለሽ የምትጠሪው በወገብሽ ልክ አጣብቀሽ የሰዉነት ክፍልሽን የሚያሳይ አድርገሽ ከሴቶች ሱሪ ከሚለብሱት የማይሻል አድርገሽ የምታሰሪዉ ሳይሆን ኢስላም/ሸሪዓ ሒጃብ ብሎ ያስቀመጠልሽን ሒጃብ ነው የምልሽ።

⇘ሒጃብ የህፍረተ–ገላ መደበቂያ ነው። ሴት ልጅ ደግሞ መላ ሰውነቷ ህፍረተ–ገላ ነውና መላ ሰውነቷን ልትሸፍነው ይገባታል!! አንዳንድ (ፈቂህ መስለው ሙተፈቂሆች) ስለ ዲኑ ሳይገነዘቡ የተገነዘቡ የሚመስሉ ሰዎች እና ሴትን ልጅ ልቅ እንድትሆን ከአጂ ነብይ ጋር እንደፈለገች እንድትተራመስ ኢስላምን ታኮ የመጣ ኢስላም መስሎ ኢስላምን የሚያዳክም ሊያጠፋ የመጣ የአህባሽ አስተምሮን ይመስል አይ እጅና ፊት እንኳን ሱና ነው ኪላፍ አለበት ምናምን… የሚሉትን ተረታቸውን ትተሽ አንቺ ለአላህ ብለሽ ተቃራኒ ፆታዎችን ላለ መወስወስ ብለሽ መላ ሰውነትሽን ልትሸፋፈኚ ይገባል።

⇘ሒጃብ የሼመኝነት ምልክት ነው። የሴት ልጅ ተፈጥሮ ሼመኝነት ነውና ተፈጥሮን ጥለሽ ሌላን ለመሆን መሞከር አደጋው የከፋ ነው።
ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሴት ሁና በወንድ የምትመሳሰልና ወንድ ሁኖ በሴት የመመሳሰልን አላህ ረግሟቸዋል ብለዋል። ልብ በይ እህቴ የአላህ እርግማን ነው ያለበት!

⇘ሒጃብ መልካም የሆነች አማኝ ሴት በህሪ ነው። አላህ ይጠብቅሽና እህቴ የዚህ ተቃራኒ መሆንሽ ምንኛ የከፋ ነው? መልሱን ቆም ብለሽ እንድትመልሺው ለአንቺው ተውኩት


       አንድ ኡስታዝ ደአዋ እያደረገ.. የተለያዩ ሀይማኖቶች ስብከታቸዉን እያካሄዱ ሙስሊሙ ተዳክሟል ምን ይሻላል? ተብሎ ተጠይቆ እንዲህ ብሎ መልሷል ፡-እኔ ግን የሚያሳስበኝ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሌሎች ስብከት ሌላን ሀይማኖት ይከተላል የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በስሜት ተከታይነት ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ ብሏል፡፡
⇘አዎን! በትክክል ተጨባጩም የሚያስገነዝበው ይህን ነው
በአሁኑ ሰዓት ስለ ዲኑ ጠንቅቆ የሚያውቀው በጣም አናሳ ነው በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አብዘሀኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ትንሽ ያውቃል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበትም አላህ ያዘነለት ሲቀር የስሜቱ ተከታይ ነው በስሜት ተከታይነት ሀራሙ እንደ ሀላል ተቆጥሮዋል በስሜት ተከታይነት ሱና ቢድዓ ይደረጋል ቢድዓ ደግሞ በተቃራኒው እንደ ሱና ይታያል በስሜት ተከታይነት ሽርክ እንደ ተውሂድ የሚቆጠርበት ቦታም አለ… ሌላም ሌላም
ይህንኑ የሚያበረታቱና ባለ በሌለ ሀይላቸው የሚያስፋፉ የሸይጧን ወዳጆች ደግሞ በዛው ልክ በዝተዋሉ!

ልብ በይ እህቴ!!!!! አንቺ የህብረተሰቡ መሰረት ነሽ አንቺ ከተበላሸሽ ይህ ህብረተሰብ ይበላሻል አንቺ ከተስተካከልሽና ከለማሽ ህበረተሰቡም ይስተካከላል አንቺን ለማጥመምና ከተፈጥሮሽ ለማውጣት ከሂጃብሽ ለማላቀቅ ከአላህና ከመልዕክተኛውﷺ ተከታይነት አስወጥተው የሸይጧንና የስሜትሽ ተከታይ ሆነሽ የጀሀነምን ገደል ገብተሽ ህብረተሰቡንም ወደ ጀሀነም ገደል እንድታስገቢ ሸይጧንና የሸይጧን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት አውቀሽ ለእነሱ አላማ የሚመቻቸውን አካሂድ እርግፍ አድርሽ ትተሽ ወደ አላህ ተመልሰሽ ሒጃብሽን ጠብቀሽ ስለ ዲንሽ ተምረሽ አውቀሽ ተግብረሽ ምርጥ ትውልዶችን የጀነት ሙሹሮችን አፍሪ
ይህቺ አለም እያየሻት ነው አጭርናትና ለዘላለማዊ አለም ጥሩ ስንቅ ሰንቂ።



       እኔም ጅልባቡን ልልበስ አልልበስ እያልኩ ለብቻየ ሳመነታ ዉሳኔየ ሲምታታብኝ ለመፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ለብሼ ልመጣ ነበር የሰዉ አይን ማየት እና ሰዉ ምን ይሉኛል ብየ ፈራሁ ምን ይሻለኛል?? አልኳት
......መፍቱሀም ነዋልየ አንቺ የምፈሪዉ አላህን ከሆነ ጅልባቡን እንደለበሽ ሳታወልቂ ነይ ... አንቺንም እኔንም እነሱንም የፈጠረንን አላህን ብቻ ፍሪ አላህን ካልፈራሽ ማንን ትፈሪያለሽ ??...ግን ሰዉ ከሆነ የምፈሪዉ ቀይረሽዉ ትመጫለሽ ማለት ነዉ..ለሰዉ በጭራሽ እንዳትጨነቂ ....ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........

ነዋል ጅልባቡን ትለብሰዉ ይሆን???

#ክፍል

ይ........ቀ ......
.....ጥ.........ላ........ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.4K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 06:30:54 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ሶስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....

ዓሊይ መስጊድ ደረስን የሴቱ ጀመአ በጣም ብዙ ናቸዉ
.....መፍቱሀም አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ዉድ የኢስላም እህቶቼ ዛሬ አንድ እህታችን መጥታለች ስሟም ነዋል ትባላለች ብላ ከሁሉም ጋር በአንዴ አስተዋወቀችኝ፡፡ ደስ የሚሉ ጀመአዎች ነበሩ ሲጀመር እኔም በባህሪየ ሰዉ ጋር መቀራረብ ሰዉ ጋር መላመድ ችግር የለብኝም ..ሁሉም ጋር ብዙም ቀን ሳይፈጅብኝ ተግባባን፡፡


መፍቱሀም፡- ሁሌ ቅዳሜ መቅረት አይቻልም የጀመአዉ አባል ተብለሽ ተመዝግበሻል አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ እመጣለሁ አልኩኝ..
    መፍቱሀ ጋር ወደ ቤት እየተመለስን ግን የወደፊት አላማሽ ምንድን ነዉ ?? ለወንድ ልጅ ያለሽ አመለካከትስ እንዴት ነዉ ?? አለችኝ
.....እኔም ወንድ ልጅን በፍቅር አልቀርብም አላህ ባለቀን boyfrind ሳልይዝ እኔን ከማንነቴ ተቀብሎኝ ቀጥታ ቤተሰብ የሚጠይቅ ነዉ የምፈልገዉ ..እኔ በዘንድሮ ፍቅር አላምንም አልኳት
...መፍቱሀም ማሻ አላህ ወላሂ የኔም ሀሳብ እንደዚሁ ነዉ የኔ ሀላል ባሌ የምፈልገዉ እኔን በቻት በተለያዩ መህበራዊ ሚዲያ ሳይጀነጅነኝ በመስኮት ሳይሆን በበር የሚገባ ለቤተሰቦቼ የሚያሳዉቅ ነዉ የምፈልገዉ አለችኝ ፡፡ሁሌ ተገናኝተን ስለፍቅር ስለትዳር ካወራን አስተሳሰባችን አንድ አይነት ነዉ፡፡

መፍቱሀ ጋር ከምነግራችሁ በላይ በጣም እንዋዳደላለን ከጓደኛ በላይ እንደ እህት ነዉ የማያት ...ጓደኝነታችን በጣም ቅርርብ ስላለን ብቻየን እኔ ከሄድኩ ወይ መፍቱሀ ብቻዋን ከሄደች ምነዉ ጓደኛሽ ዛሬ የለችም ወይ?..ወይ እሷን ነዋል ዛሬ የለችም ወይ ?ብለዉ ይጠይቁናል.. ብዙ ጊዜ በጀመአም በስብሰባም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የሆነ ጥያቄ ሀሳብ ካስፈለገ የእኔና የእሷ ሀሳብ ሁሌም አንድ ነዉ፡፡ እኔ የሆነ ነገር ሳስብ እሷም አስባዉ አገኛታለሁ..የሆነ ኸይር ስራ ለመስራት ሳስብ ላማክራት ስል ወይ እሷ ትቀድመኛለች ወይ ስነግራት እሷም እንደ አሰበችዉ ትነግረኛለች ..እሷም የሆነ ሀሳብ ስታማክረኝ እኔም የአሰብኩት ሀሳብ ሁኖ አገኘዋለሁ....ከአካል አልፎ ልባችን ለራሱ ጓደኝነት ፈጥሯል..ሰዉ ብዙ ጓደኛ አለዉ  ..በጣት የሚቆጠር የልብ ጓደኛ የሚለዉ አለ ነገር ግን ጭራሽ ልብ ለልብ አይገናኙም ጭራሽ የሆድህን ለማስረዳት ጓደኛም ለመረዳት ሳይቻል ይስተዋላል..ይሄ ገና ጓደኝነቱ ብዙ ይቀረዋል ማለት ነዉ፡፡ ለምን ጓደኝነት በሀሳብ ገና ፊትህን አንብቦ የልብህን የሚያቅ ሲሆን ነዉ፡፡ የሚገርማችሁ አመናችሁም አላመናችሁም ያዉ በአላህ ፍቃዴ እኔና መፍቱሀ የወር አበባ ለራሱ የምናይበት ቀን ድረስ የተመሳሰለ ነበር...ብዙ ቀናቶች እኔ ታምሜ ሀኪም ቤት ስሄድ እሷም ትታመም ነበር...አንድ ሀኪም ሙድ ይይዝብን ነበር ዛሬ ጓደኛሽ አልታመመችም ወይ እስከ ማለት ደርሰዉ ነበር..ይሄን ያህል ድረስ ነበር የኔና የመፍቱሀ ልብ ለልብ ጓደኝነታችን


አንድ ቀን መፍቱሀ በስጦታ መሸፈኛ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...የተጠቀለለዉን ስከፍተዉ ኪታብ ነበር ...እኔም ደስ ብሎኝ አብረን ኪታብ መቅራት ጀመርኩኝ ..ለሒወቴ ትልቅ ለዉጥ እያመጣችልኝ ነዉ፡፡

ደግሞ በሌላ ቀን መፍቱሀ በስጦታ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...መፍቱሀ የተጠቀለለ ነገር ከሰጠችኝ ለኔ አስፈላጊ በጣም የሚጠቅም ነገር እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለዉም
....እኔም ምንድን ነዉ ?? አልኳት
.......እሷም የዛሬዉ ስጦታ እቤትሽ ሒደሽ አይተሽዉ ከዛ ትደዉይልኛለሽ አለችኝ
.....እኔም የሰጠችኝን ስጦታ እስከማየዉ እየቸኮልኩኝ እቤቴ ደረስኩኝ
........የስጦታ ወረቀቱን ስፈታዉ ጥቁር ጅልባብ ነዉ፡፡
እኔም ወደ መፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ወድጀዋለሁ አላህ ይስጥልኝ አልኳት
.......እሷም ነዋል ......ልበሽዉ እና በመስታወት አንቺ ጋር እንዴት እንደሚያምር ተመልከቺዉ ከዛም ዛሬ የዙሁርን ሶላት ስገጂበት...ሰግደሽበት በጣም ትወጅዋለሽ እርግጠኛ ነኝ ትሞህርት ቤት ለብሼዉ እመጣለሁ ነዉ የምትይዉ አለችኝ

እኔም መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ በመስታወት ሳየዉ በጣም ነዉ ያማረብኝ ....መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ ዙሁሩን ሰግጄ ጨርሼ ሳሰላምት አባቴ ከሆላየ ቁማል

...አባቴም ዛሬ በሰላም ነዉ እቤት የመጠሀዉ?? አልኩት
አባቴም የምፈልገዉ እቃ ነበር ጠዋት እረስቼዉ አሁን ልወስድ ነዉ .....ነዋል ጅልባቡን መቼ ገዝተሽዉ ነዉ ??? ነዋልየ የኔ ልጅ ወላሂ እንደዚህ አምሮብሽ አይቸሽ አላቅም ወደ ቤት ስገባ ጅልባብ ለብሰሽ ስሰግጂ እንዴት ደስ እንዳለኝ ከምነግርሽ በላይ ነዉ ደስታየን መቆጣጠር አቅቶኝ የደስታ እምባ አነባሁ፡፡ ነዋል አምሮብሻል አታዉልቂዉ አለኝ፡፡
....እኔም ጓደኛየ ስጦታ ሰጥታኝ ነዉ አባቢ አልኩት
.......አባቴም ጥሩ ጓደኛሽ ናት፡፡ ለወደፊትም እሷን ጓደኛ አርገሽ ያዢ ብሎ ከአንጀቱ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ ዱአ አደረገላት...ነዋል ሲመቸኝ ጓደኛሽን ታስተዋዉቂኛለሽ አለኝ አባቴ
...,,,እኔም እሺ አስተዋዉቅሀለሁ አልኩት ...አባቴም የረሳዉን እቃ ይዞ፡ከቤት ወጥቶ ሄደ
  

እኔም አምሮብኛል ማለት ነዉ ??ብየ መልሼ መልኬ እስከሚገፍ መስተዋት ላይ አፈጠጥኩኝ፡፡

ዛሬ  ከሰአት ክላስ አለን ጅልባቡን ለብሼዉ ልሂድ ወይስ አልሄድ ??ጅልባብ ስለብስ የመጀመሪያየ ነዉ ሰዉ ምን ይለኛል ??? እያልኩ ብቻየን እያሰብኩ መልበሱን ፈራሁ

★★★ በዲነል ኢስላም ሀይማኖት ዉስጥ እምነት የሚለዉ ቃል በአረበኛ ትርጉሙ ሲፈታ አንድን ነገር እዉነት ብሎ መቀበል ሲሆን ኢስላማዊ ትርጉሙና ትንታኔ ግን ሰፊ ቢሆንም የኢስላም ሊቃዉንቶች በአጭሩ ሲያስቀምጡት እንዲህ ይላሉ ..አል አሚኑ ማወቀረ ፊል ቀልብ ወሰደቀሁል አመል ..ትርጉሙም፡-እምነት ማለት በልብ ወስጥ ተደላድሎ የተቀመጠ እና ስራ ወይም ተግባር ያረጋገጠዉ ነዉ በማለት ይገልፁታል፡፡ ሌሎች የኢስላም ሙሁራን እምነትን ሲገልፁ በልባችን (በቀልባችን)እዉነት ነዉ ብለን የምንቀበለዉ..በምላሳችን ሙሉ ፍቃደኝነት የምንናገረዉ እና በሰዉነት አካላችን የምንተገብረዉ ነገር ነዉ...በማለት ይገልፁታል ፡፡እኔም ታዳ ጅልባብ መልበስ ሰዉ ምን ይለኛል ብየ ከፈራሁ እምነቴ ላይ ችግር አለ ሀይማኖቴ ከልቤ ሳይገባ ተደላድሎ አልተቀመጠም ማለት ነዉ::

ለኔ ጅልባብ መሸፈኛየ መከበሪያየ ነዉ፡፡
ምን ያህል ስለ ሒጃብ ጥቅሞች እናዉቃለን???

★★★ ሒጃብ ለአላህና ለመልዕክተኛው መታዘዝ እንጂ የሆነ ሀገር ባህል ተከታይነት አይደለም።

⇘ሒጃብ ጥብቅነትና ንፅህና ነው። ሒጃብን የማትለብስና
ከሂጃብ የተራቆተች እንስት ሁለት ነገሩዋ ቆሽሿል ፡፡ አንዱ ንፁህ ቢሆን እንኳን አንዱ ንፁህ አይሆንም አንደኛ ልቧ ቆሽሿል ፡፡ ሁለተኛ ሸይጧን አሳስቷት ሰውነቷን በተለያየ ወንጀል አቆሸዋለች በዝሙትና በተለያየ ነገር ሰውነቷን አጨማልቃው ሊሆን ይመቻል የሚፀዳው ሒጃቧን ለብሳ ክብሩዋን ጠብቃ ጥንቁቅ ሆና ወደ ጌታዋ ቁሩጥ ያለን መመለስ ስትመለስ ብቻ ነው!!!
1.4K views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 10:39:04 ትምህርት ጀመርን እኔም መማር ጀመርኩኝ...አባቴም ዩኑፎርም የለም እኮ ልብስ ጫማ እና ፓርሳ መቀያየሪያ መግዣ ብር እያለ በጣም ብዙ ብር ይሰጠኛል......በዚህም ብር በጣም የሚያማምሩ ጫማዎች ልብሶች ፓርሳዎች ስለገዛሁኝ እቀያይራለሁ፡፡ በኔ ዉበት የተነሳ የትምህርት ቤት ወንዶች እኔን አይቶ ምራቁን የማይዉጥ ወንድ የለም ..
የሚገርማችሁ ኮሌጅ ለራሱ ገብቼ የአእምሮ ዲፕሬሽን አለቀቀኝም ከሰዉ ጋር አልቀላቀልም ብቸኝነት ምርጫየ ነዉ ከክላስ ዉጭ ላይብረሪ ነዉ የማሳልፈዉ...በዚህ ፊልድ ጥሩ ዉጤት ለማምጣት ቸክየ እየተማርኩ ነዉ

ወንድም ሴትም እኔ ጋር ጓደኛ መሆን ይፈልጋሉ ለምን በትምህርቴም ጎበዝ ስለሆንኩ ብዙ ሰዉ ጓደኛ እንሁን ይሉኛል ..ግን እኔ 10ክፍል ላይ መጥፎ ጓደኞች ሒወቴን ስላበላሹት ..አሁን ያሉት የሴትም የወንድም ጓደኞች እኔ በራሴ መፈተኛ ስፈተናቸዉ አይመጥኑኝም፡፡ ሴቶቹ ወሬያቸዉ አመለካከታቸዉ..ለትምህርት ያላቸዉ አመለካከት እንደ ጊዜ ማሳለፊያ ስለያዙት እነዚህ የክላስ ልጆች ጋር አብሮ ጓደኛ መሆን ልቤ አልፈቀደልኝም፡፡ትምህርቴ ላይ ጎበዝ ሆንኩኝ ስለማጠና የሚያስተሞሩን መምህሩ ጋር በጣም ተግባባን ፡፡


             አንድ ቀን እኛ ክላስ አንዲት ጅልባብ የምለብስ ልጅ ስሟ መፍቱሀ ትባላለች ደግሞ አንዲት ክርስቲያን ልጅ አለችኝ ስሟም ብሩክታይት ትባላለች ሁለቱ አንድ ላይ መጥተዉ ከአንቺ መተዋወቅ እንፈልጋለን ብለዉ እጃቸዉን ዘረጉ....

ብሩክቲን አንግባባም እንጂ አቃታለሁኝ የእኔ እናት እና የእሷ እናት ጓደኛ ናቸዉ፡፡ ክላስ ዉስጥ ሁለታችን እንፎካከራለን ....መፍቱሀ ግን ሰነፍም ጎበዝም አትባልም መካከለኛ ናት ፡፡
......እኔም እሺ እልኩኝ
..... መፍቱሀም:- ሁሌም አንቺ ጋር መተዋወቅ እንፈልጋለን ዛሬ ደፍረን ለመተዋወቅ እኛዉ መጣን በጣም አድናቂሽ ነን ለትምህርትሽ ያለሽ ትኩረት በጣም አስደሳች ነዉ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አንቺም ለአላህ ብለሽ ዉደጅኝ አለችኝ መፍቱሀ
......እኔም 10Q ችግር የለም ከአሁን ቡሀላ ጓደኞች እንሆናለን አልኳቸዉ
.....መፍቱሀም ስልክ ቁጥር እንለዋወጥ አንዳንዴ እንደዋወላለን አለችኝ....
ስልክ ቁጥሬን ሰጠሆት የሷንም Save አረኩት..አብሬም ለብሩክቲ ስልኬን ሰጠሆት
     ስልኬን ልስጣቸዉ እንጂ ብዙም ትኩረት አላረኩም ለምን እስከ 10 በምማርበት ጊዜ ለኔ ሒወት መንገድ መሳት መጥፎ የሙስሊምም የክርስቲያንም ጓደኞች ነበሩኝ እነ መፍቱሀም ከዚህ ዉጭ ምንም አስቤ አላቅም

መፍቱሀ በቀን ሁለቴ ሶስቴ ትደዉልልኛለች የምናወራዉ ስለትምህርት በተጨማሪም ስለ ቂርአት እሷ የተለያዩ ኪታቦች እንደቀራች እና እኔም ቂርአት እንድቀራ ትመክረኛለች....,መፍቱሀ ሁሌም አብሽሪ ኪታብ መቅራት እኮ ቀላል ነዉ እኔ ስቀራ ብዙ አመት አልፈጀብኝም እያለች ...እየቀለደች እየሳቀች ሒወቷን ታጫዉተኛለች

አንድ ቀን መፍቱሀ ወደ አሱር አካባቢ ደወለችልኝና ነዋል ዛሬ ይዤሽ የምሄድበት ቦታ አለኝ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ አልኳት
....አሱርን ሰግደን ተገናኘን .... የት ነዉ የምንሄደዉ ብየ ሳልጠይቅ ወደ ምትሄድበት አብሬ ሄድኩኝ
....ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ሂደን የታመሙ ሰዎችን ዘይረን፡፡ ከሆስፒታል ስንመለስ በሌላ አካባቢ ወስዳኝ  አቅማቸዉ የደከሙ ትላልቅ ሰዎች በስራ አግዘን እና ትንሽ ብር ሰጥተን እነሱም መርቀዉን ተመለስን፡፡ መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ ዛሬ የምንሄድበት አለ እያለች ኸይር መስራት የቲሞችንን ጧሪ ቀባሪ የሌላቸዉን አዛዉንት የሆኑትን መዘየር ሁኗል ስራችን ...

የእኔ ቤተሰቦች ሀብታም ስለሆን ድህነትን አላቀዉም የተቸገሩ መኖራቸዉን ድህነት እንዴት ሰዉ እንደሚጎዳ ዘያራ በምንሄድበት ጊዜ አስተዋልኩኝ ...እኔም ልብስ ግዢ ጫማ ግዢ ተብሎ ከሚሰጠኝ ብር ላይ ለተቸገረ መስጠቱ ለኔ ደስታ ሆነኝ፡፡

መፍቱሀ የሴቶች ጀመአ አሚር ናት  በወር በወር በመዋጮ የተቸገሩትን መርጠዉ ቋሚ የብር ወይም የአስቤዛ እርዳታ ይሰጣሉ .....እስኪ ሂደን አይተናቸዉ እንምጣ ትለኛለች...አብረን ሂደን ዘይረን እነሱ ጋር ተጫዉተን ብርም ከያዝኩኝ ለአንዳንድ ነገር ይሁናችሁ እያልኩ ብር ሰጥቼ እመጣለሁ.....

እኔም መፍቱሀ ጋር በዚህ የተቸገሩትን ዘያራ በምናደርግ ሰአት እራሴን እንድፈትሽ ከኔ የባሱ ብዙ መኖራቸዉን አስተዋልኩኝ..አልሀምዱሊላህ አልኩኝ..ከኔ ጀምሬ የበታችንን ብናይ አመስግነን ባልጠገብን ነበር ግን ምነ ይደረጋል የሰዉ ልጅ ዘንጊ ነዉ እንጂ በየእለት ተግባራችን ሰንት የማንሰማዉ የማናየዉ የለም ግን ስናመሰግን አይስተዋልም፡፡
ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን በምንመለከታቸዉ የለያዪ ትዕይንቶች ልባችን ተነክቶ የአላህን ዉለታ አስታዉሰን የምናመሰግነዉ??? ወይም የምስጋና ሱጁድ የምናደርገዉ? ጥያቄዉ ለሁላችንም ይቆይ ራሳችን መልሰን እኛዉ እንረመዉ....


መፍቱሀ ለኔ ኸይር እንስራ  እያለች የምታበረታታኝ ነች፡፡ አንዳንዴም ብሩክቲም አብራን ትመጣለች...ብሩክቲ ክርስቲያን ትሁን እንጂ አለባበሷ አስተሳሰባ እንደሙስሊሞች ነዉ፡፡ ክሪም ለብሰን ፀጉራችን ከታየ ሸፍኑ ፀጉራችሁ እየታየ ነዉ ትለናለች... የቱርክ የዱባይ ጠባብ ልብስ ለብሰን ስንሄድ ይሄ እኮ ሰዉነት ያሳያል ሒጃብ ልበሱ የምትል ...,አንዳንዴ የሶላት ሰአት ደርሶ እሺ እንሰግዳለን እያልን ወሬ ስናወራ መጀመሪያ ስገዱ እያለች ትገስፀናለች፡፡ ይገርማል የብሩክታያት ቅርብ ጓደኛዋ መፍቱሀ ብቻ ናት .ብሩክቲን የኢስላምን አደብ አስተምራታለች ፡፡
 
መፍቱሀም እኔን እኛ ጀመአ መግባት አለብሽ የምንገናኛዉ በሳምንት አንዴ ነዉ እያለች ብዙ ጊዜ ነገረችኝ..
...,,እኔ ሰዉ ጋር መቀላቀሉ ሌላ ጓደኛ መፍራቱን አልፈለኩም ግን መፍቱሀ ግድ እኛ ጀመአ ገብተሽ የዲን እህቶሽን ተዋዉቀሽ ኪታብ መጀመር አለብሽ እያለች ሁሌ ስለምትናገረኝ.....እሺ ቅዳሜ እንሄዳለን አልኳት
.......ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....



በፊት አስረኛ ክፍል ስማር በመጥፎ ጓደኞች ተተብትቦ አላማየን እንዳልሳትኩኝ ዛሬ ኮሌጅ ላይ ደግሞ እንደ መፍቱሀ እና ብሩክቲ አይነት ምርጥ እህቶች እና ጓደኛ ሰጥቶኝ ...ትክክለኛ መስመር የያዝኩ ሁኛለሁ ኢስቲቃማዉን ይስጥሽ በሉኝ....

#ክፍል
ይ......ቀ.......
......ጥ......ላ........ል


JOIN
´ t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.8K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 10:38:54 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ሁለት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


.........እኔም አባቴ ትዝ ሲለኝ ጥፋተኛ መሆኔ ተሰምቶኝ አለቀስኩኝ ምን ላርግ አጎቴ ምን ላርግ ተቸግሬ እኮ ነዉ እንጂ እራሴን ማጥፋት ፈልጌዉ ወድጀዉ አይደለም እያልኩ እምባየን አፈስ ይዣለሁ ..
አጎቴም እምባየን እየጠረገ አባበለኝ፡፡

አጎቴም ዛሬ የምታዳምጭዉ ደአዋ ብሎ እራስን ስለማጥፋት ያለዉ ወንጀል ምን እንደሆነ ልኮልኝ ሄደ ፡፡ እራሱን ያጠፋ ሰዉ ጀነት አይገባም የጀሀነም ነዉ...ምንም ነገር ኸይር ቢሰራ እራሱን አጥፍቶ የሞተ ሰዉ የጀሀነም ነዉ የሚል ደአዋ አዳመኩኝ ..ደአዋዉ በጣም ረዥም ነበር አዳምጬ እንደጨረስኩኝ
ለራሴ እንደዚህ አልኩኝ...^^^^^^^^^^^ እኔ በዱንያ ደስተኛ ሳልሆን ኑሬ ደግሞ ከሞት ቡሀላ መጀመሪያ ቀብር ላይ አላህ ራሴን በአጠፋሁበት ይቀጣኛል..ደግሞም ተቀስቅሼ ሞት በሌለዉ ኑሮ ላይ በጀሀነም እሳት መሰቃየት መቀጣት አለብኝ እንዴ?? አላህ ይቅር በለኝ አልኩኝ...,ከአሁን ቡሀላ እራሴን ላላጠፋ እንኳን ላጠፋ ላላስበዉ እራሴን አሳመንኩኝ፡፡ አጎቴ የላከልኝ ደአዋ ላይ ሌላ ጥሩ ጎን ነበረዉ ተስፋ ማድረግ አላህ ጋር ተወኩል ማድረግ እንዳለብኝ ተረዳሁኝ፡፡^^^^^^^^^^^^

ለዚች ለማትጠቅም ዱንያ ፈጣሪ ስንቱን አሳየኝ?ዱንያ የፈተናዎች አለም እንጂ የደስታ አለም እንዳልሆነች ነብዪ ሰ.ዐ.ወ አስተምረዉናል
★★★ኢብን መስኡድ ረ.ዐ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፡-
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ከሳር የተሰራ በሆነ ሰሌን ላይ ተኝተዉ ሲነሱ በሰዉነታቸዉ ላይ የሰሌን ቅርፅ ይታይ ነበር፡፡"" የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የሚተኙበት ፍራሽ ላምጣልወት እንዴ?? አልኳቸዉ
....እርሳቸዉ ግን እንዲህ አሉ፡-
.ይቺ አለም ለእኔ ምኔ ናት? እኔ በዛፍ ጥላ ስር ተጠልሎ ቆይቶ ያንን ቦታ ትቶ እንደሚሄድ ጋላቢ ነኝ ፡፡ብለዋል፡፡ ነብዩ ለዚህ ዱንያ ያላቸዉ ክብር እንዲህ ብለዉ ነበር የገለፁት...ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ ለዱንያ ቅንጣት ያህል ቦታ የላቸዉም ነበር ..የመካ ቁረይሾችን እስልምናን ተቀበሉ ብለዉ ደአዋ ሲያደርጉላቸዉ ..ብር ከፈለክ ከኛ በላይ ብር እንስጥህ ወርቅ ከፈለክ ከኛ በላይ ወርቅ እንስጥህ ስልጣን ከፈለክ ከኛ በላይ ስልጣን እንስጥህ ከአንተ የምፈልገዉ እኛንም ህዝቡንም ኢስላምን ተቀበሉ አትበል ሲሏቸዉ ተወዳጁ ያአላህ ነብይ ግን ፀሀይን በቀኝ እጄ ጨረቃን በግራ እጄ ብታሲዙኝ ከዚህ አቋሜ ፍንክች አልልም ብለዉ ነዉ የመለሱት .ታዳ እኛ ዛሬ ላይ ዲነል ኢስላምን በጥብሱ በቁርሱ የሸጥነዉ ስንቶቻችን ነን??? ነብዩ ሙሀመድ ግን ከሰዉ በላይ ልሁን ቢሉ በዛን ጊዜ ከነበሩ አንባገነን መሪዎች በላይ መሆን ይችሉ ነበር...ግን አሏህ ዱንያን የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ብሎን እኛ ግን ዱንያን አፍቅረን የፈጠረንን ጌታችንን እና ቀብርን ዘንግተናል.....

በሌላ ሀዲሳቸዉ ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል ይህች አለም ለአማኞች እስር ቤት ፡ ለከሀዲያን ደግሞ ጀነት ነች..ብለዋል ..ስለሆነም አማኞች የሆናችሁ ሆይ አሁን እስር ቤት ናችሁ ..ሰዉ እስር ቤት የሚገባዉ ባህሪዉን አስተካክሎ ማህበረሰቡ ጋር ሲቀላቀል ደስታ ይኖረዋል ለምን እስር ቤት ስቃዩ ቁንጫዉ ከዘመድ ከጓደኛ ተለይቶ መኖሩ ከባድ ነዉ ከእስር ቤት ሲወጣ ደስተኛ ይሆናል፡፡ እኛም ዱንያ ላይ ስንኖር ፈጣሪ አላህ ወደ እስር ቤት ልኮን ወደ አኼራ ስንሄድ ከእስር ቤት እንደተፈታን እንቁጠረዉ..ግን ከዱንያ እስር ቤት ስንፈታ ፀባያችንን አስተካክለን ጥሩ ስራ ሰርተን ፈጣሪ እስር ቤት ገብተን የፈተንን ፈተና አልፈናል ወይ??? ፈጣሪ ከዚህ እስር ቤት ለወጣ ሁለት ሽልማት አለዉ አንዱ ግዴታ ነዉ ..እስርቤቱን ያለፈ ጀነትን ሲሸለም..እስር ቤቱ ግን ያልቀየረዉ ምን ይደረጋል መልሶ እስር ቤት ለመግባት እድል አይሰጠዉም ሽልማቱ ጀሀነም ይሆናል...አላህ ይጠብቀን ፡፡ አላህ ሆይ የዱንያን እስር ቤት ኸይር ስራ የምንከስብበት አድርገን ያረብ...
  
አጎቴም ነዋል መርዝ የመጠጣት ያደረገችዉን ሙከራ  ሚስጥሩ እዚሁ አራታችን ጋር ይቅር አላቸዉ
ሁላችንም ለአባቴ ላለመንገር ተስማማን .....አባቴ ይሄንን ወሬ ቢሰማ እኛ ቤት በጣም የከፋ ነገር ይፈጠራል...


እንደዚህ ሁኖ ግን ከእናቴ ንዝንዝ ዉጭ እቤት በማትዉልበት ጊዜ ትምህርቴን ማጥናቴን አላቆምኩኝ፡፡ ቀን እናቴ ስትዉል በዚሁ በትዳር የተነሳ ብንጣላም ማታ አዳር አጠናለሁ
.... መቼም እንደዚሁ እየተነዛነዝኩም እያጠናሁም ትዳርም እየመጣ እየመለስኩም ...አእምሮየ በልጅነቴ መደፈሬ ትዝ እያለኝ እያዘንኩኝ...የማትሪክ ፈተና ደረሰ ፕራይቤት እዛዉ ጂማ ከተማ አጂፕ (ጅሬን) ትምህርት ቤት ተፈተን .......
ክረምት ከአንድ ሀሳብ ጥናት ከሚባል አረፍኩኝ ...
የማይመጣ የለም የማትሪክ ዉጤት መጣ ዉጤቴ በጣም አሪፍ ነበር ያመጣሁት 2.9 ነዉ ...አሪፍ የሰቃይ ተማሪ ዉጤት ባይሆንም ወደ priparatory የማያሳልፈኝን ዉጤት አገኘሁኝ....ደስ አለኝ ለአባቴ ነገርኩት አባቴም በጣም ተደሰተ ..,

ይሄ ደስታየ ግን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሆኖ ቀረ እኔ ስፈጠር ተደሰች ያልተባልኩ ይመስል ሌላ አንድ ሌላ የሚያስጠላ ወሬ ደረሰኝ......

የማትሪክ ዉጤቱ በተነገረ በሳምንቱ ፈተና ስለተሰረቀ ማለፋያ ዉጤት ተጨምሯል ተብሎ የሴት የፕራይቤት ማለፊያ 3 ሆነ እኔ ያመጣሁት 2.9 ስለሆነ ለአንድ ነጥብ ተብሎ ወደኩኝ ........
የሚገርም ነዉ ምን ይደረጋል ትንሽ ቢከፋኝም ምንም አልመሰለኝም ቀደረሏህ አላህ ቀድሮታል የተሻለ አለዉ ብየ እራሴን አሳመንኩኝ....... እኔም የአቅሜን ለማለፍ ሞክሪያለሁ በመዉደቄ ምንም አልመሰለኝም አባቴም በመዉደቄ ምንም አልመሰለዉም እንደ ቀላል ነዉ ያየነዉ ፡፡

ክረምት አልቆ መስከረም ገባ...,አባቴ ጋር የዛሬ አመት ተነጋግረን ነበር መጀመሪያ በአንቺ ምርጫ ተብየ ፕራይቤት ብየ ነበር አልተሳካም፡፡ የዛን ጊዜ የአንቺ ካልተሳካ የኔን ዉሳኔ ነዉ የምወስነዉ ብሎኛል
  በቃሉ መሰረት ከአሁን ቡሀላ የእኔን ዉሳኔ ነዉ የምወስነዉ እኔ ነኝ አለኝ..
....እኔም እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አማራጭ የለኝም
.....አባቴም  በግል በዲፕሎማ እንድማር ጅማ የሚገኘዉ የግል የሆነዉ...ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ
ሊያስመዘግበኝ አብረን ሄድን ፡፡ እኔ መማር የምፈልገዉ አካዉንቲንግ ነዉ፡፡ ኮሌጁ እንደ ደረስን አባቴ የምትማሪዉ Nursing  ነዉ አለኝ ፡፡አባቴ Acounting ብማር ይሻላል ብለዉ አይሆንም ተነጋግረናል በኔ ዉሳኔ ነዉ አለኝ፡፡ Nursing ደግሞ Clinikal nursing እና ሚድ ዋይ ፋይ ነርሲግ (አዋላጅነርስ) አለ ፡፡

እኔም አባቴን እንዲህ አልኩት Acounting አትማሪም ካልከኝ ..ግን አሁን ተማሪ ካልከኝ መማር የምፈልገዉ አዋላጅ ነርሲንግ ነዉ አልኩት
.....አባቴም አይሆንም አንቺ አዋላጅ እንድትሆኝ አልፈልግም  ብሎ ሳልወድ በግዴ ሳልፈልግ Clinikal nursing አስመዘገበኝ፡፡
1.5K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:53:29   ከአንደኛ ክፍል ጀምሬ አንዲት ጓደኛ ያዝኩኝ ልጅቱም ፌሩዛ ትባላለች ...ፌሩዛ በትምህርቷ ጎበዝ ነች እኔም እንደ እሷ ጎበዝ መሆን የኔም የአባቴም ምኞት ነዉ  ጓደኛየ ማድረግ ወሰንኩ ፡፡ ክፍላችን ዉስጥ ተሰሚነት ነበረኝ እኔ ከክላስ ልጅ አንድ ልጅ ጋር ከተጣላሁ የተጣላሇትን እሷን እንዳታወሩ ካልኩኝ የሚያወራት የለም ፡፡ እኔ የወደድኩትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ....እኔ የምጫወትዉን ይጫወታሉ እኔ የማይመቸኝን ጨዋታ አይጫወቱም ፡፡

   ቁርአን ደግሞ መቅራት የጀመርኩት KG ተማሪ በነበርኩበት ሰአት ሲሆን ቁርአን የገባሁትም ጅማ ኑር (አጅፕ)መስጊድ ያለዉ ቁርአን ቤት ነዉ ..ገና አፌ መናገር ሲጀምር አባቴ ቁርአን እንድቀራ በቁርአን ጎበዝ እንድሆን ይመክረኝ ያበረታታኛል..ግን ምን ዋጋ አለዉ በአንድ ሰዉ ጥረት አይሆን..ቁርአን እንድቀራ እናቴ ትኩረት ስላልሰጠችኝ መድረሳ ቁርአን ለመቅራት እመላለሳለሁ እንጂ አሊፍ ባታ ሳ ጂም ብሎ ሁሉንም ፊደል ለመለየት  ሶስት አመታት ፈጅቶብኛል፡፡
   
    ቀን ማታ መሽቶ ነግቶ ሁሌ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር የሰፈር ልጆች ልጫወት እነሱ ጋር ስሔድ አንቺ ጋር አንጨዋትም እያሉ እኔን ለብቻየ የሚያገሉኝ ነገር ሚስጥሩን ምክንያቱን ላዉቀዉ አልቻልኩም  ..እንደ ልጅነቴ የሰፈር ልጆች ጋር የመጫወት እድል ላገኝ አልቻልኩም....እኔ ከእነሱ ጋር የማልጫወትበት ምክንያት ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እራሴን ብጠይቅ መልስ ሊመጣልኝ አልቻለም..

    አባቴንም ሁሌ ቀን በቀን እኔ ጋር አልጫወትም አሉኝ እያልኩ እነግረዋለሁ የአባቴ መልስ ግን ምንም ሊቀየር አልቻለም ...
....ተያቸዉ ልጆቹ ጋር አትጫወች የምትለዉ መልስ ብቻ ነዉ የሚመልስልኝ...ተለዋጭ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም
   

    አንድ ቀን የሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ሲጫወቱ የሚጫወቱት ጨዋታ በጣም ደስ አለኝና ...እኔም  በግድም ቢሆን ሂጄባቸዉ የሰፈር ልጆች ጋር ጨዋታ ጀመርን ....ልጅነት መቼም ጨዋታዉ ፈረሰ ዶቦዉ ተቆረሰ ከተባለ መጣላታችን አይቀርም አይደል...አንዲት የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላን ...ከዛም ከልጅቱ ጋር ሲያገላግሉን መሰዳደብ ጀመርን ....
........ተጣልተን ስንሰዳደብ እኔ የልጅነት አንቺ ማስጠሌ አይጥ እያልኩ ስሳደብ እሷ ግን የሰፈር ሰዉ በተሰበሰበት መሀል ከአእምሮ የማይዋጥ የሚዘገንን በልጅ አቅሜ መሸከም የማልችለዉ ስድብ ሰደበችኝ
....እኔም ይሄን ስድብ እንደሰደበችኝ ደነገጥኩ ... እሷ ጋር ስድብ መመላለስ አፍ መካፈቴን አቁሜ ስድቡን እያብሰለሰልኩ እየተገረምኩ እንዴት እንዲህ ብላ ትሰድበኛለች???እያልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ..

እቤት ስገባ የአላህ ነገር አባቴ ቁጭ ብሎ አገኘሁት...
ፊቴ መቀያየሬ መናደዴን ያየዉ አባቴ ምን ሁነሽ ነዉ ልጄ ፊትሽ ተቀያይሯል ሰዉ ጋር ተጣልተሻል እንዴ???? አለኝ
......እኔም አባቴ የጎረቤታችን ልጅ""" ........."""ብላ ሰደበችኝ እኮ አልኩት ..
.......ወዳዉ አባቴ ፊቱ ተቀያየረ ተናደደ እና ቁጭ ካለበት በመነሳት መኝታ ክፍል ገብቶ ሽጉጡን ከአስቀመጠበት አንስቶ ወዳዉ አቀባብሎ ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ የሰደበችኝን ህፃኒቱን የኔኑ እኩያ በሽጉጥ ሊገላት ይፈልጋት ጀመር፡፡ 


አባቴ በጣም ተናዷል ጅማቱ ዉጥርጥር ብሏል....ልጅቱ መኖሪያ ቤት ሂዶ ነይ ዉጪ የት ነሽ ዛሬ እገልሻለሁ እያለ እየፈለጋት ነዉ...

ሰፈሩ በአንድ እግሩ ቆመ ..የኛ ጎረቤቶች በኛ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ዘመድ አዝማዶች ተሰብስበዉ ንዴት አብርድ እያሉ እየለመኑት ነዉ ...

አባቴን ተረጋጋ እባክህ ተብሎ በጓደኞቹ በዘመድ አዝማዶች በስንት ጉድ ተለምኖ ተመልሶ እቤቱ ገባ፡፡ ግን አባቴ ልጅቱን አለቃትም ሌላም ቀን ቢሆን በዚህ ሽጉጥ አናቷን ብየ ነዉ የምገላት እያለ ይደነፋል............

  ማታ ተኝቼ ብቻየን ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩኝ አብረን የምንጫወት የሰፈራችን ልጅ እንዴት ልሰድበኝ ቻለች ???ይሄን ለጆሮ ለመስማት የሚዘገንን ስድብ እንዴት ሰደበችኝ ???አባቴስ ስነግረዉ ለምን እገላታለሁ ብሎ ደነፋ ???? እያልኩ ብቻየን ሳስብ አደርኩኝ....ግን ይሄን ስድብ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ማጣራት አለብኝ ብየ ወሰንኩ ...ግን ማንን ልጠይቅ ???
   
የምጠይቀዉ ሳጣ ሲጨንቀኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን የቤት ሰራተኛችንን አልጠይቃትም???ብየ አሰብኩኝ...እሷን ለመጠየቅ ወሰንኩ

የቤት ሰራተኛችንን ልጅቱ ለምን"""""""____"""""እንደዚህ ብላ እንደሰደበችኝ ጠየኳት ...ሰራተኛችን ለመንገር ፍቃደኛ አልሆነችም ... ግን እኔ ንገሪኝ እያልኩ አፋጥጬ ስይዛት የቤትሰራተኛችን እያለቀሰች ....,እንደዚህ አለችኝ.........


ልጅቱ የሰደበቻት ምን ብላ ነዉ ????  የተደበቀዉ ...ማንነት ምንድን ነዉ ???ለምን አባትየዉ ገና ነፍስ ያላወቀችን ልጅ አገላለሁ ብሎ ለምን ተነሳ ??? የተቆለፈዉ ሚስጥር ምንድን ነዉ ???
በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን


#ክፍል
ይ....ቀ...ጥ.....ላ....ል

t.me/Islam_and_Science
926 viewsedited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:53:29 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞  አንድ

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



    በሰዎች ዉሳኔና ፍላጎት ምኞት እና ጉጉት ብቻ ተፈፃሚ የሚሆን ነገር የለም የአሏህ ፍቃድ እስካልታከለበት ድረስ.. አንዳንዴ በሰዉ በዘመድ ተከበህ ሰዉ ይናፍቃል. እዉነት ነዉ በአለም ላይ በቢሊየን የሚሆን ህዝብ እያለ የዉስጡን የሆዱን የታፈነ ነበልባል አንድ ሰዉ ላይረዳህ ይችላል...የዚህን ጊዜ ብቸኝነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡

     ዉሀ ላይ ሁኜ ዉሀ ይጠማኛል
     እሰዉ ጋር ሁኜ ሰዉ ይናፍቀኛል
      የያዘኝ በሽታ ወንድም ያሰኘኛል
አንድ መንዙማ ላይ የሰማሁት ነዉ . እዉነት ነዉ ዉሀ ጠምቶህ ጠጥተሀዉ ሆድህ ቢገባም ዉሀዉ ጥምህን የማይቆርጥ ከሆነ
በሰዉ መሀል ተከበህ ሰዉ ሲያስፈልግህ ሰዉ ግን አንተን ለመረዳት ሳይፈልግ በአንተ ላይ የሚሳለቅ ከሆነ ሰዉ መሀል ተከበህ ጥቅሙ የሚሆነዉ የሰዉ ቆጠራ ጊዜ አብሮ ተቆጥሮ አለ ይሄን ያህል አለ ለማለት ያህል ካልሆነ በቀር ....

የተፈጠርንበት ማንነት ዲነል ኢስላም በወንድምነት በእህትነት አስተሳስሮን ነገር ግን ዛሬ ጓደኛ ነገ ደግሞ ጥላት እየሆነ የመጣ ይመስላል. ታዳ መቼ ይሆን ለሰዉ እዉነተኛ ሰዉ የምንሆነዉ???..ለሰዉ ልጅ በሽታዉም ህመሙም ያዉ አላህ እንደቀደረዉ ሁኖ ታንቆም መርዝ ጠጥቶም የሚሞተዉ ያዉ በሰዉ ምክንያት ነዉ ..ምክንያቱም ይህን ዉሳኔ የወሰነዉ መቼም ሰዉ ነዉ እና ጥፋት አይቀርም..አጥፍቶ መሄጃ ሲያጣ በአማከረዉ ሰዉ ወይም ለልብ ጓደኛዉ የልቡን ነግሮት ግን የተናገረዉን ከጆሮ ባልዘለለ ከልቡ ሳያስቀምጠዉ ሲቀር ያኔ ከሰዉ በላይ አላህ ይጠብቀን ሸይጧን ይቀርበዋል ይሳሳታል ይታነቃል ወይ መርዝ ይጠጣል ..ይሄን ዉሳኔ የሚወስነዉ ዱንያን መሮት እንጂ ተመቸቶኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋ የለምና...

በጥናት ዉጤት ስናየዉ አሜሪካ በአንድ አመት ብቻ 25,000 ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ቻይና በየዓመቱ 30,000 ሰዉ ራሱን ያጠፋል በአለም ላይ በየ20 ሰከንዱ ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ይህ ማለት በአለም ላይ ወደ በአንድ አመት ሁለት ሚሊየን ህዝብ እራሳቸዉን ያጠፋሉ ማለት ነዉ፡፡

ሁሉም ሰዉ ሊያወቀዉ የሚገባ የማይካድ ሀቅ ደስታ በዲነል ኢስላም አላህ ጋር ባለን ግንኙነት እንደሚወሰን መገንዘብ አለብን..የቁርአንን መመሪያ መከተል ለዚህ ያለእድሜዉ እራሱን ለሚያጠፋዉ እና በሂወት እያለ ሒወት እንደ ዥዋ ዥዌ ጨዋታ ለሆነችበት ቁርአን መፍትሄ እንደሆነ እርግጥ ነዉ .... አሁን ጊዜ ላይ ያለነዉ የሁላችንም ጥፋት የቁርአን መመሪያ እኛ መከተሉን ትተን በእኛ መስመር እንዲከተለን መፈለጋችን ነዉ፡፡

ታዳ ለዚህ ሁላ ራሱን ላጠፋዉ ተጠያቂዉ ሰዉ አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ??? ሰዉ ከሚሳሳትባቸዉ ምክንያቶች ዋናዉ እና አንደኛዉ ባለፈዉ ጊዜ ምን ምን ነገሮች ነበሩ??ዛሬ ምን ይደረጋል?ነገስ ምን ይመጣ ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ሳያስተዉሉ ሁሉንም ነገር ለዛሬ ብቻ ሲሰጡ ነዉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደስታ የሚገኘዉ በብር ብቻ ነዉ ብለዉ የሚያምኑ አሉ... ስህተት ነዉ ደስታ የሚገኘዉ በዲነል ኢስላም ነዉ :: ዲነል ኢስላምን አዉቆ ያልሰራበት ደስታ በጭራሽ አያገኝም..ለምሳሌ አሜሪካንን እንዉሰድ የአለም ኢኮኖሚ 50% በአሜሪካ እጅ ይገኛል ነገር ግን በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ አገሮች ቁጥር ተርታ ስትሰለፍ 116 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡በተዘዋዋሪ ደግሞ በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ ሀገሮች የመሪዎችን ደረጃ የያዙት ሙስሊም ሀገራት ሲሆኑ.....ቁጥር 1 ናይጀሪያ ናት ..ናይጀሪያ እንደምናዉቀዉ የሙስሊም ሀገር ናት በኢኮኖሚዋ ዝቅተኛ ብትሆንም ግን የመጀመሪያ አላማቸዉ አላህን ማስደሰት ስለሆነ በአላቸዉ ተብቃቅተዉ በደስታ ይኖራሉ

የሰዉ ልጅ ብር ደስተኛ እንደማያረግ የጃፓኑን ትልቅ ድልድይ በቀን ከ300 መኪና በላይ የሚተላለፍበትን የገነባዉ ኢንጅነር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያገኘ ቢሆንም ተመርቆ አገልግሎት በሚሰጥበት ቀን በትንሽ ቁራጭ ወረቀት ኑዛዜ አስቀምጦ ራሱን ከድልድይ ላይ በመጣል ራሱን አጥፍቷል...በኑዛዛዉ እንዳስቀመጠዉ """"እኔ የገንዘብ ችግር አላጋጠመኝም ደስታ በማጣቴ ብቻ ከዚህ አለም ለመሰናበት ፈልጊያለሁ"""" ነበር ያለዉ ፡፡

በአለም ላይ የሰዉ ልጅ ራሱን ለመቀየር 24ቢሊዮን ዶላር/ ሴቶች ለኮስሞቲክስ 18ቢሊዮን ዶላር /ፀጉርን ለመንከባከብ 38ቢሊየን ዶላር /ለሽቶ ደግሞ 15ቢሊዮን ዶላር በአመት ያወጣሉ... ታዳ ሰጥቶን ስጡ ለተባልነዉ ዱንያ የአላህ ወዴታን ለማግኘት ስንት አዉጥተናል?? ለተቸገረ ሰዉ ስንቶቻችን የችግሩ መፍትሄ ሁነናል??ስንቶቻችን ነን ደሀ እና ሀብታምን ሳንለያይ በአንድ አይን የምናየዉ???
ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰዉ ጀሀነም እሳት ዉስጥ ለመግባት ሙስሊም ወንድሙን በዝቅተኛ አይን ማየቱ በቂ ነዉ ብለዋል..እስኪ ሆድ ይፍጀዉ

    የኔ ታሪክ ስለ ሁላችንም የሰዉ ማንነት ላይ ዱንያ የደስታ ህይወት አለመሆኗን  ያተኮረ ሲሆን እስኪ ሳይረፍድ ወደ ታሪኩ እንግባ
    ቅድሚያ መተዋወቅ ይቀድማል እንተዋወቅ የእናንተን ባለቅም የእኔ ስም ነዋል እባላለሁ አሁን ላይ የኔ እድሜ አስራ ዘጠኝ ሲሆን ፡፡ እኔ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ ከእኔ በታች በሶስት አመት የምበልጠዉ አንድ ታናሽ ወንድም እና በጣም ታናሽ እህት አለችኝ..በጠቅላላ ለቤተሰቦቻችን ሶስት ልጆች ነን፡፡
ተወልጄ ያደኩት የፍቅር የመከባበር ሀገር በሆነችዉ የአባጅፋር ሀገር ጅማ ከተማ በአጂፕ ሰፈር አዲሱ ገቢዎች ግምሩክ አካባቢ ነዉ፡፡

   አባቴ  ጅማ ከተማ ላይ ታዋቂ ኮንትራከተር ህንፃ ተቋራጭ ሲሆን በዚህም የተነሳ ዉብ የሆነ ቤት እና ወደ ሰባት የሚሆን መኪና ያለን ሲሆን ጅማ ላይ እስኪ ብር ያለዉ ባለሀብት ጥሩ ቢባል ቁጥር አንድ የሚጠራዉ የኔ አባት ነዉ፡፡ እንደ መጀመሪያ ልጅ በመሆኔ ምንም ሳይጎልብኝ የፈለኩትን በልቼ የፈለኩትን ጠጥቼ ነዉ ያደኩት ፡፡ አባቴ በጣም ተንከባክቦ ነዉ ያሳደገኝ ፡፡

መቼም ማንኛዉ ሰዉ እድሜዉ ከትምህርት ከደረሰ ትምህርት ቢያነስረዉ መመዝገቡ አይቀርም  ...እኔም ጅማ የሚገኘዉ ኮምዪኒቲ ትምህርት ቤት--KG1 ተመዘገብኩ፡፡ KG ትምህርቴን እንደ ጨርሼ አንደኛ ክፍልም እዛዉ ኮምዩኒቲ ትምህርት ቤት ተመዘገብኩ፡
  
የሰፈር ልጆች ጋር ከልጅነቴ ጀምረን ስጫወት እነሱ ግን እኔ ጋር መጨዋት አይፈልጉም ነበር
.....ለምን እኔ ጋር አትጫወቱም ስላቸዉ ??
....እናት አባቶቻችን አንቺ ጋር እንዳትጫወቱ ተብለናል ይሉኛል፡፡
እኔም ልጆቹ ያሉኝን ለአባቴ ሂጄ እነግረዋለሁ
...አባቴም አንጫወትም ካሉሽ አትጫወቺ ምን ያረጉልሻል እቤትሽ አድበሽ ተጫዋቺ ይለኛል


     አንደኛ ክፍል እየተማርኩ የኔ ጓደኛ ለመሆን የማይጥር የለም ... ትምህርት ቤት ስሄድም ስመጣም መኪናዉ የራሳችን ስለሆነ አባቴ በያዘልኝ ሹፌር ነዉ የምመላለሰዉ ፡፡ የሀብታም ልጅ ስለሆንኩ ነዉ መሰለኝ ብዙ ሴት ልጆች እኔን ጓደኛ እንድሆናቸዉ ይቀርቡኛል
874 viewsedited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:52:05 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ፡፡
አንዳንድ የቻናል admin እና ዩቲዩበሮች የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት እዉተነኛ ታሪክ በ45 part የተቀረበዉን በአጭር part አርግልን ስላላችሁ በዉስጡ ያሉትን አባባሎች እና አጭር ምክሮች ተቀንሰዉ እና ሁለቱን part በአንድ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ይቀርባል መልካም ንባብ፡፡

በአስተያየት መስጫ ማንኛዉንም ሀሳብ አስተያየት አልቀበልም

አሚር ሰይድ
924 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ