2022-08-25 13:24:38
#የመራም_ማስታወሻ
ክፍል ~ ➊➋
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ
......እጁን ቀስሮ በአየር ላይ "ሪም " ከማለቱ ገና ከአፉ ነጥቄ
...... "ሪም ምን ሆነች!!?" አልኩት ልቤ ምቱ ፈጠነ " ..........መኪና ገጫት.."
በቆምኩበት ድርቅ ብየ ቀረሁ ጨለመኝ ሁሉም ነገር ዞረብኝ በደመነፍስ ሩጫ ቀጠልኩ የምሄድበትን ግን አላውቅም፡፡ አቤል ተከትሎኝ ሮጠ እማማየም ከኃላ "መራም አረ ቆይ ልጀ ተረጋጊ እንጂ" እያሉ ተከተሉኝ፡፡
እኛ ሰፈር አብሮ አደጋችን ሀቢብ ለእናቱ ክሰል አምጥቶ ሲመለስ ነበር የተገጣጠምነው መኪናውን አቁሞ " መሪ ምን ሁነሽ ነው የምትሮጪዉ?? የምትሄጅበት ቦታ ካለሽ ላድርስሽ !? ግቢ" አለኝ፡፡
ወደ ሀቢብ መኪና ገባሁ ያለገደብ ከአይኔ የሚፈሰውን እንባ አይቶ ደንግጧል "ሀቢብ በአላህ አፋጥነው! አፍጥነው ቶሎ በል!" አልኩኝ ወዴት መሄድ እንዳለበት ግራ ገባው፡፡ አቤል እየሮጠ ደረሰብኝና ሀቢብ መኪና ሲገባ "አቤሎ ምንድነው ነገሩ አንተ ንገረኝ እንጅ ሁላችሁም ዝም ብላችሁ አስጨነቃችሁኝኮ በአላህ!"አለ ሀቢብ.....
......፡ "ሪም መኪና ገጭቷት ነው ወደ ሀያት ክሊኒክ ውሰደን" አለው፡፡ "ገጭቷት" የሚለውን ቃል ስሰማ ጭንቀቱ የብስ ባሰብኝ! ሀቢብም በጣም ደነገጠ የሚለው ጠፋበት ከሪም ጋር በእድሜ በተወሰነ አመት ነዉ የሚለያዩት አቅፎ ተንከባክቦ አሳድጓታል ከልጅነቷ ጀምሮ በጣም ይወዳታል፡፡
ሀቢብ በፍጥነት እየነዳ ክሊኒኩ ደረስን፡፡ መኪናው በቅጡ ሳይቆም ለመውረድ ስሞክር በአፌ ከመደፋት አላህ ነው ያዳነኝ .......ሰወች በሁኔታየ ጮሁ እኔ ግን ሪምን ማየት ብቻ ነው ፍላጎቴ! ወደ ውስጥ ስገባ ሪም ግንባሯን እና እጇን ታሽጋ ቁጭ ብላለች ከጎኗ ፈንጠር ብሎ አንድ ወጣት ልጅ ተቀምጧል፡፡ ሳያት በእንባ የታጠበው ፊቴ መልሶ በእንባ ጎርፍ መታጠብ ጀመረ፡፡ "እንዳላቅፍት እንደብርጭቆ የምትሰበርብኝ መሰለኝ ሳሳሁላት፡፡
" ሪም የኔቆንጆ ደህና ነሽ!?" አልካት እግሯ ስር ተንበርክኬ በስስት እያየሆት
......."ደህና ነኝኮ አታልቅሽ" እያለች እንባየን ጠረገችልኝ፡፡ ከአጠገቧ ራቅ ብሎ የተቀመጠው ልጅ "እህቷ ነሽ?" ሲለኝ መልስ ከመስጠት ይልቅ "አንተ ነህ የገጨሀት አይደል!?" ብየ እንደ አራስ ነብር ተከመርኩበት፡፡ እጄን ለማላቀቅ ራሱን ለመከላከል እንካን አልሞከረም ዝም ብሎ በአትኩሮት ተመለከተኝ፡፡
እማማየ "መሪ ተይ ብየሻለሁ ቢገጫትስ ይሄው እጅ ሰቶ መጥቶ እያሳከማት ነዉ .... ገጭቷት ቢጠፋ ነበር ክፉ የሚያስብለው ልጄ እሱምኮ ፈልጎት አይደለም አላህ አገጣጥሞበት እንጅ" አሉ፡፡
.......ሪም ቀጠል አርጋ "መሪ በአላህ ተረጋጊ እሱኮ አይደለም የገጨኝ፤የገጨኝ ትቶኝ ሲሄድ አይቶ እሱ ነው አንስቶ ያመጣኝ" ስትለኝ ሰውነቴ እንደ በረዶ ቀለጠ እጆቼ ተንቀጠቀጡ "ይቅርታ" አልኩት ቃል ከአፉ ሳያወጣ ቅንጭላቱን በማወዛወዝ እሽታውን ገለፀልኝ፡፡
......ሀቢብ ሪምን አይቶ " አንች ሚዳቆ ይሄኔኮ ሩጠሽ ገብተሽበት ነዋ!?" ብሎ ሲቀልድባት
.....ሪምም እንደ አንተ እጁን ያላጠራ ሹፌር ገጥሞኝ ነዉ ብላ ሀቢብን ነካ አረገችዉ፡፡
ሪም ከባድ የሚባል ጉዳት አላጋጠማትም ትንሽ ግንባሯ ተፈርክሷል እጇ ተልጧል እንጅ የሚያሰጋ ነገር የለም፡፡ ሀቢብ ደህንነቷን ካየ በኃላ " በቃ እኔ ልሂድ ቢሮ ይፈልጉኛል አንች አይጥ ደግሞ ሙዝና ብርቱካን ፈልገሽ አይደል የተገጨሽው ከስራ ስወጣ ይዠልሽ እመጣለሁ" ብሎ አስቆን ሄደ፡፡
ሪም ደህንነቷን ደጋግሜ ጠይቂያት በጣም ደህና ነኝ ብላኛለች ..በቃ ወደ ቤታችን እንሂድ ብለን ስንነሳ እማማየ ልጅን እየመረቁ በየ መሀሉ ይመክሩት ነበር፡፡ እማማየ በቃ እንሂድ ወደ ቤት ብያቸው ቅድም ይቅርታ የጠየኩትን ልጅ አሁን ደግሞ ስላደረገልን መልካም ነገር "አላህ ኸይር ጀዛህን ይክፈልህ"አልኩት "አሜን" አለኝ፡፡
ወደ ቤታችን ለመመለስ ባጃጅ ብንጠብቅ በዋዛ ማግኘት አልቻልንም ሁሉም እየሞላ ነው የሚመጣው ጠበቅን ጠበቅን ከዛም " እዚህ ጠብቁኝ ወይ ኮንትራት ይዠ ልምጣ" ብየ መራመድ ስጀምር ለካ ባዶ እግሬን ነኝ፡፡ በባዶ እግሬ መንገድ ጀመርኩ ትንሽ እንደተራመድኩ ሪም "መሪ መሪ ነይ" አለችኝ በእጇ ምልክት እየሰጠችኝ ስመለስ አሁንም ያው ልጅ እኔ ላድርሳችሁ ግቡ ተቡለው መኪናዉ ዉስጥ ገብተዋል፡፡ በውስጤ "ኡፍ ገላገልከኝ" አልኩኝ፡፡
ወደ ሰፈር አድርሶን ሊመለስ ሲል እማማየ "ልጄ ምነው እዚህ አድርሰህን ቤት ሳትገባ መሄድህ?? በል ውረድ አንተም" አሉት
....እኔ ክው ብየ ቀረሁ ከአለባበሱ ጀምሮ መኪናውም ቢሆን ውድ የሚባሉ አይነት ነው፡፡ እሱ የሚኖርበትን የቅንጦሽ ኑሮ ከእኛ ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይደለምና እኛ ቤት ያለውን ነገር ሳስብ ደንግጨ ቁሜ ቀረሁ በሆዴ መቼም አይገባም ብየ ሳስብ
......"ማዘር ማስቸገር እንዳይሆንብኝ እንጅ ብገባ ደስ ይለኛል" ሲል የበለጠ ደነገጥኩ
........"አረ የምን ችግር ልጄ ና እንግባ" ብለው ከፊት መንገድ እየመሩት ተከተላቸው እኔ ከኃላ በድንጋጤ እራመድ ይዣለሁ ሪምን ሳያት ሳቀችብኝ
ወደ ቤት ስንገባ የሰገድኩበት ሙሰላ እንደተነጠፈ ነበር፡፡ ፈጠን ብየ አነሳሁት " ቁጭ በል የኔ ልጅ" አሉት፡፡ እኔ ጨነቀኝ ምናልባት ስራ ቦታ ላይ የማያቸው ሀብታሞች ሁኔታ ይሆናል ያስጨነቀኝ፡፡
ሪም አልጋው ላይ ጋደም ብላ የሚሆነውን ታያለች፡፡ እማማየ "መሪ መክሰስ አዘጋጅ" አሉኝ፡፡ እኔ እሺ ብየ እኛ የምንበላዉ ከምንጠጣዉ ቤት ካፈራዉ ምግብ አዘጋጅቼ ቡና አፈላሁ፡፡ ከዛም አቀረብኩኝ...የቀረበለትን መክሰስ ከእማማየ ጋር አብሮ ደስ እያለው በላ፡፡
ቡና እያፈላሁ የአዩን ድምፅ ሰማሁ " አዩ ና ወደ ቤት ግባ " አልኩት
..... "መሊ ኔማ አድ ላሳይሽ"አለኝ አየተኮላተፈ
........... "ምን ልታሳየኝ ??ነው" አልኩት
....."በፊም የሚታይ መኪና" አለኝ፡፡ አቅፌ ሳምኩትና ቤት አስገባሁት፡፡
ሪም ታሽጋ ሲያይ ለማልቀስ ዳዳው "ማነው የመታሲ"አላት በቁጣ መንፈስ
..."ወድቄ ነው እሽ ማሬ" አለችው
...."ማን ገፍትሮስ"አላት "
..... አዩ ና መክሰስህን ብላ አራበህም እንዴ??" አልኩት
......."እርቦናል ግን ሊም ማን ያበላታል አመማት" አለ፡፡
..... አንተ ብላና ለሷ እኔ አጎርሳታለሁ አልኩት፡፡ ምግብ እንዳቀረብኩለት ወደ እንግዳው ልጅ ቀርቦ "እንብላ" አለው እሱም እንደገና እጁን ታጥቦ መብላት ጀመረ፡፡ ከአዩ ጋር በፍጥነት ተላመዱ፡፡ በርግጥ አዩ የሚወደድ ልጅ ነው፡፡ ከዛ እኛን አመስግኖ ሪምንም አላህ ያሽርሽ እየመጣሁ እጠይቅሻለሁ አብሽሪ ብሎ እማማየም መርቀዉት ከቤት ወጥቶ ሄደ፡፡
እማማየ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ከልጁ ጋር ጥብቅ ወዳጅ ሁነዋል፡፡እማማየ ብቻ ሳይሆኑ አዩንም ይጨምራል ብዙ ጊዜ ቤት እየመጣ ይጠይቃቸዋል አዩን የተለያየ ቦታ እየወሰደ ያጫውተዋል ያዝናናዋል ውዴታቸው ጨምሯል እኔ ግን ስሙን እንኳን አላውቀውም፡፡
እማማየ ሳያነሱት ውለው አያድሩም ግን "ያ መልካም ልጅ"ነው የሚሉት እንጅ ስሙን ሲጠሩ አልሰማም ይገርማል ግን በምን ቋንቋ ተግባቡ??? ልጁኮ ከአፉ ቃል አያወጣም ዝምታ በሱ ላይ ነግሷል! በእርግጥ እኔ ስራ ስለምውል ብዙ አንገናኝም ነገር ግን እግር ጥሎን እንኳን ከተገናኘን ከዝምታ ውጭ ሌላ አላይበትም፡፡
ግን ደግሞ ቤት ሲመጣ ደስተኛ ይሆናል እንደሀብታም ተብየዎች አያካብድም ልክ እንደኛ ሁኖ ለሰወች ይተናነሳል፡፡
1.7K views10:24