Get Mystery Box with random crypto!

  #የመራም_ማስታወሻ            ክፍል ~ ➊➎ ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ ' መሪ | ISLAMIC SCHOOL

  #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➎
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ


" መሪ ሶስት ቀን ያህል ለመቆየት አዲስ አበባ መሄዴ አይቀርም እዛ ትንሽ እኔን የሚፈልግ ስራ አለ እሱን አስተካክየ በቻልኩት ፍጥነት እመለሳለሁ!" ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ
... "እና ትተህን ልትሄድ ነዉ ?! አዩብ አይናፍቅህም ይወድሀልኮ!" አልኩት፡፡ አዩን ምክንያት አረኩ እንጅ እኔ ራሱ ገና ሳይሄድ ልሄድ ነው ሲል ነው የናፈቀኝ
......"በጣም ነው እንጂ የሚናፍቀኝ ሁላችሁም ትናፍቁኛላችሁ መሪ ደግሞ ካልሰለቸሁሽ በየሰአቱ ነው የምደውልልሽ" አለኝ
..... "አትሰለቸኝም ደውልልኝ!? አልኩት በደስታ ከተናገርኩ በኃላ ግን መውደዴን ያወቀብኝ መሰለኝ እና አፈርኩ፡፡ ቤት እንደደረስን አዩ ገና እንዳየው ሩጦ ተጠመጠመበት
"አየሀው ከእኔ አንተን አስበለጠ" አልኩት ተገርሜ፡፡
...."እና እየቀናሽ ነው እንዴ!?" ብሎ ሳቀብኝ ገና ከመቀመጣችን ለሪም እና ለማማየ "አብደልከሪም ሊሄድ ነው!" አልኳቸው በደከመ ድምፅ ሁለቱም እኩል "የት ነው የሚሄደው!!?" አሉ ደንግጠዋል፡፡ እማማየ ወደሱ ዞረው "ወዴት ነው የምትሄደው ልጄ!?" አሉት በጣም ስለተላመድን አዲስ አበባ መኖሪያው መሆኑን ረስተነው እንጅ እንደ እውነቱ እማ አንድ ቀን ወደ መኖሪያው እንደሚመለስ ብናውቅም ተላምዶ መለየት ከበደን "ለ3 ቀን ብቻ ነው እንጅ እመለሳለሁ!" አለ በርግጥ እሱም መለየት ከብዶታል፡፡


አዩ መሄዱን ሲሰማ "እኔን ትተከኝ ልትሄድ ነው!?" አለው በአይኑ እየተለማመጠ
..... " እመለሳለሁኮ አዩ ከዛ የትም ሳልሄድ አብረን እንሆናለን እሺ" አለው፡፡ ጉንጮቹን በእጁ ይዞ ወደ ደረቱ እያስጠጋ፡፡ ሪም ምንም ሳትል ደንግጣ ወሬውን ታዳምጣለች፡፡ እማማየ በቃ ነገ መንገደኛ ከሆንክ መቼም ሰው አይሸኝም ይቀበሉታል እንጅ "ሪም ምግብ ስሪ ቡናም ይፈላል" አሉ፡፡ ሪም ተነሳች እኔም አብሪያት ተነሳሁ ምግብ ሰራን ቡና ከተጠጣ በኃላ ከፋኝ.. ለካ አብደልከሪም ይሄዳል ግን እስካሁን አዩብ አለቀቀውም እንደተቃቀፉ ናቸው፡፡

ሰአቱ እየመሸ ነው አዩብ ያለወትሮው እንቅልፍ ከሱ ርቆ ንቅት ብሏል አትሄድም ብሎ የሙጥኝ ብሏል፡፡ "ይሄ ልጅ ዛሬ አለቀቀህም ልጄ ነገ መንገደኛ ነህ ናቶሎ እዚህ ጎንህን አሳርፍ" ብለው መኝታቸውን ለቀው እኛ ጋር መተው ተኙ፡፡ "አዩብ እና አብደልከሪም ተቃቅፈው ተኝተዋል፡፡ እኔ ግን እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ ቁርስ ከበላን በኃላ አብዲ ተሰናብቶን ወጣ፡፡ ቤቱ በሀዘን ተሞላ እርስ በእርሳችን ተኮራርፈን ቁጭ አልን፡፡ እኔ በጣም ደብሮኛል ቤቱ ሁሉ አስጠላኝ! ቶሎ ወደ ስራ ሂጄ ራሴን ቢዚ ማድረግ ፈለኩ፡፡


አብደልከሪም ከሄደ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ነው፡፡ እየተደዋዉልን ስለሆነ ነገ እንደሚመጣ ነግሮኛል፡፡ የዛሬው ቀን ረዝሞብኛል ዛሬ አልፎ ቶሎ ነገ እስኪደርስ በጣም ቸኩያለሁ፡፡ በደስታና በንቃት ስራየን እየሰራሁ ነው፡፡ ከስራ ወደ ቤት ስሄድ ሪም ለነገ አቀባበል ዛሬ ሽርጉድ እያለች ነበር፡፡ ምን እሷ ብቻ አዩ ከሷ ብሷል እንጅ በደስታ እየዘለለ ይቦርቃል ለተመለከተን ሰው ሁለት ቀን የተለየን ሳይሆን ለብዙ አመታት የተለየንን ሰው የምንጠብቅ እንመስላለን፡፡

ነገን በመናፈቅ ደስ በሚል ተስፋ ደስ የሚል መኝታ ደስ የሚል ንጋት! ዛሬ አብደልከሪም ይመጣል! እኔ ወደስራ መሄድ አለብኝ፡፡ አብዲ ቀድሞ እኔ ጋር ስራ ቦታ እንደሚመጣ ነግሮኛል፡፡

እኔም እሱን በማግኘት ተስፋ ስራየን ተያይዣለሁ ደቂቃ በሰአታት እየቀፈራረቁ ሰአታትን አስቆጥረው እኩለ ቀን ደረስን ከ6-7 ባሉት ሰአት በጣም የስራ ውጥረት ይኖራል፡፡ 7 አልፎ 8 ሰአት ደረሰ አሁን ስራ ውጥረት ቀነሰ ከስራ ለመውጣት አብዲን እየተጠባበኩ ባለበት ሰአት------- አንዲት ሴት ሁለት ህፃናት ልጆችን ይዛ ወደ ካፌው ገባች አለባበሷ ቅጡ የጠፋው ከእድሜዋ ጋር የማይሄድ ሙስሊም ትሁን ካፊር ግራ የምታጋባ ግን ደግሞ በየወሬዋ መሀል ወላሂ እያለች መሀላ የምታበዛ ነች :ጫት እየቃመች አፏ የጌሾ ሙቀጫ መስሏል ከ3 ወይም 4 አመት የማያልፈው ወንድ ልጅ እና በወራት እድሜ ያለች ልጅ ይዛለች፡፡ ወንበር ይዘው ተቀመጡ የስራ ሰአቴ ስላለቀ ካሽሪዋ ጎን ቁጭ ብየ አብዲን እየጠበኩ ነው፡፡

ልጇ የተቀመጠበት ወንበር ከእኔ ፊት ለፊት ነበር፡፡ የልጁን መልክ ሳይ ልቤ ቀጥ ብላ የቆመች መሰለኝ ደነገጥኩ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ሁሉ ነገሩ የሞተውን ወንድሜ ፈይሰልን ይመስላል፡፡ "ፈይሲ" አልኩኝ ለራሴ በሚሰማ ድምፅ በእጀ ምልክት ሰጥሁት ና አልኩት ተነስቶ ወደኔ መጣ ምንም ሳልለው ተንበርክኬ አቀፍኩት ደጋግሜ ሳምኩት በደከመ ድምፅ "ስምህ ማነው?" አልኩት
......."ፈይሰል" አለኝ በሚጣፍጥ አንደበት ድንጋጤ ይበልጥ ጨመረ ስሙም የሞተዉ ወንድሜ አይነት ፈይሰል ጋር አንድ ሆነብኝ እሱን እያስታወስኩ እንባየ ያለገደብ መፍሰስ ጀመረ እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ... የመተዉ ወንድሜ ጋር በጣም ይመሳሰላል "አባትህ ማነው ስሙ?" አልኩት "
.....አባቴ እዛ ነው ምሳ በልቸ እናቴጋ እንሄዳለን" አለኝ፡፡
........ "ምሳ እስካሁን አልበላህም!?" አልኩት አንጀቴ በሀዘን እየተላወሰ ቅንጭላቱን በመነቅነቅ አወንታውን ገለፀልኝ፡፡ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኩት እና ደግሜ የአባቱን ስም እንዲነግረኝ ጠየኩት "አባቴ ስሙ አባቢ ነው" አለኝ፡፡ " እሽ ህፃኗ ስሟ ማነው አልኩት
....." እህቴኮ ናት " አለኝ፡፡ "
.....እኮ ስሟን ንገረኝ ??አልኩት
..... እናቴ ሩማን ናት ብላለች አባቴ ደግሞ ለይላ ናት ብሏል ስም የላትም" አለኝ እየሳቀ

ነገሮች ሁሉ ተዘበራረቁብኝ በድንጋጤ ደርቄ ቀረሁ እና ከተደረደሩት ኬኮች ውስጥ እያስመረጥኩት
....."ቤታችሁ የት ነው?" አልኩት በእጁ ምልክት እየሰጠኝ "እዛ ነው" አለኝ፡፡ የምፈልገውን መረጃ ከሱ ማግኘት አልቻልኩም እና አቅፌ ወደ እናቱ ወሰድኩትና ከእሷ መረጃ ለማግኘት በዘዴ ቀረብኳት፡፡
....."ሰላም እንዴት ነሽ ማሻአላህ ደስ የሚል ልጅ አለሽ" አልኳት ለመግባባት ያህል ...ግን የእሷ መልሷ አስደነገጠኝ " ......ካማረሽ ወስደሽ አሳድጊው ሰጠሁሽ ልጁን አልፈልገውም" አለችኝና ወደ ልጁ ዞራ "አንተ ደደብ ደንቆሮ አርፈህ ቁጭ በል ብየህ አትሰማም አይደል ምናለ በሞትክና በተገላገልኩህ" ብላ በጥፊ ላሰችው፡፡ በቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ እናት ስለመሆኗ ተጠራጠርኩ እማ በቅፅበት በህሊናየ ውል አለችብኝ
....." ለምን ትመችዋለሽ ??ልጅ እኮ ነው ደግሞ ምንም አላጠፋም አንችም እንደ እናት ከአጠገብሽ ሲርቅ አስበሽ የት ሄደ ብለሽ አልፈለግሽውም" አልኳት በንዴት

ልጁ ጉንጩን በእጁ ይዞ እንባው ይረግፋል፡፡ አሳዘነኝ የገዛሁለትን ኬክ አስቀምጨ እንባውን ጠረኩለት "ጎሽ ጎበዝ ልጅ ለዛሬ ራስህን ችለህልኛል ከወጭ አሳረፍከኝ ዳይ ተነስ እንሂድ" ብላ ምሳዉን ሳይበላ የገዛሁለትን ኬክ አንጠልጥላ እየጎተተች ወሰደችው፡፡ "እውነት አሁን ይችም እናት ትባል ይሆን!!?" ብየ እማን አስታውሸ እንባየ ፈሰሰ ዳግም የልጁ ሁኔታ ፊቴ ድቅን አለ


ወደ ውጭ ወጥቼ ወደ ምድር አንገቴን አስግጌ ልጁን ተመለከትኩት ከፊት ለፊቱ ወዳየው ሰው ሩጫ ቀጠለ የልጁን ሩጫውን ተከትየ ሰመለከት አይኔን ማመን አቃተኝ ......

#ክፍል ➊➏
ይቀጥላል.......


https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group