Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.55K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-08-29 10:26:10 የመራም ማስታወሻ የሚለዉ ታሪክ አልቋል

አስተያየት አልቀበልም ....ከትንሽ ቀን ቡሀላ የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት የሚለዉን በ45 Part የቀረበዉን ለዩቲዩበሮች እና ለሌሎቻ ቻናሎች እንዲመች በመሀል የገቡ አባባሎች ሀዲሶች ተቀንሶ ወደ 25 part size አንሶ አቀርባለሁ...

መልካም ቆይታ

አሚር ሰይድ
1.3K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:23:07 ግን ወንዶች ሆይ ለሴት ብቻ ማስጠንቀቂያ ሆነ አይደል እስኪ ለእናንተም አንድ የእንስሳ ተፈጥሮን እንድታስተዉሉ ላስታዉሳችሁ ሴት ዉሻ..
ሴት ዉሻ ወንድ ጋር ስትሆን ምን እንደሚያደርጋት አይታችሁ ታቃላችሁ??
እኔ በተደጋጋሚ አይቻለሁ አይታወቅም እናንተ ያላያችሁት ዉሻ እኛ ሰፈር ስለሚበዛም ይሆናል፡፡
አንድ ሴት ዉሻ ያነገር ሲያስፈልጋት አራት አምስት ወንድ ዉሾች እሷ ጋር እንትን ለማድረግ በጣም ይጣላሉ ይነካከሳሉ ከዛ ያሸነፈዉ ዉሻ ሁሉንም ያባርና ወደ ሴቷ ሲሄድ እሷ እምቢ ትለዉና ስትሄድ ሲከተል ጊዜዉን ፈጅቶ እዳዉን አሳይታ የፈለገዉን ሲያገኝ ..ከዛ ትቆልፍበታለች ..እኔ የሚያለቅስ ዉሻ ብዙ አይቻለሁ በቃ ተሰቃይቶ ተሰቃይቶ እሷ በሂደችበት እሩጦ እሩጦ የቀለፈችበትን ስትለቀዉ ልብ እርግት የሚል ነዉ የሚመስለኝ ...ግን የሚገርመኝ አምስት ዉሾችን አሸንፎ እንደገና እሷን በግድ ሳያገኝ እዛ ነገር ላይ ሳይረካ ዉሻዉ ማልቀሱ ያሳዝነኛል፡፡
ግን በሰዉ ሴት በዛ እንጂ ወንድ ቢበዛ ኑሮ ምን ይኮን ነበር???
እናም ወንድሜ ሆይ ለአንድ ሴት የሚዉጀበጀብ የሚያሳፈስፍ ሰዉ ከበዛ ተወት አድርግ ለምን እንደነዛ ዉሻ ተናክሶ ተናክሶ አንዱ ሀራም ላይ የወደቀባት አይጠፋምና .......እናም አደቧን የጠበቀች በዲነል ኢስላም ያደገች ..የጨዋ ቤተሰብ ልጅ ከሆነች ዉሻ አይቀርባትም ለምን ሀራም ፈልጋ ተቀባብታ የቱርክ ልብስ ለብሳ የተወጣጠረ ሂጃብ ለብሳ...ፋሽን ልብስ እየመረጠች የገዛችዉን ለብሳ አትሄድማ ..የሷ አለባበስ ጅልባብ ኒቃብ አንገቷን ደፊ ብዙ የሴት ጓደኛ የሌላት ከሆነች በትርፍ ጊዜዋ ቂርአት ጋር የምታሳልፍ ከሆነ ..ቤተሰቦቿን በስራ የምታግዝ ከሆነች ..ወዳጄ እሷ ጋር ክብር አለ ፣እሷ ጋር ሀያእ አለ፣ እሷ ጋር መዉደድ አለ ፣እሷ ጋር ቀይ የደም ሴል አለ ከሌለም ከቶበተች ችግር የለም እንዳታሳልፍ ...እሷ ጋር ነገ ለምወልደዉ ልጅ ዋስትና መሆን የምችል በተርብያ የማሳደጉ ብቃት አለ፣ እሷ ጋር ለስራ ምክንያት አገር ጥለህ ብትሄድ አማናህን ልጆችህን ንብረትህን የምጠብቅ ብቃት አለ ..እሷ ጋር ቆንጆ ያገባና በሬ ያረደ ብቻዉን አይበላም የሚባለዉ የጃሂል ተረት አይሰራም ..እሷ ነች የትዳር አጋር ምርጫ ማድረግ ያለብህ...
ለምን የዋሁ ትዳር ለማግባት በሚዲያዉ በስልክህ ባለ ፎቶ በምትመርጠዉ ሴት ብዛት የተወዛገብክ የቱን ላድርግ ብለህ ዉዝግብግብ ያልከዉ አንዷን ላግባ ብለህ ወስነህ ዘወር ስትል ከእሷ የተሻለ ሶስት አራቱን ስታይ ሀሳብ ለምቀይር ወዳጄ ሆይ!! እወቅ የአላህን ትዕዛዝ የማታከብር ሴት መቼም ቢሆን የኔን ትዕዛዝ ትቀበላለች ታከብራለች ብለህ አትሰብ!!!!!
አለባበሳ አነጋገሯ አካሄዷ አኗኗራ ከአላህ ትዕዛዝ ዉጭ ከሆነ የፈጠራትን ጌታ ትዕዛዝ ካላከበረች የአንተ አባወራዉን ትዕዛዝ ልታከብር አትችልም.. አደራህን ተጣላሁ እንዲህ ሆነች እያልክ እንደ ባቄላ ንፍሮ እንዳትነፋረቅ ..ወይም ሸይጧኑ አሟሙቆት በጥፊ በካልቾ ብለህ ተከሰህ በሴት መብት ወህኒ ቤት እንዳገባ ..ሸሪአ ፍርድ ቤት አፋቱኝ እያልክ ቡሀላ ጊዜ እንዳትፈጅ አሁን ባለህ ጠባብ ሰአት ጊዜህን ተጠቀምበት !!! ፈጦ የተቀመጠ አይንህን ግለጠዉና አእምሮህ ጋር አቆራኝተህ ዲነኛዋን ጀሊሉ የሰጣትን ዉበት ብቻ የያዘችዉን እንስት ነገ የማለድምበትን በእጅህ አድርግ!!!
ከስድብ ክፉ አቅሙን የማያቅ ነዉ!!!! እናም ሸርጥ መስፈርት ሳታበዛ በአቅምህ በአንተ አቅም የምትኖረዉን ሀዋህን በጊዜ በእጅህ አድርገህ የሙስሊም ኡማዉን ቁጥር አብዛዉ፡፡

ግን ሁላችንም ማወቅ መገንዘብ ያለብን ጊዜያዊ ደስታችን እና የእለት ከእለት ኑሯችን የቀበሮ ፈንጠዝያ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን ...ቀበሮ አድኖ ከገደለ ቡሀላ ደስታዉ ወሰን የለዉም...የገደለዉን አስቀምጦ በደስታ እየሮጠ በጩሀት ያቀልጠዋል በደስታ ብዙ ስለሚጓዝ ተመልሶ ያደነዉን ሲፈልግ ያጠዉና በእጅጉ ያዝናል፡፡ እናም በሰዉ ልጅ የህይወት ዉጣ ዉረድ ለደስታም ለሀዘንም ልክ ይኑረን በመሶበር የማይገኝ ነገር የለምና፡፡

ማስታወሻየ እዚህ ላይ ጨርሻለሁ ምን ይታወቃል ወልጄ በተማርኩት ተመርቄ አስተማሪ የሕይወት ዉጣ ዉረድ ለወደፊት ካሳለፍኩ በማስታወሻየ ፅፌ ጀባ እላችሆለሁ ለዛሬ በዚሁ ፡፡
ማስታወሻየን ዘጋሁ ...

ተ..............ፈ.............ፀ................መ


@Islam_and_Science
1.3K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:22:49 #የመራም_ማስታወሻ
        ክፍል ~➊➑ የመጨረሻዉ ክፍል
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ


አንድ ቀን አብዲ የ12 ክፍል ያመጣሁትን ዉጤት ካርድ ይመለከተዋል
..... እህት ወንድሞችሽን ለማስተማር ብለሽ ያቋረጥሽዉን ትምህርት በዲግሪ መማር አለብሽ ብሎ በግል ኮሌጅ በኔዉ ምርጫ Acounting ተመዝግቤ እየተማርኩ ነዉ.....በቅርቡ ደግሞ የልጅ እናት መሆኔ ነዉ ነፈሰ ጡር ነኝ ..
የታገሰ መጨረሻዉ እንዴት አማረ!!! በህይወት ዘመናት የሚፈራረቁ ደስታና ሀዘን የህይወት ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ ...ሁሌም ቢሆን ሀዘን በደስታ ሲተካ ደስታም በሀዘን ይቀየራል ሂወት እንደዚህ ነች ፡፡

አላህ ከታጋሽ እና ከአመስጋኝ ብራያዎቹ ያድርገን.....
ስኬት አጋጣሚ አይደለም ..ስኬት የአመለካከት ዉጤት ነዉ ..አመለካከት ደግሞ ምርጫ ነዉ፡፡ ስለዚህ ስኬት የምርጫ ጉዳይ እንጂ የዕድል ጉዳይ አይደለም...ስኬት በህወይወት ዉስጥ በደረስንበት ከፍታ ያህል አይለካም፡፡ ይልቅስ ስንወድቅ ምን ያህል ጊዜ ወድቀን ተነስተናል??በሚለዉ መልስ ያዘለ ጥያቄ ነዉ ስኬት የሚለካዉ ...ወድቆ የመነሳት ችሎታ ነዉ የኛን ስኬት የሚወስነዉ....

አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፡-"" እንዲሳካልህ የምፈልግ ከሆነ የዉድቀትህን ቁጥር እጥፍ አድርገዉ ..ሽንፈት የስኬት ረጅም ጎዳና ነዉ ብለዋል፡፡""
የስኬት ብቸኛዉ መለኪያ የሆነ ነገር መስራት ብቻ ከሆነ ..መዉደቅ የሚገፋን ወደ ፊት ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
ስኬትን ለማግኘት ብለዉ ብዙ ሴቶች ስኬት እየመሰላቸዉ ብዙ መጥፎ ሀራም ነገር ይሰራሉ ..በጭራሽ ይሄ የስኬት መንገድ ሊሆን አይችልም፡፡ ሴትነት በርካሽ መንገድ የሚረከስበት በሀራም መንገድ የሚሸቀልበት በአላማ በለለዉ ወንድ አላማዋን የምትስትበት አይደለም!!" ሴትነት ማለት በእሾህ የተከበበ እስር ቤት ነዉ..ማምለጥ የማይቻል ለመኖር ደግሞ አንዱ እሾህ ሲወጋ እየነቀሉ እያስታመሙ የሚኖርበት የስቃይ የፈተና ፆታ ነዉ ..ይሄን እስር ቤት በጣጥሰሸ ለመዉጣት መታገስ መሶበር በማስተዋል መራመድ እንጂ ያገኘሽዉ ጋር እነፍሳለሁ ካልሽ ...ያዉ ገለባ ንፋሽ ሁነሽ ትቀሪያለሽ ፡፡

እንደ እኔ ከችግር ጋር ከመከራ ጋር ማደግ ችግር እንዳይፈታ ያደረገ ስብዕና አልብሶ ያጠነክራል፡፡
አንድ ሰዉ በሆነ ነገር ከአንተ የተሻለ ከሆነ ምክንያቱ ሊሆን የሚችለዉ ከአንተ የበለጠ ብዙ ጊዜ የወደቀ እና ተስፋ ሳይቆርጥ ለሽንፈት ቦታ ሳይሰጥ ግቡ ላይ ደርሷል ማለት ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ ከአንተ የባሰ ከሆነ ደግሞ ምክንያቱ አንተ ባለፍክበት የሚያሰቃይ የመማር ልምምድ ዉስጥ አላለፈም ማለት ነዉ፡፡
የዱንያ ኑሮ ሲኖር መኖራችን ካልቀረ ችግር የህይወት ጅራቱን ይዞ ወደሆላ ገትቶ የድህነት ጉረኖ ሊደፍቀን አይገባም እኛም ልንፈቅድለት መፍቀድ የለብንም ፡፡
እኔ ሳድግ በቤተሰብ ግጭት አእምሮ ተጨናንቆ ነበር
ከዛም እናቴ ስትሞት ያወረሰችኝ ጥንካሬን ተስፋ አለመቁረጥ ቅንነት እና የወንድም እህቴን ሀላፊነት ብቻ ነበር ከእናቴ መዉረስ የቻልኩት...ነገር ግን ተስፋ የቆረጠ ያገጠጠ የታረዘ የደከመ እኔነቴና ሰዉነቴ በጭራሽ እንዲታይ አላደረኩም እንደዉም የእህትና የወንድሞቼን አደራ ስለተቀበልኩ ብርታቱን ሰጠኝ
የጥንካሬ መለኪያ ሚዛን መሆን ያለበት ፊት ለፊት የገጠመን የህይወት ጥያቄ በአሸናፊነት መወጣት እንጂ ምክንያት በመደርደር በመሸሽና ተስፋ በመቁረጥ ለዚች ለማትረባ ዱንያ እጅ አልሰጥም ብየ በአላህ እገዛ ብዙዉን ያሳካሁ ይመስለኛል

ትናንት የነበረዉ ዛሬ የለም ..ዛሬ ያለዉ ችግሬ ጠንካራ ከሆንኩ ነገ የለም..ለመጣዉ ችግር ሁሉ በአላህ ተስፋ አርጎ አላህን ይዤ አልቸገርም አላህን ከያዝኩ ብቻ መሸሻ መንገድ እንዳለዉ ሁሌም እርግጠኛ ነኝ፡፡

ዉድ የተከበርሽዉ እህቴ ግን ክብርሽን ደረጃሽን እወቂዉ ሴትነት መልክሽን የሰዉነት ቅርፅሽን ችግር ያላየ የሚያምር እጅና እግርሽን ጠዋት ማታ በማጠብ በመዋዋብ ከቤት ስትወጪ የወንድ የሙገሳ ምላስ እና የመንገድ ላይ ፉጨት ፊሽካ ተጠባባቂ አትሁኝ ..ወይም በመኪና መንገድ በገበያ በሚዲያ ዉበትሽን የኔ ነዉ ብለሽ ስትበትኝም ዋዉ አምሮብሻል ስትባይ አመሰግናለሁ ..አይደል አልቀረብህም እያልሽ የወንድ የጫፍ ምላስ ኮመንት አንባቢ የአንቺ ዉበት መገለጫ ሲሆን ሊያሽሞነሙነሽ ልብሽ ጩቤ እንዲረግጥ መቼም አትፍቀጅለት ፡፡የሴት ልጅ ዉበት አላማዉን በረሳ ስራ በሌለዉ ወንድ የሚገለፅ አይደለምና...የአንቺን ዉበት የምወስኚዉ እራስሽ ነሽ አላማሽ የወንድ አድናቆት ከሆነ ኢነማል አእማሉ በኒያ ገና ከቤት ስትወጭ ጀምሮ ፊሽካ ይጀምርሻል በግ ሙቶ ተኩላ ቢያለቅስ ወይም አህያ ሙቶ ጅብ ለቅሶ ቢደርስ ጥቅም የለዉም ሲያደንቅ ፊሽካዉ ሁሉ አንድ ቀን መዘዝ ይዞብሽ ይመጣል፡፡ አባቶቻችን እንዲህ ይላሉ """አህያ ቢሰባ ምኑ ረባ ይቆያል እንጂ አህያ የጅብ ናት""" ተብሏል፡፡ እዉነት ነዉ...አህያ ቢሰባ ቢወፍር ቢያምር የኛ ማህበረሰብ መቼም ቢሆን ለምግብነት አይጠቀመዉም ..ጊዜ ይፈጃል ይቆያል አህያ ከልጅነት ጀምሮ እስከ እለተ ሞቱ ሲያገለግል ሲሸከም ሲገረፍ ይኖራል ከዛም ሲያረጅ ወይ ሲሞት አህያዋን የሚበላዉ ጅብ ነዉ ..እንደዉም አህያ ሲያረጅ ወደ ጫካ ማታ ተወስዶ ይጣላል ለምን ጅቦች እንዲበሉት፡፡ እናም እህቴ አንቺ የተከበርሽ ፍጡር ነሽ ግን በዉበትሽ የምትተማመኝ ከሆነ እንደዚህ እንደ አህያ ማንም የሚወጣብሽ ማንም አምሮብሻል እያለ ቸብ የሚረግሽ ማንም እየመጣ የስሜት ማብረጃ እንዳያደርግሽ ነገ ጂብ የሚበላዉ የአህያ ህይወት ለመኖር አትወስኝ...አህያስ የተፈጠረዉ ለዚሁ አላማ ነዉ ግድ የለም ተሸከመም ተመታም አርጅቶም ጅብ በላዉ እንስሳ ነዉ ነገ የዉመል ቂያማ አፈር ይሆናል ግን አንቺ ነገ የዉመል ቂያማ ተቀስቅሰሽ ለምትጠየቂዉ ጥያቄ ምን ብለሽ እንደምትመልሽ አስበሽ ታቂያለሽ???

በዉበትሽ ተጠቅመሽ ጥሩ አማች ለቤተሰብ ለማምጣት ብር ያለዉ ባል ላይ ለመዉደቅ ብለሽ የምሰሪዉ የመዋዋብ ስራ የሚገጥምሽ ከዉበት መራጭ ሴት አሳዳጅ የሆነ ወንድ ጋር እንደሆነ አዘንጊ..ዉበት አንቺ እንዳሰብሽለት ነዉ በዉበትሽ አድናቂሽ ከበዛ ከአንቺ ችግር አለ ማለት ነዉ ነገ
ይሄ የሚጨራመት የሚያሸበሽብ ዉበት የአንቺ እድሜ ሲገፋ በዉበት ብሎ የገባዉ አባወራ ሌላ ቆንጆ ሴት መፈለጉ አይቀርምና፡፡ ይልቅ ዉበት ይረግፋል የማያምር እጅሽን ፃፊበት ተማሪበት ስሪበት በዉበት ማሰብ አቁመሽ በጭንቅላትሽ አስበሽ ለሌሎች መድረስ ቻይ...የሚያምር እግርሽን ተራመጅበት ሂጅበት ባይሆን ሀራም ቦታ ሳይሆን ቂርአት ለመቅራት ዲነል ኢስላምን ለመማር ተራመጂበት የዛን ጊዜ የሚመጣልሽ የወደፊት አጋርሽ ዉበት ተመልካች ሳይሆን የአንቺን ዲን ስብዕና ጥሩ አመለካከት አይቶ ጎጆ ይቀልሳል የዘላለም ደስታ ነዋሪ ትሆኛለሽ..ካልሆነስ በዉበትሽ ያገባሽ ወንድ 90% የሚያስበዉ አለ ቆንጆ ያገባና በሬ ያረደ ብቻዉን አይበላም የሚለዉን አባባል መቼም ከአእምሮዉ ስለማይፍቀዉ ዉበት ብቻ አይቶ ካገባሽ ቤት ሁነሽ አያምንሽ ..ቤተሰቦችሽ ጋር ብትሄጅ አያምንሽ ..እሱ ሌላ ቦታ ቢሄድ አያምንሽም ለምን ሲያገባሽ ያገኘብሽ ፊትሽን እጅሽን እግርሽን አለስልሰሽ ቀብተሽ እንጂ ልብሽን በኢማን አጠንክረሽ አይደለምና ከዛስ ከዛማ
ካልተማመኑ ፍች ነዋ..የዉበት ወጥመዱ ቆንጆ ያገባና በሬ ያረደ ብቻዉን አይበላም በሚለዉ ፍች ይሆናል
1.1K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:40:44 አካባቢ ኮንቲነር ተከራይቶ እቃ አሟልቶለት የቤት ሰራተኛ ልጆቹን የምትንከባከብለት ይዞለት እሱም እየሰራ ልጆቹን የሚያሳድግበትን የእርዚቁን ማገኛ አመቻቸለት....

አሁን የቀረን አዲስ አበባ መሄድ ነዉ
....ከአላህ ጋር እዚህ ያለዉን ነገሮች ቦታ ቦታቸዉን የያዙ መሰለኝ አለ አብዱ
...እኔም አዎ አብዲ አላህ ኸይር ጀዛህን ይክፈልህ ምንም የምለዉ ቃላት የለኝም አላህ እኔና ቤተሰቦችን አይቶ እንድደርስልን የላከህ ነዉ የመሰለኝ አልኩት
....እሱም አደራ እንደዉለታ ቆጠረሽ ከአሁን ቡሀላ እንዳታነሺብኝ ለአላህ ብየ ነዉ የሰራሁት ደግመሽ እንደዚህ አረክልኝ ብለሽ አንድ ቃል ለራሱ እንዳታነሺ አለኝ

አብዱ ጋር በራሱ መኪና አዲስ አበባ አብረን ሄድን....አዲስ አበባ በስም የኢትዮጲያ ዋና ከተማ ተብየ ስንማር እንጂ መጥቼም እመጣለሁ ብየ አስቤዉም በጭራሽ አላዉቅም ...እኔ ያሳለፍኩት የድህነትና የስቃይ ኑሮ ስለሆነ አዲስ አበባ እኖራለሁ የሚል በህልሜም ስቶኝ ታይቶኝም አያቅም ነበር..

ወሎ ሰፈር አካባቢ የተንጣለለዉ አፓርታማ ቤቱ ላይ መኖር ጀመርን ፡፡ አብዲ ጋር ያለን ፍቅር ይሄ ነዉ ለማለት ይከብዳል በጣም እንዋደዳለን ሳልሰስት ፍቅር እሰጠዋለሁ እሱም ይለግሰኛል...ፍቅር ማለት ከትዳር ቡሀላ ነዉ ከትዳር በፊት ፍቅር ከተጀመረ የትዳሩ ቀን ያበቃል ትዳር ከጀመሩ ቡሀላ ትዳር መሆኑ ቀርቶ እንደ ወንድም እህት ይሆናሉ በመሰለቻቸት የፍች ቀጠሮ የበዛባቸዉ ብዙ አሉና ..


አንድ ቀን አብዲ የ12 ክፍል ያመጣሁትን ዉጤት ካርድ ይመለከተዋል ...,ከዛም

#ክፍል ➊➑
ይቀጥላል......

Join
https://t.me/Islam_and_Science
1.6K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:40:13 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➐
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ


...ቤታችን አብሮኝ እንዲሄድ ብዙ ለመንኩት አሻፈረኝ አለ እሺ ልጆቹን ይዘህ ወዴት ነዉ የምትሄድ?? ስለዉ መሄጃዉን አያቀዉም ብቻ"እግሬ ወደመራኝ ቦታ እሄዳለሁ ቤቴን እንደሆነ ሚስቴ ሽጣ በመጠጥና በጫት ጨርሰዋለች"አለኝ

...ከልቤ አዘንኩ አባቢ ግድ የለም አብረን እንሂድ ከበላነዉ ትበላላቹህ፤ ከምንጠጣዉ ትጠጣላቹህ፤ ደስታቹህ ደስታየ ሀዘናቹህም ሀዘኔ ነዉ።
አንተ የወለድካቸዉ ልጆች ለኔ የሞተዉን ወንድሜን ማስታወሻ እና የሞተችዉ እናቴ ቅሪት ናቸዉ ..ወንድም እና እህቴችን መልሰህ አትንጠቀኝ !!!እናንተ አብራቹህን መኖር ከጀመራቹህ ቤታችን ይደምቃል የሰዉ መድሀኒቱ ሰዉ ነዉ ደሞ እነሪምን አስብ አልናፈቁህም እንዴ???.....አባቢ አብሮኝ ቤት እንዲሄድ በስንት መከራ አሳመንኩት ...ከተወሰነ ደቂቃ ቡሀላ አብደል ከሪም ከአዲስ አበባ በመኪናዉ የምሰራበት ቦታ ደረሰ ... አባቴን አገኘሁት አብደል ከሪም ብየ በደስታ አስተዋዉቄዉ አብረን ወደ ቤት ሄድን

ቤት እንደደረስን የቤቱን በር ስናኳኳ ሪም የአብዲን መምጣት በጉጉት እየጠበቀችኝ መሆኑ ያስታዉቃል ፊቷ በፈገግታ ተዉቦ በሩን ከፈተችልን።

....አባቢ ሪምን ሲያያት ደነገጠ ሪምም ያ ፈገግ ያለ ፊቷ ሆምጣጣ ሎሚ የመጠጠች ይመስል በአንዴ ኩስትርትር ብሎ ቲማቲም መሰለ ደነገጠች "አአአአ... "ምን ብላ ትጥራዉ ??አባቢ ሪምን ይዞ ልቅሶዉን ቀጠለ ጩኸቱን የሰሙ እማማየ በፍጥነት ወደኛ መጡ "ምንድን ነዉ? ምን ተፈጠረ..."አሉን አባቢን ሲያዩ እማማየም ..አልሀምዱሊላህ እንኳን ደህና መጣህ ያልሞተ ሰዉ ይገናኛል ብለዉ እቅፍ አደረጉት

..ከዘም አዩብ መጣ አባቢ በናፍቆት ሪምንና አዩብን አቅፎ የደስታ አይሉት የሀዘን ለቅሶ ያለቅሳል "እማማየ ኑ ወደዉስጥ ግቡ"ስትል ነበር ሪም" ጮክ ብላ ምን እንደተከየለባት አላዉቅም...አንተ ማን ነህ? "ብላ ከአባቢ እቅፍ ወጣች

ሪም አባቢ መሆኑን አላዉቅ ብላ ሳይሆን ይሄን ያህል ጊዜ ስለጨከነብን አባቴ ብሎ ለማለት ከብዷት ነበር ማን ነህ ያለችዉ.....
---->>>>> አባቢ ደነገጠ ምን ይበል "ሪሪሪሪሪ"ስሜን እንዳትጠራዉ ብላ ወደ ቤት እየሮጠች ገባች፡፡ እኔም ተከትያት ከገባሁ ቡላት እያለቀስኩ ሪምየ የኔ ዉድ አባታችን ነዉ አልመቸዉ ብሎ እንጂ በኛ ጨክኖብን አይደለም ያን ያህል ጊዜ ስንሰቃይ አይዟቹህ ያላለን አታይዉም ሰዉነቱን ያግርማ ሞገስ የነበረዉ አባታችን እንዴት እንደሆነ እና ተመችቶት ይመስልሻል ከኛ የራቀዉ??? ደሞ አባት ምንም ቢሆን አባት ነዉ፡፡ እዉጭ ያየሻቸዉ አንድ ወንድ እና ሴቷ ልጆች ወንድምና እህቶቻችን ናቸዉ፡፡ አባቴ ስም ያወጣላቸዉ ፈይሰል እና ለይላ ብሎ ነዉ... አየሽ እህቴ የቤተሰብ ፍቅሩ ልቡ ላይ አለ ግን አላህ ሁን ያለዉ ሁኗል ... በአላህ ሪምየ እኔ አዉፍ ብየዋለሁ አንችም አዉፍ በይዉ....... ብየ በስንት መከራ አሳምኘ ይቅር እንድትለዉ አደረኳት
ሪምና አባቢ አዉፍ ተበባሉ በጣም ደስ አለኝ አዩብም ያለ አባት ፍቅር አድጎ የአባቱን ፍቅር አሀዱ ብሎ እየጀመረ ነዉ .....አንዴ አባቢ ጋር አንዴ አብዱ ጋር
ታናሽ ወንድም እህቶቹ ጋር ሲጫወት ቤቱ የሌለ ፍቅር በፍቅር ሆነ

....በዛሬዋ ቀን አብዱንና አባቢን አገኘሁ ያ!የቀዘቀዘ ቤት በሳቅ ደመቀ ቤተሰባችን ከድሮዉ በጥፍ ጨመረ
.... ለአላህ! ክብር ምስጋና የተገባ ይሁን።
ምንም ነገር ቢሆን እንደነበረ የሚቀጥል የለም ሁሉም በጊዜ ዉስጥ ይቀየራል ያጣዉ ሲያገኝ ያገኘዉ ሲያጣ፤ ከተከፋዉ ሲደስት የተደሰተዉ ሲከፋ፤ የታመመዉ ሲድን የዳነዉ ሲታመም፤ ሂወት ስትመር አንዴ ስትጣፍጥ፤ መወለድ፤ መሞት፤ማግኘት፤ማጣት፤ማልቀስ፤መሳቅ.....በቃ ሂወት እንዲህ ናት ዝብርቅርቅ ብላ ለመግለፅ የማትመች!
አብዱም ግን መራም ልጆች እንደዚህ ሲንጫጩ ደስ አይልሽም? አለኝ
...አዎ በጣም ደስ ይለኛል
........ግን ምን እንደተመኘሁ ታቂያለሽ መራም?
.....ምንድን ነዉ??
...........የኮምቦልቻ ልጅ የነለይላ ቤተሰብ የሆነችዉን ልጅ ጋር በትዳር ተጣምሮ ደስታ የሆነ የትዳር ሂወት መስርቶ መኖር አለኝ
.....እኔም ኢንሻ አላህ ሁን ያለዉ ይሆናል አብዱ አልኩት


አሁን የምንኖርበት ቤት ጠባብ ስለሆነ አብዱ ሀሳብ አመጣ ...ኮምቦልቻ ላይ ቤት ተከራይቶ አባቴ ልጆቹን እንዲያሳድግ አዩብም አባቱ ጋር ከታናሽ ወንድም እህቶች ጋር አብሮ መኖር ጀመረ ...ሶስት ልጆች ነበርን አሁን አምስት ልጆች ሁነናል...የሞተዉ ፋይሰል እና እናቴ አሁን በተወለዱት ወንድምና እህቶች ማስታወሻ አገኘን ....
ሪም እነሱ ጋር እየሄደች መንከባከብ የሷ ስራ ሆነ

...ከተወሰነ ጊዜያት ቡሀላ እኔና አብዱ ለመጋባት ወስነን ደስ በሚል በኒካህ ፕሮግራም አድርገን አልሀምዱሊላህ አብረን የመኖር ጎጆ መሰረትን .. እንደአጋጣሚ ከአብዱ ጋር አላህ አገናኘን ለኔም ለቤተሰቦቼም ከአላህ ቀጥሎ የዱንያየ መከታ የችግሬ መፍቻ መፍትሄ ሆነን ቤታችን በድጋሚ አሸበረቀ
ግን ምን ይደረጋል የኔ ደስታ ሁሌ አትጨምር የተባለ ይመስል እኔና አብዲ ከተጋባን ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናትና እማማየ ሳይታመሙ ድንገት ሞቱብን አለቀስኩ ወደኩ ተነሳሁ... ነገር ግን በኛ ለቅሶ ከሞት የሚመለስ ሰዉ ቢኖሮ በተመለሰ ነበር
..እማማየን እንደናቴ ነበር የማያቸዉ ቤት ስገባ የሚቀመጡበትን ወንበር ሳይ ማልቀስ የሁል ጊዜም ስራየ ሆነ


ከአምስት ወር ቡሀላ አብዲም አዲስ አበባ ነዉ የምንኖረዉ ስላለኝ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ እየተዘጋጀን ነዉ..የሪም አብሮ አደግ የሰፈር ልጅ የሆነዉ ሀቢብ ሀራም ከመጀመሩ በሀላል ማሸብረቁ የተሻለ ስለሆነ መጥቶ ሀቢብ እህትሽን ዳሪኝ ብሎ ጠየቀኝ...ሀቢብ ሪምን ይወዳታል የእሱ ታናሽ ነች ከልጅነት ጀምሮ አሳድጓታል ግን ለመጥፎ ነገር መቼም ተመኝቷት አያቅም ..እናም ሪምን አማከርኳት
እሷም እኔ የእህቴን አምር አልጥስም ሀቢብም አብሮ አደጌ ነዉ ጥሩ ልጅ ነዉ መርሀባ ተቀብያለሁ አለችኝ

እኔም ሀቢብ ቀጥታ እህቴን ሳያወራት እኔዉ ለእሷ ብዙ ነገር አድርጌ ማሳደጌን ስለሚያቅ እኔን መጠየቁ አስደስቶኝ ሀቢቤ እስከ ዛሬ እኔ ከእናቴ ሀላፊነት ተቀብየ እዚህ ደረጃ አድርሻለሁ መቼም ታቃለህ ..ከዛሬ ጀምሮ እኔ ደግሞ እናቴን የሰጠችኝን ሀላፊነት ለአንተ ሰጥቸሀለሁ አደራ!!!! ሪምን እንደሚስት አርገህ ሳይሆን እንደ እህትህ እንደ እናትህ አድርገህ ተንከባክብልኝ...ሰዉ ነንና ስህተት አይጠፋም..ሪም ካጠፋች አደራ ሽማግሌ አስታራቂ እንዳትጠራ ለምን እኛ ዘመድ የለንም ሪም ሊከፋት ይችላልና ...አንተዉ ወንድም አባት ሁነህ በመመካከር ሀሳባችሁን የተፈጠረዉን ችግር በወያየት ተግባባታችሁ ኑሩ፡፡
በዚህ የማይፈታ ችግር ከገጠመህ ለሌላ ሰዉ ሳታወራ ቀጥታ ደዉለህ ለኔ ንገረኝ እንደዚህ የምልህ ሪም ታጠፋለች ብየ ሳይሆን ሸይጧን በመሀከላችሁ ከገባ ምን እንደሚፈጠር እርግጠኛ መሆን ስለማልችል ነዉ እንጂ እኔ በሪም ከራሴ በላይ እመሰክርላታለሁ
ስለዉ ሀቢብም በደስታ መርሀባ ቃል እገባለሁ መራም ብሎኝ ሪምም ከሀቢብ ጋር አብሮ የመኖር ዋስትና የሆነዉን ኒካህ አሰሩ..አልሀምዱሊላህ

ለአባቴና ለታናሽ ወንድም እህቶቼ ደግሞ አብዱ አላህ ኸይር ስራዉን ይጨምርለት ኮምቦልቻ በርበሬ ወንዝ ሰፈር ቤት ገዝቶ መናሀሪያ
1.4K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:41:37 ጥፋት ያለፈ ነገር ነዉ ሀላፊነት ደግሞ በተገኘዉ አጋጣሚ ነዉ ...ጥፋት የሚመጣዉ አስቀድመን
ባደረግናቸዉ ምርጫዎች ነዉ...ሀላፊነት የሚመጣዉ ደግሞ አሁን በየቀኑ በየሰከንዱ ከምናደርጋቸዉ ምርጫዎች ነዉ፡፡ አሁን እኔም የአባቴና የልጆቹ ሀላፊነት ተጋርጦብኛል
ስራዉን ሲያስብ ይቅርታ የማይደረግለት ስህተት ነዉና አዉፍ በማለቴ ተገረመ

እኔ አባቢን አዉፍ በማለቴ ረፍት ሲሰማኝ አባቢ ግን በሀዘን፤በቁጭት፤በፀፀት...እኔ ማን ነኝ ጨካኝ ፤አረመኔ አባት ወይስ.... "እያለ ማልቀስ ጀመረ ከልቡ ተፀፀተ ለካ ሰዉን በቀላሉ መበቀል ይቻላል የኔ ይቅርታ ማድረግ ለአባቢ ረፍት ነሳዉ ስራዉን ሲያስበዉ መረረዉ ህሊናዉ ወቀሰዉ...

        ኋለኞች ፊት ፊተኞች ኋላ
        መሆን አይቀርም የኋላ የኋላ
        በሰፈርከው ቁና ትሰፈርበታለህ
        በመተርከው ሜትር ትመተርበታለህ
        ባስለቀሰው ስራህ ታለቅስበታለህ
         ባነሳሀው ዱላ ትመታበታለህ
         በወንጀልህ ልክ ትቀጣበታለህ
         ያጠፈሀው ጥፍት ትጠፋበታለህ
         ከፊት የነበርከው ከሆላ ትሆናለህ
        ከክብርህ ማማ ላይ ዝቅ ትላለህ
        ለምን ካለክኝማ ዱንያ ነዉ ልበልህ
        ከአንድ አላህ በቀር ነገን መች ታቀዋለህ?
        ነቅተህ መጠበቅ ነዉ ለሞት ተዘጋጅተህ
        ጭማሪ ደቂቃ የለም በሂወትህ!!!!



....ቤታችን አብሮኝ እንዲሄድ ብዙ ለመንኩት አሻፈረኝ አለ እሺ ልጆቹን ይዘህ ወዴት ነዉ የምትሄድ?? ስለዉ
....አባቢም እንዲህ አለኝ.....

ክፍል ➊➐

ይቀጥላል.......


Join
https://t.me/Islam_and_Science
1.6K viewsedited  05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:40:43 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➏
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ




ወደ ውጭ ወጥቼ ወደ ምድር አንገቴን አስግጌ ልጁን ተመለከትኩት ከፊት ለፊቱ ወዳየው ሰው ሩጫ ቀጠለ ሩጫውን ተከትየ ሰመለከት አይኔን ማመን አቃተኝ .....

ከነመፈጠራችን የረሳንን አባቢን አየሁት ልጁን አቅፎ ሲሰመው ጉሮሮየን ሳግ አፈነው ቃል ማውጣት አልቻልኩም እንባ ከአይኔ ከመፍሰስ ውጭ መናገር አቃተኝ፡፡ ስጠላውና ስኮንነው የኖርኩት አባቴ ዛሬ በሀዘን ተንሰቅስቄ እንዳለቅሰ አረገኝ

ያ የሚያምረው ግርማ ሞገሱ ድምጥማጡ ጠፍቷል፡፡ስጋው አልቆ አጥንቱ ቀርቷል ሁለት ትላልቅ ጅማቶች ግንባሩ ላይ በትልቁ ተጋድመው ከሩቅ ያስታውቃል ጥርሱ አርንጓዴ አይሉት ቢጫ የነጭነቱ መልክ ጠፍቶ ወደ ጥቁነት ተቃርቧል ግንባሩ ላይ ያሉ ጅማቶች እጆቹንም ወረውታል ...ያረጀ ጫማ ኮሌታው
...ግንባሩ ላይ ያሉ ጁማቶች እጆቹንም ወረዉታል ያረጀ ጫማ ፤ኮሌታዉ የተቀደደ ሸሚዝ፤ የተቀደደ ሱሪ ...ለብሷል ደነገጥኩ ያ! ባለግርማ ሞገሱ አባቴ አልመስለኝ አለኝ በጣም አፈጠጥኩበት ከሚስቱ ጋር ከፍ ባለ ድምፅ እየጮሁ ይጨቃጨቃሉ ፡፡ ትንሽ ራቅ ስላልኩ በምን ተጣልተዉ እንደሚያጨቃጭቃቸዉ ማወቅ አልቻልኩም ብቻ ለደቂቃዎች አይኔ ከነሱ አልተነቀለም ጭቅጭቃቸዉ የሚያልቅ አይደለም

እኔም መጨረሻቸዉን ለማየት ጓጉቼ ቁሜ ቀረሁ ከመሀል ልጃቸዉ ፈይሰል ከሩቅ ሲያየኝ እየሮጠ መጣና በሀዘን አይኖቹ እያየኝ ልብሴን እየጎተተ በትናንሽ ጣቶቹ ወደእናትና አባቱ እያመለከተ እባክሽ ገላግያቸዉ የሚል ይመስላል

እኔም በጉልበቶቼ በርከክ ብየ የፈይሰልን ፀጉር እያሻሸሁ ፈይሰል ምን ሁነህ ነዉ እየሮጥክ የመጣሀዉ?? ብየ ጠየቁት የፈይሰል መልስ እንዳሰብኩት ነበር
....."እማየና አባየ ተጣሉ" አለኝ
ከነሱ መጣላት የልጁ አንገት መድፋት ሳይ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም አለቀስኩ በእዝነት አይኔ እያየሁ ጥያቄየን ቀጠልኩ
.....ፈይሰል ሁሌም ነዉ ወይስ ዛሬ ብቻ ነዉ እናትና አባትህ የሚጣሉት ??? ብየ ጠየኩት
.....ፈይሰልም " ጥዋትም ማታም ሁሌም እንደሚጨቃጨቁ ሲጨቃጨቁ ጃሮዉን በእጆቹ ይዞ ተዉ ተዉ....እያለ ከቤት እንደሚወጣ ባስ ሲልም እርስ በርስ እንደሚመታቱና በተደጋጋሚ ጎረቢቶች እንደሚገላግሏቸዉ ነገረኝ ፡፡ አዘንኩ ወደ ኋላ በሀሳብ ተጓዝኩ እማየ ትዝ አለችኝ በርግጥም በዱንያም ሆነ በአኼራ ሰዉ የዘራዉን ያጭዳል አባቢ እማየን እንዳስለቀሳት አሁን ሚስቱ ታስለቅሰዋለች!!!

...."ፈይሰል የት ሂደህ ነዉ? ለምን እዚህ መጣህ?"የአባቢ ንግግር ነበር ከገባሁበት የሀሳብ ማእበል ያነቃኝ ደነገጥኩ ቀና ብየ ለማየትም ቀፈፈኝ እባቢ አይኑን ወደ መሬት ወርዉሮ የኔ ልጂ አመሰግናለሁ ና ፈይሰል" አለና ልጁን ይዛ ለመሄድ ሲቻኳል ፊቴን ወደመሬት ስላደረኩ አላየኝም ወይም ከነመፈጠሬ ረስቶኝ ይሆናል ብየ ሳስብ ፈይሰል"አልሄድም ከአንተ ጋር አልሄድም ብሎ ተጠመጠመብኝ
..... አባቢም ና ፈይሰል እኔ እቸኩላለሁ አለና ጎንበስ ሲል አይን ላይን ተገጣጠምን

ከፊቱ ያየሁትን የመደንገጥ፤የፀፀት፤ የደስታ፤የሀዘን...ድብልቅልቅ ያለ ስሜት መቸም አረሳዉም "መመመመመ...."እንዴት ችሎ ስሜን ይጥራዉ?? አልቻለም ደጋግሞ ሞከረ መመመመ"ከሚባሉ ፈደላት ዉጭ ሙሉ ስሜት ከአፉ ማዉጣት አቃተዉ እንባዉ ጉንጫቹን አልፎ በአንገቱ እየወረደ የለበሰዉን ሸሚዝ አራሰዉ እኔም ቁሜ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?? አልቻልኩም የእማየ የስቃይ ሞት፤የኔ ሂወት፤ የእህቴና የወንድሜ በድህነት ማደግ የሁላችን ተጠያቂ እሱ እንጂ ማን ነዉ? እና እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?! እንዴት? ከበደኝ!!!

... መጥቶ በሁለት እጁ እያለቀሰ በናፈቀ ስሜት አቀፈኝ ሩጨ የምሄድበት መሰለዉ አካሌን ከፀጉሬ ጀምሮ ዳበሰዉ አላምን አለ ......በደስታ አንዴ ይስቃል አንዴ ያለቅሳል በዚህ ስሜት እያለ ሚስት ተብየዋ መጥታ "አንተ ሰዉየ ጭራሽ እኔን ትተህ ቆንጆ መዳበስ ጀመርክ?? ይሄ ነበር የቀረህ!!!! እንዲህ ነችና በል እስከዛሬም ታግሸሀለሁ አሁን ትግስቴ አልቋል ልጂህን ተረከብ እና የምትዳብሳት ሴት ጋር መኖር ትችላለህ " ብላ ልጇቹን ሰጥታዉ ሲጋራዋን እያቦለለች አባቴን ገለማምጣዉ ጥላዉ ሄደች
...አባቢ ዝም ብሎ እኔን ከማየት ከመዳበስ ዉጭ እሷን ለማየትም ለመስማትም ጊዜ አልነበረዉም ጥለዉ ስትሄድ ምንም ቃላት ሳያወጣ ዝም አለ።

ከደቂቃዎች ቡኋላ ነበር ልጆቹን እናታቹህ የት ሄደች ??? ብሎ የጠየቃቸዉ ልጆቹም ጥላቸዉ እንደሄደች ነገሩት ...እናቲቱ በሰራችዉ ስራ በጣም አዘነ


....ከአጠገቡ በፍጥነት አንድም ቃል ሳልተነፍስ ተነስቼ መንገድ ጀመርኩ
>>>>> ልጄ መራም መራሜ የኔ ልጂ እያለ ተከተለኝ
ምን ፈለክ ያንተ ልጅ ማን ናት??? እኔ እኔ ነኝ ያንተ ልጅ እኔ... የእብድ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ አባቢ ደነገጠ እይዉልሽ የኔ ልጅ የፈለግሽዉን በይኝ ፤ያሻሽን ተናገሪኝ...የፈለግሽዉን ስደቢኝ፤ ብቻ አባቴ አይደለህም አትበይኝ የኔ ልጅ በአላህ ተረጂኝ አዉፍ በይኝ ከስራየ በላይ የስቃይን ጥግ አይቻለሁ አይታይሽም ከሰዉነት ጎዳና እንዴት እንደወጣሁ??...."ንግግሩን አላስጨረስኩትም አቅፌዉ አለቀስኩ እሱም አቅፎኝ አለቀሰ .......በዚህ የሀዘን አይሉት የደስታ ለቅሶ ላይ ስልኬ ሲጠራ ነበር የነቃሁ

...የደወለዉን ስመለከት አብዲ ነዉ አነሳሁት ..ኮምቦልቻ ገብቻለሁ የምሰሪበት እየደረስኩ ነዉ ተዘጋጂ አለኝ ... ደስታየ እጥፍ ድርብ ሆነ ፡፡

አባቢ ምንም ቢሆን አባቴ አባቴ ነዉ አቃለሁ የቤተሰባችን የሀዘንና የስቃይ ሰበቡ እሱ ነዉ ግን ደሙ በእሱ ሰበብ ከደሜ ተወህዷል ስጋዉ ከሱተቆርጦ የተሰጠኝ ስጋየ ነዉ አባቱነቱን መፋቅ አልችልም! አባት በሌላ አባት እንደቁስ አይቀየርም አይሸጥ አይለወጥ ነገር.....

እናቴ ልትሞት ስትል የነገረችኝን አስታወስኩ አባታችሁ ይወዳችሆል ያለችን...ነገሮችን ሳስተነትን የወለዳቸዉን ልጆች ወንዱን በሞተዉ ወንድሜ ስም ፋይሰልና ሴቷን ደግሞ በምወዳት እናቴ ስም ለይላ ማለቱ አባቴ ተቸግሮ የሰራዉ ስራ አሳፍሮት ነዉ እንጂ የቤተሰብ ፍቅር እንዳለበት ተረዳሁ

መቸም ሰዎች ስንባል አዉቀንም ሆነ ሳናቅ እንሰሳታለን ስህተታችንን አዉቀን ከተመለስን እንዴት ይቅርታ እንነፈጋለን!
አላህ ይቅር እንዲለን ከፈለግን እኛም ለበደሉን ይቅር ማለት አለብን አላህ ይቅር እንዲለዉ የማይፈልግ እስኪ ማን ነዉ"??? ማንም!!!!

....ለአባቢን ይቅርታ ለማረግ ብዙ ማሰብ አልተጠበቀብኝም በፍጥነት ነበር አዉፍ ያልኩት ወድያዉ ወደ ቤት እንሂድ ብየ ጋበዝኩት
......መሄድ አልችልም በአላህ እሺ በይኝና ልጆቼን እንዳያቸዉ እዚሁ ይዘሽልኝ ነይ ልጄቼን የማይበት አይን የለኝም ብሎ አንገቱን ደፋ
....እኔ በሰራሀዉ ስራ አዉፍ ብየሀለሁ.... እናቴ ደግሞ የእህት ወንድሞቼ አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ...እኔ ይቅር ካልኩህ እነሱም እንደሚሉህ እርግጠኛ ነኝ አልኩት

....የእህት የወንድሞቼን አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ስለዉ አባቴም በጣም በማዘን እምባዉ ኩልል እያሉ እየወረደ እኔ ነኝ የእሷ ሞት ምክንያት እያለ ሲያለቅስ--እኔም አብሬዉ እያለቀስኩ አባቴ ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም ሰዉ መሳሳቱን አያቅም እንጂ ቢያዉቅማ አያጠፋም ነበር አልኩት
1.2K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ