Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ሷሊህ እንደዚህ አለኝ>>>>> አላህንማ የማፈሪዉ አንቺ ነሽ....... የትም ስትልከሰከሺ ማንም ጋር ስትተኚ ስትማግጪ ላስወሰድሽዉ ድንግልና ምን ታካብጃለሽ... ባለፈዉ እኮ በልጅነቴ ተደፍሪያለሁ ብለሽ ስትነግሪኝ የተቀበልኩሽ በዉበትሽ ተማርኬ ነዉ እንጂ እዉነት እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ... ዉበት ደግሞ ለማንኛችንም ወንድ ልጆች አስቸጋሪ ነዉ የፍቅር ሳይሆን የዉበት ፈላጊ ነን ....እኔ የወደፊት ባልሽ ነኝ እስከምንጋባ ድረስ አብረን አንዳንዴ ማሳለፍ አለብን ..አብሮ ለመተኛት አዲስ አትሁኚ የለመድሽዉ ነዉ አለኝ፡፡

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም አይደል የሚባለዉ ሷሊህ ሆዱ ያለዉን በዚህ ቅፅበት ዘረገፈዉ

.....,.እኔም ምንም አላልኩትም ከዶክተር ሷሊህ ቤት ወዳዉኑ ወጥቼ እቤቴ እስከምድርስ በጅማ ጥቁር አስባልት መንገድ ጥቁር እድሌን ይዤ ከለር በሌለዉ እምባ ልስልስ ባሉት ጉንጮቼ አዘንባቸዉ ይዣለሁ ፡፡
አይ ሷሊህ የተማረ ብዙ ነገር ያቃል ተብሎ ለዛዉም በዶክተርነት ዲግሪ ይዞ የብዙ ሰዎችን ሂወት ያተርፋል ተብሎ ተስፋ የተሰጠዉ ሰዉ ..ከአፋቸዉ ጤነኛ መስለዉ ዉስጣቸዉ ግን እንደ አባጨጓሬ የኮሰኮሰ ማንነት በነጭ ጋወናቸዉ ተሸክመዉ ይዞራሉ ፡፡በሷሊህ አነጋገር ልቤ እየደማ ከሚፍታህ መለየት በላይ ወደ ዉስጥ ብሶቴ ገብቶ ብዙ ግፍ ወደ ተሸከመዉ ወደ መኖሪያ ቤቴ በለቅሶ አይኔ ቅልት ብሎ ተመለስኩኝ......
 
እቤት ክላሴ ገብቼ -----የፈጠርከኝ አላህ ሆይ!!!!! አረ ምንድን ነዉ ወንጀሌ??? አላህ ሆይ ፈተናየ በዛ ፈተናዉ ይበቃሻል በለኝ... ፅናቱን ስጠኝ እያልኩ እያለቀስኩ ዱአ ሳደርግ ..ሶላትም ስሰግድ አደርኩ፡፡
አዳሬን ለሰከንድ እንኳ እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ ጨለማ ለጀንበር አስረከበች .......,



ጠዋት እቤት መሆን ሲያስጠላኝ ተነስቼ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ፡፡ግን ምን ይደረጋል እራሴን በጣም ስላመመኝ መማር ስላልቻልኩ መልሼ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ

ሷሊህ የብስ የኔን ሞራል ለመጉዳት በሶስት ቀን በሳምንት  ይደዉልና ያንን ነገር አመቻቸሽ የኛ ጨዋ መቼ አብረን እንደር ?? ወይስ የመጀመሪያሽ ወንድ ከኔ ይሻልሻል?? እያለ ይቀልድብኛል

እኔ መልስም አልመልስለት ፈጣሪ የስራዉን ይስጠዉ ፡፡ግን ከእንደዚህ ያለ ሰዉ ለሰዉ አርአያ መሆን ከሚችል ሰዉ ለምን ይሄ መጥፎ ባህሪ ጎልቶ ይንፀባረቃል??? ሷሊህ ለህዝብ ተስፋ መሆን ሲገባዉ በተለይ እንደኔ ተቸግረዉ ተስፋ ላጡ የሚረዳቸዉ አጥተዉ የሚሰቃዩ ላሉ ወገኖቹ አብሽሩ ከጎናችሁ ነኝ ብሎ ማፅናናት ተስፋ መስጠት ሲገባዉ ...ነገር ግን እንደ እሱ የወረደ አስተሳሰብ ይዞ እንደዚህ እኔን ማሸማቀቅ መስደብ ምን ያደርጋል ?? ቢቻል ማግባቱ ቢቀር ለኔ ሒወት እንዲስተካከል የስነልቦና ጫና አለብሽ ብሎ መፍትሄ እንደመስጠት እየደወለ የሚያሳምም ንግግር በቃላት እየወረወረ የብስ ሒወትን ተራራ እንደመግፋት አደረገብኝ....ታዳ ምሁርነቱ ዶኮተርነቱ ምኑ ላይ ነዉ ??መማር ማለት ይሄን ካላገናዘበ ምኑ ላይ ነዉ መማሩ ??? ነጭ ጋወን መልበሱ እና ከስራዉ ጋር የማይሄድ ስም ሷሊህ ቢሉት ጥቅም የለዉም..



በኮሌጅ ሁለተኛ አመት ፍቅር በሚባል የሰዉ አላማ ፕላን ጋር የማይመጥን የሒወት አዙሪት ጊዜየን ፈጅቼ
የሁለተኛ አመት Coc ስፈተን ወደኩኝ...ደግሞ ከወደኩኝ ሶስተኛ አመት ኮርስ መቀጠል አልችልም

ከዛም ለCoc ለመፈተን ብየ መስከረም ወር ላይ የጅማ የቅርብ ጎረቤት ወደ ሆነችዉ አጋሮ ከተማ ሄድኩኝ ..

አጋሮ ፈተና በሄድኩበት ጊዜ ከነመፈጠሩ የረሳሁት ካሊድ እየደወለ በስልክ ማዉራት ጀመርን በጣም ተቀራረብን...ጠዋት ማታ እየደወለ አብሽሪ አላህ ያሳካልሽ ይለኛል፡፡ ካሊድ ጋር ማዉራቱን እንደ አዲሱን ተያይዘንዋል አጋሮ ሁኜ እሱ ጋር ማዉራት ሱስ እስከሚሆብኝ ድረስ በስልክ እያወራን ነዉ....

ካሊድ ብዙ ጊዜ ሲደዉልልኝ እንደዚህ ይለኛል #ነዋል_ቆጣሪዉ_እየቆጠረ_ነዉ ፡፡ የምትለዉን ቃላት እየደጋገማት ነዉ
....,እኔ ደግሞ እኔ ጋር ስደዉል ነዉ ማለት ነዉ ካርድህ የሚያልቀዉ?? እለዋለሁ ..ቆጣሪ እየቆጠረ ነዉ የሚለዉን ቃላት በቀላል ማዕናዉን መረዳት አልቻልኩም

....,ለካ ይሄ ቆጣሪ መቁጠር ቡሀላ ማዕናዉ ትርጉሙን ሳቀዉ ፍቅርሽ እየጨመረብኝ ነዉ ማለት እንደሆነ በጊዜ ሳይገባኝ ከብዙ ቀን ቡሀላ ተረዳሁኝ

ካሊድ ጋር በስልክ በጣም መቃለድ ተያይዘነዋል....እሱም እንደበፊቱ አይደለም አሁን ፍርሀቱ ለቆታል.....ግን እኔ ካሊድ ጋር ስናወራ ለትዳር ይሆናል ብየ በጭራሽ አስቤዉም ትዝም ብሎኝ አያቅም ...ለምን በፊት ካሊድን እንደማልፈልገዉ ነግሬዉ እሱም ተስማምቷል ፡፡ አሁንም አጀማመራችን በእህትነትና በወንድምነት ተባብለን ነዉ፡፡ ግን ይቺ ወንድነትና እህትነት የምትለዉ ቃላት ይአጅበኛል እሱም እቤቱ ወንድም እህት እያለዉ እኔም እቤቴ ወንድም እህት እያለኝ ተጨማሪ የባዳ እህትና ወንድም ለምን አስፈለገ???ስንት በቁጥር ለመግለፅ የተጀመረ የሀላልም የሀራሙም ግንኙነት በእህትነትና በወንድምነት እየተጀመረ ከአንድ ማህፀን ዉስጥ ለወጣዉ ወንድሟ የማታወራዉን ሚስጥር እንደ ወንድምሽ እይኝ ላላት ስንቱን የቆጥ የማገሩን ስታወራ ትዉላለች??? እሱም ቢሆን እቤቱ የምታገለግለዉን አይቡን የምሸፍንለት እህቱ እያለች በሚዲያ ለተዋወቃት እህት ተብየ ምን አዲስ ነገር አለ ስትለዉ ዘጠኝ አህጉር የሰማዉን ወሬ ሲቀባጥር ይስተዋላል፡፡ በዚህ በእህት ወንድም ግንኙነት ስንት ሀራም ወንጀል እየተሰራ ነዉ??? መቼም እኔ እህት ሁኚኝ ወንድም ልሁንሽ ሲልሽ የአንቺ መልስ መሆን ያለበት እቤት ያሉት ወንድሞቼ በቂ ናቸዉ ካልሆነ ሒወትሽ አደጋ ላይ ነዉ እህቴ.,

coc ተፈተን አልሀምዱሊላህ አለፍኩኝ ..መልሼ ወደ ጂማ ተመለስኩኝ ፡፡ ትምህርቴን ሶስተኛ አመት ተመዘገብኩኝ፡፡ በዚህ ሶስተኛ አመት ትምህርት ግሬድ ለማሻሻል ፍቅር የሚባለዉን ከልቤ ፍቄ ለማጥናት ወሰንኩኝ፡፡
በዚህ አመት እቅድ ብየ ብዙ ሀሳቦችን ካሰብኩኝ ቡሀላ በጠረንፔዛ ዙሪያ ዉይይት በተረጋጋ መልኩ እኔዉ ብቻየን በብቻየ ክላስ ተቀምጬ ተወያይቼ ወሰንኩኝ፡፡ ዉሳኔየም ለአሁኑ አመት የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪ ነኝ  ቸክየ ተምሬ coc ካለፍኩኝ ስራ የማግኘት እድል አለኝ..በተጨማሪም በትምህርት ቤታችን ግሬድ ከፍተኛ ነጥብ አለኝ ዲግሪ በስኮላር ሺፕ እማራለሁ፡፡ ብየ ወሰንኩኝ


ወላሂ ቢላሂ ወንድ የሚባል ፍጡር በትምህርት ቤትም ሆነ ሰፈርም በየአየሁት አጋጣሚ እንኳን ለማዉራት በአይኔ ለማየት ጠላሁኝ ..ጭራሽ ከወንድ ልጅ ፍቅር ከመጠበቅ ጆንያ ሙሉ ቁንጫ ለቆ እነሱ ይመጣሉ ብሎ መጠበቅ ይሻላል የምትለዉን አባባል አያብሰለሰልኩ እራሴን አሳመንኩ...ፍቅር ስሙ እንጂ ተግባሩ ወንድ ልጅ ጋር የለም ብየ በአራት ነጥብ ደመደምኩ ፡፡

የሚገርማችሁ ብዙ ሴት ጓደኞቼ በትምህርት ቤትም በሰፈርም ነዋል ልናገባ አስበናል ስለትዳር ምን ትመክሪናለሽ ??ብለዉ ሲጠይቁኝ
...እኔም መልሴ ጥምም ያለ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንጂ ተስፋ የሚዘራ ከአፌ በጭራሽ አይወጣም ... የዘንድሮ ወንድን አምናችሁ አታግቡ እኔ ትዳር አለመክራችሁም...ወንድ ልጅ የሚያገባዉ ለስሜቱ እንጂ አንቺን አስደስቶ ለመኖር አይደለም እያልኩ የብዙ ሴት ጓደኞችን ሒወት በተጣመመ የትዳር እና የወንድ ልጅ አመለካከት በልቤ ቋጥሬ አበላሸሁ