Get Mystery Box with random crypto!

ከወንጀል ተከልክለዉ ኑረዉ... ትዳር ላይ ሲገቡ ምሽት ላይ በማታየዉ ምልክት አጅሬዉ ነብር ይመስል | ISLAMIC SCHOOL

ከወንጀል ተከልክለዉ ኑረዉ... ትዳር ላይ ሲገቡ ምሽት ላይ በማታየዉ ምልክት አጅሬዉ ነብር ይመስል ደም ካላየ አንቺ ድንግል አይደለሽም እየተባለች ባልሰራቸዉ ስራ ባልሰራቸዉ ዚና በባሎች ተጠርጥራ በግራ አይን እንድትታይ .... ነገሩም ከከፋ እስከ መፋታት ድረስ የሚደርሱ ብዙ ትዳሮች እያየን ነዉ፡፡ ዉድ እንቁ እህቶች በዚህ ምክንያት ፈጣሪ በሰጣቸዉ ፀጋ ለምን ደም አላየንም አንቺ ዉሸታም ድንግል ነኝ ብለሽ ዋሸሽኝ እየተባለች በባሎች ማሸማቀቅ ምነዉ አግብቼ ባልነበር እያሉ ሲያለቅሱ የሚኖሩ ብዙ እህቶች እንዳሉ ቤት ይቁጠረዉ ፡፡ ወንድሜ ሆይ!!!!! ደም መድማት ብቻ ነዉ እንዴ የድንግልና መገለጫ ??? አትሳሳት ከአእምሮህ ላይ ደም ብቻ ነዉ የሚለዉን ፍቀህ አዉጣዉ....ደም ማየት ብቻ የድንግልና ማረጋገጫ አይደለም፡፡

መጀመሪያ ስለድንግልና ትርጉም እወቅ.. ድንግልና ለሴት ልጅ ብቻ አይደለም ለወንድም አለ...ነገር ግን ምን ይደረግ የወንድ በሴት ልጅ መታወቅ አይችልም..አንተ አወኩኝ ብለህ የምታሸማቅቅ ከሆነ ...የአንተን ማንነት የሚያቅ ፈጣሪ እንዳለ አደራ አንዳትዘነጋ ፡፡ #ድንግልና ማለት የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም ማለት ከግብረ ስጋ ግንኙነት (ከሩካቤ ስጋ) መቆጠብን ይመሰክራል ፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነት ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና(የንፅህና ክብር) ወይም ድንግልና ይባላል፡፡

#ድንግልና_በምን_ይገለፃል?
በእርግጥ ሁለቱም ፆታዎች መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡንና መፅናቱን ተከትሎ የሚታይ የአካል ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል።
ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው።

ይሄ በጣም ስስ የሰዉነት ክፍል(አካል) በቀላሉ ሴት ልጅ ልታጣው ትችላለች፡፡ ለምሳሌ፡- ሳይክል በመንዳት ፣ ፈረስ በመጋለብ ፣ ጅምናስቲክ የመሳሰሉ እስፖርቶችን በመስራት...በሀይድ መደራረብ...በከባድ ህመም ወዘተ ያለምንም ፆታዊ ተራክቦ ታጣዋለች።

#የድንግልና_አይነቶች_ስንትናቸው?
አምስት አይነት የድንግልና አይነቶች አሉ። እነርሱም #አንደኛዉ ➊ ☞ ሙሉ የብልት አካል በራፍ ላይ እንደ መጋረጃ የዘጋው ሲሆን የእጃችን ቀዳዳ ምታክል ክፍተት አለው ለወር አበባ መፍሰሺያ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ። ይሄ ቀዳዳ ሙሉ የድንግልናውን ቦታ አይሸፍንም የድንግልናውን መጋረጃ ሩብ ምታክለዋ ቀዳዳ ናት።

#ሁለተኛ ➋☞ ብዙ ጊዜ ባይሆንም አንዳንድ ሴቶች ላይ የወንፊት መልክ በተያዘ በርካታ የተበሳሱ ቀዳዳዎች የተሞላ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ።

#ሶስተኛ ➌☞ በተፈጥሮዋ ምንም የተጋረደ ነገር የለዉም ፡፡ በመጀመሪያው ግንኙነትዋ ጊዜ የሚፈስ ደም የሌላት ሴት አለች ድንግል እንደሆነች የምታውቀው እርስዋ ብቻ ናት ምንም ድንግል እንደሆነች ምልክት አታሳይም ደም አይፈሳትም።

#አራተኛ ➍☞ ድንግልናው በተፈጥሮ የጠነከረና በወንዱ ብልት ሊበጠስ የማይችል ነው ፡፡ይሄ አይነት ድንግልና ያላቸው ሴቶች ድንግልናቸውን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በሰርጀሪ ወይም በቀዶ ጥገና ወቶላቸው ነው ግንኙነት የሚፈፅሙት።

#አምስተኛ ➎☞ ሴትዋ ምንም አይነት የድንግልና መጋረጃ ሳይኖራት በብልትዋ ግርግዳ በኩል ብቻ ትናንሽ ሄመኖች ሲገኙ እነሱም የሚወገዱት በወንዱ ብልት ፍትጊያ ነው።
የሴቶች ድንግልና እላይ በጠቀስኳቸዉ አምስቱ ምክንያት ከፈጣሪ የሚሰጣቸው የተፈጥሮ ፀጋ ነው፡፡
.ይህ ፀጋ ደሞ የሚገኘው በመወለድ አንድ ጊዜ ነዉ፡፡ እድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሳ አሻራን ጥሎ ሚያልፍ ነው። ብዙዎቻቹ የመጀመሪያ ግንኙነታቹን አይረሱትም ለዛ ነዉ ወንዱ ድንግል ምርጫዉ ያደረገዉ፡፡ እናም ወንድሞቼ ደም ካላየሁ ድንግል አይደለችም ብለህ ንፁህ እህትህን ሚስትህን ለተናግሮ ተናጋሪ እንዳትሰጥ በተጨማሪ ከእኔ በፊት ከሌላ ጋር ባልጋለች ብለህ እቺን ንፁህ እንስት እንዳታረክስ ፡፡ የለቅሶዋ ምክንያት እንዳትሆን፡፡


ከዛም ጁምአ ደረሰ እና ብቻችንን ሂደን የምናወራበት፡ቦታ በመኪናዉ ሄድን ... ከአሁን ቡሀላ ጊዜ አንፍጅ አንቺም እቤት አሳዉቂ እኔም አሳዉቃለሁ በቅርብ ቀን ሽማግሌ ልልክ አስቢያለሁ ..አንቺ ምን ሀሳብ አለሽ ?? አለኝ
.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? ብየ ጠየኩት
.....ካሊድም እንዲህ አለኝ_

#ክፍል

ይ.............ቀ.................
........ጥ............ላ...................ል

join

        . t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science