Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ አራት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ካሊድ የላኩለትን message እየደጋገመ አነበበዉ አነበበዉ ፊቱ ተቀያየረ መናደዱ ፊቱ ላይ ያስታዉቃል ...የፈራሁት ስጨነቅበት የነበረዉ ደረሰ ብየ አሰብኩኝ
......... ካሊድ አብሽር አትደንግጥ አልፈልግሽም ማለትህ አይደል? በቃ ልነሳ እና ልሂድ አንተን ማስጨነቅ አልፈልግም ብየ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ
......እሱም ነይ ተቀመጭ ምንድን ነዉ የምትይዉ?? አሁን ከአፌ ምን ሲወጣ ሰማሽ?? ብሎ ሲቆጣኝ መልሼ ተቀመጥኩኝ
......እሱም አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅሽ message በደንብ አልገባኝም እስኪ አብራሪልኝ የአራት አመት ልጅ ሁኜ ነዉ ያልሽዉ ወይስ ከአራት አመት በፊት ነዉ ??? ብለሽ የፃፍሽዉ?? አለኝ
.....የአራት አመት ልጅ ሁኜ ነዉ አልኩት
......ካሊድም ዝም ብሎ ቆየና... ያላሰብኩት ይለኛል ብየ ያልገመትኩት መልስ ሰጠኝ >>>>> #እንዴት_ሰዉ_የአራት_አመት_ልጅ_ጋር_ስሜቱ_ይታዘዝዋል ???<<<<<<< ግን የምርሽን ነዉ የኔ ፍቅር መቼም አፕሪል ዘፉል እያልሽ ሰዎቹ እንደሚጃጃሉት እየተጃጃልሽ አይደለም አይደል ?? አለኝ
.....እኔም አዎ እዉነቴን ነዉ አልኩት
........እኔን ለመፈተን አይደለም ???እንደዚህ ስለዉ ከተወኝ ልተወዉ ከተቀበለኝ ደግሞ የወደፊት የትዳር ምርጫየ ነዉ ብለሽ አስበሽ እኔን ለመፈተን..የአንቺ የፈተና መሰናክሉን ማለፍ አለማለፌን ለማረጋገጥ ብለሽ  አይደለም ??? አለኝ
.....አዎ አይደለም እዉነተኛ ነዉ የነገርኩህ አልኩት
..........እሱም ወላሂ በይ ??? አለኝ
..............ወላሂ ቢላሂ ብየ ማልኩለት
......እሱም እንዴት ሰዉ ገና ለጋ በሆነች የአራት አመት ልጅ ጋር ስሜቱ ይታዘዝዋል ???ምን አይነት ጨካኝ ቢሆን ነዉ ??? የኔ ፍቅር አለኝ
....እኔም ጥያቄ እያበዛህ አታጨናንቀኝ .....አልኩት
.......አንድ ነገር ልጠይቅሽ ፍቃደኛ ከሆንሽ ??አለኝ
.... እሺ ምን ነበር ጥያቄዉ??? አልኩት
.......እዚሁ ቁጭ እንዳልሽ የማስብበት ሀያ ደቂቃ ብቻ ስጭኝ አለኝ
......እሺ ቅድም እንዳልኩህ እንኳን ሀያ ደቂቃ አንድ ቀን እሰጥሀለሁ አልኩት
   
ካሊድ ለ20 ደቂቃ ያህል እየደጋገመ ቴክስቱን እያነበበዉ ነዉ ...የካሊድ ሁኔታ በጣም አስጨነቀኝ ወላሂ እምባዉ እያነበበ ዱብ ዱብ እያለ ይወርዳል ....

ከዛም ከ20ደቂቃ ቡሀላ እንደዚህ አለኝ ...ነዋል እኔ የምወደዉ አንቺን ነዉ ሁሌም ቢሆን እወድሻለሁ፡፡ ፍቅር ማለት ከነማንነት መቀበል ነዉ፡፡ እኔ የምፈልገዉ አንቺን ነዉ ...እኔ ምኞቴ አንቺ የኔ ስትሆኝ ዱአየ ደርሶ ማየቴ ነዉ ፡፡ እኔ አንቺን ምን ያህል እንደማፈቅርሽ አታዉቂም ማለት ነዉ ??? ፍቅር ማለት እንደ አሁን ዘመን ሰዎች ተገናኝተዉ ስሜታቸዉን ማብረድ ..መንገድ ለመንገድ ተገናኝተዉ መጋተት መገባበዝ ብቻ መሰለሽ እንዴ ???አለኝ
.......እኔም ካሊዶ አታስጨንቀኝ ነገሮችን አታወሳስብብኝ ግልፁን ንገረኝ አልኩት

....ነዋል አንቺ ምንም ሁኚ ምንም የምፈልገዉ ነዋል የኔ እንድትሆኝ ብቻ ነዉ ..አንቺን አግብቼ አቅፌሽ እንድተኛ...ከአንቺ ጋር ደስተኛ ሁኜ ልጅ መዉለድ ....ልብሽ ከልቤ ጋር እየመታ እንዲኖር ነዉ የምፈልገዉ ..ለኔ ሌላዉ ትርፍ ነዉ ምንም አልፈልግም ...ይሄ እኮ ቀላል ነገር ነዉ እኔ የተማርኩ ሰዉ ነኝ ብዙ ነገር አዉቃለሁ ..የግድ ድንግል አይደለሽም ብየ ሀገር የምበጠብጥ በረዶ ይቆላልኝ እያልኩ የምለፈልፍ መስሎሽ ነበር እንዴ ??? ድንግልና እኮ ለትዳር መስፈርት አይሆንም ...እንዴት ፍቅርን በዚህ ተራ መስፈርት የምተዉ መስሎሽ ነበር እንዴ??? ብሎ እንደመቆጣት አለኝ
.......እኔም ካሊድ የሚያወራዉ እዉነት እዉነት አልመሰለኝም... ከምርህ ነዉ ??? አልኩት
...........እሱም የሰዉ ልጅ ከወደደ እንኳን አንቺ በማታቂዉ በልጅነትሽ ክብርሽን የአጣሽዉን.....አንዴት ሴት አግብታ ልጅ ወልዳ ተፋታ ከአንዴም በላይ አራት የተለያዩ ባሎች ጋር ኑሮዉን አይታ መፋታት የምታበዛ ፀባይ የሌላት ጨቅጫቃ...... በዛም ላይ  ልጅ ኑሯት ይችን ሴት በፍቅር አምነዉ ወድቀዉ ተዋደዉ ....እያገቡ አይደል እንዴ ???  አለኝ
......እኔም ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ ??ካሊድ አንድ ቃል ብቻ ንገረኝ ..ማንነቴን ተቀብልሀል አልተቀበልክም??? አልኩት
......የሰጠሁትን ቀለበት መልሶ እጄን ይዞ አስተካክሎ  በጣቴ አረገልኝ ፡፡ ስሜታዊ ስለሆነ አጂ ነብይ የሚለዉን ዘንግተንዋል
......እኔም በኔ ማንነት ተስማምተሀል ማለት ነዉ ???አልኩት..ጭራሽ የሚሆነዉን ነገር ማመን አልቻልኩም
............እሱም ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ ??ይሄ እኮ ቀላል ነገር ነዉ ቀለል አርገሽ እይዉ....የኔ ፍቅር እስከዛሬ ለዚህ ቀላል ነገር እንደዚህ ተጨንቀሽ ነበር ማለት ነዉ ?? አንቺስ ተጨንቀሽ እኔንም ያስጨነቅሽኝ ለዚህ ተራ ነገር ነዉ ??? ወላሂ እኔም ተጨንቄ ቀን ስራ መስራት ማታ መተኛት አልቻልኩም ነበር ..አለኝ
........እኔም ተቀብለህኛል ማለት ነዉ ??? አልኩት
እሱም አዎ ተቀብያለሁ ይሄ ተራ ነገር ነዉ ..ለወደፊት ስለዚህ ጉዳይ ማዉራትም አያስፈልግም ..በዚሁ እርሺዉ አለኝ
.....ግን አስበህበታል ??? ሁለት  ቀን ልስጥህ እና እሰብበት ቡሀላ እንዳይቆጭህ አልኩት
.....ሁለት ቀን አያስፈልገኝም አሁኑኑ ወስኛለሁ ብቻ አሁንም ለወደፊትም አንቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺ የኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔ ብቻቻቻቻቻቻቻቻ  ሁኝልኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝ አለኝ፡፡

ከዛም ይሄን ያህል አመት ከልጅነትሽ ጀምሮ እንደዚህ ስታለቅሺ የኖርሽበት ገና በአራት አመትሽ ስሜቱ ታዞት ይሄንን በደል ፈፅሞብሽ ስታለቅሺ እንድቶኖሪ የፈረደብሽን ልጅ አሳየኝ  እገለዋለሁ አለኝ
......እኔ እሱን ለአላህ ብየ ትቸዋለሁ በቀል ጥቅም የለዉም ይቅርታ ያሸንፋል...ግን ፈጣሪ የስራዉን ወይ በዱንያ ወይ በአኼራ ይሰጠዋል አልኩት
....እሱም ማሻ አላህ.. እኔ ብሆን ለእምባየ ምክንያት የሆነዉን በአገኘሁት አጋጣሚ እበቀለዉ ነበር...አንቺ ይቅር የሚል ጥሩ ልብ አለሽ አለኝ ፡፡


ከዛም ካሊድ አሁን ሳይመሽ ወደ ቤትሽ ልዉሰድሽ ብሎኝ ከቤት ወጣን...መኪናዉ ወስጥ ሁነን ነዋል እንዴት ቅልል እንዳለኝ ልነግርሽ አልችልም ..ተረጋጋሁ በጣም እየተቀጨነኩ ነበር ምን ሁነሽ ይሆን እያልኩኝ ለወደፊት በእንደዚህ ያሉ የሒወት አጋጣሚዎች ተስፋ መቁረጥ የለብሽም ብሎ የተለያዩ ምክሮች መከረኝ...

እኔም ይሄ የተጨነኩበት ቀን እንደዚህ እኔ ባልጠበኩት ሁኔታ አለፈ....አልሀምዱሊላሂ ረቢል አለሚን አልቅሸም አልቀረሁም አላህ ዱአየን ተቀበለኝ፡፡
ወንድ ልጅን ሳስብ ትዳር ሲመጣ ድንግልና ብቻ ነዉ መስፈርታቸዉ ብየ አስቢያለሁ..ባስብም አይፈረድብኝም ከአንድ ሁለቴም ደርሶብኛልና ..ደግሞ በተዘዋዋሪ እንደ ካሊድ ያሉ አስተዋይ ለሴት ልጅ የሚያዝኑ ቅንጣት ሰዎች አሉ

★★★ ግን አሁን ድረስ ወንዱ ድንግልናን ደም ጋር ያያዙታል..ግን ደም ብቻ ነዉ የድንግልናዉ መገለጫዉ???
#ድንግልና_ወይም_ክብረ_ንፅህና_የምንለው_ምንድንነው?
አንዳንድ ወንዶች ግድ ደም ካላየን ድንግል አይደለችም እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ሲያቅራሩ ይስተወላሉ፡፡ ነገር ግን ስንት ጥብቅ አላህን ፈሪ የሆኑ ሴቶች ጌታቸዉን ትዕዛዝ ተቀብለዉ ከዚህ አስከፊ ዘመን ሙሲባዉ ሹብሀዉ በበዛበት ጊዜ