Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ ስድስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ

ከዛም ጁምአ ቀን ያልተሳበ ይሆናል ብየ በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል...ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም ፡፡
 
     ቅዳሜ ካሊድ ሽማግሌ ሊልክ ጁምአ እናቴ ከአባቴ ጋር ተጣልታ ዘመዶቿ ጋር ሄደች ፡፡ በእኛ ሰፈር የሚገኙ ሽማግሌ ተሰብስበዉ ሁለቱም እንዲታረቁ ቢለመኑ ..አንታረቅም የኛ መጨረሻዉ ፍች ብቻ ነዉ መፍትሄዉ ብለዉ በጭራሽ ሊስማማሙ አልቻሉም፡፡
...እኔም ለካሊድ ደዉየ ቤተሰቦቼ እንደተጣሉ እና ሽማግሌዎቹን እንዳይልክ ነገርኩት

ጊዜያቶች እየነገዱ ነዉ....አባቴ ሌላ ሴት ለማግባት እየፈለገ ነዉ...እናቴም ፍርድ ቤት ከሳ ንበረቱን ተካፍላ ከቤት ይዉጣልኝ እያለች ነዉ፡፡ ነገሩ በጣም ሲጠና ...አባቴ ለልጆቼ ብየ እታረቃለሁ ቢልም ..እናቴ ግን በጭራሽ አልታረቅም ብላ አሻፈረኝ አለች.... የሰፈር ታዋቂ ሸሆች... የመስጊድ ኢማማችን ሳይቀር ቢለምኗት እምቢ አለች፡፡


እኔ እና ካሊድ ለመጋባት 100% ጨርሰናል ሁለታችንም ለትዳር ልባችን ቢንጠለጠልም ግን እናት እና አባቴ ተለያይተዉ በሚኖሩበት ቤት በተበታተነ ቤተሰብ ለማን ሽምግልና ይላካል??? ዱአ ከማድረግ ዉጭ ምንም አማራጭ የለም...

   ደግሞ አዲስ ነገር የማይፈጠር የለም ...ሚፍታህ ደወለልኝ እና ...ነዋል አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ነዋል ከልቤ ነዉ እወድሻለሁ ሽማግሌ ልልክ ነዉ አለኝ
......እኔም ሚፍታህ አሁን መቼም ቢሆን የአንተ መሆን አልችልም ለሁሉም ጊዜ አለዉ አንተም በጊዜህ እኔን ትተህኛል...አሁን እኔም ልቤ የሌላ ነዉ ...ተስፋ ቁረጥ እንደፈለክ የምከፍተዉ የምዘጋዉ የቤትህ በር አይደለሁም አልኩት ቆጣ ብየ
 

አይጠቅምም ብለዉ የጣሉት እቃ ሌላ ሰዉ አንስቶ ሲጠቀምበት ምነዉ ባልጣልኩት ብለዉ ይቆጩ የለ... ..ሚፍታህ እኔን ትቶኝ ላገባ ፕሮሰስ ላይ መሆኔን ሲያቅ ..እንደገና ካላገባሁ ሙቼ እገኛለሁ..ሽማግሌ ልልክ ነዉ እያለ አሁንም ተስፋ ያልቆረኩ ይመስለዋል..ሴት ልጅ ስወድ ወደደች ነዉ ከጠላች ደግሞ በእሷ መስፈርት ሁሉንም አሟልተህ ብትገኝ ከጠላችህ መቼም በልቧ መግባት እንደማችል እንደነ ሚፍታህ ያሉ ወንዶች ዘንግተዉታል... መቼም ካሊድን በማንም የማልቀይረዉ እዉነተኛ የትዳር አጋሬ ነዉ፡፡

✿✿✿ ምርጥ ጓደኛየ መፍቱሀም ተመርቃ የግል ሆስፒታል ዉስጥ ገብታ እየሰራች ነዉ..

✿✿✿ብሩክታይትም ቢላል የሚባል የወንዶች የጀመአ አባል ብሩክታይት ዲነል ኢስላምን አስተምራለሁ ቁርአን አቀራታለሁ ብሎ መፍቱሀን እና እኔን አማከረን ...እኛም ብሩክታይትን አማከርናት ... ቢላልን ታቀዋለች በትዳር ጥያቄዉ ተስማማች .. ስሟንም በራሷ ፍቃድ ብሩክ ታይት ሳይሆን ራዉዳ ነኝ ብላ ከቢላል ጋር እህል እና ዉሀቸዉ ገጥሞ በትዳር አለም አብረዉ መኖር ጀምረዋል፡፡

✿✿✿ ካስታወሳችሁ በአለፉት ክፍል ናርዶስ(በአጎቷ እና በአባቷ ጓደኛ በልጅነቷ የተደፈረችዉ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ተምራ ተመርቃለች

✿✿✿ የሱፍ (ለሚፍታህ ነዋልን ዳረኝ ብሎ ስልኩን የሰጠዉ) እሱ ደግሞ ሚፍታህ ጋር አንዴ ተጣልተዉ...ነገሩ ከብዶ ፓሊስ ጣቢያ ድረስ ሂደዉ ነበር በሽምግልና ታረቁ ቢባል የሱፍ በጭራሽ አልታረቅም እበቀለዋለሁ እንዳለ ቂም እንደያዘ .. በመጨረሻም የሱፍም ቤተሰቦች እነሱዉ አምጥተዉ እሱም ጎጆ ቀልሶ እየኖረ ነዉ፡፡

✿✿ ሚፍታህም በንዴት ይሁን አስቦበት አላቅም እኔ ላገባ ነዉ ከአሁን ቡሀላ አንተ እና እኔ አንድ ላይ መሆን አንችልም ካልኩት ቡሀላ ...ብዙም ሳይቆይ አንድ ወር ባልመላ ቀናት ዉስጥ እኔን አናዳታለሁ ብሎ አስቦ ይሁን ..ትዳሩን አምኖበት ይሆን...ነዋልን ልቀደማት ብል አስቦም ይሆን አላቅም እሱም የትዳር ጎጆዉን ቀልሷል

✿✿✿ ካሊድም የቤት እቃ እያማሏ ነዉ ፡፡ እኔም ነገሮች እስከሚስተካከሉ ብየ ጅማ የሚገኝ የመንግስት ሆስፒታል በተመረኩበት ፊልድ ማገልገል ጀመርኩኝ...አልሀምዱሊላህ አባቴ ያሰበዉ ደረጃ ደረስኩኝ ..

ሆስፒታል መቼም የብዙ ሰዉ ብሶት መቀበያ አይደል....እንደ እኔ በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች በጣም ብዙ ገጥመዉኛል ..ልጆችን በማፅናናት ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን ማገዝ የአእምሮ ጭንቀት እንዳይዛቸዉ የስነልቦና አገልግሎት መስጠት የዘወትር ስራየ ነዉ. .በተጨማሪም በፍቅር ለተጎዱ ሴቶች ...እንደ እኔ በቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ለአደጉ ልጆች..በተለያዩ ጉዳዮች ዲፕሬሽን(በአእምሮው ጭንቀት) የተጎዱ የዱንያ የአኼራ እህቶቼን ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን መንከባከብ በሀሳባቸዉ ተረድቼ መፍትሄ ስሰጥ ለኔ የዉስጥ ደስታ ሰላም ይሰጠኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ደስታዉ ብቻዉን መቀየሩ ደስታን ማግኘቱ ሳይሆን በእሱ የተነሳ ስንት ሰዉ መቀየሩ መደሰቱ ታላቅ ደስታ ነዉ..

የሚገርማችሁ እዛዉ ጤና ጣቢያ በሴት ልጆች ላይ የሚደርሰዉ በደል ሳይ የኔ ምን አለበት አልሀምዱሊላህ ያልኩባቸዉ ብዙ ቀናቶች አሉ..
እኔ ከገጠመኝ በታላቅ ወንድሞቻቸዉ የተደፈሩ ልጆች ገጥሞኛል..በተዘዋዋሪ ጭካኔ የበዛበት ዘመን መሆኑ ያሳዝናል ብዙ ህፃናት በአባቶቻቸዉ ተደፍረዉ የሚመጡ ብዙ ልጆች ገጥመዉኛል፡፡እኔ አንድ ሴት ነኝ ከጎኔ ማን አለ?? ሁሉም ከጎኔ ባይሆኔም ግን እንደ እኔ ተብድለዉ በሆዳቸዉ አፍነዉ የሚኖሩ ቤት ይቁጠረዉ,..... መቼ ድረስ ነዉ የሴት ልጅ እምባ መዉረድ የሚያቆመዉ ??? ሁሌም በልቤ ቁጭት አለ ታዳ ምን ያደርጋል አንድ ሰዉ አስቦ አንድ በሬ ስቦ አይሆንም...እኔ የራሴን ታሪክ በፁሁፍ ዘረገፍኩት እንጂ ብዙ ሴቶች አሁን ድረስ ዛሬ ከነገ ይሻላል ቢሉም ግን የብስ እየጨለመ የሚሰቃዩ ለቁጥር አይገባም. ... እንደ እኔ እንቅልፍ አጥተዉ የሚኖሩ ሴቶች አይናገሩ ሰሚ የለ ....ለማን ይነገር?? በእንባ ጎርፍ ለፈጣሪ አቤት ከማለት በቀር ፡፡ ስለሆነም ወንዶች እባካችሁ ለሴት ልጆች እዘኑ ይሄ ሁሉ ለቅሶየ ስቃየ በኔ በራሴ የመጣ አይደለም በጨካኝ ስሜቱን መቆጣጠር በአቃተዉ ወንድ የተፈጠረብኝ በልጅነት መደፈር ነዉ ፈጣሪ ሁላችንንም ልቦና ይስጠን

ቢያንስ ከ5 ወራት ቡሀላ በስንት ሽምግልና አልሀምዱሊላህ እናት እና አባቴ ተስማምተዉ መልሰዉ አብረዉ መኖር ጀመሩ ..

እናት እና አባቴ ታርቀዉ ብዙም ቀን ሳይቆዩ በቤተሰብ የትዳር ጥያቄ መጣ ...
ማታ ላይ ሳሎን ቁጭ ብለን አባቴም፡- ነዋል ይሄ መታለፍ መመለስ የሌለበት ትዳር ነዉ..እኛ እንተማመንበታለን ጥሩ ሰዉ አላህን ፈሪ ነዉ ፡፡ነዋል እኔ አባትሽ ለምወድሽ ልጄ መጥፎ ምርጫ እንደማልመርጥ ታቂያለሽ .. አሁን የመጣዉን ትዳር እንድታገቢ ምርጫየ ነዉ እሺ በይኝ አለኝ
....... አባቴ አንተ የተናገርከዉ ልክ ነህ ...ነገር ግን እኔ ትልቅ ልጅ ነኝ የሚጠቅመኝን የሚጎዳኝን ለይቻለሁ ..እኔን በደስታ ሊያኖረኝ የሚችል የኔ የራሴ የምለዉ አንድ ሰዉ አለኝ አልኩት
.....አባቴም ማን ነዉ ልጁ እኔ አቀዋለሁ??አለኝ
....እኔም አዎ ታቀዋለህ ካሊድ ነዉ ብየ ... እሱን እንዲያቁት በምልክት ሰፈሩን ቤተሰቡን ስነግራቸዉ እናቴም አባቴም አወቁት