Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ አምስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? አልኩት
......ካሊድም ቤተሰቦቼ በሌላዉ ሒወቴ እንጂ ጣልቃ የሚገቡት በዚህ የትዳር ሒወት የምወስነዉ እራሴ ነኝ ...ደግሞም ቤተሰቦቼ ስለፀባይ ስለዲን ነዉ የሚጠይቁኝ እንጂ አንቺ ስለምትይዉ በጭራሽ ትዝም አይላቸዉ አለኝ

  እኛ ሀገር አንድ ባህል አለ ..ሁለት ጥንዶች እንደተጋቡ ...አዳሩ ላይ በሩ ላይ ሁነዉ ዘመዶች ያዳምጣሉ የሴቷ የጩኸት የማቃሰት ድምፅ ካልሰሙ አይተኙም ...ከአዳራቸዉ ቡሀላ ጠዋት ላይ የወንዱ ዘመዶች በር ላይ ሁነዉ ይጠብቃሉ... አዲሱ ሙሽራ በቀይ ደም የተበከለዉን አንሶላ ካላሳያቸዉ ድንግል ናት ብለዉ አያምኑትም፡፡ ማታ የወንዱ ቤተሰብች ገብተዉ አንሶላዉን ያነጥፋሉ ጠዋት ደግሞ አንሶላዉን ማሳየት አለበት ፡፡ ሙሽራዉ ድንግል ናት ብሎ ሲናገር..የወንዱ ቤተሰቦች ደስታ በደስታ ነዉ የሚሆነት እልልታዉ ጭፈራዉ #ሰበታ_መቀነት ይባላል... ከሰርጉ ያልተናነሰ ጭፈራ ይጨፈራል የወንድ ቤተሰብ ቤት ይደምቃል ፡፡ ከዛም ሴቷ ቤተሰብ ቤት ተሂዶ ልጃችሁ ስነስርአት ያላት አደበኛ ጨዋ የሽማግሌ ልጅ ናት ተብሎ ስጦታ ይሰጣል ......

እኔም ይሄን ባህል ስለማቀዉ ካሊድ ለቤተሰቦችህ እንዴት ልታደርግ ነዉ አንተ ??? አልኩት
.....እሱም አብረን የምናድረዉ እኔ እና አንቺ ነን እነሱ ምን አገባቸዉ መቼም መኝታ ክፍላችን ገብተዉ አፍጥጠዉ አያድሩ ...እኔ እራሴ የምላቸዉን አቃለሁ ....ለምን እንደዚህ አይነት ሀሳብ ታስቢያለሽ ???  ብሎ እኔ በተናገርኩት እሱ ይናደዳል ...
ነዋል እኔ ብቸኛ አንድ መሆኔ ሰልችቶኛል ..ከአንድ ይልቅ ሁለት መሆን ስቃይ ደስታን ለመጋራት ይመቻል...እኔ የናፈቀኝ ሀሳብ የሆነብኝ መቼ ይሆን እኔ እና አንቺ እኔም የአንቺ አንቺም የኔ የምትሆኝዉ ነዉ ሀሳቤ ጭንቀቴ....እናም ትዳር ነዉ የናፈቀኝ አለኝ..

ትዳር ሐላል አክሲዮን ነው፡፡ አክሲዮኑ በሁለት ተፈቃቃጅ በሆኑ ወንድ እና ሴት መካከል የሚመሰረት ግንኙነት ነዉና እንደዋዛ መታየት የለበትም፡፡ እንደዋዛ ከታየ እንደዋዛ ይፈርሳል፡፡

ትዳር ከሐራም ኑሮ ወደ ሐላል ግቢ ሽሽት ነው፡፡ ከጉድለት ሕይወት ወደ ሙሉነት ቤት ሩጫ ነው፡፡ ጠፍቶ የቆየን ግራ ጎን ማሟያ ፍለጋ ፅድቅ ስደት ነው፡፡

ትዳር የንፅህና ሻወር ነው፡፡ ሲንከራተት ለኖረ ዐይን ማረፊያ ነው፡፡ ሲባዝን ለኖረ ልብ ማስከኛ ነው፡፡ ፍላጎትን ሐላል እና ነፍስ በምትወደው መልኩ ለማሳካት ምክንያት ነው፡፡

ትዳር ባልና ሚስት ተፈጥሯዊ ስሜታቸዉን ሐላል እና አላህ በፈቀደው መልኩ የሚያረኩበት ጥምረት ነው፡፡ ለዚህ ጥምረት ዘላቂነትና ስኬት ከወዲሁ ሀሳብን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ “ከሞቀኝ እቀጥላለሁ ከበረደኝ እወጣለሁ” በሚል ስሜት የተገባበት ቤት የመፍረስ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከሙቀቱ ይልቅ ብርዱ ሊበዛ ይችላልና፡፡ ሀብት ንብረት ለመካፈል ብለው የሚገቡበት ጥምረት ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ሀብት ንብረቱ አልገኝ ሲል ያነጫንጫልና፡፡ “አለው” ብለው የተቀበሉት ኪዳን አይዘልቅም፡፡ ያጡ ቀን ባህሪን ያባላሻልና፡፡

ትዳር በሕይወት በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ባልና ሚስት የሚኖሩበት ህንፃ ነው፡፡ በዚህ ህንፃ ግንባታ ላይ የአላህ እጅ እንዲኖርበት መፍቀድ ብልህነት ነው፡፡ ብቻችንን የምንሰራው ቤት.. ቤት አይሆንም፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) የሌለበት ቤት መሰረቱ ደካማ ነው፤ ጣሪያውም ያፈሳል፣ ግድግዳው በቀላሉ ይዘማል፣ ምሰሶው ያረገርጋል፣ ሁለመናው ስጢጥ ስጢጥ ይላል፡፡
ትዳርን ስናስብ ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ሰበቡን እናሟላ፡፡ አላህን በቤታችን ስናኖረው ያኔ የቤታችን መሰረት ፅኑ ይሆናል፣ ምሰሶው መሬት ይይዛል፣ ግድግዳው ቀጥ ይላል፡፡
ለአላህ ብለው ያሰቡት ነገር የሱ ጥበቃ አለበት፡፡ አላህ የሰራው ቤት አይፈርስም፣ እሱ ያነጸው ህንፃ አይዘምም፡፡ አላህን ከፊታችን እናድርገው፡፡ ትዳር ወሳኝ ነገር ነዉና ቤታችንን በበረከትና በፍቅር ይሞላልን ዘንድ እሱን እናስቀድመው፡፡ ዋናዉና መቅደም ያለበት እሱ ነዉና የሚቀድመውን በማስቀደም የሚከተለውን እናስከትል፡፡ ለባለትዳሩም የትዳር እድሜ ይስጣችሁ ..ላላገባንም አላህ ፈላጊ ከፈላጊ ያገናኝ አሚን...

           ካሊድ ለኔ ያንን ሁሉ የሒወት ዉጣ ዉረድ አልፌ ለዚህ በቃሁኝ ....ደስተኛ ለመሆን መሞከር ረጅም ለመሆን የሞመከር ያህል ለኔ በጣም ከባድ ነበር የሆነብኝ
ዛሬ የምወደዉ የሚወደኝ ፍቅር ምን እንደሆነ በዱንያ ምድር ካሊድ አሳየኝ፡፡ ፍቅር ማለት ይሄ ነዉ ..ፍቅር ከሆነ ግድ መተማመን አለ .. ካሊድ ቢወደኝ ቢያመነኝ ነዉ ሒወቴን ያረጋጋዉ...ደግሞ ባለፈዉ ታሪኬ እንደ ዶክተር ሷሊህ ያለ ተስፋ እንድቆርጥ የስነልቦና ጫና አድሬሶብኝ...ወንድ እና ቁንጫ በልቶ እሩጫ ብየ ከትዳር አለም ተስፋ ቆርጬ ነበር........የብዙ አመት ጠባሳየ ሲያመኝ ሳለቅስ ከሰዉ በታች ነኝ ብየ ሁሌ እራሴን እንደ አሰብኩ እንደ ካሊድ አይነት ጥሩ አስተሳሰብ ያለዉ ሒወቴን ልቤን ማንነቴ ሳይቀር በእሱ መለሰልኝ ..እኔ ሁሌ ድንግል ነኝ ብየ እንዳስብ አረገኝ...አዎ ሁሌም እኔ ድንግል ነኝ... ለምን አስቤበት አምኜበት ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ አሳልፌ የሰጠሁት አይደለም... ገና በልጅነቴ እህሉን ከአፈር በማለይበት ጊዜ ተገድጄ የተቀበልኩት ነዉ፡፡

በሳምንቱ ጁምአ ደርሶ በተለመደዉ ሰአት ተገናኝተን...... ካሊዶ ጋር እያወራን ሁሌም ድንግል ባለመሆኔ ስቆጭ
.....እንደዚህ አለኝ ... ነዋል አትሰቢ አትጨናነቂ ይሄ ተራነገር ነዉ እኮ...አንቺ ግድ መሆን አለብኝ ብለሽ ካሰብሽ የአላህ ነገር አይታወቅም ተስፋ መቁረጥ አንችልም ..... ድንግልም ልትሆኝም ትችያለሽ እኮ.......ለምን ብትይኝ ገና በልጅነትሽ በ4 አመትሽ ነዉ ይሄ በደል የደረሰብሽ ..እና በዛ እድሜ ደግሞ ልጅ ስለሆንሽ የሚጠብቅሽ መላኢካ ነዉ ..እናም ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጭ በአላህ ፍቃድ አንቺ የለኝም ብለሽ የምታስቢዉ ነገር ሊኖር ይችላል አለኝ......


.....,እኔም የHealth ተማሪ እንደመሆኔ መጠን አንዴ ድንግልና ከሄደ እንደማይመለስ አቃለሁ ..ካሊድ በጭራሽ መሆን አልችልም አልኩት
..... ምነዉ ነዋል ከአላህ እኮ ተስፋ አይቆረጥም አለኝ፡፡ ካሊዶ እንደዚህ ሲለኝ እዉነቱን ነዉ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብየ እንደገና ሞራል ሰጠኝ፡፡

    አንድ ቀን የሞባይሌ ባትሪ ተበላሽቶ ለመግዛት ጂማ መርካቶ ሰፈር አካባቢ አንድ ኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ስገባ..ያየሁትነ ማመን አቃተኝ ...በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ሚፍታህ ጋር ተገናኘን
....እሱም ድንጋጦ ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
.......እኔም ወአለይኩም ሰላም ሰላም ነዉ አልኩት
....እሱም እንዴት ነሽ ሁሉ ሰላም ቤተሰብ ሰላም ናቸዉ?? አንቺስ እንዴት ነሽ ??አለኝ