Get Mystery Box with random crypto!

....እኔም አልሀምዱሊላህ ደህና ነኝ አልኩት .......እሱም ቀለበቴን እያየ ነዋል ልታገቢ ነዉ | ISLAMIC SCHOOL

....እኔም አልሀምዱሊላህ ደህና ነኝ አልኩት
.......እሱም ቀለበቴን እያየ ነዋል ልታገቢ ነዉ እንዴ ??? አለኝ
....እኔም...አዎ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን አስቢያለሁ አልኩት
ሚፍታህም :- ሽማግሌ ተልኳል ወይስ አልተላከም??? አለኝ
....እኔም ገና አልተላከም በቅርብ ቀን ይልካል አልኩት
....... ነዋል ወላሂ ብየ ነዉ የምነግርሽ በጣም ነዉ የምወድሽ ..አንቺ የሌላ ስትሆኝ ማየት አልችልም... ወላሂ ሁሌም ህልሜ አንቺ ጋር ተጋብቶ መኖር ነዉ፡፡

አንድ ነገር እንድታቂልኝ እፈልጋለሁ ... አንቺ የሌላ ሰዉ ሁነሽ ..ትዳር ከሌላ ሰዉ ጋር ብትመሰርች ፀቤ ከአንቺ ወይም ከአገባሽ ሰዉ አይደለም..ፀቤ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር ነዉ..... ለምን ብትይ ሀጅ ባደረኩበት ጊዜ አላህን ከሁሉም ሀጃየ አስበልጬ ስጠይቀዉ ስለምነዉ የነበረዉ....አንቺ የኔ እኔድትሆኝ ነበር... አላህን ስለምነዉ የነበረዉ ከአንቺ ልጅ መዉለድ እስከ እለተ ሞቴ አንቺ ጋር አብሮ መኖር ነዉ አለኝ
....ይሄን ሲለኝ አብረዉ ጓደኞቹ ነበሩ... ይሄን እየተናገረ ሚፍታህ እምባ ነዉ የቀረዉ፡፡
ቁርጤን ንገሪኝ ቁርጤን ንገሪኝ ..የሌላ ስትሆኝ ማየት አልፈልግም የኔ ብቻ ሁኜ እባክሽ እያለ ይለምነኛል
........እኔም በጣም ተወዛገብኩ ግራ ገባኝ...ሚፍታህ ዉሳኔየን በስልክ ደዉየ አሳዉቅሀለሁ አልኩት

ከሱቁ ወጥቼ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ ነዉ... ልቤ ተሸበረ ...ዉሳኔ መወሰን አልቻልኩም ...የማልክደዉ እዉነት ቢኖረዉ ሚፍታህ በጣም እወደዉ ነበር ለመጋባት ድረስ ደርሰን ቤተሰብ ለቤተሰብ ተጠይቆ እሺ ተብሎ ጨርሰን እንደነበር በአለፈዉ ታሪክ ላይ ታስታዉሳላችሁ...ሚፍታህ አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ሲለኝ የማላቀዉ ስሜት ከየት መጣ የማልለዉ ወረረኝ ...እሱ ጋር ያሳለፍኳቸዉ የፍቅር ገጠመኞች ጊዚያቶች ፊቴ ላይ እንደመስተዋት መልሶ ያሳየኛል

  ከዛ እንደዚህ እየተጨናነኩ የምወስነዉ ግራ ገብቶኝ ሁለት ልብ ሁኜ ለካሊድ ደወልኩለት፡፡
  ሰላምታ ከተለዋወጥን ----- ካሊድ እኔን ብታጣኝ የሌላ ብሆን ምን ይፈጠራል ብለህ ታስባለህ ? እኔን አጥተህ ብትኖር ምን ይሰማሀል ??? ብየ ጠየኩት
......ካሊዶ ለካ እንደሌሎቹ ወንዶች አይደለም የመለሰልኝ መልስ አስገራሚ ነበር እንደዚህ አለኝ ... #አንቺን_ማጣት_ምን_እንደሆነ_ነዋል_የኔ_ባትሆን_የሚለዉን_በጭራሽ_ማሰብም_መገመትም_አልፈልግም ፡፡ አንቺ የሌላ ስትሆኝ እንዲህ እሆናለሁ ብየ ምሳሌ እንኳ መስጠት አልፈልግም ... ነዋል እኔን ለመቀለድ ብለሽ እንኳን እንደዚህ አይነት ጥያቄ ዳግመኛ እንዳትጠይቂኝ...አለኝ

ወላሂ ጥፋቱ የኔ ነዉ.... ሶስት አመት በትዕግስት ጠብቆ ከነማንነቴ ተቀብሎኝ...ገና ሚፍታህ አንቺን ነዉ ማግባት የምፈልገዉ ሲለኝ ልቤ ወላዉሎ ካሊድን ይሄን ጥያቄ መጠየቄ ከደወልኩ ቡሀላ ብቻየን አፈርኩኝ..

ዉየ ሳላድር ወዳዉኑ ለሚፍታህ Text ላኩለት ...እንደዚህ አልኩት>>>>> ሚፍታህ ከአሁን ቡሀላ ወደ ሆላ መመለስ አንችልም ትናንት ከትናንትናዉ ጋር አብሮ አልፏል ..በርግጥ የማልዋሸህ በፊት እወድህ ነበር ያደግሞ በጊዜዉ አልፏል ...፡፡ አሁን ላይ መጉዳት የማልፈልገዉ የምወደዉ የሚወደኝ እሱን አጥቼ እሱም እኔን አጥቶ መኖር የማይችል እኔም እሱን አጥቼ መኖር አልችል ሁኜ ልቤ ዉስጥ ያስቀመኩት እሱም ያስቀመጠኝ ሰዉ አለ ብየ ላኩለት......
 

  ሚፍታህ ጋር በዚሁ message አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያየን...አንድ የወንድ ልጅ ድክመት አለች እየወደዱ ማግባት እየፈለጉ የተሻለ አገኛለሁ ብሎ ከኔ ዉጭ አታገባም ትጠብቀኛለች ብለዉ እያሰቡ ነገር ግን እሷን የሚወዳት አግኝታ ልታገባ ስትል ትጠብቀኛለች ብሎ ያሰበዉ እንደ አዲስ ከእንቅልፉ ሲባንን ይስተዋላል፡፡ ታዳ ሚፍታህም አገባሻለሁ ብሎ ሽማግሌ ልኮ አጭቶኝ ጥፋቴን ሳላቀዉ አመታት ያህል ረስቶኝ ነገር ግን ላገባ ነዉ ስለዉ እንደገና በቅናት ተንገብግቦ አንቺን ነዉ የማገባዉ ማለቱ አግባብ አይደለም..ሴትነት የእናት ነት የእህትነት ደረጃ እንጂ የምርጫ የቅርጫ ለትዳር መወዳደሪያ አይደለችምና፡፡



ካሊድ ከ 15 ቀን ቡሀላ ቅዳሜ ሽማግሌ እልካለሁ አለኝ
....እኔም መርሀባ ብየ ተስማማሁኝ፡፡


እነዚህ አስራምስት ቀናት ለሁለታችንም እርቃልብናለች ቀን በቀን በተደዋወልን ቁጥር ይሄ ቀን ቀረን እያልን ሲቀርብ ሲቀርብ ..ሶስትም አልፎ ሁለት ቀናት ቀረን ፡ ነገ ቅዳሜ ሁኖ ዛሬ ጁምአ ላይ ደርሰናል  
......ከዛም ጁምአ ቀን የኔ ፈተና መቼም አይለቅ ...ያልተሳበ ይሆናል ብየ ያልገመትኩት በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል....ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም.....



#ክፍል

ይ...............ቀ.............
..........ጥ...........ላ...............ል

Join
_ ___
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group