Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 18.51K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-11-02 17:34:26 ...... አላጋጠማችሁም.......

ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታል ፣ በተስፋ ይሞሉናል ፣በምኞት እሩቅ ያሳዩናል ፣ምርኩዝ የሆኑ መስለው እጃችንን አጥብቀው ይይዙታል ፣ያን ሰሞን ሆን ብለው ቀድሞ የማናውቀውን አለም ያሳዩናል  ያው ሰው አይደለን እኛም ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ያ አርፎ የተኛ ልባችን ዳግም ይቀሰቀሳል ፡ትናንትናውን ረስቶ አዲስ የሂዎት መንገድ ይጀምርና ፡ አሻግሮ ነገውን  ያልማል፡ አጥብቆ የያዘን እጃቸው የማይለቀን የማይተወን  መስሎን ሙሉ እኛነታችንን እነሱ ላይ እንጥላለን ፡ እነሱን እንደገፋለን .... ያን ጊዜ ድንገት እንደመጡት ድንገት ምስስ ብለው ከሂወታችን ይወጣሉ... ውረድ ብንለው በዋዛ የማይወርድ የትዝታ ጓዝ አሸክመውን ፡ የማይመለስ ጥያቄ ሰጥተውን እንዲህ ነው ብለው እንኳ ምክኒያታቸውን ሳይነግሩን  ድንገት እንደገቡት ድንገት ጥለውን ይወጣሉ ...

ሼን


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
797 views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 10:13:55
318 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 09:50:46
ለርሱ ሳይሆን ለራስህ ብለህ ከጎኑ ቁም!

ውዱ ወንድማችን ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሀመድ(አቡ ሀይደር) በርሱ ዘርፍ እርሱን መሰል በርካቶችን ማፍራት እስካሁን ባይሳካልን እንኳ እንዴት ኡስታዝ አቡሀይደር በሚያደርገው  የደእዋ ስራ ከጎኑ ለመቆም አንነሳሳም?
ኡስታዝ አቡሀይደር የአ ክ✧ፍ✧ሮ✧ት ኃይላት በበረቱበት በየገጠሩ እንደልብ ተንቀሳቅሶ በሚያደርገው ዳዕዋ መኪና ለመግዛት በወንድሞች የተጀመረው ዘመቻ እጅግ ተገቢ ነው።የርሱ ዳዕዋ ተፈልጎ ገጠር ለገጠር በሚጠራበት ጊዜ እርሱ በምስሉ ላይ እንደምታዪት ሆኖም ጭምር ተቸግሮም ይደርሳል። እያንዳንዳችንን የአ✧ክ✧ፍ✧ሮ✭ት ኃይላትን ማደናገሪያ ወክሎ ይመክታል።ሌላው ቢቀር ገጠር ድረስ መግባት የሚችል ለዳዕዋው አስፈላጊ የሆነውን መኪና ለመግዛት እያንዳንዳችን ከጎኑ ልንቆም ይገባል።
ይህን መልዕክቴ የደረሰህ ወንድሜ እንዲሁም እህቴ ሞባይል (ኢንተርኔት)ባንኪንግ አካውንት ካላችሁ ለአቡሀይደር ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ አሁኑ የየድርሻችሁን አስገቡ።ሞባይል ባንክ የሌላችሁም ሳትዘገዩ ነገውኑ የየድርሻችሁን አስገቡ።

አላህ አቅሙን የሰጣችሁ አቡሀይደር ይሉኝታ የሚያጠቃው ሰው ስለሆነ በአካል ገፍታችሁ በመቅረብ የርሱ የዳዕዋ ዘርፍ የሚጠናከርበት መንገድ ላይ ማገዝ ስለምትችሉበት ሁኔታ ሀሳብ ተለዋወጡ።ምከሩ።ሌሎቻችሁ በሉ ወደሞባይል ባንኪንግ አካውንታችሁ አሁኑኑ ግቡ።ይኸው የኡስታዝ አቡሀይደር የባንክ አካውንት: —

አካውንት ስም = SADIK MOHAMMED AHMED

1) የሂጅራ ባንክ አካውንት ቁጥር:- 1001162290001

2) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA): - 1000329226712

3) አቢሲኒያ ባንክ(ABYSSINIA BANK)
83047178

እኔም የቻልኩትን አስገብቻለሁ እናተም አስገቡ ስሙ የተሰረዘዉ የራሴ ምክንያት ነዉ
362 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 09:17:18 መቼም የማትረሳውን የህይወት ትምህርት የምትማረው ከትልቁ ስህተትህ ነው፤ ብዙም አትናደድ በቀሪው ዘመንህ እንዳትረሳው የተፈለገ ወሳኝ መልዕክት ደርሶሀል  ስለዚህ ሁለት ነገር አድርግ
1. አትድገመው
2. ተማርበት

ህይወትን በጥበብ የሚኖር ሰው ከዚህ የተለየ ምንም አያደርግም።

─━━━━ ⊱✿⊰ ━━━━━─


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
847 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 09:14:54 " አንዳንዴ……………………………………

አንዳንዴ ነገሮች ከመወሳሰባቸው የተነሳ መግለፅ እስከሚከብድ ድረስ ቃል ይጠፋል ። የሚመጣው ፣ የሚሄደውና የሚቀረው በመሰለው መልኩ ሀሳቡን ይፈተፍታል ። አንዳንዴ በመኖራቸው ብቻ ደስተኛ የሚያደርጉን ሰዎች አሉ ። ብዙ ፍራፍሬዎች ቢኖሩ አንዷን ፍሬ በተለየ መልኩ ለኛ ጣፋጭ ትሆናለች ። ያቺ ፍሬ ግን ጥፍጥናዋን አታውቅም ። አንዳንዴ ልብ ገና በእንጭጩ ይሸብታል ፣ በቧልት ፣ በቅስም ሰባሪ ንግግሮች ለጥሩ ነገር መበርታት ተስኖት ያረጃል ። ያን የሸበተ ልብ ከሽበቱ መሀል ውበቱ የሚታየው ሌላ ልብ ስለመኖሩ አያስተውልም ። አንዳንዴ ሰው መሆን ክብሩ ይወርዳል ፣ ፣ መኖር ከሞት ያንሳል ፣ እስትንፋስ ይከረፋል ። አንዳንዴ ሰው መሆን ከግዑዝ በታች ይሆናል ። ግዑዛን ግን ሰው መሆን ባለመቻላቸው መለጎማቸውን ባለ አንደበቱ አይረዳም ። አንዳንዴ በጨዋ ማልያ ባለጌ ሲያገባ የልክነት ሚዛን መጠኑ ይዛባል ። በጥሩና በመጥፎ መሀል አለመገኘት ፣ ከሁለት አንዳቸው አለመሆን ይከሰታል ። አንዳንዴ ሰው ሆነው ሰው መፍራት ይገጥማል ፣ ብቸኛ ከመሆን በላይ ከሰው ጋር መሆን ያስፈራል ። አንዳንዴ ቁራጭ ፍቅር የሚወረውር ጠፍቶ በብቸኝነት ረሀብ አብሮነትን መለመን ይለመዳል ። አንዳንዴ ተስፋ ከማጣት በላይ ተስፋ ማጣትን ማሰብ ያሳምማል ። አንዳንዴ እድለኛ ያልሆኑ ሰዎች እድለኛ አደላቹም ብለው በንግግራቸው እድለቢስነታቸውን ያቀብሉናል ። ነገር ግን እድለኛ ስለመሆናችን ማሰብ ያቃተን ንግግራቸውና የነደፈን መርዛቸው መሆኑን አናምንም ። አንዳንዴ የመከራ መዓት የተሸከምን ፣ አቅመ ቢስ እንደሆንን ፣ መኖራችን ፋይዳ እንደሌለው ይሰማንና ትክክል ነው ብለን አምነን ቀናችንን ማስጌጥም ማጠልሸትም የሚችለው እኛነታችን እየገደልነውና አሰልቺውን ጎዳና እያደላደልን ለመጓዝ እየተዘጋጀን መሆናችንን ረስተን ሰበብ አምላኪ እንሆናለን ። አንዳንዴ የደስታችን ምንጭ እራሳችን መሆናችንን ዘንግተን መደሰትንም እንፈራለን ። አንዳንዴ ሰብዓዊነታችንን ደብቀን ፣  ክብራችንን አዋርደን በሰዎች ዘንድ ክብራችንን እንፈልጋለን ።አንዳንዴ ትካዜዎች ትዝታ ይሆናሉ አልፈው ይታወሳሉ ። አንዳንዴ በሰማይ ላይ ጨረቃና ከዋክብት እየደመቁ ፣ ከደመቁበት ሰማይ በበለጠ ይደነቃሉ ። አንዳንዴ ፀሀይ ትናፈቅና ስትበረታ ትሰለቻለች ። አንዳንዴ……………………………………………………………………………………………………………… ከብዙ ንክሻ በኋላ መሻር ፣ ከብዙ ንድፊያ በኋላ ማገገም ፣ ከበሽታ በኋላ ፈውስ ፣ ከብዙ ጨለማ በኋላ ንጋት ፣ ከጦርነት በኋላ ሰላም ፣ ከማጣት በኋላ ማግኘት ፣ ከመሀይምነት በኋላ እውቀት ፣ ከሴት በላይ እናት ፣ ከወንድ በላይ አባት ፣ ከበደል በኋላ ፍትህ ፣ ከጥላቻ በላይ ፍቅር ፣ ከሁሉም ነገሮች በላይ የሁሉም የበላይ ፈጣሪ አለ ። ከብዙ…………………………………………እጅግ ከብዙ ነገሮች በኋላ ጥሩ ነገሮች አሉ ። ነገር ግን ወደፊት ጥሩ ነገሮች ስለመኖራቸው የተጠራጠሩ በጥርጣሬያቸው ወድቀው የሚጠሉትን ወደውና ፈቅደው ለሚጠሉት ተገዝተው ይኖራሉ ። "
     የጉዞ ማስታወሻዬ(@ቶፊቅ)

Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
914 viewsedited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 11:46:35
የልጅነት ትዉስታዎች ስልክ ባልነበረበት ዘመን የምንዝናናበት የክበበዉ ቀዳ ቀልድ ጀባ ብያለሁ


ቡጥቡጥ..ፀቡ ወደ ግድግዳ ዙሮ መተኛት ነዉ


ጋበዝኳችሁ ደስ የሚል የልጅነት ትዉስታ


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.4K viewsedited  08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ