Get Mystery Box with random crypto!

...... አላጋጠማችሁም....... ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱ | ISLAMIC SCHOOL

...... አላጋጠማችሁም.......

ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታል ፣ በተስፋ ይሞሉናል ፣በምኞት እሩቅ ያሳዩናል ፣ምርኩዝ የሆኑ መስለው እጃችንን አጥብቀው ይይዙታል ፣ያን ሰሞን ሆን ብለው ቀድሞ የማናውቀውን አለም ያሳዩናል  ያው ሰው አይደለን እኛም ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ያ አርፎ የተኛ ልባችን ዳግም ይቀሰቀሳል ፡ትናንትናውን ረስቶ አዲስ የሂዎት መንገድ ይጀምርና ፡ አሻግሮ ነገውን  ያልማል፡ አጥብቆ የያዘን እጃቸው የማይለቀን የማይተወን  መስሎን ሙሉ እኛነታችንን እነሱ ላይ እንጥላለን ፡ እነሱን እንደገፋለን .... ያን ጊዜ ድንገት እንደመጡት ድንገት ምስስ ብለው ከሂወታችን ይወጣሉ... ውረድ ብንለው በዋዛ የማይወርድ የትዝታ ጓዝ አሸክመውን ፡ የማይመለስ ጥያቄ ሰጥተውን እንዲህ ነው ብለው እንኳ ምክኒያታቸውን ሳይነግሩን  ድንገት እንደገቡት ድንገት ጥለውን ይወጣሉ ...

ሼን


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group