Get Mystery Box with random crypto!

Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @horn_african_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.70K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-08-12 07:42:32 #ደምቢ_ዶሎ

• " በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ

• " እንዲህ አይነት ክስተት የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው " - ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ማስተማሪያ ሆስፒታል 2 ጭንቅላት ያለው ህፃን ተወለደ።

የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ በሰጡት ማብራሪያ ህፃኑ ሁለት ጭንቅላት ኖሮት መወለዱን ተናግረዋል።

ዶ/ር ፀጋዬ ፤ በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለፅም ህፃኑ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወለዱን አስረድተዋል።

በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ እና በእናቶች ማህፀን ውስጥ በሚስተናገዱ እንቁላሎች ብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ አብራርተዋል።

በኢኒስቲትዩቱ የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ በበኩላቸው ክስተቱ በመንታ ምድብ የሚመደብ እና የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ እናትም ሕፃኑም #በጥሩ_ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
Tikvah
514 viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 16:32:16 የጉራጌ ዞንን በክላስተር ለመደራጀት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ተደረገ

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ፤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጓል።

በደቡብ ክልሉ በተለምዶ የማዕከላዊ ዞን የሚባሉት የሃድያ ፣ የከንባታ ፣ የሀላባ ፣ የሥልጤና የጉራጌ ዞኖች በአንድ ክልልነት እንዲደራጁ ውሳኔ ቢቀርብም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት እስካሁን ውሳኔ ሳያሳልፍ ቆይቷል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤው የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ሥር ከሚገኙ ሌሎች አራት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በ 52 የምክር ቤቱ አባላት ተቃዉሞ እና በ 40 ድጋፍ ውድቅ ማድረጉም ታውቋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በፊት ወስኖት የነበረውን የጉራጌ በክልልነት የመደራጀት ውሳኔን አፅንቷል::

የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎም በወልቂጤ ከተማም ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እየገለጸ እንደሚገኝም ታውቋል።
476 viewsedited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:29:36
አቶ ጀዋር ተመልሰዋል!!

ላለፉት ሁለት ወራት በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ አባልና ደጋፊዎቻቸውን ሲያነጋግሩ የከረሙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጀዋር መሐመድ ተልዕኳቸውን አጠናቀው ወደሀገራቸው መመለሳቸውን ፓርቲው አሳውቋል።
አቶ ጀዋር ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ይህ የመጀመሪያ ጉዞአቸው ነበር።
Fidel post
655 views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:26:47
628 views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:25:45 የሕዳሴ ግድበ 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።
599 views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:44:45
ቻይና፤ አሜሪካ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን ገለጸች ፤ አሜሪካ ከዚህ በኋላ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ዋሸንግተን በቻይና ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች እንደማይታገስ ገልጿል፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ዛሬ በመግለጫቸው አሜሪካ፤ ቻይናን ለመያዝ ታይዋንን ከመጠቀም እንድትቆጠብ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
645 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:39:05
እስክንድር ነጋ ከባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንትነትና አባልነት መልቀቃቸውን አስታወቁ!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በመንግስት ጫና ምክንያት በፓርቲ አመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።ፓርቲው ለአዲስ ዘይቤ በላከው እና በእስክንድር ነጋ ፊርማ የተረጋገጠው ደብዳቤ ላይ እንደሰፈረው “ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” ብለዋል።

እስክንድር ነጋ “ካሉበት ለፓርቲው ፅፈውታል” በተባለው ደብዳቤ ሌላ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አላሰፈሩም። ይሁን እንጂ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ አባላት እና አመራሮች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አምሃ ዳኘው ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።በመጨረሻም ፓርቲው ያካሄደዋል ተብሎ ለሚጠበቀው ጠቅላላ ጉባኤ ስኬት ያላቸውን ምኞት በደብዳቤው ገልፀዋል።
639 views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 07:37:10 የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት
የኢትዮጵያ መንግስት የሕዳሴ ግድብን የውኃ ሙሌት ዛሬን ጨምሮ ከሰሞኑ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በግድቡ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ሰራተኞች ውኃ ሙሌት ስራው መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
ይሁንና እስካሁን ሙሌቱን በተመለከተ በይፋ የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራሪያ የለም፡፡
669 views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:18:11
" የክልል እንሁን ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ መልኩ ሊፈቱ ይገባል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ የ " ክልል እንሁን " ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ መልኩ ሊፈቱ እንደሚገባ አሳስቧል።

ፓርቲው የክልልነት ጥያቄን በተመለከተ የሀገሪቱን ተጨባጭ ኹኔታና የሕዝቡን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦች ጠቁሟል።

የመፍትሄ ሀሳቦች ፦

1. የሀገሪቱ አብዛኛው ችግር የሚመነጨው ከሕገ መንግሥቱ " የክልል አወቃቀር " ጋር በተያያዘ መሆኑ ታውቆ ከጊዜያዊ መፍትሔ ይልቅ ዘለቄታዊ መፍትሔና የችግሩ ምንጭ ላይ ያተኮረ አፋጣኝ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ጠይቋል።

2. በአሁኑ ሰዐት የክልልነት ጥያቄ እየጠየቁ ላሉ የማኅበረሰባችን ክፍሎች መንግሥት የኃይል አማራጭን ከመከተል ይልቅ ከሕዝቡ ጋር በቅርበት በመነጋገርና በመግባባት ብቻ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እንዲያደርግ አሳስቧል።

3. ሰላም ወዳድ የሆነው ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች እጅግ #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ውጤት ላይ መድረስ እንጂ አላስፈላጊ መሥዋዕትነት ከሚያመጡ ድርጊቶች እንዲቆጠብ ጥሪ አስተላልፏል።
734 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:12:27
አቡብከር ናስር ከተጠባባቂ ወንበር ላይ ነው::
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከ ቲኤስ ጋላክሲ::
ጨዋታውምሽት 2:30 SuperSport 224 ላሊጋ ቻናል ላይ በቀጥታ ይተላለፋል:: From Aweke Abreham
660 viewsedited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ