2023-03-20 16:39:59
ውድ የሚዲያችን ቤተሰቦች ዛሬ ከባድ የዘረፋ ወንጀል ተፈጽሞብናል
ዘረፋው በ ETHIO 251 MEDIA እና Arat Kilo
ሚዲያ ላይ ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ለዛሬ ለሰኞ አጥቢያ የተፈጸመ ሲሆን አራት ዘመናዊ ካሜራዎችን ጨምሮ ሌሎች የቀረጻና የፕሮዳክሽን መሣሪያዎችን ተዘርፈናል።
ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት የተዘረፉት ንብረቶቻችን አራት ዘመናዊ ካሜራዎች፣ ኔክማይክ፣ ዙመር እና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶች ሲሆኑ ግምታዊ ዋጋቸው 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ይደርሳል።
ቁሳቁሶቹ ኢትዮ 251 እና አራት ኪሎ ሚዲያን ጨምሮ ነገረ ወልቃይት ጭምር የሚገለገሉባቸው ነበሩ።
ኢትዮ 251፣ አራት ኪሎ ሚዲያ እና ነገረ ወልቃይት ወቅታዊ ሃገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በመዘገብና ጥልቅ ትንታኔዎችን በመስጠት ከሚታወቁ ቀዳሚ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መካከል መሆናቸው ይታወቃል።
832 views13:39