Get Mystery Box with random crypto!

Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @horn_african_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.70K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-09-01 11:24:43 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሐረሪ ክልል መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በሐረሪ ክልል መጀመሩን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ፤ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መቀጠል ይችላሉም ተብሏል።

በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ፤ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጿል።

አዲስ ማለዳ &YeneTube
1.1K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:24:18
አዲስ አበባ

ቤተል አካባቢ አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ አጋጥሟል

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት በተለምዶ ስያሜው ቤተል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የኘላስቲክ መጋዘን በሆነ ህንጻ ላይ ከባድ የእሳት አደጋ ማጋጠሙ ተነግሯል፡፡

እሳቱን እስከአሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም አደጋዉን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
1.1K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:09:17 የፌደራል መንግስት በአውደ ውጊያ ባሉ አዳዲስ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰጠውን መግለጫ እናደርሳለን
319 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:18:35
የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ከፍተዋል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስታት ዛሬ ያሉት ነገር የለም።
533 viewsedited  05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 17:07:02
ሰበር መረጃ

ትናንት በህውሃት ወረራ የተፈፀመባቸው የደቡብ ቆቦ አካባቢዎች ሮቢትን ጨምሮ ዛሬ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ እየመጣ የነበረው ወራሪ ሃይል በመከላከያ፣ልዩ ሃይሉ እና ፋኖ በተወሰደበት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ፊቱ አዞሮ ቆቦን ለቆ ወደ አላማጣ በመውጣት ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።በግዳን በኩል ጠዋት 4:30 ሙከራ ቢያደርግም ተመቶ መመለሱን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
wasu Mohammed
1.2K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 11:02:57 ከአብን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቄን ስለማሳወቅ፤
/ክርስቲያን ታደለ/
*
የምወዳችሁ የአብን አባላትና ደጋፊዎች ይህን እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ባለመናገሬ እጅጉን አዝናለሁ። ይሁንና ጉዳዩን ከዚህ በላይ ማዘግየት ንቅናቄያችን የተሟላ ሁለንተናዊ ሪፎርም እንዳያደርግ እንቅፋት ስለሚፈጥር እና በለውጥ ፈላጊ ብርቱ አባላትና ደጋፊዎቻችን ዘንድ የተሰነቀውን በጎ ተስፋ ጨርሶ እንዳያጨልም ስጋት ስላደረብኝ ዛሬ የግድ ኃቁን መናገር ይኖርብኛል።

በተጨባጭ ከግንቦት 1፣ 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንደሥራ አስፈፃሚ ተወስነው መሰራት የነበረባቸው ጉዳዮች ለውጥ ፈር በሆኑ ጥቂት ግለሰቦች ምክንያት ከስነስርዓት ውጭ እየተወሰኑ በመሆኑ የእኔ በስም ብቻ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተብሎ መቀጠል ትክክል አለመሆኑን ተረድቻለሁ። የቤት ኅመማችንን በቤት ተነጋግረን እንቀርፋለን በሚል በዝምታ መቆየቴም በየደረጃው ባሉ የመዋቅራችን አባላትና አመራሮች ዘንድም ለምን ኃቁን አትነግረንም የሚል ወቀሳ አድርሶብኛል። ለተቋም ማዕከላዊነትና ወንድማማችነት እሴት በሚል በዝምታ መቆየቴ ድርጅቱን ከማዳን ይልቅ እንዲፈርስ የመተባበር ያህል በመሆኑ እያደር ስጋት ፈጥሮብኛል።

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸው ሁኔታዎች ተደማምረውበት በተለይም የለውጡ ሂደት የመደናቀፍ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ፤ መላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎችም ይኸንኑ ተገንዝባችሁ፥ አብንን እንደድርጅት ለማስቀጠልና የሚጠበቅበትን ትግል በማድረግ የቆመላቸውን የፖለቲካ ግቦች ያሳካ ዘንድ፥ የሚቻላችሁን በጎ ሚና እንድትወጡም ጥሪዬን አቀርባለሁ። እንደአብንን መስራች፣ ፓርቲውን ወክሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል እንደሆነ ኃላፊነት እንደሚሰማው ግለሰብ እና እንደ አንድ አማራ ንቅናቄያችንን ወደ ቀደመ ሥፍራውና ትክክለኛው የትግል መስመር ለመመለስ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ አንዳችስ እንኳን የምቆጥበው ነገር እንደማይኖረኝም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫዎችንም የምንሰጥ ይሆናል።
564 views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 02:22:38 Funy News

በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ላይ ሆኖ በአጋጣሚ ብልቱን ቆረጠ

በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ላይ እያለ በአጋጣሚ የወንድ የዘር ፍሬውን በከፊል ቆርጦ ብልቱ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል፡፡ኮፊ አታ የተባለዉ ግለሰብ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል።

የ47 አመቱ ግለሰብ ከደረሰበት ጉዳት ለመታደግ ለቀዶ ህክምና ገንዘብ እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡አታ ከሆስፒታል ሆኖ አደጋው እንዴት ተከሰተ ሲናገር ወንበሬ ላይ ተቀምጬ አሸለብኩኝ፤ በእንቅልፍ ልቤ ከፊቴ ሥጋ እየቆረጥኩ እንደሆነ አየሁ።"ቢላውን እንዴት እንዳነሳሁ አላስታውስም"ሲል አክሏል፡፡

በእንቅልፍ ልቡ ሆኖ ሲጮህ የደረሱለት ጎረቤቶቹ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን ሆኖ ከፍተኛ ደም ሲፈሰዉ እንደደረሱለት መናገሩን ጠቅሶ ሸገር ፕሬስ አስነብቧል::
Wasu
375 views23:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:59:31 የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የመንግሥት ኃይሎች በተለያዩ ግንባሮች በትግራይ ኃይሎች ላይ ትንኮሳ ፈፅመዋል በማለት በትዊተር ገጻቸው ከሰዋል። ፌደራል መንግሥቱ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎት የለውም ሲሉ የከሰሱት ጌታቸው፣ መንግሥት አቋቋምኩት ያለው ዐቢይ የሰላም ኮሚቴ ዛሬ ያወጣው መግለጫ ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት እና ጊዜ ለመግዛት ያለመ ነው ብለዋል። ጌታቸው የመንግሥት ኃይሎች መቼ እና በየትኞቹ ግንባሮች ትንኮሳ እየፈጸሙ እንደሆነ ለይተው አልጠቀሱም።
748 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:27:04
ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የግብጽ ብሔራዊ ባንክ ገዢን አማካሪያቸው አድርገው ሾሙ የግብጽ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡

ጣሪቅ አመር በራሳቸው በፕሬዝዳንት አል ሲሲ ነው አማካሪ ሆነው የተሾሙት፡፡ጣሪቅ አመር ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ነው በብሔራዊ ባንክ ገዢነት ሃገራቸውን ያገለገሉት፡፡በሃገሪቱ ህግ መሰረት አንድ የባንክ ገዢ ለአራት ዓመታት እንዲያገለግል የሚሾም ሲሆን ለሁለት የገዢነት ዘመናት ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡

የመጀመሪያዎቹን አራት ዓመታት በ2019 ያጠናቀቁት አመርም በ2020 ጥር ላይ በድጋሚ ተሾመው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡ ሆኖም አሁን የገዢነት ዘመናቸው መጠናቀቂያ ገና ሳይቃረብ ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው፤ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡
779 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:25:58
እስራዔል እና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

እስራዔል እና ቱርክ ያቋረጡትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ መሥማማታቸው ተገለጸ፡፡ የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ የየሀገራቱ አምባሳደሮች እና ቆንስላ ጀነራሎች ወደ ቀድሞ መደበኛ ሥራቸው ይመለሳሉ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
698 views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ