Get Mystery Box with random crypto!

Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @horn_african_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.70K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-08-10 20:11:12
አሜሪካዊቷ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሀገራት “ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር አለ” ማለታቸው እያነጋገረ ነው
ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ አስጠንቅቀዋል።
644 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:10:28
1ሺህ 19 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺህ 19 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
579 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:09:21
563 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:08:53 በመርሻ ጥሩነህ አዲስ ማለዳ ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ በዚህ ስዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው እንዳይገቡ በመንግሥት ታግደዋል

ዕረቡ ነሐሴ 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከተለያዩ የሰሜን ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ ከጥዋት ጀምሮ መንገድ ተዘግቶባቸው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አሽከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው ሲንገላቱ አዲስ ማለዳ በቦታው ተገኝታ ተመልክታለች።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው አሽከርካሪዎች ከአንድ ወር ወዲህ ተሳፋሪ ጭነው ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ብሔርን መሰረት ያደረግ ክልከላና ድብደባ እየተፈጸመብን ነው ብለዋል።

ዛሬ ማለዳ ደብረ ብርሃን ላይ የተዘጋው መስመር በወጣቶች ነው ቢባልም፣ የታጠቁ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አካላት ተሽከርካሪዎች እንዳያልፋ በመስመር ዘግተው ሲጠብቁ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

አዲስ ማለዳ ያነጋገርናቸው የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊዎችን እንዲጉላሉ ምክንያት የሆነው የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ናቸው ብለዋል። አሽከርካሪዎች በበኩላቸው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ተሳፋሪዎቻችን በብሔር ተለይተው ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ከመደረጋቸው በተጨማሪ፣ ድብደባና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

የኦሮሚያ ክልል (ኦ ሮ) ታርጋ ያላቸው ተሽከርካሪዎች በነጻነት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ነበር የሚሉት አሽከርካሪዎች፣ በአንጻሩ የአማራ ክልል (አ ማ) ታርጋ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ከ500 እሰከ 1,000 ብር ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል ለመክፈል ይገደዳሉ ተብሏል።

ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስም ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው ቆመው እንደሚገኙም አዲስ ማለዳ ለመመልከት ችላለች።
598 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:58:29
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሕዝቡ ኤሌክትሪክን እንዲቆጥብ አሳሰቡ

የግብፅ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ፍጆታውን እንዲቆጥብ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ ማድቡሊ፤ የግብፅ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይልን መጠቀም ያለበት በጥንቃቄ እና በቁጠባ ነው ብለዋል።
ለህዝቡ የቀረበው ጥሪም የጋዝ ፍጆታን ለመቆጠብ የሚያገለግል እንደሆነም ተገልጿል። ሀገሪቱ ይህንን ያደረገችው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላጋጠማትና ይህንንም ለመፍታት እንደሆነም ተገልጿል።
ግብፅ አሁን ላይ ለሕዝቧ ይህንን ጥሪ ያቀረበችው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አጋጥሟት ነው ተብሏል።
ይህንን ችግር የመፍቻ መፍትሄው ኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ መቀነስና ጋዝን ወደ ውጭ መላክ ነውም ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ ማድቡሊ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመንግሥት ተቋማት ላይ ጠበቅ ያለ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ህግ ይተገበራል ብለዋል። በዚህም መሠረት የመንግስት ተቋማት እና የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች
ከስራ ሰዓት በኋላ መብራት እንዲያጠፋ ታዘዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ በመንግሥት ተቋማት ከስራ በኋላ ኤሌክትሪክ እንደሚቋረጥ ተናግረዋል። ከዚህ በኋላ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ከስራ በኋላ መብራት የሚበራው አስፈላጊ ለሆኑ ስራዎች ብቻ ነውም ብለዋል። በመንግሥት ህንጻዎች ላይ ከውጭ ይበሩ የነበሩትም ጭምር እንዲጠፉ ይደረጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ኤሌክትሪክን የመቆጠብ ስራው መጀመሩንና በታህሪር አደባባይ ተግባሩ መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።
703 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:49:53
642 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:49:45 አ.ብ.ን ያጋጠመውን ችግር በውስጥ ለመፍታት ቢሞክርም እንዳልቻለ ተነገረ

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አ.ብ.ን) ያጋጠመውን ችግር በውስጥ ለመፍታት ቢሞክርም እንዳልቻለ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ የሱፍ ኢብራሂም አስታወቁ፡፡

አቶ የሱፍ ፓርቲው ሊያካሂደው ያሰበውን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹‹ … አብን የሚያካሂደውን የሪፎርም ሂደት ባስቸኳይ ግልጽ፣ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ ማድረግ አለበት … በተለይ ከመነሻው የሪፎርም ጥያቄ ያቀረቡ አባላቱን በመግፋትና በማግለል በምትካቸው ተቀባይ ስብስብ ለመፍጠር የሚደረግ ሙከራ ትክክል አይደለም … ይህ የህዝብ ተቋም ጉዳይ ስለሆነ ልክ እንደግለሰብ ሰርግ የተወሰኑ ባለሟሎች በድብቅ ብቻ መክረው የሚቋጩት ጉዳይ አይሆንም … ችግሩን በቀላሉ በውስጥ ለመፍታት ብንሞክርም አልተቻለም›› ብለዋል።

የፓርቲው ዋነኛ ችግር ከፖለቲካ መስመር ጋር የተገናኘ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ የሱፍ፤ ችግሩ ሳይፈታ መቆየቱንና ተባብሶ መቀጠሉንም ገልፀዋል፡፡

አቶ የሱፍ፣ ሰፊ አባላቱን ለድጋፍና ለመዋጮ ብቻ የሚፈልግ ነገር ግን የሃሳብ ልዩነቶችን የሚፈርጅና የማያስተናግድ ተቋም በህዝብ ላይ ተጨማሪ እዳ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ሊኖረው እንደማይችል አመልክተው፤ ‹‹ለአመታት በየቀጠናው ስንባዝን የኖርነው ለህዝባችን መብትና ክብር ብለን ነው። ህይወታችንን አደጋ ላይ ጥለንና በፕላስቲክ ድንኳን ውስጥ እያደርን የታገልነው ለዋዛ ፈዛዛ አይደለም! በየሚዲያው በር ስንኳትን የከረምነውም የዝና ፍለጋ ተግባር ለማከናወን አይደለም›› ብለዋል፡፡

ሌላው የአብን አመራር ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም በበኩላቸው፤ አብን ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ ‹‹ድምፁን አጥፍቶ ሽር ጉድ እያለ›› እንደሆነ ገልጸው፣ ‹‹በያቅጣጫው የሚሰማው የጉባኤ ዝግጅት ድራማ አስቂኝም፣ አሳፋሪም፣ አስጊም ነው›› ብለዋል።
646 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 16:49:01
አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ጋር ተወያዩ

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል አርማንድ ሃመር ከኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ሐመር ኢትዮጵያውያን ጥቅሞቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ዘላቂ የችግር መፍትሄዎችን ለመፈለግ ባሳዩት የጋራ ቁርጠኛነት መበረታታቸውን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በትዊተር ገፁ አስታውቋል፡፡
አምባሳደር ሐመር ሰሞኑን ከአምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውም ይታወሳል፡፡
299 viewsedited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 16:10:42
375 views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 14:38:17
471 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ