Get Mystery Box with random crypto!

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሕዝቡ ኤሌክትሪክን እንዲቆጥብ አሳሰቡ የግብፅ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ፍጆ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሕዝቡ ኤሌክትሪክን እንዲቆጥብ አሳሰቡ

የግብፅ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ፍጆታውን እንዲቆጥብ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ ማድቡሊ፤ የግብፅ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይልን መጠቀም ያለበት በጥንቃቄ እና በቁጠባ ነው ብለዋል።
ለህዝቡ የቀረበው ጥሪም የጋዝ ፍጆታን ለመቆጠብ የሚያገለግል እንደሆነም ተገልጿል። ሀገሪቱ ይህንን ያደረገችው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላጋጠማትና ይህንንም ለመፍታት እንደሆነም ተገልጿል።
ግብፅ አሁን ላይ ለሕዝቧ ይህንን ጥሪ ያቀረበችው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አጋጥሟት ነው ተብሏል።
ይህንን ችግር የመፍቻ መፍትሄው ኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ መቀነስና ጋዝን ወደ ውጭ መላክ ነውም ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ ማድቡሊ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመንግሥት ተቋማት ላይ ጠበቅ ያለ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ህግ ይተገበራል ብለዋል። በዚህም መሠረት የመንግስት ተቋማት እና የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች
ከስራ ሰዓት በኋላ መብራት እንዲያጠፋ ታዘዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ በመንግሥት ተቋማት ከስራ በኋላ ኤሌክትሪክ እንደሚቋረጥ ተናግረዋል። ከዚህ በኋላ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ከስራ በኋላ መብራት የሚበራው አስፈላጊ ለሆኑ ስራዎች ብቻ ነውም ብለዋል። በመንግሥት ህንጻዎች ላይ ከውጭ ይበሩ የነበሩትም ጭምር እንዲጠፉ ይደረጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ኤሌክትሪክን የመቆጠብ ስራው መጀመሩንና በታህሪር አደባባይ ተግባሩ መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።