Get Mystery Box with random crypto!

Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ horn_african_news — Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @horn_african_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.70K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-08-17 19:25:24
ፑቲን የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት “ቀጠናውን ለማተራመስ ያለመ ነው” አሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ “በቻይናዋ ታይዋን ግዛት” ያደረጉት ጉብኝት "የአንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ፖለቲከኞች ጉዞ ብቻ ሳይሆን አላማ ያለው እና አሜሪካ በቀጣናውም ሆነ በዓለም አለመረጋጋትን ለመፍጠር እና ትርምስ ለመዝራት የሄደችበት የተጠና ስትራቴጂ ነው" ሲሉ ተናገሩ።

ፑቲን ይህን ያሉት ቻይና፣ ሩሲያ እና ኢራንን ጨምሮ 12 ሀገራት እየተሳተፉበት ባለውና ከነሃሴ 13 አስከ 27 ቀን በሚቆየው የ2022 ዓለም ጦር ሰራዊት የልምምድ መድረክ ላይ ነው።
673 views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 17:51:14 የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ መግለጫ:
ወደተኩስ አቁም ስምምነት ሲገባ በሚፈጠረው አስቻይ ሁኔታ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በተቻለ ፍጥነት መልሶ ማቅረብ ይቻል ዘንድ፣ አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን፤
የአፍሪካ ህብረትም የሰላም ንግግሩ በአስቸኳይ ተጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ዘንድ፣ የሰላም ንግግሩ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ በፍጠነት ወሰኖ ንግግሩ እንዲጀመር፣ ይህን ማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ ገምግሟል።
673 viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 17:26:29
መንግስት ከህወሃት ጋር አደርገዋለሁ ያለው ድርድር የሚካሄድበትን ቦታ ለመወሰን ከአፍሪካ ህብረት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አስታወቀየኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሃት ጋር አካሂደዋለሁ ያለው የሰላም ንግግሩ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ ለመወሰን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

መንግስት “አሸባሪ” ብሎ ከፈረጀው ህወሃት ጋር የሰላም ንግግር እንደሚያደርግ ቀደም ብሎ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ለዚህ የሚሆን ቡድንም ማቋቋሙን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
690 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 18:11:26
ወሰን ማካለል

በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለል ስራ መጠናቀቁን በተመለከተ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተደረሰው ስምምነት እና ውሳኔ " ታሪካዊ እና ዘመን ተሻጋሪ ነው " በማለት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡ ኮንዶሚኒየሞች ለአብነት
ኮየፈጨ፤
ቱሉዲምቱ በከፊልና
ጀሞ ቁጥር ሁለት የሚገኙበትን ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን ተካለዋል ብለዋል።

ኦሮምያ ክልል የገነባው የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ ከፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞች ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለሉ በማድረግ ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል።

ከዚያ ውጪ ሁሉም ባለበት ቦታ እንዲያስተዳድር ስምምነት ላይ መደረሱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

የአስተዳደር ወሰን በሚነካባቸው አካባቢዎች፦
የትኛውም አይነት መንግስታዊ አገልግሎት እንደማይቋረጥ፤
- የአገልግሎትና የፀጥታ ስራዎች በሁለቱም ወገን በጋራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰራ ፤
- በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንደማይቆሙ፤
- የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት እንደሚቀጥል፤
- የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች ላይ ቋንቋ ምንም አይነት ተፅእኖ እንዳያሳርፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
525 views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:53:34
የጉራጌ ዞን፤ የክላስተር አደረጃጀት የተቃወመበትን ውሳኔ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ማስገባቱን አስታወቀ
የጉራጌ ዞንቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የክላስተር አደረጃጀት በአብላጫ ድምጽ ተቃውሟልየወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ጉባዔዎችን በተመለከተ የዞኑ አመራሮች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል

የጉራጌ ዞን፤ የዞኑ ምክር ቤቱን ከሰሞኑ ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ያሳለፈውን ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማስገባቱን አስታወቀ፡፡

የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ ዛሬ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የምክር ቤቱ ውሳኔና ተያያዥ ሰነዶች ለኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡
707 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:28:26
በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ምክትል ፕሬዝደንቱ ዊልያም ሩቶ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አሁን አስታውቋል።

ሩቶ ያሸነፉት ከተሰጠው ጠቅላላ ድምፅ 50.49% በማግኘት ሲሆን ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ራይላ ኦዲንጋ 48.8% ድምፅ አግኝተዋል።

የ77 አመቱ ራይላ ኦዲንጋ ካለ ስኬት ለፕሬዝደንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለአምስተኛ ግዜያቸው ነበር፣ ይህ የመጨረሻቸው ነው ተብሏል።

ከአሁኑ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብተው የነበሩት ምክትል ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ደግሞ በመጀመርያው የፕሬዝደንትነት የምርጫ ፉክክራቸው አሸናፊ ሆነዋል።
705 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 11:37:32
በቅርቡ ከዩኒቨርሳል ሚውዚክ ግሩፕ ጋር የተፈራረመውና "ስድስት" የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ያደረሰው ሙዚቀኛ ሮፍናን በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተገናኝቶ በስራው ዙሪያ መምከሩን ኢንባሲው ገልጿል::
733 views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:46:33
አለም ዋንጫው የቀን ለውጥ ተደረገበት !

የ 2022 የኳታሩ አለም ዋንጫ ከጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ ሲካሄድ በመክፈቻ መርሐ ግብር ቀናት ላይ ማሻሽያ መደረጉ ይፋ ሆኗል ።

አስተናጋጇ ሀገር ኳታር በመክፈቻው ጨዋታ መርሐ ግብሯን ማካሄድ እንዳለባት ታውቆ ውድድሩ በአንድ ቀን ቀድሞ ሊጀመር መሆኑ ይፋ ሆኗል ።
554 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:43:43
የዓባይ አሁናዊ ፎቶ
560 views04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:42:55
499 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ