Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ምክትል ፕሬዝደንቱ ዊልያም ሩቶ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ምክትል ፕሬዝደንቱ ዊልያም ሩቶ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አሁን አስታውቋል።

ሩቶ ያሸነፉት ከተሰጠው ጠቅላላ ድምፅ 50.49% በማግኘት ሲሆን ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ራይላ ኦዲንጋ 48.8% ድምፅ አግኝተዋል።

የ77 አመቱ ራይላ ኦዲንጋ ካለ ስኬት ለፕሬዝደንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለአምስተኛ ግዜያቸው ነበር፣ ይህ የመጨረሻቸው ነው ተብሏል።

ከአሁኑ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብተው የነበሩት ምክትል ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ደግሞ በመጀመርያው የፕሬዝደንትነት የምርጫ ፉክክራቸው አሸናፊ ሆነዋል።