Get Mystery Box with random crypto!

ወሰን ማካለል በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

ወሰን ማካለል

በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለል ስራ መጠናቀቁን በተመለከተ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተደረሰው ስምምነት እና ውሳኔ " ታሪካዊ እና ዘመን ተሻጋሪ ነው " በማለት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡ ኮንዶሚኒየሞች ለአብነት
ኮየፈጨ፤
ቱሉዲምቱ በከፊልና
ጀሞ ቁጥር ሁለት የሚገኙበትን ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን ተካለዋል ብለዋል።

ኦሮምያ ክልል የገነባው የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ ከፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞች ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለሉ በማድረግ ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል።

ከዚያ ውጪ ሁሉም ባለበት ቦታ እንዲያስተዳድር ስምምነት ላይ መደረሱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

የአስተዳደር ወሰን በሚነካባቸው አካባቢዎች፦
የትኛውም አይነት መንግስታዊ አገልግሎት እንደማይቋረጥ፤
- የአገልግሎትና የፀጥታ ስራዎች በሁለቱም ወገን በጋራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰራ ፤
- በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንደማይቆሙ፤
- የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት እንደሚቀጥል፤
- የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች ላይ ቋንቋ ምንም አይነት ተፅእኖ እንዳያሳርፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።