Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የመንግሥት ኃይሎች በተለያዩ ግንባሮች በትግራይ ኃይሎች ላይ ትን | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የመንግሥት ኃይሎች በተለያዩ ግንባሮች በትግራይ ኃይሎች ላይ ትንኮሳ ፈፅመዋል በማለት በትዊተር ገጻቸው ከሰዋል። ፌደራል መንግሥቱ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎት የለውም ሲሉ የከሰሱት ጌታቸው፣ መንግሥት አቋቋምኩት ያለው ዐቢይ የሰላም ኮሚቴ ዛሬ ያወጣው መግለጫ ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት እና ጊዜ ለመግዛት ያለመ ነው ብለዋል። ጌታቸው የመንግሥት ኃይሎች መቼ እና በየትኞቹ ግንባሮች ትንኮሳ እየፈጸሙ እንደሆነ ለይተው አልጠቀሱም።