Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የግብጽ ብሔራዊ ባንክ ገዢን አማካሪያቸው አድርገው ሾሙ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የግብጽ ብሔራዊ ባንክ ገዢን አማካሪያቸው አድርገው ሾሙ የግብጽ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡

ጣሪቅ አመር በራሳቸው በፕሬዝዳንት አል ሲሲ ነው አማካሪ ሆነው የተሾሙት፡፡ጣሪቅ አመር ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ነው በብሔራዊ ባንክ ገዢነት ሃገራቸውን ያገለገሉት፡፡በሃገሪቱ ህግ መሰረት አንድ የባንክ ገዢ ለአራት ዓመታት እንዲያገለግል የሚሾም ሲሆን ለሁለት የገዢነት ዘመናት ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡

የመጀመሪያዎቹን አራት ዓመታት በ2019 ያጠናቀቁት አመርም በ2020 ጥር ላይ በድጋሚ ተሾመው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡ ሆኖም አሁን የገዢነት ዘመናቸው መጠናቀቂያ ገና ሳይቃረብ ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው፤ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡