Get Mystery Box with random crypto!

የጉራጌ ዞንን በክላስተር ለመደራጀት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ተደረገ የጉራጌ ዞን ምክር ቤ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የጉራጌ ዞንን በክላስተር ለመደራጀት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ተደረገ

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ፤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጓል።

በደቡብ ክልሉ በተለምዶ የማዕከላዊ ዞን የሚባሉት የሃድያ ፣ የከንባታ ፣ የሀላባ ፣ የሥልጤና የጉራጌ ዞኖች በአንድ ክልልነት እንዲደራጁ ውሳኔ ቢቀርብም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት እስካሁን ውሳኔ ሳያሳልፍ ቆይቷል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤው የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ሥር ከሚገኙ ሌሎች አራት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በ 52 የምክር ቤቱ አባላት ተቃዉሞ እና በ 40 ድጋፍ ውድቅ ማድረጉም ታውቋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በፊት ወስኖት የነበረውን የጉራጌ በክልልነት የመደራጀት ውሳኔን አፅንቷል::

የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎም በወልቂጤ ከተማም ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እየገለጸ እንደሚገኝም ታውቋል።