Get Mystery Box with random crypto!

እስክንድር ነጋ ከባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንትነትና አባልነት መልቀቃቸውን አስታወቁ! የባልደራስ ለ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

እስክንድር ነጋ ከባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንትነትና አባልነት መልቀቃቸውን አስታወቁ!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በመንግስት ጫና ምክንያት በፓርቲ አመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።ፓርቲው ለአዲስ ዘይቤ በላከው እና በእስክንድር ነጋ ፊርማ የተረጋገጠው ደብዳቤ ላይ እንደሰፈረው “ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” ብለዋል።

እስክንድር ነጋ “ካሉበት ለፓርቲው ፅፈውታል” በተባለው ደብዳቤ ሌላ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አላሰፈሩም። ይሁን እንጂ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ አባላት እና አመራሮች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አምሃ ዳኘው ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።በመጨረሻም ፓርቲው ያካሄደዋል ተብሎ ለሚጠበቀው ጠቅላላ ጉባኤ ስኬት ያላቸውን ምኞት በደብዳቤው ገልፀዋል።