Get Mystery Box with random crypto!

Habib Kedir

የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir H
የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir
የሰርጥ አድራሻ: @habib_kedir
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.93K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-06 21:42:03
እስቲ ይህንን ጀግና እናመስግነው
290 ሺ ብር
ሁለት መቶ ዘጠና ሺ ብር
አላሁ አከበር
ወጣት ባለሀብት ፈድሉ ዱላ በቀቤና ባህል ማዕከል ምርቃት ላይ ቀቤና ደምቆ ይገኝ ዘንድ፣ አርቲስቶቻችን፣ አመራሮቻችን የኪነት ቡድኑና እንግዶች በባህላችን እንዲዋቡ 290,000 ብር አውጥቶ የባህል ልብስ አሰፍቷል።
***
ወንድማችን ፈድሉ ዱላ ከዚህ በፊትም ለሙሉ ኪነት ቡድን የባህል ልብስ አሰፍቷል፣ በባህል ማዕከሉ ግንባታ ትልቅ አሻራውን ጥሏል፣ በወረዳችን እሳት አደጋ ሲደርስ የቀደመው አልነበረም፣ በኮቪድ ግዜ ህዝባችን እንዳይጎዳ ከፊት ተሰልፏል፣  ለታመሙ ሁሉ ደርሷል፣ ለአንጋፋዎች ቤት ሲሰራ ቀዳሚ ደጋፊ ነበር፣ አንጋፋ ታጋያችን ለማቋቋም(መሀመድ ቡሌ) ከፍተኛው ድጋፍ የሱ ነው። በአጠቃላይ በቀቤና ህዝብ ጉዳይ አንድም ግዜ ወደ ኋላ ሆኖ አያውቅም።
***
ኢንሻ አላህ ለወደፊቱ በዝህኛው ትውልድ ዙርያ በሚዘጋጅ የታሪክ ሰነድ ስማቸው ከፍ ብሎ በወርቅ ቀለም ከሚፃፉት ውስጥ ይሆናል።
አላህ የሱ አይነቱን እንደ ምድር አሻዋ ያብዛልን
አላህ ረዥም ሀያት ከጤና ይስጠው
1.1K viewsHabib Kedir, edited  18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 13:19:56
ወልቂጤ ኤፍ ኤም ጀርባ የሚጣለውን ቆሻሻ በተመለከተ ብዙ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው።
***
ከግል ክሊኒኮችና ከአልቢርና መሰል ጤና ጣቢያ ያገኘሁት መረጃ ከጠቅላላ ታካሚ ህፃናትና አዋቂዎች ውስጥ 60% የሚሆኑት ቆሻሻ መጣያው አከባቢ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ነው።
ከጠቅላላው ታኪሚ ህዝብ 60% የሚሆነው የአንድ መንደር ሰው ከሆነ እጅግ የሚያሳዝንና ለወደፊቱም ከባድ አደጋ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
***
ይሄን ሁሉ ግዜ በህዝብ መኖርያ አከባቢ ቆሻሻ ሲጣል ለምን ዝም እንደ ተባለ ግራ ይገባል። አሁንም መፍትሄው አስቸኳይ መሆን አለበት። ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች፣ መሪዎች በጉዳዩ ፈጣን ውይይት ማድረግ አለባችሁ። ቆሺሻ የሚጥሉ መኪኖችና ጋሪዎች ማቆም ይገባቸዋል።
***
እንደ መፍትሄ
በከተማው አማራጭ ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ብዙ አሉ።
አሁን ቆሻሻ ሚጣልበትን አከባቢ አስውቦ
1 የአከባቢው ወጣትና ህዝብ መዝናኛ ማዕከል ማድረግ
2 ፍቃዶ ኬላ አከባቢ ለገበያ አስፓልት ዳር ከመኪና ጋር የሚጋፉ እናቶቾን ወደዛ አዘዋውሮ ደማቅና ደረጃውን የጠበቀ ገበያ በቦታው መመስረት
ህፃናትና አዋቂዎች በበሽታ አይለቁ፣ ይህን ጉዳይ ችላ ማለት አይገባም። ከተማ አስተዳደሩ የቀቤና ህዝብ ቢታመም ቢሞት ግዱ አይደለም፣ ወጣቱ ከህዝቡ ጋር ተናቦ መብቱን ማስከበር አለበት።
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
1.1K viewsHabib Kedir, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 18:45:26
ይህን መንገድ ተመልከቱ
ከቀቤና ወረዳ ዋና ከተማ ወልቂጤ ወደ ሌላኛው የወረዳው ከተማ ወሸርቤ የሚወስድ ነው
***
ከ25 ኪሎ ሜትር ያልበለጠ መንገድ በመኪና ከ4 ሰዓት በላይ ይፈጃል።
አቅመ ደካሞች፣ ነብሰ ጡሮችና የታመሙ ሰዎች ሆስፒታል ለመድረስ በዚህ መንገድ የሚደርስባቸውን ስቃይ መገመት በጣም ቀላል ነው
በድፍን ወረዳው አንድ ኪ ሜ እንኳን አስፓልት መንገድ የለም። ለወረዳው የሚበጀተው በጀት የ6 ወር የሰራተኞች ደሞዝ አይከፍልም። አሁን በዚህ አመት እንኳን ከየካቲት ጀምሮ በብድር ነው ደሞዝ እየከፈለ የሚገኘው።
***
የሚያስፈልገን "የሚያዝን፣ እንዲህ አይነት ጭቆናና በደል በዘራችሁ አይድረስ" የሚልና "ከንፈር የሚመጥ" ሳይሆን፣ አምርሮ የሚታገልና ከዚህ ዞን ህዝቡን ነፃ የሚያወጣ ትውልድ ነው።
ቀቤኖች ያለን አማራጭ አንድና አንድ ነው
ከዚህ ትውልድ ከሚያጠፋ ዞን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ታግለን ነፃ መውጣት።
እየዬ አይሰራም
መቁረጥ፣ አምርሮ መታገልና የትኛውም መስዋዕትነት መክፈል ከጭቆና  ለመገላገል ብቸኛው መፍትሄ ነው።
***
ቀቤና እራሱን በራሱ እያስተዳደር ከጠባቂነት ወጥቶ ሀገሩን በትብብር ማልማት ነው።
የተጨቆኑ ጨቋኞች ፈላጭ ቆራጭ ሊሆኑብን አይገባም፣ የነፃነት እድሉ ይጠን እንጂ ለራሳችን እራሳችን እንበቃለን።
በቁጭት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳን እውን እናድርግ
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
1.3K viewsHabib Kedir, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:49:44
የዚህ ጀግና ትውልድ አካል መሆን ትልቅ ኩራት ነው
***
የቀቤና ህዝብ ባህል ማዕከል በድምቀት ለማስመረቅ የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ዛሬ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቀቤና ልማት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች በባህል ማዕከሉ ምርቃት ዙርያ ውይይት አድርገናል።
***
በመድረኩ የቀቤና ወረዳ አስተዳደር አቶ ዘይኑ ሻቡዲን፣ የቀቤና ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከማል ሱልጣን፣ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ መሀመድ ሀሰን እንዲሁም ከአዲስ አበባ የማህበሩ ቦርድ አባላት አቶ ሙደር ሰማንና ዶ/ር ኢንጂነር ሙአዝ በድሩ ተገኝተው ስለ ምርቃት ፕሮግራሙ ገለፃ በማድረግ ውይይቱን መርተዋል።
***
የባህል ማዕከላችንን ምርቃት በድምቀት ለማስኬድ እንደ አዲስ አበባ በጋራ መንቀሳቀስ ወሳኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለምርቃቱ ድምቀት ወደ አንድ ሚልየን ብር የሚጠጋ ገቢ በዛሬው እለት ተሰብስቧል።
ይህንን የምርቃት እና የሲፖዝየም ፕሮግራም ታሪካዊና አይረሴ ለማድረግ ከሁላችንም ትልቅ ድጋፍና ርብርብ ይጠይቃል።
የጀመርነው ያልቃል
ያለቀው ይመረቃል
ሌላም ይጀመራል
ምክንያቱም፡- እኛ ሞያችንን በልባችን ያኖርን፣ የአባቶቻችን ልጆች ጀግኖች ነን
***
502 viewsHabib Kedir, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 20:11:15
መሀመድ ሸመድየንን እንርዳ እንቅስቃሴ እስከ ሸዋል 15 ተራዝሟል
***
1ኛ በረመዳን ለማስገባት ያልተመቸው ብዙ ሰው በመኖሩ
2ኛ በየ አከባቢው ያልተጠናቀቀ ገቢ አሰባሰብ ስላለ
3ኛ ሲቪል ሰርቫንቶች ከደሞዛችን የቻልነውን እናደርጋለን ትንሽ ታገሱን ስላሉ፣ በኮሚቴ ውሳኔ የገቢ አሰባሰባችን ለትንሽ ቀን ተራዝሟል።
***
በመሆኑም እስከ ሸዋል 15 ድረስ ቃል ገብታችሁ ያልፈፀማችሁ እንዲሁም በረመዳን ያልተመቻችሁ በተጨመሩት ጥቂት ቀናት ትብብር ታደርጉ ዘንድ በማክበር እናሳውቃለን።
***
የእቅዱ 70% ላይ ነን በቻላችሁት ሁሉ እጃችሁን ትዘረጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን
አካውንት
CBE (ንግድ ባንክ) 1000532001521
Iklas ዳሽን 2943842990911
754 viewsHabib Kedir, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 17:22:41 ጉዳቱ የህዝቡና የሀገሪቱ ነው
***
በሁኔታው ከማዘኔ የተነሳ ምንም ለማለት አልፈለኩም ነበር።
ከወንድም ግርማ የሺጥላ ግድያ የሚያተርፍ ማንም የለም።
ካለፈው ሳንማር አሁንም ጎበዝ ጎበዝ ሰዎችን እያጣን ነው።
እንደ ቀልድ የሚገደሉ ባለስልጣናት፣ ሙሁራንና አዋቂዎች እዚህ ለመድረስ የከፈሉት ዋጋ ማንም አያስተውልም።
አንድን ሰው ትልቅ ደረጃ ለማድረስ ማህበረሰቡና ሀገሪቱ ኢንቨስት ያደረጉትን ጉልበት ማንም አይገነዘብም።
አሁን በቀላሉ ወጥተው የሚቀሩ ሙሁራንን ለመተካት ሰላሳና አርባ አመት በትንሹ ይፈጃል።
***
ሰዎችን ስንገድል እራሳችንንም እየገደልን ነው።
ብዙ ቤተሰቦችን ሜዳ እየበተንን ነው።
ሰው በገደልን ቁጥር ክፋትን እየዘራን ነው፣ እርስ በርሱ የማይተማመንና ልቡ በቂምና በበቀል የተሞላ ትውልድ እያፈራን ነው። በአጠቃላይ እምነታችንን፣ የመቻቻል እሴታችንን እንዲሁም ሀገራችንን ወደ ኋላ እያስቀረን ነው።
በሰዎች ሞት የምንጎዳው እራሳችንን ነው። ገዳይ ማንም ይሁን ማን ሰው ሲገደል እራሱን እየገደለ ነው።
***
ከኢንጂነር ስመኘው ጀምሮ በሀገራችን መሰል አሰቃቂ ግድያዎች ተደጋግመዋል። አስፈላጊው መጣራት ተደርጎ የተደረሰበት የፍርድ ውሳኔ እስካሁን አላየንም። አጥፊው በተናጠል ታውቆ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ ሌላው ይማርበት ነበር። ገዳዮችን አድኖ መያዝና ለህግ ማቅረብ፣ ወንጀል ሰርቶ ማምለጥ እንደማይቻል እና ጠንካራ የደህንነት ስርዓት እንዳለን ማሳያ ስለሚሆን ሟቾች አይበዙም ነበር።
ይህ መንግስት የደህንነት ስርዓቱን ሊፈትሽ ይገባል። ወንጀሎች ሲከሰቱ የእነ እከሌ ስራ ነው ብሎ ማለፍ ሳይሆን በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ማሳየት የመንግስትና የፀጥታ ሀይሉ ተግባር ነው።
***
ደህንነቶች በፌስቡክ ከአክቲቪስቱ እኩል እየተፈራረጃቹ መዋል የችግሩን ምንጭ ለማግኘት አይረዳም። በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የደህንነት ተቋም ያስፈልጋል። መንዝ መሀል ሜዳ እኔ በስራ የማውቀው አከባቢ በመሆኑ ከመንግስት ጥበቃ የራቀ ወይም ሪሞት አከባቢ የሚባል አይደለም። መንግስት የሌሎች ዜጎችን ቀርቶ የራሱን ሀላፊዎች መጠበቅ ካቃተው ምን ይባላል?
***
እኛም እንደህዝብ በመገዳደል መፍትሄ እንደማይመጣ አውቀን፣ ፈጣሪያችን በክብር የፈጠራት የሰው ልጅ ነብስ ቀኗን ጠብቃ የተፈጥሮ ሞት ትሞት ዘንድ እድል እንስጣት። በሁሉም ሀይማኖቶች የሰዎችን ነብስ ማጥፋት በዓለማዊው ህይወት የህሊና ስቃይ፣ በመንፈሳዊ ህይወት ደግሞ ሀጢያት ነው።

በሀዘኑ ለተጎዳችሁ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ
***

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ከቀቤና_ልዩ_ወረዳ
949 viewsHabib Kedir, edited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:55:55 #ሸዘታ_ቀቤኒ_ኦሶታቲ…
#ሼሪ_ኧቴኒ_ታኪሽዬ
***
ኒ ወረዳኒ፣ ወልቂጢታ አፊ ገበል ገበላን ዮኢ ቀበላካኒ ሞጮጪናሚ ፈያ ኢኮበኢ ጠው ዊሙ ዮ።
ኧዚ ሸዣኒ ገዓቺ ከበሪ ጠውሲ መከኑ ይን ሰዕሚ ይኖሚቂ።
ቴሱ በር በሬቺ ባሰነኒ ኧሜቾ
መኪነታ ኡሪሴኒ ወቀሩላ ወቃ ሀመኑ ሀልቃ ሻሲዙ፣ ሆጎጋ ወለዔኒ ሌንቄቂቴነንታ ኒ ኦሲቻከቲ ኧጉሪዬ
***
ቴሱ ሞጮጪነነኒ ዮሚ ሀለቴኒ ፌደራሊቺ አፊ ክሊሊታ ኢሊ ዮኢ ባዱ ኧገርታኢሩ ግብረ ሀይሊ መኪሲ ሂታጋሙ ሪቺን ዮኢራ ወቀሪሀ በሪ ኧገርተነኒ ዮ፣ ቆሊላ ሩሙጊ ውዲን።
ወዱን ኔሳ ወቀርሲሲሀ ሰበበታ ሀሰኑሁ ሹሊ በርገሚ ኬዮ፣ ከ ጠዋ ሀቢብ ሞጮጪ ሰሚይዎ ይቶንቺዬ።
***
ቀይ ቀዬን ዮንተኢ ኦሲቻከቲ ነገዴኒ፣ ጎና ኢኪኔ ተማርቴኒ ሄቸኪና መኪሺዬ። ሁንዳ ቄሎሂና ጎረ ኡለኪና አልባሸታ አቡሪቴን ኢቺዬ።
***
ባጢሊ አፌኒ፣ መና ዘረፌኒላ ሻዚሴኒ ፈያ ሄቸታ ደኤኑባ።
ገውኪዕነሁ መነዕኪነሁ ሚርቴነንታ።
ቀቤኑ ነጣ ፉለኑሁላ መባቲሲ ደዓኑሁ ሀንቂኔታ ቤቀራ ባጢሌኔቲባ። ሬውታ ኢኮጎራ መኖማተዕናላ ባዲሀና ቤቀራ ጎደቢሀዕና ኢሁንካ። ዘናዓኒ መኒ ሀንቂ ዞለመነኒ ሬዮኢሃ፣ ማጉላሀ ጎሬ ጋኣታ ጎናሃ ይኒ ጠወናምባ። ካጠዋ በትናሻ ወቅቲ ሞጮጨነኒ ዮሚ ቆሊላ ሩሙጊ ቀበሌኔቲ፣ ኧሌኒ ኩሎንኪዕና ግብረ ሀይሉሲ ሂካ አከባቤ ኦሲቹ ወቀሪሂ ኬዮ። ሂቲጋሙ ሪቺ ኣዚ ዮንቲኢሪ ከጲቺ ሱሙዕኪና ኬኣኑበኢጋ ሸዘቀሚዬ፣ ካኒ ኧታኢሩ መቱመቱ ኦሶታ ጎሬ ኡርሺዬ ኧደረታ።
***
ቀቤኒ መባቱ ዋለሚሃ ባ ባ ኢኸነኒ ዮ። ቴሱ ቀቤኒጋ ሱመዕና ቤሰኑሪቺች ቆረጱ ሀሲሰኑ። ጠቀመኑበኢ ኮንትሮባንዲሀላ በሬ ቀለቢሃ አናከዕናላ መኑዕና ሄንካ ወተዮኢ ጠዋ ቤሶንቺዬ። ባዲናላ ወረዲና መጨታ ኧገርኖ። ጉዕሙ ሪቹ መኪ፣ መባቲና ደኢኒ፣ መኖመዕና ዋሺኒ፣ ገውና ገዑን ገሺናሚራ፣ ኡሲቹዕና ሀልቁና ሆጎታ ሆገኑባ፣ ሄንካኢላ ሰበርዬ። ኦሪሾሲ ቢሃ ሬዮኢሁ ዮባ፣ ፈረኪዬ ቀው ኢለታ።
***
ቴሱ ነኡ ሌንቄቁ ዮና ሱመዕና መኪሲሀ፣ መባቲሀናላ ማሳዓሚ ኢሊዮኢ ዓዳና ሚኔ ጠዋኒ ኢሁ ዮሲ። ከኒቺ ኤተሩ ቀቤኒ ኦሱቲ ዘናዕኒ መና አዛ ኧታ፣ መኪነታ ኡሪስ ወቀርታ፣ ሆጎታ ኧሰኑ ባለሀብቲ ኡሪሳ፣ መኒቺ ሀንቂ ቤሉ ፈረንካ መጣ ዬኑ ጠዋ ሞጮጩ ዮነባ። መቱ መና ኢኮጎሬ ግብረ ሀይሊኒ ከጠዋኒ ወቀረሙ ዮስባ፣ ኔሳ ሮራ ሚረኑዕና። ኦሲቻካ ኧጉርዬ፣ ኡሪዮ። ቀይቀዬን ዮንተኢ ባሊቀታ ካጠዋ መኪሺዬ፣ ወረዲና ጋሻኑላ ባዱ ኧገርቴነንታ ኒ ፖሊሰቲ ጢቸቴኒ ኧገረቀሚዬ።
ጋኣታ ማለለኑ ጠው ሀለቀሙንካ፣
ባጢሌኒ ሀለቀምናምባ
ሀንቂ አንፊ መባቲና ዋሺናሚ
ሬዎታ ጎሬ መኖማተናዕ ቤቀራ ጎደቢሃዕና ሬኑንካ
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
1.1K viewsHabib Kedir, edited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 23:43:14
የጉራጌ ሙስሊሞች ለማንነታቸው ያላቸው ቦታ ሁሌም ይገርመኛል። የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ይደናቀፋል፣ እርስ በርስ ክፍተትና መሳሳብ ይመጣብናል ብለው ብዙ ነገር ችለዋል። በእምነታቸው እንኳን የመጣን በደል ዋጥ አድርገው ከርመዋል።
***
በጉንችሬ ለአንድ አመት ያህል ልጆቻቸው ከትምህርት ቀርተው ዝም ብለዋል። ይህን የትም አከባቢ፣ ማንም ችሎ አይታገስም።
በክልልነት ጉዳይ አብዛኛውን ግዜ ባልተገባ ቀንና ጁመዓ ተለይቶ አድማ ሲጠራ፣ ሙስሊሙ የጥቃት ታርጌት ሲሆኑ፣ እምነት ተለይቶ ከስራ የተባረሩና የታሰሩ ሲጠዩቁ፣ የተሰበሰበ ገንዘብ እንኳን ሲከፋፈል እምነት ሲታይ፣ ትግሉ ይጎዳል ብለው አንድ ቀን እንኳ ቅሬታ አላቀረቡም።
በረመዳን የኢፍጣር ፕሮግራም ሰላት በቆሙበት አፀያፊና ነጃሳ የቢራ ጠርሙስ ሲወረወርባቸው(ድንጋይ ይሻላል)፣ ጉራጌ በመጥፎ እንዳይጠራ፣ ማንነታቸው፣ ስማቸው እንዳይጠፋ ህመሙን ዋጥ አድርገዋል።
የጉራጌ ሙስሊም ከእምነቱ በላይ ለጉራጌነቱ ብዙ ዋጋ ከፍሏል። ጉራጌ በመጥፎ እንዳይጠራ እራሱን ሰውቷል።
***
የጉራጌ ሙስሊም የተናጠል ክልል ይሰጠን ብሎ ሲታገል ከጉራጌነት አንፃር እንጂ ከእምነት አንፃር ጠቃሚው እንዳልሆነ ያውቀዋል።
እነ ተስፋ ግን ለጉራጌነት ብለው የሚሸፍኑት አንድ ነገር የለም፣ በእምነቱ ከመጣህበት "ማርያምን ጉራጌነት በአናቱ ይተከል" ይልካል።
ችግሩ የጉራጌ ሙስሊም የሚረዳው አለማግኘቱና እንደሞኝ መቆጠሩ ነበር
አሁን አሁን ግን እምነቴ ከማንነቴም በላይ ነው ብሏል
ትክክል ነው
መቻል ሳይሆን መቻቻል ወሳኝ ነው
#Mutualuzation
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
1.6K viewsHabib Kedir, 20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 21:52:12 በወልቂጤ ዙርያ ትልቅ ግጭት ተደግሷል
#ሼር በማድረግ ለሁሉም አድርሱ
***
የቀቤና ወጣትና ህዝብ ለማይቀረው መራር ትግል እራስህን አዘጋጅ።
የክልልነት አጀንዳ የከሸፈበት መሰሪ አመራር የጎንዮሽ ብጥብጥ ለመፍጠር ከክልል እስከ ክፍለ ከተማ ተናቦ እኩይ ሴራ እያሴረ ነው።
ዞኑ እንኳን በቅጡ ባልተረጋጋበት በዚህ ወቅት ወልቂጤ ዙርያ ህገ ወጥ ቤቶችን እናፈርሳለን ብለው ዝግጅት አጠናቀዋል።
***
ሰሞኑን የከተማው ከንቲባና የማዘጋጃ ሀላፊዎች በአንድ ግዜ መልቀቂያ አስገብተው ከስልጣን የወረዱት በቀቤና ህዝብ ላይ የታሰበ ከባድ ሴራ ሥላለ ነው። ሁለቱ ሀላፊዎች በመልቀቃቸው ቦታው በቀቤና ምክትሎች መመራት ጀምሯል። የቤት ማፈረሱንና ሌሎች የታሰቡ እኩይ ተግባራትን በነዚህ ምክትሎች እንደተፈፀሙ ለማስመሰልና፣ እራስን በራስ ለማጋጨት ነው። ይህ ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ተንኮል ሲሆን ከዚህ በፊትም የተጠቀሙበት መርዝ አካሄድ ነው።
***
ቀድሞ መንቃትና ህዝቡ እራሱን እንዲከላከል ማድረግ አስፈላጊ ነው። በአዲስ አበባ ዙርያ ህገ ወጥ ተብለው የተሰደዱ ዜጎቻችንን እምባ እያየን፣ ሌላ ህዝብን ለሰቆቃ ማዘጋጀት ነውር ተግባር ነው።

የሚገርመው፡- በወልቂጤ ዙርያ ለተቋማትና ለማህበራት በሚል ተልካሻ ምክንያት በጉልበት እርሻውን በግፍ የተነጠቀ የቀቤና ገበሬ በቀረው ማሳ እንኳን ጎጆ ቀልሶ እንዳይኖር በህገ ወጥ ሰበብ ሌላ ግፍ ሊሰራበት መሆኑ ነው።
***
በወልቂጤ ዙርያ ከቀቤና ህዝብ በተለያየ ምክንያት መሬት ዘርፈው የገነቡ የጉራጌ ተወላጆች በሙሉ በፍጥነትና በነፃ ህጋዊ እንዲሆኑ ተደርጓል። የቀቤና ህዝብ ከማሳው በቀረችው ቦታ አንድ ቤት እንኳን ገንብቶ ህጋዊ ላድርግ ቢል፣ ብዙ አመት ሲያንከራትቱትና ውድ ዋጋ ሲጠይቁት መሮት የተወ ነው። አሁን የራሳቸውን ህጋዊ አድርገው ሲያበቁ፣ እምቢ ብለው ያንከራተቱትን ቀቤና ሊያፈናቅሉት ሴራ ሸርበዋል።
****
በሌላ አከባቢ ህገ ወጥ ተብሎ የሚፈርስበት የጨረቃ ቦታ ገዝቶ የገባ ነው። በወልቂጤ ግን ህገ ወጥ ተብሎ የሚሳደደው ማሳው የተነጠቀበትና በቀረችው ጎጆ ቀልሶ ኑሮውን የሚመራው ነው። መሬትህም ተወስዶብህ 200 ካሬ ላይ እንኳን እንዳትኖር ከተደረክ የት ትሄዳለህ? ስለ እውነት ይህ እጅግ አሳዛኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። ከሰው ሀገር ገዝቶ ገብቶ የሰራው ቢፈርስበት ወደ ሀገሩ ይሄዳል፣ እርሻው የተነጠቀበት ወዴት ይሂድ? ያለው አማራጭ እዛው ተጋድሎ ማድረግ ነው።
***
በዚህ እኩይ ሴራ ከክልል ከአቶ ንጉሴ አስረስ እስከ ዞን አቶ ላጫ የተንኮል መረብ ተዘርግቷል። አቶ ላጫ ለቀቤና ህዝብ ትልቅ ጥላቻ ያለው መሰሪ ሰው ነው። አቶ ንጉሴ አስረስ ግን የምዕራቦችን ጥላቻ ሰምተህ ህዝባችን እንዳታስገድል በማክበር እንጠይቅካለን፣ የትውልድ ተወቃሽ እንዳትሆን ይህንን ግፍ አስቁምልን።
***
በሌላ በኩል ይህንን ጉዳይ እየመራችሁ ያላችሁት የየክፍለ ከተማው አመራሮች የምትኖሩት በህዝባችን መካከል ነው፣ ዞራችሁ ስትመዘግቡና ለአፈፃፀሙ ደፋ ቀና ስትሉ እያየን ነው። ህዝብ ሳይወያይና ሳያምንበት ለሞታደርጉት እያንዳንዱ ተግባር ዋጋ ትከፍላላችሁ። ህዝቡን በግፍ ከርስቱ አፈናቅላችሁ፣ በማሳችን በተገነባው የማህበራት ቤት ተንደላቅቄ እኖራለሁ ካላችሁ ስህተት እሳቤ ነው። ታረሙ ወጣቱ ከናንተ ላይ በፍፁም አይወርድም።
***
በመጨረሻም የቀቤና ወረዳና ከተማው ግልፅ የሆነ ድንበር አላቸው። ህግ በማስከበር ሰበብ ወደ ቀቤና ወረዳ ዘልቆ የሚገባ የከተማ አስተዳደር ማስቆም የሉዓላዊው ብሔረሰብ ወረዳና ህዝብ ሀላፊነት ነው። ወረዳው የሰጠውን ፍቃድና የመሬት ማረጋገጫ ከተማው የማይቀበልበት ሁኔታ በፍፁም መኖር የለበትም።
***
ገዢው ፓርቲና መንግስት፣ በአከባቢው ግጭት ለመፍጠር በቀቤና ህዝብ ላይ በጉራጌ አመራሮች የተሴረውን ሴራ ተረድተው ይህን ጉዳይ በአንክሮ እንዲያዩትና አስፈላጊው እርምት እንዲወሰድ አሳውቃለሁ። የተናጠል ክልልነት ስላጣ በቀቤና ህዝብ መፈናቀልና ስቃይ የሚደሰት ካለ ነግ በኔ ነውና ከህዝባችን ጎን ይቁም። በደል ሞልቶ ሲፈስ ገፈት ቀማሹ ብዙ ይሆናል።
***
የቀቤና ህዝብ ሆይ በጉራጌ ዞን ስር እስካለህና አፍራሽም ገዳይም፣ ፈላጭ ቆራጭም እነሱ እስከሆኑ ድረስ እረፍት የለህም። እራስህን በራስህ ለማስተዳደርና ነፃነትህን ለማወጅ ስልጣኔ፣ ደሞዜ፣ ሀብቴ፣ ንብረቴና ትምህርቴ ሳትል ቆርጠህ ተነሳ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
1.6K viewsHabib Kedir, edited  18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 17:10:48
ጉራጌ ዞን፣ ጉንችሬ
***
በፊት ጀምሮ በዞኑ ፅንፈኝነት አጎጠጎጠ ስል "ከፋፋይ ነህ ዝም በል፣ ክልልነቱን ለማደናቀፍ ነው" ብለውኝ ነበር። አሁን በጉንችሬ ሙስሊሞች ላይ በተናበበ መልኩ ጭካኔ እየተፈፀመባቸው ነው።
የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት ያድርግ።
***
1.2K viewsHabib Kedir, 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ