2023-03-27 02:08:32
የወደቀን እናንሳ፣ ኸይር ስራ እንስራ
የረመዳን ሰደቃችንን መንቀሳቀስ ለማይችለው፣ ለታመመው ወንድማችን፣ ለታላቁ ባለውለታችን እናድርግ
መሀመድ ሸመድያን(መሀምድ ቡሌ)
***
ዛሬ የቀቤና ብሔረሰብ የምንለው መጠርያ በብዙ ታላላቆቻችን ትግልና መስዋዕትነት ጸንቶ የቆየ ነው።
በ1976 የህዝባችን ጉዳይና መጻኢ እጣ ፈንታ አሳስቧቸው ከተንቀሳቀሱ ታላላቆቻችን አንዱ ነው መሀመድ ቡሌ። በወቁቱ በቀቤና የመጀመርያ የትግል ችቦ የሆነውን የምክክር ኮንፈረንስ እና የወጣቶች ግንኙነት በግንባር ቀደምትነት መርቷል። በውይይቱ ጥናታዊ ጹሁፍ በማቅረብ ህዝባችን ለነጻነቱ በሚታገልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ሰጥቷል
በደርግ አገዛዝ ወቅት በየአመቱ በሚከበረው የመስከረም 2 ክብረ በዓል የቀቤና ኪነት ቡድንን በመድገፍና በመምራት የቀቤና ብሔረሰብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ታሪኩና ወጉ እንዳይጠፋ ከአዲስ አበባ እየተመላለስ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል
ከደርግ ውድቀት በኋላ የቀቤና ህዝብ የነጻነት ትግሉን ያቀጣጠለው ድርጅት ቀብዴድ ሲመሰረት ከብርቱ አባቶቻን ጋር በመሆን በሀሳብና በአካል ተንቀሳቅሶ ደግፏል
የቀቤና የምንግዜም ታላላቅ አባቶቻችን እነ ሀጅ ፈትሁዲንና ሀጅ አህመደል ሀዲ በ1985 አዲስ አበባ ድረስ መጥተው የቀብዴድ ቅርንጫፍ ሲያቋቁሙ ኮሚቴ በመሆን ተመርጦ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ በመሆን በትጋት ህዝቡን አገልግሏል።
መሀመድ ቡሌ በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀቤንኛ ቋንቋ አዘጋጅ የነበረው ጀግናው ጋዜጠኛ ሙባሪክ ሙደሲር ለስልጠና ሲሄድ እሱን ተክቶ ከ1986 እስከ 1987 በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀቤንኛ ቋንቋ አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን የቀቤና ብሔረሰብ ቋንቋ እንዲጎለብትና ተደራሽ እንዲሆን ለፍቷል።
በ1987 የቀቤና ህዝብ በጉራጌ ዞንና በጎሮ ወረዳ መደራጅቱን በመቃወም በ28 ቀበሌ የሚገኘው ቀቤና ግብር አልገብርም ብሎ ትግሉን ሲያቀጣጥል ከአዲስ አበባ ድረስ በመሄድ የህዝቡን እንቅስቃሴ መስመር በማስያዝ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የቀቤና ተወካዮች በመዋቅሩ ተካተው ምክር ቤት እንዲገቡና ትግሉ ህጋዊ መስመር እንዲይዝ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል።
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በቀቤንኛ ቋንቋ እንዲተረጎም የብሔረሰቦች ምክር ቤት በጠየቀው መሰረት በመተርጎምና በማስተባበር ከጀግና ወንድሞቹ ከዘይኑ አክመልና ሙዜ ጋር በመሆን 44 ገጽ ለህትመት እንዲቀርብ በማድረግ ለፌደሬሽን ምክር ቤት(አልማዝ መኮ) አድርሷል።
የደቡብ ብሔረሰቦች አጠቃለይ እንቅስቃሴ ወደ ሀዋሳ ከዞረ በኋላ ብዙ ግዜ የቀቤና ህዝብን መብት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ሀዋሳ ድረስ በመመላለስ መርቷል፣ አስፈጽሟል።
በ1991 ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሄደም በኋላ የቀቤና ብሔረሰብ እድር ጠንካራ እንዲሆን በመደገፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ታላቁ የቀቤና ልማት ማህበር በሳውዲ ሲመሰረት መድረክ የመራው ይህ ጀግና ወንድማችን ነው። ልማት ማህበሩ ተቋቁሞ በሁለት እግሩ እንዲቆምና እውን እንዲሆን ትልቅ መስዋትነት ከከፈሉ ወንድሞች ውስጥ ቀዳሚው ነው።
በአጠቃላይ በሳውዲ ቆይታው የቀቤና ህዝብ በሚገጥሙት ኩነቶች ሁሉ መድረኮችን በመምራት፣ በኢቲቪና በተለያዩ ሚድያዎች እንዲቀረጹና እንዲተላለፉ በማድረግ በቆንጽላና በኤንባሲዎች በመገኘት፣ የተቸገሩትን በመርዳትና በማስተባበር፣ የተጣሉትን በማስታረቅ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር በተግባር የገለጸና ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ጀግና ነው።
በአጠቃላይ ታላቃችን መሀመድ ቡሌ አንድም ቀን ለራሱ ያልኖረ፣ ሁል ግዜም ስለ ህዝቡ ከፍታና ነጻነት የሚጨነቅ፣ አርቆ አሳቢና ባለ ብሩህ አዕምሮ ጀግናና ደፋር ነበር።
አሁንስ?
አሁንማ ያ ጀግናና ታታሪ ለሰው አዛኝና ሩሁሩህ ሰው ታሞ ቤት ከዋለ አመታት ተቆጥረዋል፣ መንቀሳቀስ አይችልም ውሎ አዳሩ ዊልቸር ላይ ሆኗል። እራሱን ችሎ መጸዳዳት አይችልም። ህመሙ ከባድ በመሆኑ በየወሩ መድሀኒት ያስፈልገዋል በዊልቸር መጸዳጃ እንኳን ለመድረስ የተስተካክለ ቤትና ግቢ የለውም።
የልጆች አባት ነው፣ በማረፍያ እድሜው በሰው እጅ ወድቋል
መድሀኒቱ ውድ ከመሆኑም ባሻገር በየግዜው ጥቁር አንበሳ መመላለሱም ወጪው ከፍተኛ ነው
***
ይህን ለህዝቡ ታላቅ ውለታ የዋለ ዋርካ ሰው የመጨረሻ ዘመኑን በደስታ ያሳልፍ ዘንድ ማድረግ የሚገባን ሁለት ነገር አለ
1ኛ የሚኖርበትን ጠባብ አንድ ክፍል ቤት ማሻሻል። ተሸክማ መጸዳጅ የምትወስደው የልጆቹ እናት ባለቤቱ ናት፣ ይህን ለማስቀረት ደህና ዊልቸር ኖሮት በተስተካከለ ግቢ እንዲንቀሳቀስና መጽዳጃ በዊልቸር እንዲሄድ በማድረግ ባልቤቱ ተሸክማ እንዳትወስደው ማድረግ
2ኛ የህክምና ወጪውን በመሸፈን ጥሩ ህክምና እንዲያገኝና ቤተሰቦቹ እንዳይራቡ ድጋፍ ማድረግ
ለዚህ የሀገር ባለውለታና ታላቅ ሰው ይህን ማድረግ አያቅተንም ግዜው ረመዳን ነው መሀመድ ቡሌ ደጅ ጠንቶ የሰው እጅ አይቷል፣ እርዱኝ ብሏል። የዘንድሮ ሰደቃችንን ለሱ እናውል እንደ ህዝብ ከወደቅንበት ለማንሳት የታገለን ብርቱ ሰው እኛ ከወደቀበት እናንሳው
በየ ሀገሩ የምትገኙ የቀቤና ተወላጆች አስተባብሩ
#ሼር በማድረግ ለደጋግ ኢትዮጵያዊያን አድርሱ
***
አስተባባሪ ኮሚቴ ተዋቅሯል
በጣም በምትወዷቸውና በምታምኗቸው ታላላቅ ሰዎች፣ አካውንት ተከፍቷል።
1 ኢማም ሸምሱ አስፋ
2 ሀጅ ረውነቅ ሰማን
3 ኑረዲን አህመዲን(አሊ)
ንግድ ባንክ 1000532001524
Iklas ዳሽን 2943842990911
***
የኮሚቴዎች ስልክ
1 አሊ(ኑረዲን) 0900830529
2 ኢማም ሸምሱ 0955328641
3 ሼህ ረውነቅ 0938959926
የራሱ የመሀመድ ቡሌ 0910650822
እኔንም በውስጥ አናግሩኝ
ደግ ደጉን እናስብ
በጎ በጎውን እንስራ
መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና
ሰውን ለመርዳት ደግሞ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው
***
የበጎ ተግባር ማስተባበርያ የቴሌግራም ግሩፕ ተቀላቀሉ
https://t.me/Yosisi_Charity
ለማስተባበር ተብሎ የተከፈተውን የዋትስ አፕ ግሩፕ በሚቀጥለው ሊንክ ተቀላቀሉ https://chat.whatsapp.com/JyQbadxGkEoDFRpITDKjsT
927 viewsHabib Kedir, 23:08