Get Mystery Box with random crypto!

Habib Kedir

የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir H
የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir
የሰርጥ አድራሻ: @habib_kedir
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.93K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-01 18:26:17
በሀድያ ሆስዕና የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
ሙሹራዋ ዋቻሞ እንግዶቿን ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች እንደሆነ እየሰማን ነው።
#ያድርሰነ
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
604 viewsAdu Emru, 15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 12:32:56
20 ሺ ብር አላሁ አከበር
የወደቀ ወንድማችንን መሀመድ ቡሌን የመደገፉ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል
እየተደረገ ያለው ርብርብ እጅግ ደስ ይላል
ታላቃችን የሁሉ ግዜም የተቸገሩ ደራሽ መሀመድ ሻፎና ቤተሰቡ 20,000 ብር ሰደቃ አድርጓል።
መሰሎቹን ያብዛልን፣ ረዥም ሀያት ከአፊያ ጋር ይስጥልን
***
መሀመድ ቡሌ ትናንት ጀግናና ታታሪ፣ ለህዝቡ የሚደክም ወጣት ነበር። ዛሬ እጅ ሰጥቶ እኛን ተማፀነ።
ነገ ምን እንደሚገጥመን ማናችንም አናውቅም
ሁላችንም ትንሽ ትልቅ ሳንል ድጋፍ እናድርግ
በተለይ ሲቪል ሰርቫንቶች፣ ለህዝቡ የለፉ ሰዎችን ውለታ እንዲሁም የመተባበርን ሀይል ከናንተ በላይ የሚያውቅ የለም። ትንሽ ሳንቲም ሲጠራቀም ብዙ ይሆናል። ደሞዛችን ይበረክት ዘንድ ሰደቃ እናውጣበት መቶ ብርም ቢሆን።
***
መሀመድ ቡሌን እንደግፍ
#ኮሚቴዎች
1 አሊ(ኑረዲን አህመዲን 0900830529)
2 ኢማም ሸምሱ አስፋ (0955328641)
3 ሀጅ ረውነቅ ሰማን (0938959926)
#አካውንት
CBE (ንግድ ባንክ) 1000532001521
Iklas ዳሽን 2943842990911
***
ቀጥታ መሀመድ ቡሌን ማግኘት የምትፈልጉ 0910650822
ቴሌግራም ግሩፕ ተቀላቀሉ
https://t.me/Yosisi_Charity
ዋትስ አፕ ግሩፕ ተቀላቀሉ
https://chat.whatsapp.com/JyQbadxGkEoDFRpITDKjsT
708 viewsAdu Emru, 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 00:03:07
#ሼር አድርጉት
***
ሳውዲ ያላቹ ወንድሞች ከስር የምትመለከቱት የወንድማችን (ቶዮታ ኮሮላ) መኪና ስለጠፋ በዬትኛውም ሁኔታ ካያችሁ በስልክ ቁጥር 0509074102 አሳውቁ
ሼር በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ
መኪናውን ተጠቅመው ወንጀል እንዳይሰሩበት እንተባበር
***
ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
837 viewsHabib Kedir, 21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:51:43
በአዲስ አበባ ዙርያ የድሆች ስቃይ
***
1ኛ መሬቶቹን ባለቤት ነን ያሉቱ ሽጠውት ነው
2ኛ ቤቶች ሲሰሩ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ገንዘብ ተቀብለውበት ነው ያሰሩት
3ኛ ይገባኛል የሚል ሲመጣ፣ ለልማት ሲባል፣ እንዳይፈርስባችሁ እንከላከል በማለት ገዢው ብዙ ገንዘብ አውጥቷል
***
ቤቶቹ ሲሰሩ ከመሰረቱ መከላከል ይቻል ነበር
አንዱ አመራር ጉቦ ተቀብሎ ቆሞ ቤት ያሰራል፣ ያሻሽጣል፣ ሌላኛው አመራር ደግሞ ዶዘር ይዞ መጥቶ የድሆችን ቤት ያፈርሳል።
ይህ የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ጭካኔ ነው
የሚገርመው እኮ፣ ቤት የሚፈርስባቸው የተረፋቸው፣ ባለሀብቶች ወይም ደላላና ነጋዴዎች አለመሆናቸው ነው።
የቀን ስራ የሚሰሩና ከእጅ ወደ አፍ የሚኖሩ ሚስኪኖች ናቸው።
***
አብዛኛው ሰው ሜዳ ወድቋል
ቤተሰቡን የሚበትንና ጎዳና የሚወጣ በርካታ ህዝብ እንዳለ መገመት ቀላል ነው
ትምህርት የሚያቋርጡ ብዙ ህፃናት እጣ ፈንታቸው ምን እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልጋል
የፌደራልና የኦሮሚያ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጡበት ይገባል
ቢያንስ የተሰሩትን በክፍያም ቢሆን በፕላንና ህጋዊ አድርጎ ከዚህ በኋላ የሚሰሩ ህገ ወጥ ቤቶችን ማስቆም ይቻላል
በዜጎች ላይ ከመጠን ያለፈ ጭካኔ ተገቢ አይደለም
ድሀ ጉልበት ባይኖረው እምባ አለው
****
በመጨረሻም በየ አከባቢው ቤታቸው ፈርሶባቸው ሜዳ የወደቁና የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ አለብን፣ ፆም ነው ሙስሊሞች ማፍጠርያ እንዳያጡ እንረባረብ። የክርስትያኖቹም ፆም ነው፣ መጪው ፋሲካ በሀዘን እንዳያሳልፉ መረዳዳት እንዳንረሳ። በተለይ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኙ ህዝቦች ናቸው ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀቤና፣ ወለኔ በርከት ያሉ ናቸው። ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ዩኒቨርስቲዎችና ተቋማት እንደ ዋዛ የትም የተጣሉ ዜጎቻችንን በቅንጅት አግዙ።
***
976 viewsAdu Emru, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 05:04:35 ወንድማችን
363 viewsHabib Kedir, 02:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 05:00:38
370 viewsHabib Kedir, 02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 22:14:42
#ሂቲጎት
***
የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት የግብር ከፋዮች የእለት ገቢ ግመታ ማድረግ ጀምሯል።
ወልቂጤ ከተማ ዙርያ ያላችሁ ነጋዴዎች አመታዊ ግብራችሁን ለቀቤና ልዩ ወረዳ መገበር እንዳትረሱ
ቅድመ ግመታም የወረዳው ገቢዎች እንዲገምቱላችሁ አድርጉ
የንግድ ፍቃድ የሌላችሁም በወረዳው ንግድ ቢሮ በኩል ፍቃድ አውጡ
***
በወረዳው ከተማ ዙርያ ቀበሌዎች በርካታ የንግድ ተቋማት አሉ። ገቢያቸውን ለወረዳው እንዲያደርጉና ድንበር አቋርጠው ከወልቂጤ የሚላኩ ሴረኛ ግብር ሰብሳቢዎችን መከላከል አስፈላጊ ነው። አዲስ አበባ ዙርያ ሸገር ከተማ እንደተመሰረተው ሁሉ ቀቤናም ከሸገር ተሞክሮ በመውሰድ በልዩ ወረዳው አምስት ክፍለ ከተማ ያለው ትልቅ ከተማ መመስረት ይችላል።
የሚመሰረተው ከተማም ለወልቂጤ ጠባቂዋ ይሆናል
ቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት
#አሲኖ
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ
666 viewsHabib Kedir, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:33:20
#እንተዛዘን
በሁሉም እምነት ወቅቱ የፆም ነው
***
ታላቃችን መሀመድ ቡሌ አንድም ቀን ለራሱ ያልኖረ፣ ሁል ግዜም ስለ ህዝቡ ከፍታና ነጻነት የሚጨነቅ፣ አርቆ አሳቢና ባለ ብሩህ አዕምሮ፣ ጀግናና ደፋር ነበር።
አሁን ያ ጀግናና ታታሪ፣ ለሰው አዛኝና ሩሁሩህ ሰው ታሞ ቤት ከዋለ አመታት ተቆጥረዋል፣
መንቀሳቀስ አይችልም ውሎ አዳሩ ዊልቸር ላይ ሆኗል።
እራሱን ችሎ መጸዳዳት አይችልም።
ህመሙ ከባድ በመሆኑ በየወሩ መድሀኒት ያስፈልገዋል
በዊልቸር ወደ መጸዳጃ እንኳን ለመድረስ የተስተካክለ ቤትና ግቢ የለውም።
የህጻን ልጆች አባት ነው፣ በማረፍያ እድሜው በሰው እጅ ወድቋል
**
ይህን ለህዝቡ ታላቅ ውለታ የዋለ ዋርካ ሰው፣ የመጨረሻ ዘመኑን በደስታ ያሳልፍ ዘንድ ማድረግ የሚገባን ሁለት ነገር አለ
1ኛ የሚኖርበትን ጠባብ አንድ ክፍል ቤት ማሻሻል። ተሸክማ መጸዳጅ የምትወስደው የልጆቹ እናት ባለቤቱ ናት። ደህና ዊልቸር ኖሮት በተስተካከለ ግቢ እንዲንቀሳቀስና መጽዳጃ በዊልቸር እንዲሄድ በማድረግ ይገባናል
2ኛ የህክምና ወጪውን በመሸፈን ጥሩ ህክምና እንዲያገኝና ቤተሰቦቹ እንዳይራቡ ድጋፍ ማድረግ አለብን
****
ለዚህ የሀገር ባለውለታና ታላቅ ሰው ይህን ማድረግ አያቅተንም ግዜው ረመዳን ነው መሀመድ ቡሌ ደጅ ጠንቶ የሰው እጅ አይቷል፣ እርዱኝ ብሏል። የዘንድሮ ሰደቃችንን ለሱ እናውል እንደ ህዝብ ከወደቅንበት ለማንሳት የታገለን ብርቱ ሰው እኛ ከወደቀበት እናንሳው
***
በኮሚቴ አካውንት ተከፍቷል።
1 ኢማም ሸምሱ አስፋ
2 ሀጅ ረውነቅ ሰማን
3 ኑረዲን አህመዲን(አሊ)
ንግድ ባንክ 1000532001524
Iklas ዳሽን 2943842990911
**
ዋትስ አፕ ግሩፕ በሚቀጥለው ሊንክ ተቀላቀሉ https://chat.whatsapp.com/JyQbadxGkEoDFRpITDKjsT
654 viewsHabib Kedir, edited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 21:34:11 የእስከዛሬው ጭቆና #ይበቃል
ፊታችንን ወደ ልማት እናዙር
***
አጎቶቼ የክልልነት አጀንዳ አለመሳካቱን ካረጋገጡ በኋላ፣ ሰሞኑን በተለያዩ መድረኮች ቀቤናና ማረቆ እራሳቸውን ችለው አይውጡብን፣ ጉራጌ ይበታተናል እዬዬ ማለት ጀምረዋል
የሚገርም ነገር ነው
የጉራጌ አንድነት የተመሰረተው በሌሎች ብሔረሰቦች ጫንቃ ላይ ነው እንዴ?
ጉራጌ እንደይበታተን ተብሎ የቀቤና ብሔረሰብ የሚጨፈለቅበት ምክንያቱ ምን ይሆን?
የቀቤና እራስን በራስ ማስተዳደር በዬትኛው ስሌት ነው ጉራጌን መበታተን የሚሆነው?
***
አንድ ግልፅ እውነት መናገር እችላለሁ
ቀቤና ከጉራጌ ዞን ነፃ ሰለወጣ ጉራጌ የሚበታተን ከሆነ፣ "በሌሎች ጫንቃ የተገነባ ማንነት ካለ አስፈላጊ አይደለምና" ሺ ግዜ ይበታተን።
እራሱን የቻለ፣ ነፃ ቀቤና እንጂ የጉራጌ አኗኗሪ አለመሆናችንን ሁሉም ይወቅ።
እንደ ድሮ ከንፈር የሚመጥላችሁ፣ የዋህና የሚታለል የቀቤና ትውልድ አሁን የለም
ቁርጣችሁን አወቁ፣ እርማችሁንም አሁኑኑ አውጡ #ቀቤና_እራሱን_በራሱ ያስተዳድራል።
***
የጉራጌ አመራሮች፣ ሙሁራን፣ ፖለቲከኞችና ወጣቶች ቁጭ ብላችሁ ምከሩ። ብልጥ ሁኑ፣ ጉራጌ እራሱን ችሎ ካልቆመና አሁንም ቀቤናን ማረቆንና ወለኔን ጨፍልቄ አቆያለሁ ካለ ከባድ ፈተና ይገጥመዋል። ዞኑም ይሁን ቀጠናው ወደ ልማት መሻገር አይችልም። የመጣንበት የአዙሪትና የጭቅጭቅ ግዜያት ይቀጥላሉ። ጉራጌ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጫንቃና የዘመናት ጭቅጭቅ ነፃ ሆኖ እራሱን ችሎ መቆም አለበት። እዛኔ ተረጋግቶ መልማትም ይሁን እራሱን መፈተሽ ይችላል።
****
የጉራጌ አመራሮችና ባለሀብቶች አከባቢያችሁን ለምን አላለማችሁ ሲባሉ ምክንያታቸው በአከባቢው ጭቅጭቅ ስላለ የሚል ነው። ይህ ጉዳይ መቀጠል የለበትም እልባት ማግኘት ይገባዋል። በዞኑ ሌላ የግጭትና የንትርክ አመታት አያስፈልጉም፣ ጉራጌ እራሱን ችሎ ይቁም። ቀቤናም ከጉራጌ ነፃ ሆኖ እራሱን በራሱ ያስተዳድር እዛኔ ቀጠናው ሰላም ይሆናል፣ ህዝቡም ፊቱን ወደ ልማት ያዞራል።
****
ከዚህ በኋላ የቀቤና ህዝብን በጉራጌ ዞን እንዲቀጥል ሴራ ማሴር ማለት አከባቢውን ወደ ለየለት ግጭትና ጦርነት መክተት ነው። በፍፁም የተረጋጋ ቀጠና አይፈጠርም፣ ይህን ሁሉም ማወቅ አለበት። በፈለጋችሁት እምላለሁ የቀቤና ህዝብ በጉራጌ ዞን መዋቅር አይቀጥልም። ስጋቱ ከተማ ከሆነ ለሁሉም ይበቃል፣ ቀቤና ውስጥ ጉራጌ ካለ ደግሞ በፈለገው መዋቅር ይገባል፣ ሌላ ወረዳ ያለው ቀቤናም እንደዛው። ከዛ ውጭ አበደን የዚህ ትውልድ ቀቤና #በጉራጌ_አይገዛም(ጊምቦም ከደሜን ገሉ) ካለ ቆይቷል።
ጉራጌ እራሱን ይቻል
ቀቤናም እራሱን ይችላል።
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ
779 viewsHabib Kedir, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 18:39:13 #አሞታል(መሀመድ ቡሌ)
ሰው በሌለን ሰዓት ሰው ሆነው ያገዙንን ባለውለታዎች አንርሳ
****
በ1976 የህዝባችን ጉዳይና መጻኢ እጣ ፈንታ አሳስቧቸው ከተንቀሳቀሱ ታላላቆቻችን አንዱ ነው መሀመድ ቡሌ። በወቁቱ በቀቤና የመጀመርያ የትግል ችቦ የሆነውን የምክክር ኮንፈረንስ እና የወጣቶች ግንኙነት በግንባር ቀደምትነት መርቷል። በውይይቱ ጥናታዊ ጹሁፍ በማቅረብ ህዝባችን ለነጻነቱ በሚታገልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ሰጥቷል
በደርግ አገዛዝ ወቅት በየአመቱ በሚከበረው የመስከረም 2 ክብረ በዓል የቀቤና ኪነት ቡድንን በመድገፍና በመምራት የቀቤና ብሔረሰብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ታሪኩና ወጉ እንዳይጠፋ ከአዲስ አበባ እየተመላለስ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል
ከደርግ ውድቀት በኋላ የቀቤና ህዝብ የነጻነት ትግሉን ያቀጣጠለው ድርጅት ቀብዴድ ሲመሰረት ከብርቱ አባቶቻን ጋር በመሆን በሀሳብና በአካል ተንቀሳቅሶ ደግፏል
የቀቤና የምንግዜም ታላላቅ አባቶቻችን እነ ሀጅ ፈትሁዲንና ሀጅ አህመደል ሀዲ በ1985 አዲስ አበባ ድረስ መጥተው የቀብዴድ ቅርንጫፍ ሲያቋቁሙ ኮሚቴ በመሆን ተመርጦ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ በመሆን በትጋት ህዝቡን አገልግሏል።
መሀመድ ቡሌ በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀቤንኛ ቋንቋ አዘጋጅ የነበረው ጀግናው ጋዜጠኛ ሙባሪክ ሙደሲር ለስልጠና ሲሄድ እሱን ተክቶ ከ1986 እስከ 1987 በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀቤንኛ ቋንቋ አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን የቀቤና ብሔረሰብ ቋንቋ እንዲጎለብትና ተደራሽ እንዲሆን ለፍቷል።
በ1987 የቀቤና ህዝብ በጉራጌ ዞንና በጎሮ ወረዳ መደራጅቱን በመቃወም በ28 ቀበሌ የሚገኘው ቀቤና ግብር አልገብርም ብሎ ትግሉን ሲያቀጣጥል ከአዲስ አበባ ድረስ በመሄድ የህዝቡን እንቅስቃሴ መስመር በማስያዝ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የቀቤና ተወካዮች በመዋቅሩ ተካተው ምክር ቤት እንዲገቡና ትግሉ ህጋዊ መስመር እንዲይዝ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል።
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በቀቤንኛ ቋንቋ እንዲተረጎም የብሔረሰቦች ምክር ቤት በጠየቀው መሰረት በመተርጎምና በማስተባበር ከጀግና ወንድሞቹ ከዘይኑ አክመልና ሙዜ ጋር በመሆን 44 ገጽ ለህትመት እንዲቀርብ በማድረግ ለፌደሬሽን ምክር ቤት(አልማዝ መኮ) አድርሷል።
የደቡብ ብሔረሰቦች አጠቃለይ እንቅስቃሴ ወደ ሀዋሳ ከዞረ በኋላ ብዙ ግዜ የቀቤና ህዝብን መብት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ሀዋሳ ድረስ በመመላለስ መርቷል፣ አስፈጽሟል።
በ1991 ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሄደም በኋላ የቀቤና ብሔረሰብ እድር ጠንካራ እንዲሆን በመደገፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ታላቁ የቀቤና ልማት ማህበር በሳውዲ ሲመሰረት መድረክ የመራው ይህ ጀግና ወንድማችን ነው። ልማት ማህበሩ ተቋቁሞ በሁለት እግሩ እንዲቆምና እውን እንዲሆን ትልቅ መስዋትነት ከከፈሉ ወንድሞች ውስጥ ቀዳሚው ነው።
በአጠቃላይ በሳውዲ ቆይታው የቀቤና ህዝብ በሚገጥሙት ኩነቶች ሁሉ መድረኮችን በመምራት፣ በኢቲቪና በተለያዩ ሚድያዎች እንዲቀረጹና እንዲተላለፉ በማድረግ በቆንጽላና በኤንባሲዎች በመገኘት፣ የተቸገሩትን በመርዳትና በማስተባበር፣ የተጣሉትን በማስታረቅ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር በተግባር የገለጸና ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ጀግና ነው
***
አስተባባሪ ኮሚቴ ተዋቅሯል
በጣም በምትወዷቸውና በምታምኗቸው ታላላቅ ሰዎች፣ አካውንት ተከፍቷል።
1 ኢማም ሸምሱ አስፋ
2 ሀጅ ረውነቅ ሰማን
3 ኑረዲን አህመዲን(አሊ)
ንግድ ባንክ 1000532001524
Iklas ዳሽን 2943842990911
***
የኮሚቴዎች ስልክ
1 አሊ(ኑረዲን) 0900830529
2 ኢማም ሸምሱ 0955328641
3 ሼህ ረውነቅ 0938959926
የራሱ የመሀመድ ቡሌ 0910650822
እኔንም በውስጥ አናግሩኝ
ደግ ደጉን እናስብ
በጎ በጎውን እንስራ
መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና
***
የበጎ ተግባር ማስተባበርያ የቴሌግራም ግሩፕ ተቀላቀሉ
https://t.me/Yosisi_Charity
ለማስተባበር ተብሎ የተከፈተውን የዋትስ አፕ ግሩፕ በሚቀጥለው ሊንክ ተቀላቀሉ https://chat.whatsapp.com/JyQbadxGkEoDFRpITDKjsT
792 viewsAdu Emru, edited  15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ