Get Mystery Box with random crypto!

Habib Kedir

የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir H
የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir
የሰርጥ አድራሻ: @habib_kedir
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.93K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-20 21:30:55
በመጀመርያ ለውድ ቤተሰቦቼ፣
በመቀጠል ለቀቤና ህዝብ በተለይ ለኢወማ ወጣቶች፣
እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ
እንኳን አደረሳችሁ፣ የደስታ ዒድ አልፈጥር እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኛለሁ!
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
408 viewsAdu Emru, edited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:36:10 ነገ ጁመዓ የረመዷን ኢድ መሆኑን ሳውዲ አሳውቃለች
እንኳን አደረሳችሁ
ለዓመቱ ሳይለይ ያድርሰን
526 viewsAdu Emru, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 01:08:28
ስልጤ እና ሀላባ እራሳቸውን ችለው ከመደራጀታቸው በፊት ልክ እንደኛው ነበሩ። ነፃነታቸውን ካወጁ በኋላ በብዙ ደረጃ ተለውጠው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆነዋል።
ኢንሻ አላህ
በሚቀጥለው ረመዷን…
የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ደማቅ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቶ
የቀቤና ልጆች ከያለንበት ተሰባስበን
የጉራጌ ዞን ህዝበ ሙስሊምን በክብር ጋብዘን
አጠቃላይ ጎሮቤት ህዝቦችንና የሚወዱንን ጋብዘን ደማቅ የጎዳና ኢፍጣር እናዘጋጃለን። ልክ እንደ ሀላባ፣ ልክ እንደ ስልጤ #ታላቅ_የጎዳና_ላይ_ኢፍጣር_በቀቤና ልዩ ወረዳ ተብሎ የአለም ሚድያ ይቀባበለዋል
ይሄ በአላህ ፍቃድ እውን ይሆናል
***
ሌሎችም እራሳቸውን ችለው ሲያዘጋጁ ከጋበዙን በፍቅርና በክብር፣ በቀና መንፈስ ተገኝተን ፕሮግራማቸውን እናደምቃለን፣ ፍትሀዊነትና መከባበር በመሀላችን ይነግሳል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
1.2K viewsAdu Emru, 22:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 23:30:29
በቀቤና ወረዳ ሞክር ቤት እንደ እርምት ቢወሰድ የምለው ሀሳብ አለኝ።
ዞን ያሉ አመራሮች ያለ በቂ ምክንያት በማንነታቸው ምክንያት ሲባረሩ ለምን ብሎ መጠየቅና ተተኪ ሲፈለግ ፍቃደኛ አለመሆን አስፈላጊ ነው። በፈለጉት ሰዓት ጠንካራ ልጆችን በግፍ አባረው ሲያበቁ እልል ብሎ ተቀብሎ ተተኪ ሌላ ጠንካራ ሰዎችን መመልመል አያዋጣም። ነገ በየተራ ዞን እያወጡ ይፈጠፍጡናል፣ ከዞኑ ጋር ያለንን ግንኙነት በጥርጣሬ መመልከትና በአቋም መቆም ተገቢ ነው።
***
ወንድማችን አብዲ በማንነቱ ምክንያት ከሀላፊነት ተነሳ እያልን፣ እሱን በፀጋ ተቀብለን ሌላ ጎበዝ ሰው መሸኘት ይምታታል። አቶ ላጫ እጅግ አደገኛ መርዝ ይዞ እተንቀሳቀሰ መሆኑን አንዘንጋ፣ ወጣቶቾ ረመዳን እየወጣ ነው የተደገሰልንን ክፋት ተመልክተን ወደ ማይቀረው የነፃነት ትግላችን እንግባ፣ መዘናጋት ገዳያችን ነው።
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
1.1K viewsHabib Kedir, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 13:25:54
በቀቤና ወረዳ የተደረገ የአመራር ሽግሽግ
**
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የነበረው አቶ አብደላ ጀማል በሀላፊነት ወደ ዞን ሄዷል
አቶ ዘይኑ ሻቡዲን የቀቤና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ሲሾም
አቶ ካፉ አረቦ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆኗል
አላማው በህብረት ጠንክረው የቆሙትን በማሸጋሸግ ንፋስ እንዲገባ ማድረግ ነው፣ ነገር ግን ለኔ ምንም አይነት ለውጥ ያለው ጉዳይ አይደለም። ሁሉም ልጆች በጥንካሬያቸው የምናውቃቸው የቀቤና ህዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ላይ ለአፍታም ቢሆን አቋማቸው የማይዋዥቅ ድንቅ ልጆች ናቸው።
***
ባለፈው ጠንካራ ወንድማችንን ከዞኑ ሀላፊነት አነሱት፣ አሁንም በጣም ተናበው የሚሄዱ የወረዳው አመራሮችን ሊበታትኑ በማሰብ ወንድማችንን ዋና የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አብደላ ጀማልን ወደ ዞን ወስደውታል። ሆኖም በሁሉም አመራሮቻችን ላይ ሙሉ እምነት ያለን በመሆኑ የሚያስደነግጠን አንዳች ነገር የለም።
***
ለመበታተንንና ለመከፋፈል ያሰበው አቶ ላጫ በህዝባችን የነጻነት ትግል ዙርያ በወረዳው ያለ የትኛውም የቀቤና አመራር አቋሙ አንድ መሆኑን ማወቅ አለበት። አቶ ላጫ ምንም ብትቀያይር ቁርጥ የሆነውን የቀቤናን እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ የሚያስተጓጉል አታገኝም እናም ባትለፋ ባይ ነኝ።
***
በዞኑ የቀቤና አመራሮች ከስራ መባረርና አሁንም አየተደረገ ባለው ሹም ሽር ክልል ያላችሁ የቀቤና ከፍተኛ አመራሮች አቋማችሁን ማወቅ እንሻለን። ዞኑ ከናንተ ሳይወያይና ሳይማከር በአንድ ሉዓላዊ የብሄረሰብ ወረዳ ጉዳይ እየፈተፈተ ከሆነ በግልጽ መቃወም አለባችሁ።
***
አንድ ሁሉም እርግጠኛ መሆን ያለበት የህዝባችን የነጻነት መሻት ከልጅ አስከ አዋቂ የጋራ ያደረገው የሞት ሽረት ጉዳይ ስለሆነ በሰዎች መቀያየር የሚደበዝዝ አያደለም።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
1.1K viewsHabib Kedir, 10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 01:03:49
በዚህ በተወደደው ለሊት የአዲስ አበባ የቀቤና ወጣቶች ኮሚቴ አንድ ሚስኪን ቤተሰብ ዘይረናል።
***
በግፍ ራይድ ላይ በዘራፊዎች የተገደለው ሳላሃዲን ወንድማችን ቤተሰቦች፣ ውድ ልጃቸውን ቢያጡም ሌላ ልጆች እንዳሏቸው አጠገባቸው ሆነን አሳይተናል።
የተከፉትን፣ የተቸገሩትን፣ ጤና የሌላቸውን፣ አቅመ ደካማዎችን አላህ ይድረስላቸው።
ክፉ አሳቢዎችን፣ ዛሊሞችን አላህ ቀልብ ይስጣቸው
በረመዳን የኛን ድጋፍ ለሚሹ ከጎናቸው እንቁም
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
353 viewsAdu Emru, 22:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 14:56:29 ይህን ተቋም እንደግፍ
የየቲም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው
#አንሷር የየቲሞችና የአቅመ ደካሞች መርጃ ማህበር
***
ለአዲስ አበባ ቅርብ ሆኖ፣ ብዙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያልገቡበት አከባቢ ልጥቀስ ብትሉ ቀቤና ወረዳ ወይም ወልቂጤና አከባቢው ቀዳሚ ነው።
አንሷር፦
ማንም አስታዋሽ በሌለበት፣
ብዙ ድርጅቶች ፊታቸውን ባዞሩበት አከባቢ፦
ትልቅ አላማ አንግቦ ተስፋ ባለመቁርጥ፣
በጽናትና በቁርጠኝነት የሚውተረተር ማህበር ነው
*
ይህ በጎ አድራጎት ማህበር ከተቋቋመ አጭር ግዜ ቢሆንም ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በርካታ ናቸው
አቅመ ደካሞዎችና ተረጂ ህጻናትን በየቀበሌው እየዞሩ የሚብሱትን ይለያሉ
ረመዳን ያሲዛሉ፣ ያስፈታሉ፣
ቤት ያድሳሉ፣ ይሰራሉ፣
የሚቀመስ ለሌላቸው እህል ያቀርባሉ፣
ሰዎች ጾም ወለው እንዳያድሩ ይተጋሉ፣
የትምህርት ቁሳቁስ ለህጻናት ያቀርባሉ፣
ልብስ ያለብሳሉ የሚስኪኖችን እምባ ያብሳሉ
ከዚህ በላይ የሚያስደስት ተግባር የትም የለም
***
ይህን የሚያስተባብሩ ወንድሞች ፍጹም በሆነ ቅንነትና በነጻ ተግባራቸውን ይፈጽማሉ፣
ፈጣሪ ለሃይር ስራቸው በመልካም ይመነዳቸው ዘንድ ዱኣ እናድርግላቸው።
የያዙት ግዙፍ ሀሳብ ነው
በቅርብ ቀን እንኳን ለብዙ ህፃናትና አቅመ ደካማ ተረጂዎች በነብሳቸው ደርሰዋል።
የማህበሩ ገቢ የአከባቢው ህዝብና ሲቪል ሰርቫንቱ ነው።
የሚያግዛቸው ሀገር በቀልም ይሁን የውጭ ድርጅት የለም።
የማህበሩ መፈክር “#ሰደቃ_ገንዘብን_አታጎድልም” የሚል ነው።
እውነት ነው “መስጠት አያጎልም” ።
ሁላችንም የማህበሩ አባል በመሆን በጎ ተግባራቸውን ባለንበት እናግዝ፣ ማህበሩን ከፍ ያለና ጠንካራ እናድርገው።
***
አባል ለመሆን የምትፈልጉ መስፈርቱ ቀላል ነው፣ ሰው መሆንና ቅን መሆን ብቻ፣
ዛሬውኑ አባል ይሁኑ፣ መታወቂያ ይውሰዱ፣ በአካልም ጠይቋቸው፣
ወራዊ መዋጮ 20 ብር ነው
መታወቂያ ወስደን የአመት ባንዴ እንክፈል ብንል እንኳን 240 ብር ነው
እናፍጥነው ለበጎ ስራ ረፍዶ አያውቅም
ጽህፈት ቤታቸው
ወልቂጤ ኢሊናም መንደር አንሷር መስጅድ አጠገብ
የየቲም ጉዳይ የኔም ጉዳይ ነው።
***
በባንክ አካውንት ማህበሩን ለመርዳት፦

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000528883595(Ansar yeytimochna akmdekamoch)
አንድ ጉዳይ ባንተ ላይ ሲያስጨንቅህ ሰደቃ ስጥ፣
ሰደቃ ጉዳይን ያቃልላል ፣የልብ እረፍትም ይሰጣል።
ግሩፓቸውን ለመቀላቀል
በዋትሳፕ

Follow this link to join my WhatsApp group: https://chat.whatsapp.com/FcZ44j9aw5hB9VKelmCXT3
በቴሌግራም

https://t.me/+k5QVT8mMR85iYzg0
አንሷር የቲሞች እና አቅመ ደካሞችን መርጃ ማህበር
አንሷር
የየቲሞች አጋር
796 viewsHabib Kedir, edited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 10:57:48
ዛሬ ደማቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ ይካሄዳል። ወለኔዎች በባህላቸው ደምቀው ያፈጥራሉ፣ የተቸገሩትን ያስፈጥራሉ፣ የህዝባቸው ነፃነትም ቅርብ እንዲሆን ዱዓ ያደርጋሉ።
ማንም እንዳይቀር ብለዋል
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
የወለኔ ብሔረሰብ ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
575 viewsAdu Emru, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 21:41:39
ሀድያ(ስጦታ)
ደማቅ ኢፍጣር
***
ሰዎች ሊያጠለሿት፣ ስሟን ሊያጠፉ አቃቂር እየፈለጉላት ይውላሉ
እሷ ግን እንደ ፈንዲሻ ከዕለት ዕለት እየፈካች፣ መቻቻልን የሀይማኖት እኩልነትንና ሰላምን ለመላው ደቡብ እያስተማረች ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፈርጥ ሀድያ ሆስዕና
My favourite and lovely town
****
753 viewsHabib Kedir, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 17:13:52 ከአንገት በላይ ኢፍጣር በወልቂጤ
***
ኢፍጣር በወለኔ መሀል አምባ
አፍጣር በማረቆ
አፍጣር በሀላባ
ኢፍጣር በሀድያ
ሁሉም በዚህ ሳምንት ቀጠሮ ይዘዋል
***
#አፍጣር_በቀቤና መደረግ አለበት
መሰል ተግባራትን እራሳችንን ችለን ማድረግ ካልቻልን የውሳኔ ችግር አለብን ማለት ነው።
#ኢፍጣር_በወልቂጤ የተባለው ጥሩ ነው፣ ከተማ አስተዳደሩ እራሱን ችሎ ያድርግ፣ በወሰኑ ያሉ ልጆች ያስተባብሩ። የቀቤና ወረዳ ግን እራሱን ችሎ ኢፍጣር ማዘጋጀት ነበረበት።
***
የጎዳና ላይ ኢፍጣር እልም ያለ ፖለቲካ ከሆነ ቆይቷል። ሰዎች እምነታቸውን፣ ህብረታቸውን፣ ባህልና ቋንቋቸውን ለሌላው የሚያስተዋውቁበት አንዱ ዘዴ ሆኗል። ስለዚህ እንደግዜው መሆንና የቀቤናን ህዝብ ጠንካራ እምነትና እሴት ማስተዋወቂያ አድርጎ ኢፍጣሩን በራስ ቀለም ማካሄድ ወሳኝ ነው።
***
ኢፍጣር በወልቂጤ በሚል የዳቦ ስም፣ የሚሰሩት ፌክ አንድነት ብዙም አይጥመኝም፣ ሁሉም ለማሰመሰል ትንሽዬ ደቂቃዋን ይሳሳቃል እንጂ ከልብ የሚደሰት ማንም የለም። ኢፍጣር የጋራ ሲሆን ደስ የሚለው እውነተኛ መከባበርና መተሳሰብ ቢኖር ነበር። የበላይነትን ለመውሰድ የሚጋጋጡና በንቀት ከተሞሉ ኡስታዝ ነኝ ባዮች ጋር አደባባይ ባልታይ ምርጫዬ ነው።
****
ኢፍጣር በወልቂጤ የውሸት አንድነት መስበኪያ ነው፣ አፍጣሪውም ሆነ አዘጋጁ እራሱን ይፈትሽ። የቀቤና ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም ነው፣ ሲበደል፣ ሲሰቃይ ንብረቱ ሲወድም ግምባር ቀደም ወጊዎች እነዚሁ አፍጣሪዎች ናቸው። መጀመርያ የጥላቻ ካባ ከልባቸው ቢያስወግዱ ደስ ይለኝ ነበር።
***
በወልቂጤ ካፊሩ አንድም ግዜ ቀቤናን ደፍሮ በድሎ አያውቅም። ከነ ዳውድ ጀምሮ ሲያስገድሉን ንብረት ሲያወድሙብን፣ ቤት ሲያቃጥሉብን የነበሩት ለሰላት አወል ሰውፍ አብረው የቆሙት ናቸው። አሁንም ከኢፍጣሩ በፊት መነኻርያ በብሔር የሚሰሩትን ደባ ያቁሙ፣ በብሔራቸው ምክንያት ከተማ እንዳይሰሩ የተከለከሉ የሩሙጋ ባጃጆች መፍትሄ ያግኙ፣ በከተማ ትንኮሳው ይቁሙ፣ በሚድያ የበላይነት ለማሳየት መጋጋጥ ይቁም። ሀቅ ሀቁን ስናወራ የሚተናነቀው ብዙ ሰው አለ። እውነት ሁሌም እውነት ነው። በሙሉ ልብ አብረን ለማፍጠር ቀቤናን የሚጠሉ ሙስሊም ጉራጌዎችና ኡስታዞች ይስተካከሉ። ቀቤናን የሚበድሉ የሚያስተባብሩ እነ ማንና የነ ማን ልጆች እንደሆኑ ይታወቃል። በሚድያ እንኳን ሀሳብ ስንገልፅ ተሳዳቢዎቹና ጥላቻ የሚያንፀባርቁት 90% ሙስሊሞቹ ጉራጌዎች ናቸው ይህ እንኳን በቂ ማሳያ ነው።
***
ረመዳን ላይ ውሸትና ማስመሰል የማይሰለቸው ካለ 30 ደቂቃ ይንቀዋለል። ካልሆነ በትክክል ውስጣቸውን አስተካክለው ችግሮችን ፈትተው ይምጡ፣ አብሮ ማፍጠሩ ቀላል ነው። አዘጋጅ የኛ ልጆች የአብዛኛዎቹን ተንኮል የምትረዱ ናችሁ፣ ሙስሊሞቹን ጥላቻቸውን በልኩ እንዲያደርጉና እንዲያስተካክሉ ብትመክሯቸው ጥሩ ነው። ከአንገት በላይ ፍቅር አላህም አይወድም።
ያለፈው አልፏል ከዚህ በኋላ ቀቤና የአደባባይ ኢፍጣር እራሱን ችሎ ያዘጋጅ፣ ለዛ ከበቂ በላይ እስፖንሰርም አስተባባሪም አለን፣ ከመሀል አምባ፣ ከማረቆና ሀላባ በቂ ተሞክሮ ይወሰድ።
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
861 viewsHabib Kedir, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ