Get Mystery Box with random crypto!

Habib Kedir

የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir H
የቴሌግራም ቻናል አርማ habib_kedir — Habib Kedir
የሰርጥ አድራሻ: @habib_kedir
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.93K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-25 14:25:25
979 viewsAdu Emru, 11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 14:18:23
938 viewsAdu Emru, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 12:57:13
ወልቂጤ 7
***
ወልቂጤ ጠባቂ ባለቤት ህዝብ እንዳላት ዛሬ አስመስክረናል
ይህን ቀውጢ የዶክተር አብይ አቀባበል በወልቂጤ ተመልከቱ ሼር በማድረግ ውሸታቸውን አጋልጡ።
***
ለመሪ ክብር በመንፈግ የፖለቲካ ጥቅም የሚገኝ የመሰላቸው ሁሉ ጠቅላዩን አንቀበልም ብለው ቤት ቢቀመጡም፣ ጀግናውና እንግዳ አክባሪው የቀቤና ህዝብ መሪውንና እንግዳውን በደማቁ ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል። የህዝባችን ታላቅነትና ክብር ማረጋገጫው ይህ ነው
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
ወልቂጤ
945 viewsAdu Emru, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 12:02:22
ወልቂጤ6
***
ለሊት 11 ሰአት ተነስቶ ባዶ አስፓልት ፎቶ በማንሳት የሚሳካ የፖለቲካ ሴራ አይኖርም። እንግዳ አክባሪው የቀቤና ህዝብ በባህሉ ደምቆ፣ መሪውን አክብሮ፣ በታሪካዊ ርስቱ ወልቂጤ ከተማ ለጠቅላዩ ደማቅ አከባበር በማድረግ ለልዩ ወረዳው ጥያቄ ጠንካራ መሰረት ጥሏል
**
ዝቅ ሲያደርጉት ከፍ የሚል ጀግና ህዝብ
ቀቤናዬ ኮርቻለሁ
ከጠቅላዩ ጀርባ all my People
መሪውን ያከበረ ይከበራል
ያላከበረ አይከበርም
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ
ወልቂጤ
946 viewsHabib Kedir, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 21:59:15
መቅናት ካለብህ በመልካም ነገር ቅና
***
በስልጤ ረመዳን ከመገባቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ #የዱዓ፣ #ይቅር_የመባባል እና #የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ የዞኑ ሁሉም ወረዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣  ከክልል እስከ ፌደራል የስልጤ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል።
እርስ በርስ አውፍ ተባብለዋል፣ ለሀገር ሰላም ተመራርቀዋል፣ ስልጤን ለማልማት ቃል ተገባብተዋል፣ ተሸላልመዋል።
***
ከሁሉም በላይ ለስልጤ ነፃነት ትግል ላደረጉ ሁሉ መታሰቢያ የሚሆን ቤተ መፃህፍት ለማስገንባት መሰረተ ድንጋይ ተጥሏል። ሚ/ር ሙፈሪያት ካሚል ለህዝቧ ነፃነት ላበረከተችው ከህዝቧ የክብር ካባ ተደርቦላታል።
ከቀናህ በዚህ መቅናት ነው
***
ከስልጤ ብሔረሰብ የምንማረው ብዙ ነገር አለ
በስልጤ የማያልፉ የሚመስሉ የጨለማ ግዝያት በብዙዎች መስዋዕትነት አለፈዋል።
ጨቋኞች የስልጤ ሴቶች በባህላቸው መሰረት የተሰሩትን ሽሩባ ዞረው ያስፈቷቸው ነበር፣ ባህላቸውን እንዳያቆዩ። ሁሉንም አልፈው ዛሬ የእድገት ሞዴል የሆነ ከተማና ዞን መስርተዋል።
***
ይህ በቀቤናም እውን ይሆናል
በትግላችን ነፃ እንወጣለን፣ የቀቤና ሙሁራን፣ አመራሮች፣ ባለሀብቶችና ታጋዮች በያላችሁበት ጠንክሩ። ከፊታችን ግዜው ብሩህ ነው፣ በትክክልም መንጋቱ አይቀርም፣ የነፃነት ጮራ በቀቤና ይፈነጥቃል። አሻራ ያሳረፋችሁ ከነፃነት በኋላ በስማችሁ መታሰብያ ተቋም ይገነባል፣ ትውልድ ሁሌም እየዘከራችሁ ይኖራል። በሽማግሌዎች ዱዓ እንደ ሙፈርያት ተጠርታቹ ትመረቃላችሁ።
እንበርታ!
***
#ስልጤነት
ስልጥነት ኡንኮ መጥ ኤበልነት
ስልጥነት ሀድነትን
ስልጥነት ሙሃባን
ስልጥነት ቲናነሶትን
ስልጥነት የሳድ ባድ አጥናቦትን
ስልጥነት ዲን ቂሮትን
ስልጥነት ባድ ቂሮትን
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ
482 viewsAdu Emru, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 17:44:39 አጎቶቼ ክልል "#አይጠቅማችሁም" ተብለዋል
***
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከጉራጌ ባለሀብቶች ጋር በአአ ተወያይቷል፣ ስብሰባውም በተናጥል የሚሰጥ ክልል የለም በሚል ተቋጭቷል።
ዶክተር አብይ "#አይጠቅማችሁም" ብሏል።
"የሚጠቅማችሁ ቢሆን ጉራጌን ክልል ማድረግ ቀላል ነበር። ጉራጌ ክልል የማይሆነው ህጉ ስለማይፈቅደው ሳይሆን ስለ ማይጠቅመው ብቻ ነው።" ብለዋል ጠቅላዩ። እንግዲህ እኛ ለአመታት ስንለው ካልሰማችሁ እንኳንም ከጠቅላዩ አንደበት ሰማችሁት።
***
ስብሰባው ምንም እንኳን የጉራጌ ዞን ባለሀብቶች ቢባልም የቀቤና፣ የማረቆና የወለኔ ተወካዮች አልተጠሩም።
በውይይቱ…
ከሌሎች ብሔረሰቦች በተለየ ሁኔታ ጉራጌ ክልል የሚሆንበትን ምክንያት አስረዱ ተብለው አንድም አሳማኝ ሀሳብ ሳያነሱ ቀርተዋል ባለሀብቶቹ። ይልቁንስ ለጉራጌ ህዝብ አብሮነትና አንድነቱን መጠበቁ አስፈላጊው እንደሆነ ሀሳብ ሰጪዎች ጠቁመዋል።
***
የምስራቅ ጉራጌ ባለሀብቶች ምዕራቦችን "ህዝባችንን አዋርዳችኋል" ያሉ ሲሆን እንደ ተለመደው ኮከብ ሆነው ውለዋል። ጉራጌ በማይታወቅበት ሁኔታ በመጥፎ ስም እንዲጠራ ያደረጉት ጥቂት አጀንዲስቶች እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲገነዘቡ ጠይቀዋል።
***
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጉራጌ ጠቃሚው አብሮነት እንደሆነ ደጋግመው የተናገሩ ሲሆን "ጉራጌን በስራው በቅርበት የማውቀው ህዝብ ነው" በማለት በማይረቡ የተልዕኮ አጀንዳዎች ግዜውን ሀብቱንና ክብሩን እንዳያጣ አጥብቀው ተናግረዋል። በተለይም ክልልነትን ምክንያት ተደርገው የተካሄዱ እንቅስቃሴዎች እንድምታቸው የክልልነት አጀንዳ እንዳልነበሩ የመረጃና የደህንነት ጥቆማ እንደሚያሳይ ገልፀዋል።
***
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው የብሔር ፖለቲካና የተናጠል ክልልነት ለጉራጌ ህዝብ አስፈላጊው እንዳልሆነ በመረጃ አስደግፈው ትንተና ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም ባለሀብት በሚባል መልኩ በሀሳቡ ተስማምተዋል። ባለሀብቶቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተለየ ክብርና ሙገሳ ሲያንበሸብሿቸው ውለዋል በተለይ አቶ ጠንክር የተባለ ሰው የጠቅላዩ ምክትል ነበር የሚመስለው።
***
በመጨረሻም የጉራጌ ባለሀብቶች መሪው ድርጅት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከመንግስት ጎን በመሆንና ከጎሮቤት ብሔረሰቦች ጋር በህብረት ሀገራቸውን እንደሚያለሙ ቃል የገቡ ሲሆን ጠቅላዩም በዚህ ሁኔታ መቀጠሉ "አይጠቅማችሁም" ከዚህ በኋላ "ይህ አጀንዳ ተዘግቷል" ብለው ባለሀብቱ ከመንግስት ጎን ቆሞ ልማቱን እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል።
***
ሲጠቃለል፡-የሶሻል ሚድያ የነ ዘሀበሻ ዘመቻና መሬት ላይ ያለው ሀቅ የተለያየ ነው። እንደ ዛሬው የባለሀብቱ ሁኔታ ጉራጌ ነገ ክልል ይሁን ተቀበሉ ቢባሉም እምቢ ክላስተር ይሻለናል የሚሉ ይመስለኛል፣ እውነቴን ነው
**
መረጃውን የሰጡኝን የምስራቅ ኮከቦችን አመሰግናለሁ
ለልማት እንዲመች…
ምስራቅ ጉራጌ ዞን ነው
ምዕራብ ጉራጌም ዞን ነው
ቀቤና ልዩ ወረዳ ነው
ማረቆ ልዩ ወረዳ ነው
ወለኔ ብሔረሰብ ነው
605 viewsHabib Kedir, 14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 02:10:42
መልካም የረመዳን ዖም ይሁንላችሁ
***
ለኢወማዎች፣
ውጭ ሀገር ለምትገኙ በሙሉ በተለይም ሳውዲ ለምትገኙ ወዳጅ ዘመዶቼ፣
ለቀቤና ህዝብ በሙሉ፣
በመላው አለም ለምትገኝ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ፣ ለተከበረውና ለታላቁ ወር ረመዳን እንኳን አደረሳችሁ
የቀቤና ህዝብ ነፃነት ከዚህ ረመዳን እንዳያልፍ ዱዓችንን እናቀርባለን
***
729 viewsHabib Kedir, 23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 17:08:17
ነገ ሀሙስ የጉራጌ ዞን ማህበረሰብ የሚሳተፍበት መድረክ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
ቀቤና ልዩ ወረዳ መሆኑን እራሳቸው እያረጋገጡ ነው
***
ነገ በአዲስ አበባ በሚደረገውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመሩት መድረክ ሁሉም የዞኑ ምክር ቤት አባላት ሲጠሩ የምክር ቤቱ የቀቤና ተወካዮች አልተጠሩም።
ጥሩ ነው
ስጋታቸው ጥያቄ ያቀርባሉ የሚል ቢሆንም ሴራው ከጉራጌ ዞን ጋር ላንገናኝ መለያየታችንን ያመለክታል።
***
ዘንድሮ እንደ ሌላ ግዜ ረመዳን ነው ብለን የምናቆመው የሶሻል ሚድያ እንቅስቃሴ አይኖርም
11ኛው ሰአት ላይ በመሆናችን ሁሉንም ነገር በንቃት እንከታተል።
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
885 viewsHabib Kedir, 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:39:59
#ረመዷን

የረመዷን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ታላቁ የረመዷን ጾም ሀሙስ መጋቢት 14 ይጀምራል።

እንኳን ለታላቁ የረመዷን ጾም በሰላም አድረሳችሁ።

ረመዷን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ
1.0K viewsHabib Kedir, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 08:20:14
329 viewsHabib Kedir, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ