2022-07-07 22:27:30
ክላስተርን በተመለከተ ግራ ለገባችሁ
***
የተለየ ምንም ነገር የለም
በክልሉ የተነሳውን የመዋቅር ጥያቄ በተመለከተ መንግስት ከአንድም ሁለት ግዜ አስጠንቶ ባገኘው መረጃ መሰረት ክልሉ በሁለት ክላስተር እንዲደራጅ ወስኗል።
አዲስ ክልል ሲመሰረት ባለው ህገ ደንብ መሰረት ውሳኔውን ወደ ህዝብ አውርዶ ማጸደቅ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። በመሆኑም ለአፈጻጸም ወደየ ዞኑ ተልኳል።
***
የደቡብ ሸዋ ክላስተርን በተመለከተ በመንግስት መድረክ ውሳኔውን ለማስፈጸም አምነው የወጡት የጉራጌ ከፍተኛ አመራሮች(የክልሉን መሪ ርስቱን ጨምሮ)፣ ባለሀብቶችን ካወያዩ በኋላ ፈራ ተባ ሲሉ ተስተውሏል። የጉራጌ ከፍተኛ አመራሮች ሁሉም ክላስተር ስለተስማማ ያልተስማማነው እኛ ብቻ ነን ስለዚህ ክልል እንሁን ብለው የጠቅላዩን ደጅ መጥናትም ጀምረዋል።
***
ይህንን ተከትሎ የመጀመርያ አማራጫቸውን ክላስተር ሁለተኛ አማራጫቸውን ደግሞ በየብሔረሰባቸው ክልል መሆንን ያስቀመጡት ሌሎች ዞኖች ወደ ሁለተኛው አማራጫቸው አማትረዋል። ይህ ትክክለኛ አካሄድ ነው ምክንያቱም በፖለቲካው አለም አንድ የሚባል አቋም የለም ፍለክሰብል መሆን ግዴታ የሚሆንበት ግዜ ይኖራል።
***
ዋናው ፍሬ ነገር ክልል የሚሰጥ ከሆነ ለጠየቁት ከ11 በላይ ዞኖች ይስጣል የሚቀርም ከሆነ ለሁሉም ይቀራል። ለሁሉም መስጠት ደግሞ አንድን የአማራ የሰሜን ሸዋ ዞንን አስራ አንድ ክልል ማድረግ ነው ምሳሌው። ይህ ደግሞ አሁን ብልጽግናና ዶክተር አብይ በሚያራምዱት አቋም በፉጹም እውን አይሆንም፣ በጭራሽ አይታሰብም።
***
ዛሬ እነ ታዬ ደንደኣ የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የዘር ወይም የብሔር አደረጃጀት ነው የሚል አንድምታ ያለው ጹሁፍ ጽፈዋል። የጠቅላዩ የቅርብ ሰው የሚባለው ፕ/ር ብርሀኑ ነጋም የሀሳቡ ተጋሪ ነው።
ከመሪው ድርጅትና ከመንግስት አቅጣጫ በላይ በባለሀብቶች የሚዘወሩት የጉራጌ አመራሮች እጣ ፈንታቸው እንደ አብዲ ኢሌ ሆኖ፣ እዛው ይዘያየሩ ይሆናል እንጂ፣ የበሬ ግንባር የምታክል መሬትና ተመሳሳይ ባህል፣ ታሪክና፣ መልከዓ ምድር ያለው ህዝብ 11 ቦታ አይበጣጠስም። ሁሉም ዞኖች አሁን የያዙት አቋም መንግስት ክላስተሩን ለማስፈጸም ለሚሄደው ቀጣይ መንገድ አጋዥ ነው።
***
እናም ክላስተርን በተመለክተ የተለወጠ የመንግስት አቋምም ይሁን የወረደ መመርያ የለም። ክላስተር እንደ ከሸፈ ወይም እንደተቀለበሰ አስመስላችሁ እራሳችሁን በራሳችሁ የምታረኩ ሰዎች ሰከን በሉ።
ከዞን መዋቅር ውጭ ያሉ እንደ ቀቤና ያሉ ብሔረሰቦች ክላስተር የመጀመርያ አማራጫቸው ሲሆን ሁለተኛው ያለማንም ጣልቃ ገብነት እራሳቸው በራሳቸው የሚወሰኑት ነው
***
የአረፋ በዓል በማክበር ላይ ለምትገኙ መልካም የአይብና የጎመን ክትፎ ቀን ይሁንላችሁ
608 viewsAdu Emru, 19:27