2022-07-04 21:22:29
የጉራጌ ፖለቲካ አዙሪት
****
አቶ ርስቱን ጨምሮ የጉራጌ ተወካይ ነን ያሉ ግለሰቦች በአዲስ አበባ እስካይ ላይት ሆቴል ክልልነትን በሚመለከት ስብሰባ አድርገዋል።
ስብሰባው በዋናነት ያስተባበረው አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ሲሆን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደሞዝ ቀርጥፎ እየበላ በመንግስት ላይ ሲያሴር ውሏል። መንግሥት ያስቀመጠውን የክላስተር አደረጃጀት ውሳኔ በመጣስ አድማ ሲያሳድምና ክልሉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ሲቀሰቅስ ነበር።
***
በውይይቱ በጉራጌ ዞን የሚገኙ ብሔረሰቦች ቀቤና፣ ማረቆ፣ ወለኔ አንዳቸውም አልተሳተፉም። እነዚህ ብሔረሰቦች በሌሉበት እነሱን አካተን ክልል እንሆናለን ብለው ወስነዋል።
መታወቅ ያለበት ጉራጌ እራሱን ችሎ ክልል አይደለም ሀገርም ቢሆን ችግር ያለበት የለም። ጉራጌ በዞኑ ያሉ ብሔረሰቦች ባልተወያዩበት እና ባልተስማሙበት ሁኔታ በጉልበት አስተዳድራቸዋለሁ ካለ ከፍተኛ ፀብ ይፈጠራል። ተምረናል፣ ህሊና አለን የምትሉ፣ መፃፍና ማንበብ የምትችሉ የጉራጌ ማህበረሰብ አባላት ይህን ግፍ ኮንኑ፣ የሚያልቀው ያልቃል እንጂ በተለይ የቀቤና ህዝብ በጉራጌ ስር መተዳደር በፍፁም አይፈልግም።
****
በስብሰባው የምስራቅ ጉራጌ ተወካዮች ለህዝባችን የሚበጀው መንግስት ባስቀመጠውና ሌሎች ብሔረሰቦች በተስማሙት መንገድ መሄድ የተሻለ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። እንደኔ የነሱ ሀሳብ የሚደገፍና የአከባቢውን ሰላም የሚያስጠብቅ ነው። ሌሎችም ለጉራጌ ህዝብ ከልብ የሚያስቡና ሊፈጠር የሚችለውን ውስብስብ ሁኔታ ቀድመው የተረዱ ብላቴናዎች "በህብረት መኖር ይሻለናል ብለዋል" እነሱ ትክክል ናቸው። ነገ ሁላችሁም ምትፀፀቱበት ሁኔታ ካልተፈጠረ እኔ ምንም አላቅም።
***
አቶ ርስቱ ፅንፈኞችን ለማሳመን ጥረት ቢያደርግም የክላስተርን ጥቅምና ጉዳቱን ለራሱም ስላልተረዳ የሚመጣው ይመጣ ስልጣንህን ልቀቅ ካላችሁኝ እለቃለሁ ብሎ ተስማምቶ ወጥቷል። ሁለት ማጣት ማለት ይህ ነው። እናም በዚህ ሰሞን መልቀቂያ ያሥገባል የሚል እምነት አለኝ። ይህ የክላስተሩን አፈፃፀም የሚያፈጥነው በጎ ተግባር ነው።
****
በመጨረሻም ሁሌም እንደምለው ጉራጌ ክልል የሚጠይቅ ከሆነ ቀቤናን ማረቆን አካትቼ የሚለውን እቃቃ አቁሞ እራሱን ችሎ ይጠይቅ። እመኑኝ ከዚህ በኋላ የቀቤናን ህዝብ በጉልበት የሚገዛ ጨቋኝን የሚሸከም ጫንቃ ያለው የለም። የቀቤናን ወረዳና ህዝብን ጨፍልቆ የሚመሰረት የጉራጌ ክልል በአናቱ ይተከል፣ እስከመጨረሻው አልደግፈውም።
ሼር አድርጉት
791 viewsAdu Emru, 18:22