2023-03-15 22:27:46
የቀቤና ብሔረሰብ ህልውና እንዲጠፋና እንዲቀጭጭ የማድረግ ጥረት…
#ይበቃል_3
***
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ አንድን ብሔረሰብ ከሚኖርበት አከባቢና መልከዓ ምድር ለይቶ ማየት እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡ በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 3 እና አንቀፅ 98 ንዑስ አንቀፅ 1፣ በቂ የሆነ የአካባቢው አስተዳደር በየደረጃው በሚዋቀርና በሚደራጅ እንዲሁም በህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ እና አካባቢውን በማልማት ለሀገር ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክት ዘንድ መብት ይሰጣል፡፡
**
ይሁን እንጂ እነዚህ መብቶች በቀቤና ብሔረሰብ ላይ በጉራጌ ዞንና በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በኩል ተግባራዊ አይደረጉም፡፡ ለነዚህም በቂ መገለጫዎችንና ማብራሪያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋና የሆኑትን ለማንሳት የምሞክር ሲሆን የማቀርባቸው ጉዳዩች በሃቅ ላይ የተመሰረቱና ማንኛውም ንፁህ አዕምሮ ያለው ሰው ሊያረጋግጣቸው የሚችላቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አበክሬ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
***
የመጀመሪያው የብሔረሰቡን ህልውና የማጥፋት ዘመቻ የተጀመረው በ1994 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ ቀድሞ የነበረው ጎሮ ወረዳ ለሁለት ተከፍሎ ቀቤና ወረዳ እና አበሽጌ ወረዳ ተብሎ እንዲደራጅ ተወስነ:: ከውሳኔው ማግስት ጀምሮ ብሄረሰቡ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ያገኘውን ህገ-መንግስታዊ መብት ለማሳጣት በነ መኩርያ ሃይሌ ይመራ የነበረው የጉራጌ ዞን አመራር ቀቤና ወረዳ የሚባል ስያሜ እንዳይኖር ከፍተኛ ጥረትና ጫና ቢያሳድርም ከወረዳው ህዝብ ጋር በተደረገ ውይይትና ህዝበ ውሳኔ ቀቤና ወረዳ ሆኖ እንዲቀጥል ተደረገ::
***
ቀቤና የሚል መጠርያ እንዲኖር የማይፈልጉ የጉራጌ ዞን አመራሮች ቀቤናን ከካርታ ለመፋቅ የሚያደርጉትን ጥረት በማጠናከር የቀቤና ባህልና ታሪክን በማቀጨጭ ህልውናው እንዲጠፋ ማድረጋቸውን በመቀጠል በ1999 ዓ.ም የቀቤና ህዝብ ሳያውቀውና ሳይወያይበት በቀቤና ወረዳ የሚገኘውን ቆላካ ባዳ የሚባለውን ቀበሌ ሙሉ በሙሉ በመዝለል ቸሀ ወረዳ ካለ ጉብሬ ከሚባል የገጠር ማዕከል ጋር ወልቂጤን በአንድ ማስተር ፕላን ለማስተሳሰር እቅድ ወጠኑ፥ ይህ የሚያሳየው እራሳቸውን ችለው መልማት ያለባቸውንና በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ ሁለት ከተሞችን በማስተሳሰር ስም ሉዓላዊ የሆነን ወረዳ መብት በመርገጥ ቋንቋውን ለማቀጨጭና ባህሉን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ነው፡፡
***
ቀቤና የወልቂጤ ከተማ በዕቅድና በፕላን እንድትመራ የሚፈልግና የሚመኝ ቢሆንም ይህንን ብሔረሰብ ለማጥፋት በማቀድ አንድ የገጠር ቀበሌ በመካከል እያለ እሱን አልፎ ሌላ መንደሮችን በማስተር ፕላን እንዲካተቱ መደረጉና ህዝብ ሳያውቅና ሳይወያይ እጅግ በጣም ስፋት ያለውን ቀበሌ ለማካለል መሞከር የጉራጌ ዞንን አምባገነንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
***
ይህን 7300 ሄክታር ስፋት ያለውና እንደ አዳማና ሀዋሳ ካሉ የሃገራችን ትልልቅ ከተሞች የሚስተካከል ስፋት ያለው መሬት በዕቅዳቸው ውስጥ እንዲካተት ማድረጋቸው የረዥም ጊዜና ሁሉን አካታች ፕላን ለማዘጋጀት ካላቸው ቅን አመለካከት ሳይሆን የብሔረሰቡን ቋንቋና ባህል በማቀጨጭ በሂደት ብሔረሰቡን የማጥፋት ከረዥም ጊዜ ዕቅድ የመነጨ ለመሆኑ ህብረተሰቡ ሳይሳተፍ በዕቅድ ያዘጋጁት ፕላን ማሳያ ነው፡፡
***
ይበቃል_4 ቻሌንጅ ይቀጥላል…
ሁላችሁም ፁሁፉን ሼር በማድረግና ምስሉን ፕሮፋይል በማድረግ ዘመቻውን ተቀላቀሉ።
የቀቤና ህዝብ የልዩ ወረዳ ጥያቄ ለምን እንዳቀረበና አስፈላጊነቱን ለሁሉም ግንዛቤ እንፈጥራለን
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ
740 viewsHabib Kedir, 19:27