2023-03-17 20:12:42
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ወልቂጤ ይመጣሉ
****
የጉራጌ አመራሮችና አጠቃላይ ህዝቡ ገዢውን ፓርቲና ጠቅላይ ሚንስትሩን በግልፅ ይቅርታ ሊጠይቁ እንደሆነ ሰምተናል።
ቢዘገይም፣ ብዙ ኪሳራ ቢያስተናግድም ጥሩ ነው
***
የጉራጌ አመራሮች ቃለ መሀል የፈፀሙበትን የድርጅቱን መርህ በመጣስ በሁለት ቢላ እየበሉ ዞኑን ሲያሸብሩና ህዝቡን ሲያወኩ ከርመዋል።
በመጨረሻ የመንግስትን ቁርጠኛ አቋም የተረዱት ክልል አስመላሽ ኮሚቴዎች፣ በጠቅላይ ሚንስትሩ ፊት ለፈጠሩት ግርግር ይቅርታ ጠይቀው፣ እንደማይደገምም ቃል ይገባሉ ተብሏል። ከጠቅላዩ ጋር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ይመጣሉ።
****
በመድረኩ የቀቤና፣ የማረቆና የወለኔ ብሔረሰቦች ከጉራጌው እኩል ውክልናና ተሳትፎ ማግኘት አለባቸው።
ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለቀቤና ብሔረሰብ ታሪክና የመብት ጥያቄው በቂ ግንዛቤ ቢኖራቸውም፣ አንዳንዴ መድረክ ለማሞቅ የሚጠቀሟቸውና አብዛኛውን ሰው ለማስደሰት(ለማስጨብጨብ) የሚወረውሯቸውን ቃላት ተከታትሎ የሚያርም ያስፈልጋል።
***
ሁሉም ማወቅ ያለበትና መድረክም ከተገኘ መነገር ያለበት የቀቤና ህዝብ ሀቅ…
1 የቀቤና ብሔረሰብ ቀጥታ ከመንግስት መገናኘት ይፈልጋል። በጉራጌ በኩል አልፎ መንግስትን ማግኘት ማክተም አለበት
2 ቀቤና በምስለኔ የጉራጌ ካድሬዎች መመራት የለበትም፣ እራሱን በራሱ ማስተዳደር አለበት።
ለምን የሚባል ነገር የለም፣ መብት ስለሆነ ብቻና ብቻ።
***
የቀቤና ህዝብ የልዩ ወረዳ ጥያቄ የጠየቀው በጉራጌ ስለተጨቆነ ብቻ ሳይሆን በጉራጌ ስር መተዳደር ስለሌለበት ነው።
አንድ ብሔረሰብ በሌላ ብሔረሰብ የሚመራበት ምንም ምክንያት የለም። ቀቤና እራሱን እራሱ ለመምራት ብቁ ነው። ውሀ መብራት መንገድ ሆስፒታል መሬት ንጥቂያ ጭቆና ምናምን ብለን ጉንጫችንን ማልፋት የለብንም።
***
የቀቤና ህዝብ በጉራጌ ዞን ምክር ቤት በ3 ሰው ተወክሎ ለህዝቡ የሚበጅ ውሳኔ እንደማያገኝ ማንም ያውቃል። የኛ ጥያቄ የመጨቆን ያለመጨቆን ጉዳይ ሳይሆን የመዋቅርና የህገ መንግስት ትግበራ ጉዳይ ነው። በ21ኛው ክ/ዘ የቀቤናን ጉዳይ ጉራጌ እንዲወስንለት መፍቀድና ይህንንም አምኖ መቀበል ዘመናዊ ባርነት ነው
***
የማይገናኙ ነገሮችን የሚያገናኙና መጋባት መዋለድ አብሮነት ጉርብትና የሚባሉ ዲስኩሮች ከመብት ጋር የሚገናኙ አይደሉም። የቀቤና ህዝብ እራስን በራስ ማስተዳደር ከጉራጌ ጋር መጋባት፣ መዋለድ፣ አብሮ መኖርና መተሳሰብን የሚጨምር እንጂ የሚከለክል አይደለም። ቀቤና 70% ከኦሮሞ ጋር ድንበር ነው። ሁለቱ ህዝቦች በማዋቅር ሌላ ሌላ ክልል ናቸው ነገር ግን ፍቅራቸውና አብሮነታቸው መጋባቱ መዋለዱ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም።
***
ማካለል በሚል አጀንዳ ዞኑ ደብዳቤ ካልፃፈ ተብሎ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ያላገኙ መዓት የቀቤና ገበሬዎች አሉ። በቀቤና ህዝብ አንጡራ መሬት ወሳኙ ጉራጌው ነው ማለት ነው። ይህ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ መቋጫ ማግኘት አለበት።
ዋናው ጥያቄያችን ቀቤና የራሱን ጉዳይ እራሱ የሚወስንበት አደረጃጀት እንዲፈጠር ነው፣ ያ ደግሞ ለግዜው ልዩ ወረዳ ነው።
***
በመጨረሻም ወረዳውና ወጣቶች እንደ ተለመደው ጠቅላዩ ወልቂጤ ሲመጣ ከመግብያው ጀምሮ በደማቅ ዝግጅት አሜተ ኤሳ ብለን መቀበላችንን እንዳንረሳ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ
721 viewsAdu Emru, edited 17:12