Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ቤቶች የሁሉም ነገር መሰረት ናቸው #ሼር አድርጉት *** አንድ ህዝብ ባህልና ታሪኩን እን | Habib Kedir

ትምህርት ቤቶች የሁሉም ነገር መሰረት ናቸው
#ሼር አድርጉት
***
አንድ ህዝብ ባህልና ታሪኩን እንዲሁም የመረዳዳት እሴቶቹንና ግብረገብነትን ታች ካሉ ትምህርት ቤቶችና ከህፃናት ቢጀምር ውጤታማ ይሆናል።
አሁን ያሉ ጅማሮዎች ከጎለበቱ ቀጣይ የቀቤና ትውልድ በእርግጠኝነት ገናና ታሪኩን የሚመልስ ይሆናል
***
በቀቤና ልዩ ወረዳ ወሸርቤ ጣጤሳ #ኡንጀሞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የህዝባችንን ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ለማሳደግ ብሎም የመረዳዳት ባህሉን ለማዳበር በታዳጊ ተማሪዎች ላይ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እሰይ የሚያስብል ነው።
***
ባለፈው ህዳር በብሔረሰቦች በዓል ወቅት ተማሪዎቹ በጨቅላ አዕምሯቸው የቀቤና የባህል አልባሳት፣ የባህል ቁሳቁስ እንዲሁም ባህላዊ የአመጋገብ ስርዓትን አቅርበዋል።
የዛው ትምህርት ቤት ህፃናት አሁን ደጎሞ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብል በመሰብሰብ አግዘዋል።
***
ህዝባችን ታዳጊዎች ላይ መልካም ዘር ከዘራ ቀጣዩ ግዜ ብሩህ ይሆንለታል።
በየትምህርት ቤቱ የባህል አብዮት በመፍጠር፣ ብሔረሰቡን የሚወድ፣ ባህሉን የሚያከብር፣ በማንነቱ የሚኮራ ትውልድ እንፍጠር።
በዚህ ረገድ የኡንጀሞን ትምህርት ቤት አርዓያ እንከተል
የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር መሀመድ ሁሴን እና እስታፉ አጠቃላይ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ በመሆኑ በዚሁ ቀጥሉ።
***
በመጨረሻም እነዚህ ለባህላቸው እድገት እንዲህ የሚለፉ ህፃናት የተሟላ መማርያ መፅሀፍ የላቸውም፣ ወንበር የላቸውም መሬት ላይ የሚማሩ አሉ፣ ክፍሎቹ የፈራረሱና መስኮት በር ያልተሟላላቸው ነው። እነዚህን አይታችሁ ልባቹሁ የሚራራና የምታዝኑ ለጋሾች ትብብር አድርጉ፣ ለNGO ወይም ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች በማሳወቅ የዜግነት ሀላፊነት እንወጣ።
***
መጪው ግዜ ለቀቤና ህዝብ ብሩህ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#ቀቤና_ልዩ_ወረዳ