Get Mystery Box with random crypto!

ወልቂጤ ኤፍ ኤም ጀርባ የሚጣለውን ቆሻሻ በተመለከተ ብዙ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው። *** ከግል ክ | Habib Kedir

ወልቂጤ ኤፍ ኤም ጀርባ የሚጣለውን ቆሻሻ በተመለከተ ብዙ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው።
***
ከግል ክሊኒኮችና ከአልቢርና መሰል ጤና ጣቢያ ያገኘሁት መረጃ ከጠቅላላ ታካሚ ህፃናትና አዋቂዎች ውስጥ 60% የሚሆኑት ቆሻሻ መጣያው አከባቢ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ነው።
ከጠቅላላው ታኪሚ ህዝብ 60% የሚሆነው የአንድ መንደር ሰው ከሆነ እጅግ የሚያሳዝንና ለወደፊቱም ከባድ አደጋ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
***
ይሄን ሁሉ ግዜ በህዝብ መኖርያ አከባቢ ቆሻሻ ሲጣል ለምን ዝም እንደ ተባለ ግራ ይገባል። አሁንም መፍትሄው አስቸኳይ መሆን አለበት። ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች፣ መሪዎች በጉዳዩ ፈጣን ውይይት ማድረግ አለባችሁ። ቆሺሻ የሚጥሉ መኪኖችና ጋሪዎች ማቆም ይገባቸዋል።
***
እንደ መፍትሄ
በከተማው አማራጭ ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ብዙ አሉ።
አሁን ቆሻሻ ሚጣልበትን አከባቢ አስውቦ
1 የአከባቢው ወጣትና ህዝብ መዝናኛ ማዕከል ማድረግ
2 ፍቃዶ ኬላ አከባቢ ለገበያ አስፓልት ዳር ከመኪና ጋር የሚጋፉ እናቶቾን ወደዛ አዘዋውሮ ደማቅና ደረጃውን የጠበቀ ገበያ በቦታው መመስረት
ህፃናትና አዋቂዎች በበሽታ አይለቁ፣ ይህን ጉዳይ ችላ ማለት አይገባም። ከተማ አስተዳደሩ የቀቤና ህዝብ ቢታመም ቢሞት ግዱ አይደለም፣ ወጣቱ ከህዝቡ ጋር ተናቦ መብቱን ማስከበር አለበት።
****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ