Get Mystery Box with random crypto!

ይህን መንገድ ተመልከቱ ከቀቤና ወረዳ ዋና ከተማ ወልቂጤ ወደ ሌላኛው የወረዳው ከተማ ወሸርቤ የሚወ | Habib Kedir

ይህን መንገድ ተመልከቱ
ከቀቤና ወረዳ ዋና ከተማ ወልቂጤ ወደ ሌላኛው የወረዳው ከተማ ወሸርቤ የሚወስድ ነው
***
ከ25 ኪሎ ሜትር ያልበለጠ መንገድ በመኪና ከ4 ሰዓት በላይ ይፈጃል።
አቅመ ደካሞች፣ ነብሰ ጡሮችና የታመሙ ሰዎች ሆስፒታል ለመድረስ በዚህ መንገድ የሚደርስባቸውን ስቃይ መገመት በጣም ቀላል ነው
በድፍን ወረዳው አንድ ኪ ሜ እንኳን አስፓልት መንገድ የለም። ለወረዳው የሚበጀተው በጀት የ6 ወር የሰራተኞች ደሞዝ አይከፍልም። አሁን በዚህ አመት እንኳን ከየካቲት ጀምሮ በብድር ነው ደሞዝ እየከፈለ የሚገኘው።
***
የሚያስፈልገን "የሚያዝን፣ እንዲህ አይነት ጭቆናና በደል በዘራችሁ አይድረስ" የሚልና "ከንፈር የሚመጥ" ሳይሆን፣ አምርሮ የሚታገልና ከዚህ ዞን ህዝቡን ነፃ የሚያወጣ ትውልድ ነው።
ቀቤኖች ያለን አማራጭ አንድና አንድ ነው
ከዚህ ትውልድ ከሚያጠፋ ዞን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ታግለን ነፃ መውጣት።
እየዬ አይሰራም
መቁረጥ፣ አምርሮ መታገልና የትኛውም መስዋዕትነት መክፈል ከጭቆና  ለመገላገል ብቸኛው መፍትሄ ነው።
***
ቀቤና እራሱን በራሱ እያስተዳደር ከጠባቂነት ወጥቶ ሀገሩን በትብብር ማልማት ነው።
የተጨቆኑ ጨቋኞች ፈላጭ ቆራጭ ሊሆኑብን አይገባም፣ የነፃነት እድሉ ይጠን እንጂ ለራሳችን እራሳችን እንበቃለን።
በቁጭት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳን እውን እናድርግ
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ