Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-09-17 11:42:15
ሜዲቴሽን ወይንም በጥልቅ ማሰላሰል ወይም ተመስጦ ሰፊ ፍልስፍና ነው። ዝምብሎ እግርን አጣምሮ፣ አይንን ከድኖ፣ ትንፋሽን መቆጣጠር አይደለም። ሜዲቴሽን ከሃሳብ እስር፣ ከጭንቅላት አለም ወጥቶ ህልውናን እንዳለ ማስተዋል ነው። ሜዲቴሽን ከሃሳብ ግርግር ማረፍ ነው። ሜዲቴሽን ከእንቅልፍ ወደ ንቃት አለም መሸጋገሪያ ነው። ከማሰብ ወደ መሆን ከፍ ማያ ነው።

ሜዲቴሽንን በቀላሉ የምታስረዳ አንድ ምሳሌ አለች። የኩሬ ውሃ ጭቃ ሞልቶት ቢደፈርስ እየነካካን አናጠራውም። በነካካነው ቁጥር ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚመጣው። መፍትሔው ኩሬውን አለመንካት ነው፤ መፍትሔው ኩሬው ዳር ተቀምጦ የተፈጥሮን ትንግርት ማስተዋል ነው። ኩሬው ለራሱ ሲተው እየጠራ፣ እየጠራ ይመጣና ኩልል ያለ ንፁህ፣ የተጣራ ውሃ ይሆናል።

አእምሯችን እንደ ተንጣለለው ኩሬ በሃሳብ ጭቃ ደፍርሷል። ኩሬውን እየነካካን እንደማናጠራው ሁሉ አእምሮንም በሃሳብ ጉልበት መግራት አይቻልም። ኩሬው ራሱ በራሱ እንዲጠራ እንደምንተወው ሁሉ፣ አእምሮም ንቃት ላይ እንዲደርስ፣ ከሃሳብ ግርግር አሳርፎ ለራሱ ምትሃታዊ አርምሞ መተው አለበት። በጥልቅ አሰላሳዩም ተፈጥሮ በአእምሮ ላይ የራሱን ተአምር ሲሰራ በዝምታ ተውጦ ያስተውላል። በጥልቅ ማሰላሰል ሌላ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም። በአጭሩ ከሃሳብ ነፃ ሆኖ ወደ መሆን ማእቀፍ መሸጋገር ነው። Meditation is a state of thoughtlessness. It's a state of being. It's a state of consciousness.
@gasha_tube
@gasha_tube
1.8K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 10:51:29 ለመታረቅ የመጀመሪያ ሁን

ብዙዎቻችን በአንድ ወቅት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ወይም በደረሰብን በደል ምክንያት ለረጅም ጊዜ እናቄማለን። የምታረቀው ያስቀየመን ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል እራሱ መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀን ብቻ ነው ብለን ድርቅ እንላለን።

አንዴ ጤንነቷ ጥሩ ያልሆነ የማውቃት ሴት ከወንድ ልጇ ጋር ለሰባት አመታት እንደማይነጋገሩ ነገረችኝ። " ለምን ?" ብዬ ጠየኳት። ከልጇ ጋር በሚስቱ ምክንያት አለመግባባት እንደነበረና እሱ ካልደወለ ላለመደወል እንደወሰነች ነገረችኝ። አንቺ የመጀመሪያው ብትሆኚስ ?" ብዬ ጠቆም ሳደርጋት " አይሆንም " እሱ ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት !" አለችኝ። እሷ ከምትደውል ሣታገኘው ብትሞትም ምንም እንደማይመስላት ነገረችኝ። ከተወሰነ የማበረታቻ ንግግር በኋላ ሀሣቧን ለውጣ እሷ የመጀመሪያዋ ለመሆን ተስማማች። ስትደውልለት ልጁ በመደወሏ በጣም እንደተደሰተ ነገረችኝ። ቀጥሎም ለጥፋቱ ይቅርታ ጠየቃት። ይቅርታውን ስላልጠበቀች እጅግ ተገረመች።

በአብዛኛው አንዱ ደፍሮ የመጀመሪያውን እርምጃ ሲራመድ ሌለኛውም የበለጠ ይቀርብና ሁሉም አሸናፊ ይሆናል። ቂም ይዘን ስንቆይ በአእምሯችን ውስጥ ቀላሉን ነገር ወደ ከባድ እና ውስብስብ እንለውጠዋለን። አቋማችን ከደስታችን በላይ አስፈላጊ ይመስለናል። አይደለም !

ሰላማዊ ሰው መሆን የምትፈልግ ከሆነ ትክክል መሆን ደስተኛ ከመሆን እንደማይበልጥ እየተረዳህ ትመጣለህ። ደስተኛ ለመሆን ያለፈውን መርሣትና ለመታረቅ የመጀመሪያ መሆን ትልቅ ሚና አለው። አንተ የመጀመሪያው መሆንህ ስህተት መሆንህን አያሳይም። ነገር ግን ሁኔታዎችን ወደ መልካም ይለውጣል።

ያለፈውን ስትተው ሰላምህ ፣ ለመታረቅ የመጀመሪያው ስትሆን ደግሞ ሰዎችም ለስለስ ብለው ይቀርቡሃል። እንዲያውም የበለጠ ሊቀርቡህና ስትፈልጋቸው የበለጠ ሊደርሱልህ ይችላሉ። ግን በሆነ ምክንያት እንደዚያ ባያደርጉም ችግር የለውም። ቢያንስ ቢያንስ የድርሻህን ስለተወጣህ ውስጣዊ እርካታ ይሰማሃል። በእርግጠኝነት ደግሞ ራስህን ሰላማዊ ሁነህ ታገኘዋለህ።
____
ምንጭ
፦ ቀላሉን ነገር አታካብድ መጽሐፍ
ጸሐፊ ፦ ዶክተር ሪቻርድ ካርሰን
ተርጓሚ ፦ ዶክተር ዮናስ ላቀው
@gasha_tube
@gasha_tube
1.8K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 10:50:49
1.4K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 16:00:50
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ "እንደ ሀገር ዘርፉን አካታች ለማድረግ ስለ ተጓዝናቸው ምዕራፎች ይህንን ሽልማት በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ መሆኑን ገልጸዋል።በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገትና መሻሻል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነው ከዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ፋይናንስ አመራር ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡
  
@gasha_tube
1.9K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 12:47:03
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የአዲስ ዓመት ስጦታና ማዕድ አጋሩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቂርቆስ ልደታና አራዳ ክፍለ ከሞች ለመጡ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ነው ማዕድ ያጋሩት። ለእንግዶቹ የአዲስ ዓመት ስጦታ በመስጠት መልካም በዓልን ተመኝተዋል።

@gasha_tube
464 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 11:27:17 አትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀበለች

በዓሉን በማስመልከትም በማለዳው 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።

አዲስ ዓመትን በማስመልከት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት መልዕክት፥ 2014 ዓመተ ምህረት በብዙ መልካምና እኩይ አጋጣሚዎች ተሞልቶ ማለፉን አስታውሰዋል።

“አዲሱን ዘመንን በጉጉት ስንቀበለው እንደ መስከረም አደይ ተስፋችን እንደሚፈካ፣ እንደ አዝመራው ውጥናችን ፍሬ አፍርቶ እንደምናይ፣ እንደ በጋ ወንዝ ሰላማችን ከአደፍራሾች እንደሚጠራ፣ ጭጋግ ጭለማው ከላያችን ተገፍፎ ብርሃን እንደሚፈነጥቅብን በመተማመን ነው” ብለዋል በመልካም ምኞት መልዕክታቸው።

“አሁን አንድ፣ ምንም ያልተነካ ተአምር ሊሠራበት የሚችል ውድ ሀብት ከፊታችን ቆሞ ይጠብቀናል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

“አዲስ ዓመት ማክበር ትርጉም የሚኖረው በጊዜ ውስጥ ለማለፍ የምንችል ከሆነ ነው። ጊዜ ይዞን ለሚሄድ ሰዎች አዲስ ዓመት የሚባል ነገር የለም” ብለዋል።

“አዲሱን ዓመት አዲስ እናድርገው። በራሱ ጊዜ የሚሄድና የሚመጣን ዓመት፣ አዲስና አሮጌ ማለት ትርጉም የለውም። የራሳችንን አዲስና አሮጌ ዘመን እንፍጠር።” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

“ዘመኑን በአዲስ ሥራ አዲስ አድርገነው አዲስ ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ” በማለትም መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

መልካም
አዲስ
ዓመት


@gasha_tube
@gasha_tube
539 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 22:19:05
ከባድ ማስጠንቀቂያ

ሰሞኑን ከዉጪ እቃ ወይም ዶላር እንልካለን በማለት እቃዉ እዚ ስለደረሰ ለግሙሩክ የሚሆን ክፍያ አዉኑኑ ላኩ እያሉ በዉጫዊ ዜጋ በማስመሰል ብዙ ሰዎችን እየተጭበረበሩ እንዳሉ ብዙ የጋሻ tube ቤተሰቦች መልእክት ልከዉልናል

ስለዚ ማንኛውም የዉጭ ዜጋ በቴሌግራም አካዉንታቹ inbox እያወራቹ ያላቹ እና እንደዚ አይነት የማጭበርበር ሙከራ ሲደረግባቹ ማንኛዉንም ብር ከመላክ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን

ይሄንን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶ በመላክ እባኮትን ከዚ አይነት የመጭበርበር ተግባር ይታደጉአቸዉ

ከላይ ባሉት አካዉንት እና የዉሸት ማስረጃዎች ብዙ ሰዎችን እያታለሉ ስላለ በማስተዋል ሆነዉ ይመልከቱት

@gasha_tube
@gasha_tube
839 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 23:16:48
𝗕𝗿𝗮𝗻𝗱 ጫማዎች ከ𝗔𝗕𝗗_𝗙𝗮𝘀𝗵𝗶𝗼𝗻𝘀
እንኳን ለአዲስ አመት
በሰላም አደርሳችሁ።
አዲሱን #ዓመት አምረው #ደምቀው እሚታዩበት #ኦርጅናል እና #አዳዲስ ጫማዎች በታላቅ #ቅናሽ እንሆ ብለናል በፈለጉት ብራንድ ከለር መርጠዉ የሚገዙበት? #አማራጭ አለ
𝗩𝗔𝗡𝗦               𝗡𝗜𝗞𝗘
𝗝𝗢𝗥𝗗𝗔𝗡         𝗣𝗨𝗠𝗔
𝗔𝗟𝗟𝗦𝗧𝗔𝗥        𝗔𝗗𝗜𝗗𝗔𝗦
ጫማዎችን ከኛ ጋር ያገኛሉ::
ብዛት ለሚፈልጉ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን::
#በተጨማሪም የአዉሮፓ እስታንዳርድ ያላቸዉ ምርጥ ጥራት ያላቸዉን እና ማራኪ ልብስ እና ጫማ በአይነት በአይነት ከ ሀገረ ከአሮፓ አስመጥተናል
ሸሚዞች
ሱሪዎች
ቲሸርቶች
ብቻ ምን አለፋን ሁሉም እርሶን ከነጥራታቸዉ ተዘጋጅተዉ የእርሶን መደወል እየጠቀቁ ነዉ
መልካም አዲስ ዓመት

#ያሉበት ሀገር ድረስ እንልካለን

▀▄▀▄▀▄▀▄▀▄▀▄
 
ያናግሩን

       ╚»★𝐵𝑒 𝑜𝑢𝑟 𝑓𝑎𝑚𝑖𝑙𝑦★«╝
           ቻናላችንን አዉኑኑ ይቀላቀሉ
      ︎@ABD_Fashions_1 ︎
     ︎@ABD_Fashions_1 ︎
     ︎@ABD_Fashions_1
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
          𝐂𝐀𝐋𝐋 𝐓𝐄𝐗𝐓     
     𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲 ☞ 0900296333
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 ☞ @ABD_Fashions
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አድራሻ ጎፋ ማብራት ሀይል
570 viewsЄαgℓє Advertisement, 20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 19:30:18
#የዛሬ__ትምህርቴ
" አንድ ሰው ሊፈጠርበት ከሚችለው ቁጭት ሁሉ የከፋው ህይወቱ ፍፃሜ ላይ ህልሞቹን ለማሳካት ምንም እንዳላደረገ ማወቁ ነው"
"ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን ከማቀድ ይልቅ የዕረፍት ጊዜያቸውን እንዴት እንደሚያሳልፉ በማቀድ የበለጠ ጊዜ ያጠፋሉ"
#ጁልያን #ሮቢን_ሻርማ
@gasha_tube
426 viewsЄαgℓє Advertisement, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:00:46 በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማችን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰፊው  ከመከረ በኋላ በቀጣዮቹ ነጥቦች ላይ ጥብቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።

1ኛ የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብ ረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል ።

2ኛ  በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የምትሰጡ  ታክሲዎች እስከ  11 ሰዓት  ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ውሳኔ ተላልፏል ።

3ኛ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ  ይወሰዳል።

4ኛ ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች በመጠጥ ቤቶች በካፌዎችና በግረሶሪዎች ላይ እስከ 11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው።

5ኛ  የአልጋ አከራይ ሆቴሎዎች የመኖሪያ ቤትና የመደብ አከራዮች የተከራዩን ማንነት የሚገልጽ  መረጃ  በመያዝ  እንድታስገለግሉና በአቅራቢያችሁ ለሚገኝ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት የተከራዩን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ  ጭምር የመሰጠት ግዴታ አለባችሁ።

6ኛ በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም  ድርጊቶች ጸጉረ ልውጥ ሰዎች አጠራጣሪ ተሽከርካሪዎች ወዘተ ሲታዩ  ለጸጥታ ተቋማት መጠቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

7ኛ በከተማው ውስጥ የሚገኙ DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

8ኛ  በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

9ኛ  የከተማችን የጸጥታ ኃይሎች ከመንግዜውም በላይ በመናበብ በመቀናጀት የተሰጣችሁን ኋላፊነት በብቃት በመወጣት  ህግ የማስከበር ሚናችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን። የከተማችን ነዋሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በበሬ ወለደ በሀሰተኛ በሚለቀቁ  መረጃዎች  ሳይደናገር እና አላስፈላጊ ውዦብር ውሰጥ ሳይገባ በተረጋጋና በሰከነ መልኩ መደበኛ ሰራችሁን እንድታከናውኑ ተገልጿል።

10ኛ ከተፈቀደላቸው የከተማችን የፀጥታ ኃይሎች ወጭ የጦር መሳሪያ ይዞ በቡድንም ሆነ በግል  ይዞ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

11ኛ  መንግስት  ከሚሰራቸው የተቀናጀ ድጋፍ አሰባሰብ ስርዓት ውጭ ለመከላከያ ፣ ለልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ሰበብ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ፈጽሞ የተከለከለ ነዉ። ያለ ከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና  በግልም ሆነ በቡድን ወደ ግንባር መንቀሳቀስ  የተከለከለ ነው።

13ኛ ማንኛውም ተቋማት ተሽርካሪዎችን  ለጸጥታ ሰራ በተፈለጉ ጊዜ የጸጥታ ተቋሙ ሲጠይቅ  ቀና ትብብር እንድታደርጉ ከተማ አስተዳዳሩ አሳስቧል።

14ኛ .ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በቀጣይም የጸጥታ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች እናሳውቃለን ሲል የከተማ መስተዳድሩ ማስታወቁን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@gasha_tube
@gasha_tube
718 viewsЄαgℓє Advertisement, 14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ