Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-07-11 10:51:33 የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አለመውጣትን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አለመውጣትን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።

አስተዳደሩ የሰጠው ማብራሪያ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:-

እንደሚታወቀው የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው ሳምንት የ20/80 የ14ኛ ዙር የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በ20/80 ፕሮግራም የባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች በእጣው አለመካተትን መነሻ በማድረግ ከአንዳንድ ግለሰቦች የደረሰንን የግልፅነት ጥያቄ አስመልክቶ የሚከተለውን ማብራርያ ለማቅረብ እንወዳለን፡-

በዚህ ዙር ለ20/80 የቤት ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እጣ የወጣባቸውና የተስተናገዱት የ1997 ተመዛጋቢዎች ብቻ ናቸው።

የ2005 የ20/80 ተመዝጋቢዎች ግን ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ በሙሉ በእጣ ውስጥ አልተካተቱም።

የ40/60 የቤት ፕሮግራም ግን በ2005 ዓ.ም ብቁ የሆኑ ሙሉ ለሙሉ በእጣ ተካተው በዚህ ዙር የእጣ አወጣጥ በ40/60 ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ ቤቶች እጣ እንደወጣላቸው ልብ ሊባል ይገባል።

ስለሆነም በዚህ ዙር ያልተስተናገዱት 1997 ዓ.ም የተመዘገቡ ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸው።

ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በ12ኛ ዙር እጣ የ1997 ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ ለሙሉ አስተናግደናል በሚል መነሻ መረጃቸው የተሟላ የሆኑት ተስተናግደው የባለሶስት መኝታ ፕሮግራም ተዘግቶ ነበር።

ከዚህ በኋላ በ1997 ተመዝጋቢዎች ውስጥ በ20/80 ባለሶስት መኝታ እጣ ሊወጣለት የሚችል ተመዝጋቢ የለም በሚል ቤቶቹን በሚያስተዳድረው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።

በዚህም ምክንያት በዚህኛው (በ14ኛ) ዙር እጣ ማስተናገድ አልተቻለም።

ነገር ግን ከተዘጋ በኋላ ከባንክ የተገኘው መረጃ ጥቂቶች ቢሆኑም ቁጠባ በመቀጠላቸው ብቁ የሆኑ ጥቂቶች ተገኝተዋል።

በአሁን ሰአትም ምዝገባው ከባንክ በሚወሰድበት (በሚከለስበት ወቅት) በተገኘው መረጃ ከ1997 ተመዝጋቢዎች መሃከል ጥቂት ሰዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉና ብቁ የሆኑ የ20/80 ተመዝጋቢዎችን ማግኘት ተችሏል።

ስለሆነም አስተዳደሩ እነኚህን ተመዝጋቢዎች ምንም እንኳን ፕሮግራሙ በይፋ የተዘጋ ቢሆንም ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት በአግባቡ እስከቆጠቡ ድረስ ማስተናገድ እንደሚገባ ያምናል።

ነገር ግን ከመረጃ ውስንነትና በሲስተሙ ላይ የሚያስከትለውን ተጨማሪ የመረጃ መመሰቃቀል ለመከላከል ሲባል ወደ በኋላ ተመልሶ ሲስተሙን ለቀሩት ጥቂት ቆጣቢዎች ብቻ መክፈት አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት እነዚህን ተመዝጋቢዎች ለብቻቸው በልዩ ሁኔታ ልናስተናግድ ይገባል የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢ ሆናችሁ ባለሶስት መኝታ ቤቶች በአግባቡ የቆጠባችሁ አስተዳደሩ በሚያወጣው ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ የምትስተናገዱ መሆኑን እያሳወቅን፤ ህብረተሰቡ ይህንን አስመልክቶ አንዳንድ የሚናፈሱ የተሳሳቱ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን!!

በተጨማሪም ዘርፉን የሚመሩ አመራሮች ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ ሚድያዎች የሚያደርሱ መሆኑንም እናሳውቃለን!!

@gasha_tube
977 viewsЄαgℓє Advertisement, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 23:58:44
የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 96 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ

ባለስልጣኑ በተለያዩ የክልል ከተሞች በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትላይ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ ከመመሪያ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ሲያስተምሩ ባገኛቸው ካምፓሶች ነው የእርምት እርምጃ የወሰደው፡፡

ጥሰቶቹም የእውቅና ፈቃድ ባልተሰጠባቸው ካምፓሶች እና የትምህርት መስኮች ተማሪ ተቀብሎ ማስተማር፣ እንዲያስተምሩ ባልተፈቀደበት የትምህርት አሰጣጥ ክፍለ ጊዜ ተማሪ መዝግበው ለማስመረቅ ማስተማር፣ ፈቃድ ባገኙበት ካምፓስ (ህንጻ) ላይ አለመገኘትን ያካትታል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በእውቅና ፈቃድ እና በእውቅና ፈቃድ እድሳት ወቅት ተሟልተው የነበሩ ግብዓቶችን አጓድለው መገኘታቸውን እና ያልተፈቀደላቸውን የደረጃ ስያሜ መጠቀም እና የመሳሰሉት ጥሰቶች በድንገተኛ ፍተሻ የተረጋገጡ መሆናቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በተወሰደው ርምጃ መሰረትም ለተቋማቱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ጀምሮ በፕሮግራም፣ በካምፓስና በተቋም ደረጃ የእውቅና ፈቃዳቸው ተሰርዞ ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጉ፣ ከህግ-ውጪ የተቀበሉትን ተማሪዎች እንዲያሰናብቱ መደረጉን ባለስልጣኑ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

@gasha_tube
891 viewsЄαgℓє Advertisement, 20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:21:55
እንኳን ለ1443ኛው የዒድ አል አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ

@gasha_tube
1.0K viewsЄαgℓє Advertisement, 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:52:27
የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያካሄደ ሲሆን፥ በ2015 የፌደራል መንግስት በጀት ላይ በምክር ቤቱ የተገኙ እና ከህዝብ የተሰበሰቡ ግብዓቶችን መሰረት አድርጎ በመወያየት ነው ያፀደቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የ2015 የፌደራል መንግስት በጀት፥ ብድር መቀነስ፣ የበጀት ጉድለት መቀነስ፣ ያለን ሀብት በቁጠባ መጠቀም እና የዋጋ ንረትን ማረጋጋት የሚሉ ነጥቦችን የትኩረት አቅጣጫ እንዳደረገ ተናግረዋል።

እንደዚሁም መልሶ ማቋቋም፣ ሰብዓዊ እርዳታ እና የሀገር ደህንነት እና ሰላምን ማስጠበቅን በማጠናከር ላይ ትኩረት እንዳደረገም ተመልክቷል።

@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:50:13
በቻናላችን Promotion ማሰራት ለምትፈልጉ:-

የሱቆች፣ የድርጅቶች፣ የፊልም ፣ የድራማ፣ የyoutube እና tiktok ቪዲዮዎች፣ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በቻናላችን በቅናሽ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ!! በቻናላችን አንድ የቪዲዮ ሊንክ/ማስታወቂያ ሲለቀቅ ለብዙ ጊዜ ሳይጠፋ የሚቆይ ሲሆን በመቶ ሺዎች ይታያል። እድሉን ይጠቀሙ፣ በቻናላችን ያስተዋውቁ! በታማኝነት እንሰራለን።

ማሳሰቢያ - በቻናላችን ማንኛውንም ማስታወቂያ ስታሰሩ or ለማሰራት ስትነጋገሩ, ክፍያ ስፈፅሙ በቅድሚያ የቻናሉን ዋና አድሚን ያነጋግሩ!

በዚህ ሊንክ ያነጋግሩን።
@gasha_manager
Youtube Video Channel
1.1K viewsЄαgℓє Advertisement, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:49:35
የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ሚኒሰቴሩ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እንዲሁም የትራንስፖርት መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

(አዲስ ይፋ የተደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ከላይ ተያይዟል)

@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:29:37 የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውሷል።

የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት
- ባለ3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
- መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
- ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
- መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
- የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
- የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
- ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 14:29:24 ምክር ቤቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ አወገዘ

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ከጥቃቱ በመሸሽም በምእራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮንኗል።ቡድኑ በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋም በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ "በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘን ይህንን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንድናስወግደው" ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።

@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:42:21
በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን መገደላቸውን ተነገረ

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በዛሬዉ እለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት እንዳለፈ ተነግሯል። በጥቃቱ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መገደላቸዉንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ በዉል ባይታወቅም ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ንጹሀን ሲገደሉ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም አረጋግጠዋል። " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው " ብለዋል።

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

@gasha_tube
1.3K viewsЄαgℓє Advertisement, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:02:08 በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ እየገባ ነው

የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ነዳጅ ለመቅዳት በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

በአቅርቦት በኩል ክፍተት እንዳይኖርም ቀድሞ በቀን ይቀርብ ከነበረው 9 ሚሊዮን ሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ማሳደጉን የባለስልጣኑ የነዳጅ ስታንዳርድ ጥራት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል።

ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር እና ስርጭቱ ላይ ችግር እንዳይኖር ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት እንደሀገር 200 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ከጂቡቲ ተነስተው 18ቱ ሞጆ ወደብ መድረሳቸውን እና የተቀሩት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው አቶ ለሜሳ ገልጸዋል።

@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ