Get Mystery Box with random crypto!

ምክር ቤቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ አወገ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ምክር ቤቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ አወገዘ

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ከጥቃቱ በመሸሽም በምእራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮንኗል።ቡድኑ በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋም በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ "በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘን ይህንን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንድናስወግደው" ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።

@gasha_tube