Get Mystery Box with random crypto!

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን ጀመረ የህዝብ ት | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውሷል።

የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት
- ባለ3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
- መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
- ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
- መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
- የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
- የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
- ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

@gasha_tube