Get Mystery Box with random crypto!

በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን መገደላቸውን ተ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን መገደላቸውን ተነገረ

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በዛሬዉ እለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት እንዳለፈ ተነግሯል። በጥቃቱ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መገደላቸዉንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ በዉል ባይታወቅም ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ንጹሀን ሲገደሉ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም አረጋግጠዋል። " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው " ብለዋል።

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

@gasha_tube