Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ የህዝብ ተወካዮች ም | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያካሄደ ሲሆን፥ በ2015 የፌደራል መንግስት በጀት ላይ በምክር ቤቱ የተገኙ እና ከህዝብ የተሰበሰቡ ግብዓቶችን መሰረት አድርጎ በመወያየት ነው ያፀደቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የ2015 የፌደራል መንግስት በጀት፥ ብድር መቀነስ፣ የበጀት ጉድለት መቀነስ፣ ያለን ሀብት በቁጠባ መጠቀም እና የዋጋ ንረትን ማረጋጋት የሚሉ ነጥቦችን የትኩረት አቅጣጫ እንዳደረገ ተናግረዋል።

እንደዚሁም መልሶ ማቋቋም፣ ሰብዓዊ እርዳታ እና የሀገር ደህንነት እና ሰላምን ማስጠበቅን በማጠናከር ላይ ትኩረት እንዳደረገም ተመልክቷል።

@gasha_tube