Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-08-29 17:21:28
ተራ ተራራነት

ስሜት አለ ውስጤ ትልቅ፣
.የሚያፍን የሚያስጨንቅ፣
..ህመም አለ የማያመኝ፣
በመብሰልሰል የሚገድለኝ፣
..የመገለ መጥፎ ቁስል፣
ሲታይ ደህና የሚመስል።
        
 ይሰማኛል ግራ ስሜት፣
የማቅለሽለሽ መውደቅ አይነት፣
.................ደሞ የመሞት!

ምወድቅ ምወድቅ ምወድቅ ይመስለኛል፣
ሰው አያውቅልኝም እኔን ግን ያመኛል፣
አለማወቃቸው ብሶ ይገድለኛል፣
ፍርሃት ፍርሃት ፍ_ር_ሃ_ት ይሰማኛል፣
ደርሶ ልቤን......... ያፍነኛል፣
የፊት ደመና የት ይዘንብልኛል፣
የውስጤ ገሞራስ ወዴት ይፈነዳል?
እዚያው ተደባልቆ ውስጤኑ ይፋጃል።

በውስጤ ገሞራ ላልበስል እያረርኩ፣
የፊቴን መዳመ'ን ትልቅ ጠባሳዬን፣
...............ለመሸሸግ በጣርኩ ፣
ካለኝ ተራራነት ወደ ጠጠር ፈረስኩ።

                      Hami
@gasha_tube
@gasha_tube
1.0K viewsЄαgℓє Advertisement, 14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:27:59
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ የሙከራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል።

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉ። የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎት መጠቀም መቀጠል ይችላሉ፡፡

በከዚራ፣ መስቀለኛ እና ኮርኔል ያሉ 3 የሳፋሪኮም ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት እንደሆኑ ተገልጿል።በድሬዳዋ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡
 
@gasha_tube
1.1K viewsЄαgℓє Advertisement, 10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:59:03
የአለማየሁ ዋሴ እሸቴ መፅሐፍ

1.እመጓ
2.ዝጎራ
3.መርበብት
4.ሰበዝ
5.ሜተራሊዮን በቅርቡ የታተመ ስለሆነ በpdf ለምትፈልጉ ልንለቅ ነዉ
@gasha_tube
1.3K viewsЄαgℓє Advertisement, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:56:33
ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ


ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው።

የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፤ የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፤ የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ፤ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል፡፡

ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።''

<ዝጎራ
@gasha_tube
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:01:38 ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ
ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች፡
*21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ
ስልክ ቁጥርዎ 0954323411 ከሆነ ወደ
*21*095432341# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ!

ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ሲፈልጉ
*21*0943554433# በ0943554433 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ
ቁጥር ያስገቡ ከዘ ወደርሶ ሲደወል ወድ የስገባነው ቁጥር ይደወላል
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው
ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል

. ስልክዎ ሲጨናነቅ(busy) ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ
. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት
ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ

. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!

. ኮል ዌቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል

. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ
#31#"የሚደውሉት ቁጥር" ከዛ መደወል
.አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር ስናስገባ በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል::
▬▬ Share ▬▬▬▬
@gasha_tube
@gasha_tube
1.5K viewsЄαgℓє Advertisement, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:01:10
1.2K viewsЄαgℓє Advertisement, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:35:47
በመዲናዋ የመኖሪያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለስድስት ወራት ተራዘመ

የከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖሪያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ደንቡ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷልም ነው ያለው።

የከተማ አስተዳደሩ በመግለጫው "አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ተወስኗል ብሏል።

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ እንዲጠቁም መጠየቁን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@gasha_tube
1.4K viewsЄαgℓє Advertisement, 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:47:58
አታውቅም !

ሳልፈልግ የመራቅ ወኔዬን እርቀት ፤ ይሉኝታ ቢስ ፊቴን ፤ ካልፈለኩ አካሌ እንዴት እንደሚያምፅ፣ የሚጣፍጥ እንዴት እንደሚመረኝ፣ ሰከንድ አልሄድም እንደሚለኝ፤

አታቅም ! አታቀኝም !

ፍቅርህ ነው ያለሰለሰኝ ። ሲከፋኝ የማላንባረቀው፣
አሁን ወሰኜ መልሼ የምከልሰው፣ አቋም አልባ ያደረገኝ፣ በግዜ ብዛት የገዛኝ ለኔ ያሳየኸኝ ስሜትህ ነው ።

ደመነብሴ እንደሚታዘዝህ ፤ መነጫነጬ ከፍቅር እንደመነጨ ፤ የማላነሳውን ስልክህን እንደምጠብቀው ፤

ሳማክ እንኳ እንዳይጠሉብኝ ብዬ አንዳንዱን እውነት ቆርጬ እንደማስቀርው ።

አስሬ እንደ ልጅ ስትመክረኝ ፤ ሳጠፋ እንባዬ አይኔ ላይ አቆጥቁጦ የምሰማህ፤ ንዴትህ ውስጥ ፍቅር ስለሚታየኝ ነው ።

አንተ ጋ ሌላ ነኝ፤ አንተ ጋ በምሆነው እንዳትመዝነኝ !!
@gasha_tube
@gasha_tube
1.5K viewsЄαgℓє Advertisement, 15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:29:33
ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር /570 ሺ ሊትር / ነዳጅ ዘረፈ

ዱጃሪክ ፤ " የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ታንከር 570,000 ሊትር ነዳጅ ወስደዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

በቦታው የነበሩ የመንግስታ ድርጅት እርዳታ ሰጪዎች ዝርፊያውን ማስቆም እንዳልቻሉ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ተመድ ለሰብዓዊ ስራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊያ አጥብቆ እንደሚያወግዝም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

@gasha_tube
1.6K viewsЄαgℓє Advertisement, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ